ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS
前往频道在 Telegram
👉 "የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።" ሃርፐር ሊ Fiction (ልቦለድ), History (ታሪክ), Politics (ፖለቲካ), Psychology (ስነልቦና), Biography (ግለ-ታሪክ), Self-help(ራስ አገዝ),& Philosophy(ፍልስፍና) የሀገር ውስጥ & የውጪ ሀገር መጽሐፎችን ያገኛሉ!አስተያየትዎን እዚህ @Desutech_bot ያድርሱን
显示更多1 991
订阅者
-124 小时
-67 天
-5330 天
帖子存档
✨ከስህተታችን ምን እንማር
🗣 ቶማስ ኤዲሰን፦
ስለስህተቶቹ ሲያወራ እንዲህ ይላል "እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው" ይለናል። ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን። ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።
✍️ህልመኛው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
ውበትሽን ተመክተሽ የሰዎችን አድናቆት ሰምተሽ ፍቅርን አትግፊ፤የቃላት ጋጋታ ልብሽን እንዳያሳስተው፤በዚህ ምድር አንቺን ከልቡ እንዲያፈቅር የተፈጠረው አንድ ሰው ነው እናም የነሱ አድናቆት በዝቶ ያንን ሰው እንዳያሳጣሽ።
አንድ አሪፍ የእንግሊዞች አባባል አለ
<<❣❣ዕድለ ቢስ ቁንጅና ከሁነኛ ባል ይልቅ ብዙ አፍቃሪዎችን ይስባል❣❣>>
ዛሬ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ውበትሽን አይተው ወዳንቺ ሊመጡ ይችላሉ ግን እመኚኝ ማናቸውም ቢሆን አንቺን አያፈቅሩሽም፤እነሱ ፍቅር የያዛቸው ካንቺ ማንነት ሳይሆን ከውጫዊ ውበትሽ ጋር ነው ዛሬ ላይ ብዙ ነገር ሊያደርግልሽ ይችላል፤ምክንያቱም ቆንጆ ስለሆንሽ እሱ ቢተውሽ ሌላ ብዙ ፈላጊ እንዳለሽ ስለሚያውቅ።
⚡️ግን ደግሞ ነገ ከነገ ወዲያስ??? መቼስ እድሜ ልክ እንደዛ ቆንጆ ሆነሽ አትኖሪ ውበትሽ መርገፉ አይቀርም እና ያኔስ???
⚡️እውነት ያ ሰው በዛ ደረጃ ላንቺ ቦታ ይሰጥሻል???
በፍፁም……………መቼም ቢሆን አያደርገውም ምክንያቱም
እሱ ያፈቀረው ውበትሽን ነበር ዛሬ ላይ ደግሞ ያንን ውበት ካንቺ ሲያጣ ዞር ብሎ አያይሽም።
ስለዚህ ምርጫሽ ላይ በደንብ አስቢበት የቃላት ዶፍ ልብሽን አይበግረው ምናልባት እውነተኛ አፍቃሪሽ ምን እንደሚልሽ ግራ ገብቶት በዙሪያሽ እየተንከራተተ ይሆናል፤አርቆ ማሰብን አትርሺ።
➻..ይሄን መልክት ለሶስት ሰዎች ልካችሁ አነዛ ሶስት ሰዎች ለሌላ ሶስት ሶስት ሰዎች እንዲልኩ አስረዷቸው.........።
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
