ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

前往频道在 Telegram

This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.

显示更多
4 435
订阅者
-424 小时
-167 天
-9130 天
帖子存档
ዛሬ በፓርላማ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ "የኒቃብ ጥያቄ ጥያቄ ሆኖ የሚዘልቀው እስከመች ነው? አይሰለቻችሁም ወይ?" ብለው የጠየቁ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ "ኒቃብን ለብሶ መማር የኢትዮጵያ ሕግ እና ፖሊሲ አይፈቅድም!" ብለዋል:: @EHEMSU

ከጁሙዓ ሶላት ጋር ተያይዞ የፕሮግራም ማስተካከያ እንዲደረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በጠየቀው መሠረት በAAU School of commerce ማስተካከያ ተደርጓል:: በካምፓሱ
ከጁሙዓ ሶላት ጋር ተያይዞ የፕሮግራም ማስተካከያ እንዲደረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በጠየቀው መሠረት በAAU School of commerce ማስተካከያ ተደርጓል:: በካምፓሱ የት/ክ/ጊዜ ከጧት እስከ 5:30 የሚቆይ ሲሆን ከሰዓት ደግሞ 7:30 የሚጀምር ይሆናል:: ጥሩ ጅማሮ ነው ••• ሁሉም ካምፓስ ••• ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ••• ከKG ጀምሮም ያሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉ መሠል አርዓያነትን ሊከተሉ ይገባል:: ጁምዓ ቀን በሕግ እንደፀናው የትኛውም የመንግስት እንቅስቃሴ ከጧት እስከ 5:30 ሲሆን ከሰዓት ደግሞ ከ7:30 ጀምሮ ነው:: ይህንን መተላለፍ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ከመጣስ ባሻገር ሕግንም መተላለፍ ነው:: @EHEMSU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዩኒቨርሲቲው ከጁምዓ ሶላት ጋር ተያይዞ የሚወጡ ፕሮግራሞች ላይ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት በሚጥሱ መልኩ ማውጣቱን ተከትሎ እንዲያስተካክል የሳምንት
+3
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዩኒቨርሲቲው ከጁምዓ ሶላት ጋር ተያይዞ የሚወጡ ፕሮግራሞች ላይ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት በሚጥሱ መልኩ ማውጣቱን ተከትሎ እንዲያስተካክል የሳምንት ቀነ- ገደብ መስጠቱን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ለኮሌጅ ዲኖች ማስተካከያ እንዲያደርጉ በኢሜይል አሳውቋል! እንደሚታወቀው በጁምዓ ቀን የትምህርት ተቋማትም ሆኑ የትኛውም የመንግስት ተቋማት የስራ ሰዓታቸው ከጧት እስከ 5:30 ሲሆን ከሰዓት ደግሞ ከ7:30 ጀምሮ ነው:: ሆኖም የትምህርት ተቋማትና አየር መንገድ በተደጋጋሚ ጥሰት ሲፈፅሙ ተስተውሏል::

የህዝብ ተወካይ ካሉ እንዲህ ነው ••• ወ/ሮ ኸዲጃ! ወ/ሮ ኸዲጃ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔን ተከራክራ የሙስሊም ተማሪዎችን ጥያቄ አቅርባለች:: "የሙስሊሙ በዓል በደረሰ ቁጥር ትምህርት ሚኒስቴር ፈተና በበዓል ቀን የሚያወጣው ለምንድን ነው?" ብላ ጠይቃለች:: ደጋግመው የሚሰሩትን ስህተት እስኪስተካከሉ ድረስ በአደባባይ ደጋግሞ መጠየቅ ያሻል ••• ጀግኒት! @EHEMSU

