不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች | Amazing Facts 💡
前往频道在 Telegram
😊 እንኳን ወደ "4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች" ቻናላችን በሰላም መጣችሁ ! 🎙 ይህ ቻናል ያልተወቀውን አስገራሚ ነገር በቪዲዮ፣ በፎቶ እና በጽሁፍ የምታገኙበት ቦታ ነው ! . . 📨 ለማስታወቂያ ስራ: 💬 መወያያ: https://t.me/+h34iz-kYQ6wzNjNk
显示更多2 631
订阅者
-224 小时
+177 天
+830 天
525
帖子浏览量
~ 26724 小时
~ 33448 小时
19.93%
参与率
~ 3
每日帖子数
吸引订阅者
九月 '26
九月 '26
+17
在0个频道中
八月 '26
+116
在0个频道中
Get PRO
七月 '26
+99
在1个频道中
Get PRO
六月 '26
+81
在1个频道中
Get PRO
五月 '26
+94
在2个频道中
Get PRO
四月 '26
+86
在1个频道中
Get PRO
三月 '26
+153
在0个频道中
Get PRO
二月 '26
+139
在1个频道中
Get PRO
一月 '26
+190
在9个频道中
Get PRO
十二月 '25
+195
在0个频道中
Get PRO
十一月 '25
+155
在2个频道中
Get PRO
十月 '25
+92
在0个频道中
Get PRO
九月 '25
+10
在0个频道中
Get PRO
八月 '25
+24
在0个频道中
Get PRO
七月 '25
+44
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+40
在0个频道中
Get PRO
五月 '25
+50
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+98
在0个频道中
Get PRO
三月 '25
+217
在0个频道中
Get PRO
二月 '25
+551
在0个频道中
Get PRO
一月 '25
+714
在0个频道中
Get PRO
十二月 '24
+255
在8个频道中
Get PRO
十一月 '24
+1 337
在46个频道中
Get PRO
十月 '24
+163
在20个频道中
Get PRO
九月 '24
+460
在2个频道中
Get PRO
八月 '24
+344
在3个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 05 九月 | +2 | |||
| 04 九月 | +2 | |||
| 03 九月 | +6 | |||
| 02 九月 | +4 | |||
| 01 九月 | +3 |
频道帖子
✅ግርማዊ_ቀዳማዊ_ኃይለስላሴ✅
☆ በአለም እጅግ ከተከበሩ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች 20 የክብር ዶክተሬት ዲግሪ ያገኙት ግርማዊ ጃንሆይ ናቸው ።
☆ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በአለማችን ካሉ 20 ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ዲግሪ ተቀብለዋል! በየዩኒቨርሲቲዎቹም ተገኝተው ታላላቅ መሪዎችና ምሁራን በታደሙበት ውብ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡
☆ እኚህን ታላቅ ንጉስ የሚከተሉት የምድሪቱ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ አበርክተውላቸዋል፡፡
1️⃣ ግንቦት 20 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
2️⃣ ግንቦት 25 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ዶክትሬት ዲግሪ
3️⃣ ግንቦት 28 1946 ዓ.ም ከሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
4️⃣ግንቦት 30 1946 ዓ.ም ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
5️⃣ግንቦት 1946 ዓ.ም ከመክጊል ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
6️⃣ ሐምሌ 16 1946 ዓ.ም ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
7️⃣ ሐምሌ 29 1946 ዓ.ም ከአቴና ብሔራዊና ካፓዲስትሪን ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
8️⃣ 1946 ዓ.ም አትላንታ ጆርጂያ ከሚገኘው ሞርሐውስ ኮሌጅ የሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