🎗ሁሉም ነገር ስለ #Consistency (ወጥነት) ነው በየቀኑ የምታጠና ከሆነ ወይም በቀን አንድ ምዕራፍ የምታነብ ከሆነ ፈተናዎች ሲመጡ ለመጻፍ ለመዘጋጀት ብዙም አትቸገርም። ከፈተና ቀን በፊት ሙሉውን መጽሐፍ ለማንበብ ምንም ነገር የማያነቡ እና ምንም የማያጠኑ አሉ, ለዚህም ነው የሚወድቁት።
🎗 በሳምንት ለ 5 ቀናት ለ 30 ደቂቃዎች ወደ ጂም በሚሄድ እና በሳምንት አንድ ጊዜ ለ 3 ሰዓታት በሚሄድ ሰው መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ለ 3 ሰዓታት በሳምንት አንድ ጊዜ የሚሄድ ሰው ወጥነት የለውም። በሳምንት 5 ቀናት የሚሄደው ወጥነት ያለው ነው. ለዚያም ነው, ለአጭር ደቂቃዎች ቢሄድም, በዓመቱ መጨረሻ ላይ ከሌላው የበለጠ ውጤት ይኖረዋል። የትኛው ቀን ሰውነቱ እንደተለወጠ እንኳን አያስተውሉም ወደ ጥሩ ብቻ ይለወጣል።
🎗 ከስኬት ወይም ከአስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ ቁሳቁሶችን ወይም መጽሃፎችን በተከታታይ የምትጠቀም ከሆነ ትለወጣለህ፣ ሃሳቦችህ ይለወጣሉ እና አስተሳሰባችሁም ይለወጣል። ለ 5 ዓመታት ያህል በፋይናንስ ላይ መጽሐፍትን ካነበቡ, በዚህ ጉዳይ ላይ ኤክስፐርት ይሆናሉ። ወጥነት ይኑርዎት! የዛሬን ስራ ለነገ አትተዉ። የዛሬዋ ቀን የአንተ ናት እግዚአብሔር ያዘጋጀልህ! ነገ ምን እንደሚይዝ አታውቅምና ዛሬውኑ ማድረግ ያለብህን አድርግ!
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
#አፋልጉኝ
ዓመታት ሆኖታል ከቤቱ ከወጣ
ማወቅ አልተቻለም መቼ እንደሚመጣ
አፋልጉኝ ፍቅርን ድንገት ካያችሁት
ወረታ ከፋይ ነኝ ከልቤ መልሱት
ሰው እኮ የጠፋው አፋልጉኝ የበዛው
ተስፋ እየቆረጠ ወጥቶ የሚቀረው
ቀድሞ ፍቅር ጠፍቶ ጥላቻ ነግሶ ነው
አፋልጉኝስ ማለት ዛሬ ፍቅርን ነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
📚ርዕስ:- የሕይወት መመሪያ
👤ትርጉም:- ሃኒም ኤልያስ
📜ዘውግ:- ሳይኮሎጂ
📅ዓ.ም:- 2009
📖የገፅ ብዛት:- 304
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
"ፍቅር ግንኙነት ሳይሆን የመሆን
ሁኔታ ነው"
ምንጭ ፦ ህያውነት (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ
ፍቅር ግንኙነት ሳይሆን የመሆን ሁኔታ ነው፤ ከማነም ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ አንድ ሰው ፍቅር ውስጥ ነው ወይም አፍቅሯል ሳይሆን የሚባለው <እገሌ ፍቅር ነው> ነው የሚባለው፡፡ በእርግጥ አንድ ሰው ፍቅር ሲሆን በፍቅር ውሰጥ ነው ያለው ነገር ግን ይህ ምርጫ ሳይሆን ውጤት ነው፡፡ ምንጩ ፍቅር መሆኑ ነው፡፡