ከኢፍጣር መልስ ••• ከዒድ ማግስት ___ ዩኒቨርሲቲዎች! • ብዙ ዩኒቨርሲቲዎች በረመዳን የኢፍጣር ድግስ አሰናድተዋል:: ሙስሊም ተማሪዎች ከኢፍጣር ጋር በግቢ ውስጥ በጀመዓ በአደባባይ ሰግደዋል::
ከኢፍጣር መልስ ••• ከዒድ ማግስት ___ ዩኒቨርሲቲዎች! • ብዙ ዩኒቨርሲቲዎች በረመዳን የኢፍጣር ድግስ አሰናድተዋል:: ሙስሊም ተማሪዎች ከኢፍጣር ጋር በግቢ ውስጥ በጀመዓ በአደባባይ ሰግደዋል:: ሶላት ስለማያልፍ ሰው እያለም ለግል መስገዱ ክልክል ስለሆነ በጀመዓ ሰግደዋል:: ለምን በጀመዓ ሰገዳችሁ ብሎ የከለከላቸውም አልነበረም:: ለመከልከልም የተክለፈለፈ አልነበረም:: ይልቁኑም ዩኒቨርሲቲዎቹ ፎቶ ለማንሳት ተጣድፈው የተነሳውንም በይፋ ለሕዝብ ለቀዋል:: በዚያ ውስጥ የተረበሸም ሆነ መብቱ የተነካበት የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ክፍል የለም:: • ከሶላት ባሻገር ሁሉም ሙስሊም ለኢፍጣሩ ሐይማኖቱ ያዘዘውንና እርሱ ይሆነኛል ብሎ የለበሰውን አለባበስ ለብሶ ነው የተሰለፈው:: አለባበሱ የነካው ግለሰብም ሆነ ያጎደለው እሴት የለም:: ይልቁኑም የሙስሊም ተማሪዎችን እሴት አክብሮ ለዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ውበት ሆኗል:: • በዒድም ላይ የተስተዋለው ተመሳሳይ ነገር ነው:: ■ ከኢፍጣር መልስ _ ከዒድ ማግስት ያለውን ስናይ ግን አሁንም ድረስ ሶላት እና ኒቃብ ላይ ችግር ያለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች አሉ:: አሁንም ድረስ የጀመዓ ሶላትን በመመሪያ የሚከለክሉ ኒቃብንም የሚከለክሉ ግቢዎች አሉ:: ቢቻል በረመዷኑ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የታየውን መከባበር አይተው ቢያከብሩ ጥሩ ነው:: ካልሆነ ደግሞ ሙስሊሙ ተማሪ በፍትሕ እና እውነት ላይ ቆሞ ፍትሕ እስኪሰፍን ሊጠይቅ እና ሊታገል ይገባል:: @EHEMSU

ዒድ ••• በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ!‌‌ @EHEMSU
+9
ዒድ ••• በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ!‌‌ @EHEMSU

ዒድ ••• በድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ! @EHEMSU
+2
ዒድ ••• በድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ! @EHEMSU

ዒድ ••••• በወሎ ዩኒቨርሲቲ !
+6
ዒድ ••••• በወሎ ዩኒቨርሲቲ !

ዒድ ••• በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ! በAAU የጥቁር አንበሳ ካምፓስ ሆስፒታል ከተማሪዎቹ ባሻገር በሆስፒታሉ ካሉ ከ300 በላይ ታካሚዎች ጋር ዒድን አክብሯል! @MohammadamminKassaw
+2
ዒድ ••• በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ! በAAU የጥቁር አንበሳ ካምፓስ ሆስፒታል ከተማሪዎቹ ባሻገር በሆስፒታሉ ካሉ ከ300 በላይ ታካሚዎች ጋር ዒድን አክብሯል! @MohammadamminKassaw

Eid Mubarak! Gooftaan Hojii gaggaarii keenna nurraa haa qeebalu. Iidni iida gammachuu kan barakaa isiniif haa ta'u. firaa fi maatii keessa hunda waliin yeroo gaarii. @EHEMSU

ዒዱኩም ሙባረክ! ኢዱ ነገ መሆኑ ተረጋግጧል:: ቀሪ ዘመናችሁ እንደ ለይለተል ቀድር ሰላም እና ሰኪና የሞላበት ይሁን !" @MohammadamminKassaw
ዒዱኩም ሙባረክ! ኢዱ ነገ መሆኑ ተረጋግጧል:: ቀሪ ዘመናችሁ እንደ ለይለተል ቀድር ሰላም እና ሰኪና የሞላበት ይሁን !" @MohammadamminKassaw