9️⃣ ጥቅምት 10 1947 ዓ.ም ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣0️⃣ከቦን ዩኒቨርሲቲ በእርሻ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣1️⃣ ሕዳር 4 ቀን 19 49 ዓ.ም ከባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣2️⃣ ሐምሌ 5 ቀን 1951 ዓ.ም ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣3️⃣ ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም ከፕራግ ከቻርልስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣4️⃣ ህዳር 27 ቀን 1952 ዓም ከላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣5️⃣ መስከረም 22 ቀን 1956 ዓ.ም ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሑፍ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣6️⃣ መስከረም 18 ቀን 1957 ዓ.ም ከሩማኒያ ከቡካሬስት ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣7️⃣ መስከረም 30 ቀን 1959 ዓ.ም ከሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቻርልስ ሄሉ ባሉበት በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣8️⃣ ሚያዚያ 24 ቀን 1960 ዓ.ም ከታይላንድ ከተማስት ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
1️⃣9️⃣ግንቦት 9 ቀን 1960 ዓም ከምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ
2️⃣0️⃣ ግንቦት 13 ቀን 1960 ዓም ከደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዶክሬት ዲግሪ ተቀብለዋል፡፡
ምንጭ፦ ከአጼ ኃይለስላሴ የታሪክ መጻሕፍት ስብስብ
| 2 | ያልተገኘው ነፍሰ ገዳይ
ከ19ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በምርመራ ያልተደረሰበት Jack ብቻ በሚል የመጀመሪያ ስሙ የሚታወቀው ነፍሰ ገዳይ 5 ሴተኛ አዳሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የተሰወረ ሲሆን ከአገዳደሉ ሁናቴ በማየት ወይ የቀዶ ህክምና ወይ የልኳንዳ ባለሙያ ይሆናል ተብሎ ተገምቷል። አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመንም ያለምንም ምክንያት የሰውን ደም የሚያፈስሱ ነፍሰ ገዳዮች የተበራከቱ ሲሆን በተለይም በምሽት እየጠበቀ የ93 ሰዎችን ነፍስ በአሰቃቂ ሁናቴ በመግደል Samuel Little በአሜሪካ የብዙ ሰው ህይወት የቀጠፈው ሰው ሆኗል
@FACT_433 💡 | 251 |
| 3 | የ22 ዓመቱ ማሙዱ ጋሳማ ከማሊ ተሰዶ በፈረንሳይ ፓሪስ ነበር የሚኖረው።
ጋሳማ በፓሪስ ከተማ ከሚገኝ አንድ አፓርታማ በረንዳ ላይ የአራት ዓመት ህፃን ልጅ ተንጠልጥሎ ይመለከታል፤ ግዚ ሳያጠፋ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ ወደ አፓርታማ በረንዳ በመውጣት የህፃኑን ያድነዋል ።
ጋሳማ ሰዎች ከታች ምድር እየተመለከቱ ያለምንም ማመንታት ከህንፃው ውጭ ወጥቶ በሰከንዶች ውስጥ ከሰገነት ወደ በረንዳ እየጎተተ ህፃኑን ከመሞት አድኖታል ።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከመድረሳቸው በፊት በፍርሃት የተዋጠውን ልጅ ከአደጋ ነፃ እንዲሆን አድርጎታል ።
የጋሳማ አስደናቂ የማዳን ስራ በቪዲዮ ተቀርጾ በዓለም ዙሪያ በፍጥነት ተሰራጨ፣ ጋሳማን ለድፍረቱና ለራስ ሰፊ አድናቆት አስገኝቶለታል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን 'በኤሊሴ' ቤተ መንግስት በግል አስጠርተው አመስግነውታል።የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጥቶት በፓሪስ የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እንዲቀጠርም ተደርጓል ።
በጎ መሰራት ለራስ ነው!!
--- | 243 |
| 4 | < የጃንሆይ ውሻ ሉሉ🐕🐕🐕🦺
ክፍል 1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
⭐፨...........የጃንሆይ ድንክዬ ውሻ የነበረችውን <ሉሉ> ጥግ ድረስ ያከብሯት የነበሩ ሲሆን፣ የሚሊተሪ ፕሮቶኮልን የጠበቀ ወታደራዊ ሰላምታ የሚሰጧትም ብዙሃን ሰዎች ነበሩ።
ሉሉን ውሻ ነሽ ብሎ የሚመታ ይቅርና በተጨማደደ የጥላቻ ገጽታው የተመለከተ ሰው ቢኖር ፀቡ ቀጥታ ከጃንሆይ ጋር እንደሆነ አሳምሮ ያውቀዋል።
ለተንኮል ቅርብ የሆነችው ሉሉ አንዳንዴ ስንት የወታደር ኮከብ የጫነ እና የተከበረ የሚሊተሪ ልብስ የለበሰ ጄኔራል ላይ ሽንቷን ብትሸና ትንፍሽ ብሎ የሚገስፃት የለም።
✅️በአንድ ወቅት ቤተ-መንግስት ግብዣ ላይ ያስቸገረቻቸውና እላያቸው ላይ እየወጣች ሙጥኝ ያለችባቸው አንድ ባለስልጣን ሊቆጧት ሞክረው ጃንሆይን ሲያዩ....<ወይግዱ> ብለው ሉሉን በአንቱታ ለማባበል ሞክረዋል። ውሻን <ወይግዱ> ብለው በትልቅ ሰው አክብሮት ከመጥራት በላይ ስልጣን ከየት ይገኛል?.... እናም....<ሉሉ> በእርግጥም በዚያ ዘመን ከሰው በላይ የምትፈራ ራሱን የቻለ ባለስልጣን ነበረች ቢባል ካላት ልቅ ነፃነት እና ገደብ-የለሽ መብት አንፃር አባባሌ ፈፅሞ ግነት የለውም።
፨...........ድንክዬዋ ሉሉ ከተንጣለለው ቤተ-መንግስት ውጪ አውሮፕላን ሁለተኛ ቤቷ ነው ቢባል ፈፅሞ ሐሰት የለውም።
እስኪ ጃንሆይ ከሄዱባቸው ሀገራት ያልሄደችበት ሀገር በምድሪቱ የትኛዋ ናት? ቢባል ከአውስትራሊያ ውጪ ማንንም አታገኙም። አውስትራሊያ ጥብቅ የእንስሳት ሕግ ያላት ሀገር ናት።
⭐ከእንስሳት ሕጎቿም መሃል የማይሻረው አንቀፅ ሉሉን ከኦሽኒያዋ ልሳነ-ምድር እንዳትረግጥ አግዷታል። ምክንያቱም <ማንኛውም ሰው የቤት እንስሳት ከሌላ ሀገር ይዞ ወደ አውስትራሊያ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው!> የሚል ህግ ያቺ ሀገር ካሰፈረች ዘመናት ተቆጥሯል። በእንዲህ አይነት ሀገሮች ደግሞ ህግ-ህግ ነው።
ለማንም ለማጎብደድ ተብሎ አይለወጥም። ስለዚህ በሕጉ መሠረት <ለማንኛውም ሰው ከተባለ ጃንሆይ መልአክ አይደሉም፤ ሉሉም ሰው አይደለችም!>..... ስለዚህ ከዚያ ሀገር ውጪ ሉሉ ዕድሜዋን ሙሉ አለሙን አካላለች። ይልቅ ከጉዞ እና ከመግቢያ ቪዛ ጋር በተገናኘ የሚገርመው ሉሉ ካናዳ የገባችበት መንገድ ነው።
በወቅቱ ኃይለስላሴ አሜሪካ፤ ሜክሲኮ እና አንዳንድ የካሪቢያን ሀገራትን በየተራ እየጎበኙ ቆይተው በመጨረሻ የጉዟቸው መደምደሚያ ከሆነችው ካናዳ ደረሱ።
ካናዳ ደግሞ እንደ-አውስትራሊያ ፅንፈኛ ህግ ባይኖራትም የቤት እንስሳ አንድ ሰው ይዞ መግባት ከፈለገ ከሶስት ወር በፊት ለሀገሪቱ መንግስት የማሳወቅ ግዴታ አለበት። ሉሉ ደግሞ ድንገት ጃንሆይን ተከትላ ወደአሜሪካ ዞን አመራች እንጂ ህጉ በሚጠይቀው መስፈርት ቀድማ በተጠቀሰው ጊዜ አፕላይ አላደረገችም።
ታዲያ ምን ይደረግ? የጉዞ ፕሮግራሙ ይሰረዝ ወይስ ካናዳን ጎብኝተው እስኪወጡ አሜሪካ በአደራ ትቀመጥ?...ይሄ ደግሞ ከአይናቸው እንድትርቅ ለማይፈልጉት ጃንሆይ የማይታሰብ ነው። በመጨረሻ ሉሉ ካናዳ የምትገባበት አንድ መላ በህጉ ክፍተት ውስጥ ተገኘ። | 342 |
| 5 | ✅አባትና ልጅ 🏰👑
💰በምስሉ ላይ አባቱ ኃይለ ሥላሴ ከልጃቸው ከልዑል መኮንን ጋራ ሆነው ይታያሉ 📸👨👦። ጃንሆይ ለልዑል መኮንን የተለየ ፍቅር እንደነበራቸው ይታያል 💖🤝።
እንደ መረጃችን ከሆነ ጃንሆይ ለልዑል መኮንን ካላቸው ውዴታ የተነሳ አልጋ ወራሽ ሊሆን አልፈቀዱም 🚫👑። በፓትርያርኩ (ባሲሎስ) ተቃውሞ ምክንያት ሳይሆን ቀርቷል ⚖️📜። ልዑል መኮንን በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው ተቀብሎ ነበር ተብሏል 🚗💔🕯።
Second son of Emperor Haile Selassie I (v) and Empress Menen of Ethiopia (v) 👑🇪🇹. He was made Mesfin or Duke of Harer in 1930 at the coronation of his parents 🎉📅. He married Sara Gizaw and had five sons 👨👩👧👦. He was killed in a car accident in Ethiopia in 1957 🚗💥 and is buried in the Holy Trinity Cathedral in Addis Ababa ⛪️📍.
Jemal abdulazuz
@FACT_433 💡 | 355 |
| 6 | አባባ ጃንሆይ ( አፄ ሀይለስላሴ ) ቶዮታ ለተባለው የጃፓን መኪና አምራች ኩባንያ መኪና እንዲሰራላቸው ትእዛዝ ይሰጣሉ ። የቶዮታም ስራ አስኪያጅ ለክብርዎ
የሚመጥን ምን አይነት አዲስ ሞዴል ይሰራልዎት ሲል ጥያቄ ያቀርባል ።
ጃንሆይም #ለአንድ ኩሩ ዘር የሚሆን ሞዴል ፈልስፉ ብለው ነገሯቸው ከዛ በኋላም የተሰራው ሞዴል " LAND CRUISER" ተብሎ እስከ አሁን ድረስ ለመኪና ብራንድ ሆኖ ያገለግላል
የምር ስለዚህ አስገራሚ ነገር የማታቁ ከሆነ Like👍
@amazing_fact_433 | 329 |
| 7 | በሰማይ ላይ የሚንሳፈፉት ደመናዎች ምን ያህል እንደሚመዝኑ ያውቃሉ? ☁️🐘
ደመናዎች በሰማይ ላይ እንደ ጥጥ ቀልለው ሲንሳፈፉ ስናይ ምንም ክብደት የሌላቸው ይመስሉናል። ነገር ግን እውነታው ፍጹም የተለያየ ነው!
ሳይንቲስቶች እንደሚያስረዱት፣ አንድ ተራ መካከለኛ መጠን ያለው ነጭ ደመና (Cumulus cloud) በአማካይ 500,000 ኪሎ ግራም (ግማሽ ሚሊዮን ኪሎ!) ይመዝናል!
☁️ ይህንን ክብደት ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ... ሰማይ ላይ የሚንሳፈፈው አንድ ደመና ወደ 100 የሚያህሉ ግዙፍ ዝሆኖች በአንድ ላይ ይመዝናል።
☁️ ታዲያ ይህን ሁሉ ከባድ ክብደት ይዘው እንዴት በሰማይ ላይ ሊንሳፈፉ ቻሉ? ምክንያቱ ደመናው የተሰራበት የውሃ ቅንጣት እጅግ በጣም ተበትኖ በሰፊ ቦታ ላይ ስለሚገኝ እና ከስር ያለው ሞቃት አየር ወደ ላይ ስለሚገፋው ነው። 😄
በሰማይ ላይ 100 ዝሆኖች የሚመዝን ነገር ተንሳፎ ማየት እንዴት ይደንቃል! ይህን አስገራሚ መረጃ ለወዳጆችዎ ያጋሩ። ☁️
@Amazing_fact_433 | 325 |
| 8 | ✔️ጉጉቶች አይኖቻቸውን ማንቀሳቀስ አይችሉም።አይኖቻቸው የሲሊንደር ቅርፅ ያለው ሲሆን ውስጡ በአጥንት የተያያዙ ናቸው።በዚህም ምክንያት ጉጉቶች Evolve አርገው አንገታቸውን ወደ ጎን 270° እንዲሁም ወደ ላይ እና ታች ደግሞ 90° ዲግሪ ድረስ ማዞር ይችላሉ።
@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433 | 531 |
| 9 | ስለ ሆሳዕና (Palm Sunday) የሚገርሙና ምናልባትም የማታውቋቸው እውነታዎች፦
"ሆሳዕና" የሚለው ቃል ትርጉም
ብዙዎቻችን "ሆሳዕና" ማለት የምስጋና ቃል ብቻ ይመስለናል፤ ነገር ግን ትርጉሙ "አሁን አድን" (Save us now/Please save) ማለት ነው። ሕዝቡ ኢየሱስን ሲቀበሉት "ጌታ ሆይ አሁን አድነን" ብለው እየለመኑትና እየጸለዩለት ነበር።
የአህያዋ ምስጢር (ሰላም እንጂ ጦርነት አይደለም)
በጥንት ዘመን ነገሥታት ለጦርነት ሲወጡ በፈረስ ላይ ይሳፈሩ ነበር። በሰላም ጊዜና ለደስታ ሲመጡ ግን በአህያ ላይ ይሳፈራሉ። ኢየሱስ በአህያ ላይ መሳፈሩ "እኔ የሰላም ንጉሥ እንጂ የጦርነት ንጉሥ አይደለሁም" የሚል ትልቅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው።
የዘንባባው (Palm) ምስጢር
ዘንባባ በዛ ዘመን "የድል" (Victory) ምልክት ነበር። ሰዎች ዘንባባውን መሬት ላይ ያነጠፉት ኢየሱስን እንደ አሸናፊ ንጉሥ ስለቆጠሩት ነው። እኛም ዛሬ በጣታችን ላይ የዘንባባ ቀለበት የምናደርገው ያንን የድል ምልክት ለማስታወስ ነው።
የሕፃናት ጩኸት
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው፣ በዛን ዕለት በቤተ መቅደስ ውስጥ በከፍተኛ ድምፅ "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ" እያሉ የጮሁት ሕፃናት ነበሩ። ሽማግሌዎቹና ፈሪሳውያኑ ዝም እንዲሉ ቢፈልጉም፣ ኢየሱስ ግን "እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ብሎ የሕፃናቱን ንጹሕ ምስጋና ተቀብሏል።
የኢትዮጵያ ሆሳዕና ልዩነት
በሌሎች ሀገራት ዘንባባውን ይዘው ብቻ ነው የሚሄዱት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግን ዘንባባውን ቀለበት፣ አክሊልና መስቀል አድርገን እንሰራዋለን። ይህ የሚያሳየው ኢየሱስን በልባችን አንግሰን፣ በመስቀሉ ድል ማግኘታችንን የምንገልጽበት የራሳችን ውብ ባህልና ዕምነት ነው።
እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
@FACT_433 💡 | 558 |
| 10 | ቅንነት የክቍ ቀን ስንቅ 🌟
እንዲህ እንደዋዛ ቀን ሳይጥላት በፊት ህንድ ውስጥ በምትገኝ ኪራላ በምትባል ከተማ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሂሳብ መምህርት ነበረች። አንድ ቀን የቀድሞ ተማሪዋ ባቡር ልትሳፈር ተሰልፋ ዘወር ስትል ከአመታት በፊት የሆነ ቦታ የምታውቀው ፊት ጋር ተገጣጠመች። ይሄንን ኑሮ ያጎሳቆለውን የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር የተፈራረቁበትን ፊት የት እንደምታውቀው ለማስታወስ ብዙ ጥረት ካደረገች በኋላ የቀድሞ ሂሳብ መምህሯ መሆኗን አስታወሰች።
ተማሪዋም ከሰልፉ መሀል ፈጠን ብላ በመውጣት ይቅርታ "አድርጊልኝ እና አንቺ ሂሳብ አስተማሪ አልነበርሽምን?" አለቻት። መምህርትም መለሰች፡ "አዎ ከአመታት በፊት የሂሳብ አስተማሪ ነበርኩ። ነገር ግን ጡረታ ስወጣ ደሞዜ ለኑሮ በቂ አልነበረም። ድህነት እና እርጅና ሲጫኑኝም ልጆቼ ጥለውኝ ሄዱ። አሁን ጭራሹን ደብዛቸው ጠፍቱዋል፣ የት እንደደረሱም አላውቅም። እኔም ይሄው ከባቡር ጣብያ ደጃፍ ምጽዋት እየለመንኩ የእለት ኑሮዬን እገፋለሁ" ብላ መለሰች።
ተማሪዋም ልጅ እያለች የአስተማሪዋን ቅንነት እና ለተማሪዎቹዋ የነበራትን ፍቅር ባሰበች ግዜ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። በአንድ እጁዋ እንባዋን እየጠረገች በአንድ እጅዋ መምህሩዋን ይዛ ወደቤቱዋ ተመለች። የመምህሩዋን ገላ አጥባ ልብሱዋን ቀይራ የእለት ጉርስም ሰጠቻት። ከዛም በሁዋላ ድሮ አብረዋት የተማሩትን ተማሪዎች በማስተባበር የመኖሪያዋን እና ለኑሮ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አመቻቹላት።
የራሱዋ ልጆች ቢሸሹዋትም ያስተማረቻቸው ልጆች ደረሱላት። ቅንነት እና በየተሰማሩበት መልካምን ሰርቶ ማለፍ የክፉ ቀን ስንቅ ይሆናል።
@FACT_433 💡 | 566 |
| 11 | በአለም ላይ በፍፁም የማይበላሽ ብቸኛው ተፈጥሯዊ ምግብ ማር እንደሆነ ያውቃሉ? 🍯
የሳይንስ እና የታሪክ ተመራማሪዎች በጥንታዊ ግብፅ ፈርኦኖች መቃብር ውስጥ ሲቆፍሩ... ከ3,000 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ የማር ማሰሮዎችን አግኝተዋል። በጣም የሚገርመው ነገር ግን ይህ ማር ዛሬም ድረስ ሳይበላሽ፣ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ እና መበላት የሚችል መሆኑ ነው!
ለመሆኑ ማር ለዘላለም ሳይበላሽ የሚኖረው በምን ምክንያት ነው?
1. ማር በተፈጥሮው በጣም ደረቅ እና አነስተኛ የውሃ መጠን ያለው በመሆኑ ባክቴሪያዎች በውስጡ መኖር አይችሉም።
2. ማር በውስጡ ያለው ፒኤች (pH) መጠን በጣም አነስተኛ በመሆኑ ማንኛውንም ተህዋሲያን ወዲያውኑ ይገድላል።
ስለዚህ ማርን "ጊዜ የማይሽረው ተአምረኛ ምግብ" ብንለው ማጋነን አይሆንም!
@FACT_433 💡 | 551 |
| 12 | በምረቃ ቀን የሚለበሰው ረጅሙ እና ከባዱ የምረቃ ልብስ (Gown) ፋሽን የመጣው ለክብር ተብሎ ሳይሆን ከቅዝቃዜ ለመከላከል እንደነበር ያውቃሉ? 😄
🎓ይህ አስገራሚ ታሪክ የሚጀምረው በ12ኛው እና 13ኛው ክፍለ ዘመን በአውሮፓ (እንደ ኦክስፎርድ ባሉ ጥንታዊ ዩኒቨርሲቲዎች) ውስጥ ነው::
🎓 በወቅቱ የዩኒቨርሲቲዎቹ ክፍሎች ምንም ዓይነት የማሞቂያ ሲስተም (Heating) አልነበራቸውም። ህንጻዎቹ ከድንጋይ የተሰሩ በመሆናቸው ክፍሎቹ እጅግ በጣም ይቀዘቅዙ ነበር።
🎓 ተማሪዎች እና መምህራን በክፍል ውስጥ ቅዝቃዜውን ለመቋቋም እና ሰውነታቸውን ለማሞቅ ሲሉ ረጅም፣ ወፍራም ጋውን እና ራሳቸውን የሚሸፍኑበት ኮፍያ (Hood) ማድረግ ጀመሩ።
🎓 በኋላ ላይ ዩኒቨርሲቲዎቹ ይህንን ልብስ በህጋዊ መንገድ(Officially) የተማሪዎች መለያ አደረጉት፤ በሂደትም ተሻሽሎ ዛሬ የምንለብሰው ታሪካዊ የምረቃ ልብስ ለመሆን በቃ!
@FACT_433 💡 | 564 |
| 13 | (The Kissing Bug) 🦟
ይህች ተባይ ስሟ ሲሰማ በጣም የፍቅር ይመስላል፤ “ሳሚዋ ተባይ” (Kissing Bug) ትባላለች 💋። ነገር ግን ፍቅሯ ፍጹም መርዛማ ነው ☠️።
ቀን ቀን አልጋህ ስር ወይም ግድግዳ ስንጥቅ ውስጥ ትደበቅና፣ ማታ መብራት ሲጠፋ ትወጣለች 🌙። የምትፈልገው የሰውን ፊት ነው።
በሰውነታችን ላይ ካሉ የቆዳ ክፍሎች ይበልጥ ለስላሳና ሞቅ ያለውን የከንፈር አካባቢ ትመርጣለች 🎯። ተኝተህ ሳለህ መጥታ ከንፈርህን ትስማለች (ደምህን ትመጣለች) 🩸።
ደምህን ጠጥታ ስትጠግብ፣ እዚያው ከንፈርህ ላይ አረጋግጣ (አይነምድር ጥላ) ትሄዳለች 💩። ያንን ቦታ በገደልከው ቁጥር ባክቴሪያው ወደ ደምህ ውስጥ ይገባል ⚠️። (የፍቅር መጨረሻዋ ይሄ ነው! 💔)
@FACT_433 💡 | 497 |
| 14 | 1959 አንድ ግለሰብ 24 ጥንቸሎችን አውስትራሊያ ውስጥ የለቀቃቸው ሲሆን፣ በአሁን ጊዜ ላድ በዝተው ተባዝተው በ70 ዓመታት ውስጥ ወደ 10 ቢሊዮን ያህል ናቸው 🫡
@FACT_433 💡 | 572 |
| 15 | እንቅልፍ የሚነሳው ገዳይ በሽታ (Fatal Familial Insomnia) 🧠❌
በአለም ላይ በጣም አስፈሪ የሚባል "ፋታል ፋሚሊያል ኢንስኦምኒያ" የተባለ ብርቅዬ የዘረመል (Genetic) በሽታ አለ። ይህ በሽታ የያዘው ሰው በአዋቂነት እድሜው ላይ ሲደርስ በድንገት ጨርሶ መተኛት ያቅተዋል። ምንም አይነት የእንቅልፍ ክኒን ወይም ማስታገሻ አይሰራም።
ታካሚው ለሳምንታትና ለወራት ሙሉ በሙሉ ሳይተኛ ይቆያል፤ በመጨረሻም አዕምሮው እረፍት በማጣቱ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ስራውን ያቆማል፣ ያብዳል፣ ከዚያም ህይወቱ ያልፋል።
@FACT_433 💡 | 516 |
| 16 | Heath Ledger
የ Jokerን ገፀባህርይ ግን እንደ እሱ የተጫወተው አለ?
የሚገርመው ነገር ሌጀር Batman Begins ላይ Batman እንዲሆኑ ዳይሬክተሩ ከፈለጋቸው አክተሮች መካከል አንዱ ነበር Heath ግን እንደዚ አይነት የComic Book ፊልሞችን መስራት አልፈልግም ብሎ ነበር ግን በኋላ ላይ ነበረ Batman Beginsን ካየ በኋላ ሀሳቡን የለወጠዉ
ለገፀባህርይዉ ለመዘጋጀት ሲል ለ 1 ወር ከ15 ቀን ራሱን አንድ ሆቴል ውስጥ አሽጎ ሲያዘጋጅ ነበር እነዚህ ራሱን ከአለም አግልሎ የቆየባቸው 45 ቀናት ካራክተሩን ለማሳደግ በጣም ጠቅመውታል 👌 ብዙዎቹ ነገሮች :- አሳሳቁን ፤ከሰዉ መገለሉ፤ አካሄዱ በግል ህይወቱ ላይ ጭምር ትልቅ ችግር ፈጥሮበት ነበር
ካራክተሩን ተለቅ አድርጎ ለማሳየት ብዙ ለፍቷል። ተሳክቶለታልም!