ማን ፍቅር ሊሆን ይችላልን? ማን እንደሆናችሁ የማታውቁ ከሆነማ ፍቅር ልትሆኑ አትችሉም፡፡ ይልቁኑ ፍርሃት ትሆናላችሁ፡፡ ፍርሃት የፍቅር ተቃራኒ ነው፡፡ ሰዎች እንደሚያስቡት የፍቅር ተቃራኒ ጥላቻ አይደለም፡፡ ጥላቻ የፍቅር ተቃራኒ ሳይሆን ፍቅር ተገልብጦ ሲቆም ነው፡፡ እውነተኛ የፍቅር ተቃራኒ ፍርሃት ነው፡፡ ፍቅር ያሰፋል፣ ፍርሃት ያጠብባል፡፡ ፍርሃት ይዘጋል፣ ፍቅር ይከፍታል፡፡ ፍርሃት ያጠራጥራል፣ ፍቅር ያሳምናል፡፡ ፍርሃት ብቸኛ ያደርጋል፡፡ ብቸኛ ከማድረግም አልፎ ያጠፋል፡፡ የሌለ ሰው እንዴት ብቸኛ ይሆናል? እነዚህ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ደመናዎች፣ ፀሃይ፣ ከዋክብት በሙሉ እናንተ ውሰጥ ናቸው፡፡ ፍቅር ማለት ውስጣዊ ቁልፋችሁን ስታውቁ ነው::
ማንም ህፃን ከፍርሃት ነፃ ነው፤ ህፃናት የሚወለዱት ያለምንም ፍርሃት ነው፡፡ ማህበረሰቡ ፍርሃት አልባ እንዲሆኑ ቢረዳቸውና ቢደግፋቸው ዛፎችና ተራሮች ላይ እንዲንጠለጠሉ፣ ውቅያኖሶችንና ወንዞችን እንዲያቋርጡ በረዳቸው ነበር፡፡ ማህበረሰቡ ጀብደኛ እንዲሆኑ፣ ካረጀ እምነት ይልቅ የማይታወቀውን እንዲመረምሩ ቢያደርጋቸው ኖሮ፤ ታላላቅ የህይወት አፍቃሪዎች ባደረጋቸው ነበር፡፡ ይህ ነው እውነተኛ ሃይማኖት፡፡ ከፍቅር በላይ ሃይማኖት የለም፡፡
ተመሰጡ፣ ደንሱ፣ ዝፈኑ፣ ወደ ውስጣችሁ ጠልቀችሁ ግቡ፡፡ የአዕዋፋቱን ዝማሬ በአንክሮ አድምጡ፡፡ አበቦቹን በአድናቆት ተመልከቱ፡፡ አዋቂ አትሁኑ፤ ነገሮችን አትፈርጁ አዋቂ መሆን ማለት ይህ ነው ለእያንዳንዱ ነገር መደብ፣ ፈርጅ ማውጣት፡፡ ከሰዎች ጋር ተገናኙ፣ ከሰዎች ጋር ተቀላቀሉ፣ በተቻላችሁ መጠን ከብዙ ሰዎች ጋር ተገናኙ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተለያየ ሁኔታ የእግዚአብሄርን መልክ ያሳያል፡፡ ከሰዎች ተማሩ፡፡ አትፍሩ፡፡
ፍቅር እምብዛም የማይገኝ አበባ ነው፡፡ ብቅ የሚለው አንዳንድ ጊዜ ነው፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አፈቀርን ብለው የውሸት ኑሮ ይኖራሉ፡፡ እንደሚያፈቅሩ ያምናሉ፡፡ ከእምነት የዘለለ ግን አይደለም፡፡
ፍቅር ብርቅዬ አበባ ነው:: ብቅ የሚለው አልፎ አልፎ ነው፡፡ የሚከሰተው ፍርሃት ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ፍቅር የሚከሰተው በጣም መንፈሳዊ ሃይማኖተኛ ለሆነ ሰው ነው፡፡ ሁሉም ወሲብን፣ መላመድን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ፍቅርን ግን ሁሉም አያገኙትም፡፡
ፍቅር ድፍረት ይሰጣል፤ ፍቅር ፍርሃትን ያጠፋል ጨቋኞች የእናንተ ፍርሃት ጥገኛ ናቸው፡፡ አንድ ሺ አንድ ፍርሃት ይፈጥሩባችኋል፡፡ ስለዚህ በፍርሃት ትከበባላችሁ፤ ሥነ - ልቡናችሁ በፍርሃት ይሞላል፤ በውስጣችሁ ትሸበራላችሁ:: ፊታችሁ አንድ አይነት ገፅታ ብቻ ነው ያለው፣ ውስጣችሁ ግን በፍርሃት ድርብርብ የተሞላ ነው::