የዒድ ቀንን ለመወሰን የሳዑዲ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተሰይሟል:: ከደቂቃዎች ቡሃላ ውጤቱ የሚታወቅ ይሆናል::
የዒድ ቀንን ለመወሰን የሳዑዲ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተሰይሟል:: ከደቂቃዎች ቡሃላ ውጤቱ የሚታወቅ ይሆናል::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ- ግብር አዘጋጅቷል! መጋቢት 17/2017 ዓ.ል የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለሙስሊም ተማሪዎች
+6
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ- ግብር አዘጋጅቷል! መጋቢት 17/2017 ዓ.ል የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ -ግብር አዘጋጅቷል::

ጂግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጅቷል! በትላንትናው እለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር በሺር አብዱላሂ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጅግጂጋ ዩኒቨርሲቲ
+3
ጂግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጅቷል! በትላንትናው እለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር በሺር አብዱላሂ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጅግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሆነ የኢፍጣር መርሐ- ግብር ተዘጋጅቷል:: ተማሪዎች ከአመራሮቹ ጋር በመሆን በምግብ አዳራሹ ውስጥ የጀመዓ ሶላትንም ከውነዋል::

በድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ የነበረ የኢፍጣር መርሐ- ግብር:: ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጋራ አፍጥረው ነበር::
+2
በድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ የነበረ የኢፍጣር መርሐ- ግብር:: ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጋራ አፍጥረው ነበር::

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች ልዩ የሆነ የኢፍጣር መርሐ- ግብር አሳውቋል! በመጋቢት 17/2017 ዓ.ል የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች ልዩ የሆነ የኢፍጣር መርሐ- ግብ
+5
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች ልዩ የሆነ የኢፍጣር መርሐ- ግብር አሳውቋል! በመጋቢት 17/2017 ዓ.ል የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች ልዩ የሆነ የኢፍጣር መርሐ- ግብር አዘጋጅቷል:: በዝግጅቱ የዩዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋሲል ደሊልን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል:: ተማሪዎችም መሠል ፕሮግራሞች ዩኒቨርሲቲው ከተማሪዎቹ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት እንደሚያግለብት ገልፀዋል::

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለወራቤ ማህበረሰብ እና ለወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ- ግብር አዘጋጅቷል! በመጋቢት 18/2017 ዓ.ል የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ያዘጋጀ ሲሆን
+6
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለወራቤ ማህበረሰብ እና ለወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ- ግብር አዘጋጅቷል! በመጋቢት 18/2017 ዓ.ል የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ያዘጋጀ ሲሆን በመርሐ-ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጅነር ተውፊቅ ጀማልንና የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ታድመዋል::

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ- ግብር ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል:: በኢፍጣር ፕሮግራሙ ላይ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአብሮነ
+4
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር መርሐ- ግብር ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል:: በኢፍጣር ፕሮግራሙ ላይ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአብሮነት የተሰባሰቡ ሲሆን የጀመዓ ሶላትንም ከውነዋል! @MohammadamminKassaw

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ! መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙ 200 ተማሪዎችን እና ከማህበረሰቡ ውስጥ የተውጣጡ የሐይማኖት አባቶችን ያሳተፈ የኢፍጣር ፕሮግራም እንዳዘጋ
+4
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ! መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙ 200 ተማሪዎችን እና ከማህበረሰቡ ውስጥ የተውጣጡ የሐይማኖት አባቶችን ያሳተፈ የኢፍጣር ፕሮግራም እንዳዘጋጀ አሳውቋል:: ከኢፍጣር ቡሃላ ተማሪዎች የጀመዓ ሶላት የሰገዱ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችም መልዕክቶችን አስተላልፈዋል::

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ! በዛሬው እለት ማለትም መጋቢት 19/2017 ዓ.ል አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች በዋናው ግቢ ታላቅ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጅቷል
+8
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ! በዛሬው እለት ማለትም መጋቢት 19/2017 ዓ.ል አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች በዋናው ግቢ ታላቅ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጅቷል:: በዝግጅቱ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በሐይማኖት እሴቶች መካከል መከባበር እንዲኖር ለማድረግ እንደሆነ ተወስቷል:: ከዚህም በተጨማሪ የተማሪዎች ህብረት አመራሮች እና የሌላ እምነት ተከታይ ተወካዮች ተገኝተው የፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነዋል::