ch
Feedback
ዋን ፕላኔት ሚዲያ - One Planet Media

ዋን ፕላኔት ሚዲያ - One Planet Media

前往频道在 Telegram

እያዝናና፣ እያሳወቀ እያስተማረ ለዓለም መሻሻል የሚተጋ ሚዲያ!! JOIN Request ላኩ 👇👇👇

显示更多

📈 Telegram 频道 ዋን ፕላኔት ሚዲያ - One Planet Media 的分析概览

频道 ዋን ፕላኔት ሚዲያ - One Planet Media (@timihrt_minister22) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 31 628 名订阅者,在 教育 类别中位列第 6 021,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 070

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 31 628 名订阅者。

根据 26 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -1 448,过去 24 小时变化为 -42,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 0.57%。内容发布后 24 小时内通常能获得 0.26% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 181 次浏览,首日通常累积 81 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 1

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
እያዝናና፣ እያሳወቀ እያስተማረ ለዓለም መሻሻል የሚተጋ ሚዲያ!! JOIN Request ላኩ 👇👇👇

凭借高频更新(最新数据采集于 27 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 教育 类别中的关键影响点。

31 628
订阅者
-4224 小时
-3137
-1 44830
帖子存档
ትምህርት ቤት ወይስ የለውጥ ማዕከል? ‘’በበሻሌ ትምህርት ቤት የፈለቀው ሕይወት" ሚያዝያ 30፣ 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ ዋን ፕላኔት ሚዲያ "ውኃ ሕይወት ነው፤ ትምህርት ደግሞ የሕይወት መሠረት!" ትምህርት ቤት ማለት በግድግዳዎች የታጠረ የዕውቀት መቅሰሚያ ብቻ ሳይሆን፣ የማህበረሰብን ቁስል የሚፈውስና ጥማትን የሚቆርጥ የለውጥ ማዕከል መሆኑን ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ዳግም በተግባር አስመስክሯል። በቅርቡ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ያከበረው ተቋሙ፣ በዓሉን ያደመቀው በቃላት ብቻ ሳይሆን በበሻሌ አጸደ ሕፃናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚታየውን የመጠጥ ውኃ እጥረት በዘላቂነት የሚፈታ የከርሰ ምድር ውኃ በማስመረቅ ነው። ይህ በበሻሌ ምድር የፈለቀው የሕይወት ምንጭ ለተማሪዎቹ የጤና ዋስትና፣ ለወላጆቻቸው ደግሞ የአዕምሮ እረፍት ሆኖ ተገኝቷል። ከአገልግሎት ባሻገር የተተከለ አሻራ ዋን ፕላኔት ላለፉት ዓመታት ለዚሁ ትምህርት ቤት ያበረከታቸው ስራዎች ቁጥራቸው በርካታ ነው፦ ዘመናዊ የአጸደ ሕፃናት ክፍሎች እና ቤተ መጻሕፍት፤ የምርምር አድማስን የሚያሰፉ የአይሲቲ እና የሳይንስ ቤተ-ሙከራዎች፤ የተማሪዎችን አካላዊ ጥንካሬ የሚገነቡ የስፖርት ሜዳዎች፤ እንዲሁም ለኑሮ ተግባራዊ ዕውቀት የሚሰጡ የችግኝ ማፍያ እና የዶሮ ማርቢያ ቤቶች። ዛሬ ደግሞ እነዚህን ሁሉ አገልግሎቶች የሚያለመልም የውኃ ፕሮጀክት በማስመረቅ፣ ተቋሙ "ችግር ፈቺ ትውልድን መቅረጽ" የሚለውን መርህ መሬት ላይ አውርዶታል። የጋራ ፍቅር ውጤት በምርቃቱ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ልመንህ  ምህረቱ፣ ተቋሙ ለማህበረሰቡ እያበረከተ ያለውን ተከታታይ ድጋፍ በማድነቅ "ይህ የውኃ ፕሮጀክት ከጤና ባለፈ ለትምህርት ጥራት መሻሻል ቁልፍ ሚና አለው" ብለዋል። የትምህርት ቤቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘላለም አማረ በበኩላቸው፣ ይህ ስኬት የተገኘው በተናጠል ሳይሆን በወላጆች፣ በተማሪዎች እና በአጋዥ ተቋማት የጋራ "የፍቅር ድምር" መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዘላለም አክለውም፣ "ትምህርት ቤት ማለት የህንፃዎች ስብስብ ሳይሆን የማህበረሰብ ለውጥ ማዕከል ነው፤ እኛም ይህንን አርአያነት ያለው ስራ ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን" ሲሉ የላቀ ራዕያቸውን አጋርተዋል። ይህ በበሻሌ ምድር የፈለቀው የሕይወት ምንጭ፣ ለነገዎቹ የሀገር ተረካቢ ህጻናት ተስፋን ያበሰረ እና ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት በ20 ዓመት ጉዞው ካስመዘገባቸው ደማቅ የታሪክ ምዕራፎች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።

