Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union
前往频道在 Telegram
This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.
显示更多4 434
订阅者
-424 小时
-167 天
-9130 天
帖子存档
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ኒቃቢስት ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት መግለጫ አውጥቷል::
"ኒቃብ የኢትዮጵያ እሴት ነው!" - ብሏል::
አላሁ አክበርር!
አላሁ አክበርርር!!
አላሁ አክበርርርር!!
Let they witness it
ፋና ••• EBC ••• ሌሎችም የመንግስት ሚዲያዎች ስለ እርሷ አውርተዋል
ስኬቷ እንደ ፀሐይ ወጥቷልና በእጃቸው ሊጋርዱት አልቻሉም
ዚክራ ሰዒድ በኒቃቧ ተውባ ክብሯን አስጠብቃ ከነፃነቷ ጋር ከፊት ተሰለፈች
ይህ በጥብቅነት ውስጥ የታየ ትልቅ ስኬት ነው
••• ኒቃብ መማር ማስተማርን ያስተጓጉላል ለሚሉት ሁሉ ላኩላቸውና ኒቃብ ለብሳ ከሁሉም ልቃ እንደተገኘች ይመስክሩ
••• ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ይሆናል ለሚሉት ሁሉ ላኩላቸውና ኒቃቧን ለብሳ ከደህንነቷ ጋር በዋንጫ እንደተመረቀች ይመስክሩ
Let they witness it !
ኒቃቢስቷ ዛኪራ ሰዒድ በወርቅ ተመርቃለች!
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ተማሪ የነበረችው ዛኪራ ሰዒድ 3.99 በማምጣት በሁለት ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ ተመርቃለች:: Congratulations 🎉🎉🎉 Our sister!
Once again ኒቃብ ከመማር ከመመረቅ ከመሸለም አያግድም:: ተምራለች: ተመርቃለች: ተሸልማለች::
ትለብሳለች
ትማራለች!
Congratulations 🎉🎉🎉🎉
"ጅማ ዩኒቨርሲቲ ኒቃብ ከለከለ!" - የሚለው ዜና surprising የሆነባቸው ብዙ ሰዎች አሉ:: "መዳ ወላቡ ለረመዳን ሾርባ አላዘጋጅም አለ!" የሚለውም ግርምትን የፈጠረባቸው ብዙሐን ናቸው::
እዚህጋ አትሳሳቱ ••• በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያለውን የመብት መገፋት ጠለቅ ብለን ካየነው ጥልቀቱ የትየሌለ ነው:: ሆኖም ዋነኛው ችግር ከእኛ ነው:: እስካሁን ድረስ በእኛ ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ እንኳ አናውቅም:: ስለ መብቶቻችን አምርረን አንጠይቅም:: ጅማ ኒቃብ ጀለብያ እና መሠል የሙስሊም መብቶችን ካፈነ አምስት አመታት ተቆጥሯል:: አሁን ለመብቱ የሚታትር ትውልድ ሲፈጠር ነው በጓዷ የነበረው ወደ አደባባይ የወጣው:: መዳ ወላቡ በታሪኩ በረመዳን ሾርባ አዘጋጅቶ አያውቅም:: የሾርባውን በጀት ወደየት እንደሚያስገቡት አላህ ይወቅ:: አሁን ግልፅ የሆነው ተማሪው እምቢኝ ብሎ ሲነሳ ነው::
አሁንም ቢሆን ••• ምን ውስጥ ነው እየኖርን ያለነው ብሎ መጠየቅ ያሻል:: ምንድን ነው የነጠቁን ብሎ ማሰላሰል ያስፈልጋል:: ከዚያም ቡሃላ መጠየቅ መጠየቅ መታገል መታገል ማለት ነው:: እነርሱ ሳያፍሩ ሳይፈሩ ሕግን ተላልፈው የከለከሉንን እኛ ተሽኮርምመን ዝም ማለት የለብንም:: እየተማርን ያለን ሙስሊም ነንና:: ካልጠየቅን ግን ተምረንም አንጠቅም!
https://t.me/EHEMSU
መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለረመዳን ሾርባ አላዘጋጅም ማለቱን ተከትሎ ተማሪዎች በሰላማዊ ሁኔታ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል!
ለረመዳን ሾርባ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባል ደረጃ ይዘጋጀል:: የሚዘጋጀው በአዲስ በጀት ሳይሆን የቁርሱን ምግብ ወደ ሾርባ በመቀየር ነው:: ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አመታትም የማያዘጋጅ ሲሆን በዘንድሮው አመት ተማሪዎች ረመዳን ከመግባቱ በፊት ጀምረው ጠይቀው እሺ ቢባሉም ሳያዘጋጅ ቀርቷል::
ለማድረግ ቀላል ለተማሪው ለእሴቱና ለዩኒቨርሲቲው ከበባቢ ትልቅ ትርጉም ያላቸውን ጉዳዮች ባያወሳስቡ ለሁሉም በጎ ነው:: ትምህርት ሚኒስቴርም በመሠል ጉዳዮች ላይ ወጥ የሆነ ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል:: አለዚያ ሙስሊም ጠል የሆኑ አመራሮች አጀንዳ መፍጠር በፈለጉ ቁጥር የሚያነዱት እሳት ሁሉንም ዋጋ ያስፈልጋል::
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
ጅንስ ሱሪን የዩኒቨርሲቲ ልብስ ያደረገው ማን ነው? ሱፍ ኮትን የዩኒቨርሲቲ የክት ልብስ ያደረገው ማን ነው? ሱሪ በኮትን የሴኩላር አለባበስ ያደረገው ማን ነው? ሲጀመር እነዚህ አለባበሶች ከየት የመጡ አለባበስ ናቸው? ይህንንስ የለበሰ አካል ጀለብያን/ሙደወርን አትልበሱ ብሎ የሚከለክለው በምን አግባብ ነው?
ይህ መሐይምነት የወለደው የጥላቻ በትር እንጅ ሌላ አይደለም:: ጅንስ ሱሪም ሆነ ሱፍ ከምዕራብም መጣ ከሰሜን ቢለብሱ ባይለብሱ ጉዳያችን አይደለም:: ይበጀናል ካሉ ይልበሱት:: ግን ለጀለብያ/ሙደወር ሌላ ስም ሰጥተው እንዲከለክሉ አንፈቅድም:: እነርሱ የመረጡትን መልበስ እንደቻሉት ሁሉ እኛም የመረጥነውን የመልበስ መብት አለን:: የእኛን ልበሱ አንልም ••• አትልበሱ እንዲሉን ግን አንፈቅድም:: ይሰመርበት!
https://t.me/EHEMSU
ጁምዓ ነው ••• በዚያ ላይ ረመዳን ••• በጅማ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችንም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ መብታቸው እየተገፋ ላሉ ሙስሊም ተማሪዎች ሁሉ ዱዓ እናድርግ:: አላህ መፍትሔውን ያቅርብ!
https://t.me/EHEMSU
"We are in the community!" ••• ይላል በጅማ ዩኒቨርሲቲ አርማ ላይ በደማቁ የሰፈረው መለያ ቃል:: ትርጉሙ "እኛ በማህበረሰቡ ውስጥ ነን!" እንደማለት ነው::
•••••••••••••••••••••••
እዚህጋ ጥያቄ አለን!
••••••••••••••••••••••••
በየትኛው ማህበረሰብ ውስጥ ናቸው? በጅማ ማህበረሰብ ውስጥ? በኦሮምያ ማህበረሰብ ውስጥ? በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ? በጅማ ውስጥ ከሆኑ የጅማ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነውን ባህላዊ አለባበስ ስለምን ይከለክላሉ? በኦሮምያ ውስጥ ከሆኑ ከኦሮምያ ክልል ብዙሐን የሆነውን ሙስሊም መብት ስለምን ይገፋሉ? ከኢትዮጵያ ከሆነ የኢትዮጵያ ግማሽ ሕዝብ የሆነውን ሙስሊም በማንነቱ ስለምን መጨቆን ይፈልጋሉ?