በፍርሃት የተሞላ ሰው ምርጫው ጥላቻ ብቻ ነው - ጥላቻ ተፈጥሯዊ የፍርሃት ውጤት ነው፡፡ በፍርሃት የተሞላ ሰው በብስጭት የተሞላ፣ ከህይወት የወጣ ነው፡፡ በፍርሃት የተሞላ ሰው ማረፊያው ሞት ይመስላል፡፡ ፈሪ ሰው ከህይወት በተፃራሪ ራሱን የሚያጠፋ ነው፡፡ ህይወት አደገኛ ትሆንበታለች፡፡ ለመኖር ማፍቀር ያስፈልጋል፡፡ ስጋ ለመኖር መተንፈስ እንደሚያስፈልገው፣ ለነፍስም ፍቅር ያስፈልጋታል፡፡ ፍቅር ደግሞ ክፉኛ ተበክሏል፡፡
የፍቅር ሃይላችሁን በክላችሁ በውስጣችሁ መከፋፈል ፈጥራችኋል፤ ውስጣችሁን ለሁለት ከፍላችሁታል፡፡ የርስ በርስ ግጭት ፈጥራችሁበታል፡፡ ሁልጊዜም በግጭት ላይ ናችሁ:: በዚህ ግጭት ሃይላችሁ ተሟጥጧል፡፡ ስለዚህም ህይወታችሁ ደስታ የራቀው ሆኗል፡፡ በሃይል የተሞላ ሳይሆን የደነዘዘ ጣዕም የሌለው፣ ብልህነት የሌለው ህይወት ሆኗል፡፡
ፍቅር ብልህነትን ይስለዋል፤ ፍርሃት ደገሞ ያዶለዱመዋል፡፡ ብልህ መሆን ማን ይፈልጋል? ስልጣን ላይ ያሉ ይህን አይፈልጉም፡፡ እናንተ ብልህ እንድትሆኑስ እንዴት ሊፈልጉ ይችላሉ? ብልህ ከሆናችሁ እቅዳቸውን ጨዋታቸውን ትነቁባቸዋላችሁ፡፡ ስለዚህ መሃይም እና የማይረባ እንድትሆኑ ይፈልጋል፡፡ ስራን በተመለከተ ውጤታማ እንድትሆኑ ይፈልጋሉ፤ ብልህ እንድትሆኑ ግን አይፈልጉም፡፡ በዝቅተኛ አቅማችሁ እንድትኖሩ ነው የሚፈልጉት፡፡
የሳይንስ ተማራማሪዎች እንደሚናገሩት የሰው ልጅ በመላ የህይወት ዘመኑ የአቅሙን አምስት በመቶ ብቻ ነው የሚጠቀመው፡፡ ተራው ሰው አምስት በመቶውን ከተጠቀመ ልዩ የሆነ ሰውስ? አልበርት አንስታይን፣ ሞዛርት፣ ቤትሆቨን? ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት በጣም ከፍተኛ ተሰጥኦ ያላቸው እንኳን ከአስር በመቶ በላይ አይጠቀሙም፡፡ እና የላቀ ችሎታ አላቸው የምንላቸው እንኳን አስራ አምስት በመቶውን ብቻ ነው የሚጠቀሙት፡፡
ሁሉም ሰው የአቅሙን መቶ በመቶ የሚጠቀም ቢሆን ይህች ዓለም ምን እንደምትመስል አስቡ.... ጣዖታት በምድር ቀንተው ምነው ምድር ላይ በተወለድን ይሉ ነበር፡፡ ምድር ገነት ትሆን ነበር፡፡ አሁን ግን ሱዖል ናት፡፡
የሰው ልጅ ብቻውን ቢተው፣ ሳይበከል ቢቀር .... ፍቅር ቀላል ይሆን ነበር፤ ምንም ችግር አይኖርም፡፡ ቁልቁል እንደሚወርድ ውሃ ወይም ሽቅብ እንደሚወጣ ትነት፣ እንደሚያብቡ ዛፎች፣ እንደ ዘማሪ አዕዋፋት ይሆን ነበር፡፡ ተፈጥሯዊና ህያው ይሆናል!
ነገር ግን የሰው ልጅ ብቻውን አልተተወም፡፡ አንድ ህፃን ሲወለድ ጨቋኞች ዘልለው ሃይሉን ያደቁታል፤ ሃይሉን ያዛቡታል፤ መኖር ያለበትን ያህል ሳይሆን የውሸት ህይወት እየኖረ እንደሆነ እንዳያውቅ፣ እየኖረ ያለው በእውነተኛ ነፍሱ እንደሆነ እንዳይገነዘብ ያደርጉታል፡፡ ለዛም ነው በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ስቃይ ውስጥ የገቡት - እነዚህ ሰዎች እንደተሰናከሉ ራሳቸውን እንዳልሆኑ፣ አንድ የተሳሳተ ነገር እንዳለ.... ይሰማቸዋል ።
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
📚ርዕሰ:- የቃየል መስዋዕት
📝ደራሲ:- ሰርቅ ዳ
📜ይዘት:-....