የዋን ፕላኔት የ20 ዓመታት የብርሃን እና የፅናት ጉዞ! በዋን ፕላኔት ሚድያ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ— ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል እ.ኤ.አ በ2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ በአንዲት አነስተኛ ጊቢ ውስጥ በ30 ህጻናት ብቻ የጀመረው ጉዞ፣ “እያንዳንዱ ልጅ ለዓለም ብርሃን የመሆን አቅም አለው” በሚል ትልቅ ራዕይ ታጅቦ ነበር። ባለፈው አርብ ግን ይህ ህልም እውን ሆኖ በአፍሪካ ሕብረት (AU Hall) ታላቅ አዳራሽ ውስጥ የድል ዝማሬ ሆኖ ተደምጧል፡፡ የስነ-ምግባር እና የእውቀት ጥምረት “የ20 ዓመታት የትምህርት ጉዞ በተግባር፦ ማህበረሰቡን ማገልገልና ማብቃት” በሚል መሪ ቃል የተከበረው ይህ በዓል፣ ትምህርት ቤት ከማስተማር ባለፈ ስብዕናን የመቅረጽ ተልዕኮ እንዳለው ያስመሰከረ ነበር። በትምህርት ቤቱ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ በአቶ ዘላለም አማረ እና በባለቤታቸው ወ/ሮ ጌይል አማረ የተመሠረተው ይህ ተቋም፣ የቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስትር አምባሳደር ገነት ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች እና ታዋቂ የትምህርት ባለሙያዎች በተገኙበት ታሪኩን በደማቅ ቀለም መዝግቧል። “ትምህርት ቤቱን ስንመሰርት ቀዳሚ ዓላማችን ከሂሳብና ከንባብ በፊት ለሥነ-ምግባር ቅድሚያ መስጠት ነበር” ሲሉ አቶ ዘላለም በንግግራቸው አስታውሰዋል። “ምክንያቱም እያንዳንዱ ልጅ በውስጡ ያለውን ብርሃን ካበራ፣ የአካዳሚክ እውቀቱ ለማህበረሰቡ የተሻለ ለውጥ ማምጫ መሣሪያ እንደሚሆን እናምናለን።” “የዓለም ብርሃን” በታሪክ መዝገብ በክብረ በዓሉ ላይ ሌላ ልዩ ትኩረት ስቦ የነበረው በትምህርት ቤቱ መስራች በአቶ ዘላለም አማረ የተጻፈው "The Light of the World" (የዓለም ብርሃን) የተሰኘው መጽሐፍ ምርቃት ነበር። መጽሐፉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተፃፈ ሲሆን የጸሐፊውን የግል የሕይወት ታሪክ ጉዞ እና ትምህርት ቤቱ ያለፈባቸውን አስቸጋሪ ፈተናዎች፣ አነቃቂ ስኬቶች እና የሁለት አስርተ ዓመታት ታሪካዊ ጉዞዎችን በዝርዝር የሚያስቃኝ ሲሆን፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎችም እንደ አርአያነት ቀርቧል። የአንድነት እና የልህቀት ውጤት በዕለቱ በተካሄደው የፓናል ውይይት፣ የቀድሞ እና የአሁኑ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች መምህራን እና የትምህርት ባለሙያ ስለ ትምህርት ቤቱ ማህበራዊ ተፅዕኖ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል እንዲሁም ለወደፊት የተቋሙ ጉዞው አመላካች ሃሳቦች ተንሸራሽረዋል። ተቋሙ ለአካዳሚክ ልህቀት ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች ማሰብን ለሚያውቁ የነገ መሪዎች መፍሪያ መሆኑን አሳይቷል። ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ ሰፊ ማሻሻያ እያደረገች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል ላለፉት 20 ዓመታት ያሳየው ስኬት ለዘርፉ እንደ ተምሳሌት ተጠቅሷል። አቶ ዘላለም በቀጣዮቹ ሁለት አስርተ ዓመታት ጥራት ያለው ትምህርትን በቴክኖሎጂ በማገዝ ለኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ ህጻናት በነፃ ተደራሽ የሚያደርግ የዲጂታል ፕላትፎርም በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉና፣ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ለትምህርት እንቅፋት የማይሆንበትን አዲስ የተስፋ ምዕራፍ እንደሚከፍት ገልጸዋል። ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል ዛሬ ከ1,200 በላይ ተማሪዎችን የሚያስተምር እና 250 ሰራተኞችን የያዘ የትምህርት ማዕከል ለመሆን በቅቷል። ከ20 ዓመት በፊት የበራው ያ ትንሽዬ ሻማ፣ ዛሬ የብዙዎችን መንገድ የሚያበራ ታላቅ ችቦ ሆኗል፡፡

የዛሬው መነፅር ፖድካስት! https://youtu.be/agpJvNHuMG0

ውድ የዋን ፕላኔት ሚዲያ ቤተሠቦች የዛሬውን ዝግጅታችንን እነሆ ብለናል:: https://youtu.be/Ui7GMYaM9xE

የዓለም መሻሻል ላይ ትኩረት የሚያደርገው 'ዓለም ታማለች' ፕሮግራም፣ ለአራት ተከታታይ ሳምንታት በሚቀርበው ዶክመንተሪ ድራማና ውይይት ሁለተኛ ክፍል፣ ከዝግ በሮች በስተጀርባ የሚፈጸመውን የቤት ውስጥ የህጻናት ጥቃት ጉዳይ ወደ እናንተ ያቀርባል። ይህ ፕሮግራም የህጻናት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ህጻናትን እውነተኛ ታሪክ የሚያሳይ ነው። እያንዳንዱ ክፍል ከጥቃቱ የስሜት ስቃይ አንስቶ የመፈወስን ጉዞ ያሳያል። የፕሮግራሙ ዋና አላማ የጥቃቱን የስነ-ልቦናዊ ጉዳት መግለጽና ለተስፋና ለለውጥ የሚበራውን ብርሃን ማሳየት ነው። ይህን ጠቃሚ ፕሮግራም ሁላችሁም እንድትመለከቱና የዋንፕላኔት ሚዲያ ቤተሰብ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን። https://youtu.be/K3fM3NCQAmA