ወይንስ ባህር ተሻግረው ማህበረሰብነትን ከፈረንሳይ መውሰድ ፈለጉ:: እንደ ፈረንሳይ ሙስሊሞችን በአለባበስ መጨቆን ፈለጉ::
የፈለጉትን ይፈልጉ:: ግን ከረሱት ያስታውሱ ዘንድ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው በአባ ጅፋሯ ጅማ ውስጥ ነው:: በአባ ጅፋር ሐገር ደግሞ የአባ ጅፋር ልጆች ባዕድ አይሆኑም:: መብታቸው ይከበራል:: ነፃነታቸው ይጠበቃል::
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ሲሰራ የነበረው ግፍ ጎንደርን ያስንቃል:: ጎንደር ኒቃብ አይከለከልም:: ላለፉት አምስት አመታት ሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ ፀጥ እረጭ ማለቱ ደግሞ በየትኛውም አካባቢ ታይቶ የማይታወቅ ንቀት ነው::
አሁን ትግሉ ተጀምሯል ••• የጀመረውን ሳይጨርስ የማያርፍ ትውልድም ተፈጥሯል ••• ለሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ ይፋዊ እና ሕጋዊ ምላሽ እስኪሰጥም ትግሉ ይቀጥላል::
መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!
ፍትሕ ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
https://t.me/EHEMSU
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ዩኒቨርሲቲው በሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጉዳይ ያለውን አቋም እስከ የካቲት 29/2017 ከቀኑ 10:00 እንዲያሳውቅ አሳሰበ:: ጀመዓው በተለይም በሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ተደጋጋሚ የሆነ የመብት ጥሰት እየደረሰ መሆኑን ገልፆ ዩኒቨርሲቲው ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ከተማሪዎቹ ጋር በመሆን ወደ ቀጣይ ሰላማዊ ትግል እንደሚሸጋገር ገልፇል::
መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!
በሚከተለው መልኩም ጥያቄያችሁን አቅርቡ
"የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ከሆነ ቡሃላ ባወጣው መመሪያ የሚከተሉት አንቀፆች ይገኛሉ:-
• አንቀፅ 6:- "ከደህንነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ማንነትን ለመለየት ሲባልና ከፀጥታ ጋር በተገናኘ ምክንያት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ፊትን በመሸፈን ማንነትን ለመለየት አዳጋች የሚያደርጉ አለባበሶችን መልበስ አይፈቀድም::"
ይህ በግልፅ ሙስሊም ተማሪዎች ሐይማኖታቸው አዟቸውና ሕገ መንግስታቸው ፈቅዶላቸው የሚለብሱትን ኒቃብ የሚከለክል ድንጋጌ ነው:: በየትኛው አግባብ ነው በአንድ ሐይማኖት ጣልቃ ገብቶ አለባበስ ለመምረጥ መመሪያ ያወጣው? ኒቃብ መልበስ እንደ ሐይማኖት ትዕዛዝ ነው:: እንደ ሕገ መንግስት መብት ነው:: ከሐገራችንም ባሻገር የሌሎች ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ልምድ ይህንን ያፀናል:: ሆኖም ግን ዩኒቨርሲቲያችን ባልታወቀ ምክንያት ይህንን ድንጋጌ አውጥቷል:: ከዚህ በመቀጠልም ተማሪዎች ጥያቄ ቢያቀርቡም መጀመሪያ አከባቢ ለማወያየት ቢሞክርም ቡሃላ ግን ከአንድ የልሕቀት ማዕከል በማይጠበቅ መልኩ የሙስሊም ተማሪዎችን ተወካዮች አናወያይም ብሎ በር ዘግቷል:: ለምን ብላችሁ እንድትጠይቁልን እንፈልጋለን::
@aaumsu
ለመላው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች እንዲሁም ለሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ "በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ጉዞ ዙሪያ ጥያቄ አለዎት?" በሚል ርዕስ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመነጋገር ተማሪዎች፣ የግቢው ማህበረሰብ እንዲሁም አጠቃላይ ህዝቡ በዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት ዙሪያ ያላቸውን ጥያቄዎች ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንደሆነ አሳውቋል።
ስለሆነም እንደ ሙስሊም ተማሪ ዩኒቨርሲቲያችን ራስ ገዝ ከሆነ ቡሃላ ሐይማኖታዊና ሰብዓዊ መብታችንን የሚረግጥ መመሪያ ለምን እንዳወጣ እንዲጠየቅልን እንፈልጋለን። ስለሆነም ሁሉም ተማሪ የሚከተለውን ቅሬታ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለዩኒቨርሲቲው እንዲያደርስልን ልንጠይቅ ይገባል።
"አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ በ2017 ዓ.ል ባወጣው መመሪያ የሙስሊም ተማሪዎችን ሐይማኖታዊ ሰብዓዊ እና ሕገ-መንግስታዊ መብት የሚያፍን መመሪያ አውጥቷል:: በመመሪያው ኒቃብ የሙስሊም ተማሪዎች ልብስ ሆኖ ሳለ "መልበስ አይቻልም!" የሚልን ድንጋጌ አውጥቷል:: ይህ ደግሞ በሐይማኖታችን ጣልቃ መግባት ነው:: ሙስሊሞች ሶላት መስገድ እንዳለባቸው የሚታወቅ ሆኖ ብሎም ባደጉት ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች የመስገጃ ቦታ ተመቻችቶላቸው እየሰገዱ ሳሉ ዩኒቨርሲቲያችን ግን ከሕግም ከልምድም ውጭ ሆኖ ሶላት በሕብረት መስገድ ይከለከላል የሚል መመሪያ አውጥቷል:: የሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች ቅሬታውን ቢያቀርቡም ዩኒቨርሲቲው ለማወያየት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል:: ይህ ደግሞ ከአንድ የልሕቀት ማዕከል የማይጠበቅ የውይይት ባህላችንን የጣሰ ተግባር ነው:: ስለሆነም ይህንን ለምን እንዳደረገ ማብራሪያ እንሻለንና ጠይቁልን::"
ጥያቄዎችን ለማቅረብ @tikvahmagbot ይጠቀሙ።
@MohammadamminKassaw
Warri Yunivarsitii jimmaa ajandaa haaraa muslimootaaf uumuu dhaabaa. Mirga barattootaa muslimaa kabajaa!
Gali Ababor
@MohammadamminKassaw
ከጅማም ሆነ ከሌሎች የመብት ጥያቄዎች የምንረዳው አንድ ሐቅ ቢኖር:- መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!" የሚለውን ነው:: ለአመታት እሽሩሩ ሲባሉ የነበሩ አካላት በ3 ቀናት ትግል ከቦታቸው ተቀምጠዋል:: አሁንም ቢሆን ግን ትግሉ ሊቀጥል ይገባል ••• መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝምና:: ቅንጣት ታክል መብት እስካትሸረፍ ድረስ ትግል ያሻል!
https://t.me/EHEMSU
በጅማ ያሉ እህቶች ዛሬም ከክብራቸው ጋር ገብተዋል!
ትግሉ ይቀጥላል!
https://t.me/EHEMSU
ትምህርት ሚኒስቴር በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተፈፀመ ያለውን ነገር አልሰማ ይሆን? ወይንስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ከተቋቋመለት አላማ ውጭ እየተንቀሳቀሰ ነው?
ጥያቄ አለን!
ከኒቃብ ባሻገር የአባ ጅፋሯ ጅማ ውስጥ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ጀለብያ: አማኢማ እና መሠል የሙስሊሞችን አልባሳት ይከለክላል!" አሉ::
ይህ በአባ ጅፋር ሀገር ያጠላው የአባ ኮስኳሴ እሳቤ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሊወገድ ይገባል::
https://t.me/EHEMSU
እስልምና ከዩኒቨርሲቲ ደጅ ተወልቆ የሚገባ ልብስ አይደለም!
https://t.me/EHEMSU
ክብር ከበር ተጥሎ አይገባም!
ትለብሳለችም
ትማራለችም !!
ፍትሕ ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
@MohammadamminKassaw
በደረቀ ሌሊት አፍነው የወሰዱትን ልጅ በደረቀ ሌሊት መልሰዋል!
ፍትሕ እስኪመጣ ትግሉ ይቀጥላል!
ፍትሕ ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