ማንኛውም የድብድብ Scene ሲሰሩ Batmanን ሆኖ ለተወነው Christian Bale የእውነት እንዲመታው በተደጋጋሚ ይጠይቀው ነበር በተለይ Famous በሆነው የምርመራ Scene ላይ ብዙ ቡጢ ከChristian ቀምሷል።
እንዲሁም ብዙ ነገሮችን Improvise(ከስክሪፕት ላይ የሌለ ነገር መጨመር) አርጓል ብዙዎቹ የJoker አስደናቂ፣ አስቂኝ እና አስፈሪ ሚባሉ ሁኔታዎች እሱ Improvise ያረጋቸው ናቸው ከነዛ ውስጥ እስር ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ የሚያጨበጭብበት Iconic Scene አንዱ ነው። ሆስፒታሉንም የሚያፈነዳበት Sceneም እንደዚው በመጀመሪያ መፈንዳት የነበረበት በቴክኒክ ችግር ሲዘገይ ቆሞ ሪሞቱን ሚጠቀጥቀው ከስክሪፕት ውጪ ነበር።
Heath እንደዚ የለፋበትን ስራውን አላየውም ፊልሙ ከመውጣቱ ስድስት ወር በፊት ነበር የሞተው።
@FACT_433 💡 | 539 |
| 17 | ጋሊልዩ ጋሊሌ 🔥
ለብዙ አመታት ፀሐይን በቴሌስኮፕ በማየት እና ለማጥናት በመሞከሩ ምክንያት አይኑ የታወረ ሳይንቲስት ነበረ።
ምድር ናት ፀሐይን የምትዞረው በማለቱ ለ8 አመት የታሰረ ለአልበረት አንስታይን ምርጡ ሳይንቲስት የነበረው ጋሊልዮ ጋሊሌ የተወለደው 1564 ነበረ።
ጋሊልዮ ጋሊሌ ቤተሰቦቹ በህክምና ዘርፍ ማለትም ሜድስን እንዲማር ቢገፍፉትም ለፊዚክስ እና ለሒሳብ ካለው ፍቅር የተነሳ ብዙ ሳይገፋበት ቀርቷል።
ጋሊልዮ መሬት ናት ፀሐይን የምትዞረው በማለቱ በወቅቱ እንግልት እና ለእስር የበቃው በዛ ጊዜ ይታመን የነበረውን ፀሐይ መሬትን እንደምትዞር ነበረ ይሄንን ሐሳብ በመቃረኑ ነበረ ለስር የበቃው።
እራሱ በሰራው ቴሌስኮፕ ጨረቃ ተራራ እንዳላት ጁፒተር የተባለ ፕላኔት ልክ እንደ መሬት የራሱ የሆኑ ጨረቃወች እንዳሉት ቀድሞ ያወቀ እንዲውም ጁፒተርን በራሱ ቴሌስኮፕ ቀድሞ ማየት የቻለ ሳይንቲስት ነበረ ።
በ1990 ናሳ ወደ ጁፒተር የላካትን እስፔስ ክራፍት በጋሊሎ ስም ሰይሟት ነበር ::
እጅግ የሚታወቅበት ግኝቱ ደግሞ ..ሁለት ነገሮች ወደ መሬት በእኩል ሰዓት ቢለቀቁ በእኩል ሰዓት መሬት ይነካሉ የሚለው ነው። ይሄንን እሳቤ የሰው ልጆች ጨረቃ ላይ አንድ የዶሮ ላባ እና መዶሻ ሞክረውት ተሳክቷል።
ይሄንን እሳቤ መሬት ላይ ብንሞክር መዶሻው ቀድሞ ይወድቃል ለምን?
gravity=9.81m/s*s ወይም አንድ ድንጋይ , የማንጎ ፍሬ ወዘተ ወደ ምድር ስትወድቅ ፍጥነቷ በአንድ ሰከንድ ውስጥ 9.81 መጠን እየጨመረ ይሄዳል እንደማለት ነው :: ለዚህ ቋሚ ቁጥር መገኘት አስተዋፆ ያደረገ አሳብ ነበረ።
እንዲሁም ሌሎች ግኝቶች አሉት....
@Amazing_Fact_433 | 537 |
| 18 | አውስትራሊያ ውስጥ በዝማሬዋ ትታወቅ የነበረች ብርቅዬ የወፍ ዝርያ በድንገት ዝማሬዋ ጠፍቶባት የተምታታና ለዛ የሌለው ዜማ እያሰማች ነው።
'ዘ ሬጀንት ሐኒ ኢተር' ተብላ የምትጠራዋ ወፍ በዓለም ለመጥፋት ከተቃረቡ የወፍ ዝርያዎች መካከል አንዷ ናት።
ከዘመናት በፊት የእሷ ዝርያ ወፎች በደቡብ ምሥራቅ አውስትራሊያ በብዙ ቁጥር ይኖሩ ነበር። አሁን ግን ከዛሬ ነገ ዝርያቸው ለዘላለሙ ይጠፋል ተብለው ከተሰጋላቸው ወፎች መካከል ሆናለች። . . .
✅ በዚህ 'ሬጀንት ሐኒ ኢተር' ዝርያ ውስጥ ከሚገኙ ወፎች ተደምረው በሕይወት የቀሩት 300 ብቻ ናቸው።
"ይህች ወፍ ለጊዜው ከዝርያዎቿ ጋር አብሮ ጊዜ ለማሳለፍ ዕድሉን አላገኘችም ነበር፤ ለዚያ ይሆናል ዝማሬዋን የዘነጋችው" ብለዋል ዶ/ር ሮዝ ክሬተስ።
ዶ/ር ሮዝ በአውስትራሊያ ካንቤራ ዩኒቨርስቲ አንድ የወፍ ዝርያዎች የጥናት ቡድን ውስጥ የሚሠሩ ሲሆን ዝማሬ የጠፋባትን ወፍ የዘመዶቿን የዝማሬ ቅኝት እያስተማሯት ይገኛሉ።
እነዚህ የወፍ ዝርያዎች በምድር ላይ ጥቂት የቀሩ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በአንድ አካባቢ አለመገኘታቸው ፈተና ሆኗል።
BBC | 508 |
| 19 | ክረምቱን Single ለሆናችሁ
በዝናብ መተቃቀፍ የፍቅረኛሞች ብቻ እንዳይመስልህ፤ ሲንግሎችም የሆነ የሳይንስና የተፈጥሮ በረከት አላቸው!
✅ ሳይንስ እንደሚለው ከሰው እቅፍ በላይ "" (ከበድ ያለ ብርድ ልብስ) በዝናብ ሰዓት ማቀፍ በሰውነታችን ላይ እኩል የደህንነት ስሜት ይሰጣል። ብርድ ልብስህ መቼም ቢሆን ጥሎህ አይሄድም፣ አይቀናም፣ ደግሞም በዝናብ መሀል "እንግባ" ብሎ አይጨቀጭቅህም!
✅አንድ ትኩስ የጂንጅብል ሻይ ወይም ቡና በሁለት እጅህ ጨብጠህ ስትይዝ፣ እጆችህ ላይ የሚፈጠረው የሙቀት ስሜት አንጎልህ ልክ የሰው እጅ እንደጨበጥክ አድርጎ እንዲያስብ ያደርገዋል። በአጭሩ፡ ማንም ባያቅፍህም፣ ማኪያቶህ ያቅፍሃል!
✅ ፍቅረኛሞች በዝናብ ውስጥ ተቃቅፈው "እርጥብ" ሲሆኑ እና ጉንፋን ሲያግዳቸው፣ አንተ ግን በሞቃት ክፍልህ ውስጥ ሆነህ በሰላም መጽሐፍህን ማንበብ ወይም ፊልምህን ማየት ትችላለህ። ያለምንም ጭቅጭቅ | 558 |
| 20 | በዝናብ መተቃቀፍ
✅በዝናብ ውስጥ መተቃቀፍ እንዲሁ ዝም ብሎ የፊልም ትዕይንት እንዳይመስልህ፤ ነገሩ እውነተኛ “የተፈጥሮ ቴራፒ” ነው! ለምን መሰለህ? ስንተቃቀፍ ሰውነታችን የደስታና የፍቅር ሆርሞን ያመነጫል። ውጪ ላይ ዝናብ ሲዘንብና ቅዝቃዜው ሲጨምር ደግሞ ሰውነታችን የሙቀት መጠንን ለማስተካከል ይበልጥ ወደ መጠጋጋት ያደላል። ይህ ደግሞ የደስታ ሆርሞኑን እጥፍ ያደርገዋል!
የዝናብ ጠብታ ድምፅ (Pluviophile ለምን እንደምንባል ያውቁታል) እና የሚወዱትን ሰው ማቀፍ በአንድ ላይ ሲደመሩ፣ በአንጎላችን ውስጥ የሚፈጠረውን ጭንቀት ሙሉ በሙሉ “Format” አድርገው ያጠፉታል።
በዝናብ መሀል ስትተቃቀፍ አለሙ ሁሉ የቆመ ያህል ይሰማሃል። ያ ቅዝቃዜና የዝናብ ድምፅ የአለምን ጩኸት ሲቀንስላችሁ፣ እናንተ ግን በራሳችሁ ሞቅ ያለ አለም ውስጥ ትሆናላች | 504 |
此内容仅面向 18 岁及以上用户
登录服务即表示您确认已年满 18 周岁。