📖ገፅ ብዛት:- 303
📆የመጀመርያ እትም:- 1995
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
ከላይኛው የቀጠለ
እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡
ብቻ ያ የሻማው ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡ አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያዬ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ደመራ ከቆለለ በኋላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡
እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ የጎዳናው ጆን እኔ ለራሴ ሚስኪን የጎዳና ሰው አላለም የቻለውን ያህል አበራላት የሱን ብርሃን የተቀበሉ ደግሞ ህይወቷን በብርሃን አደመቁት፡፡ እንዴት ደስ ይላል ማህበራዊ ድህረ ገፅም ለዚህ መሰል ተግባር ሲውልና ሰው ሲያድን እንዴት ደስ ይላል፡፡
‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
የደግነት ጥግ !!
ድፍን ኬንያውያንን በእንባ ያራጨው ምስኪን ጎዳና ተዳዳሪ የሰራው ድንቅ ስራ!!
በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነላችሁ ኬንያዊው በፎቶ የምታዩት ጆን የተሰኘው ህፃን የጎዳና ተዳዳሪ የእለት ጉርሱን ለምኖ በረንዳ የሚያድር ምስኪን ህፃን ነው ታዲያ ጆን እንደለመደው ትራፊክ መብራት ላይ መኪኖች ሲቆሙ በመስኮት ሄዶ መለመኑን ተያያዘው ከበርካታ መኪኖች ገንዘብ ተቀብሎ ወደ አንዱ መኪና በመስኮት እጁን ይዘረጋል እጁን ሲዘረጋ የመኪናው መስኮት ሲከፈት ግላዲ ካማዳ ከተባለች ሴት ጋር ፊት ለፊት ይተያያል፡፡
ግላዲ ካማዳ ያረገችውን የኦክስጅን መተንፈሻ ምንድነው ብሎ ይጠይቃታል እሷም በሰው ሰራሽ መተንፈሻ ኦክስጅን የምትተነፍስ አይኗም በቅጡ የማያይ በእግሯ መንቀሳቀስ የማትችል በየእለቱ ጤና ፍለጋ ሆስፒታል የምትንከራተት መታከሚያ ገንዘብ ያጣች 7 ዓመት ሙሉ በዚህ በሽታ የምትሰቃይ ምስኪን ሴት መሆኗን ትነግረዋለች፡፡
ይህንን ያየው የጎዳናው ህፃን ጆን እንባውን መቆጣጠር አቅቶት ለልመና የዘረጋውን እጁን ሰብስቦ የለመናትን ጥቂት ገንዘብ ታከሚበት ብሎ ይሰጣታል፡፡ እንባውና ሁኔታው የገረማቸው መንገደኞችም በሁኔታው ተደንቀው የልጁን የሃዘን ገፅታ እንዲህ በምስል አስቀሩት፡፡
ታዲያ ይህንን ምስል በፌስቡክ ይለቁታል ድፍን ኬንያ ይህንን ምስል ተቀባበለው ሁሉም የልጁ ሃዘን አሳዘነው ይሔ ልጅ ምንም ሳይኖረው የዳቦ መግዣውን ከሰጠ እኛስ ብለው ለህክምና የተጠየቀችውን 4 ሚሊዮን ሽልንግ እንዲሞላ ያቅማቸውን አደረጉላት፡፡
ዛሬ ግላዲ በዚህ በጎዳና ህፃኑ ጆን ተግባር ለህክምና የሚሆናት ገንዘብ በህዝብ መዋጮ ተሟልቶ ወደ ህንድ ተጉዛ ታክማ ኦክስጅኗን ጥላ ዛሬ በነፃነት ትተነፍሳለች ትንቀሳቀሳለች፡፡
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
የሚፈልጉትን ቻናል ይቀላቀላሉ !
📲 የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለማግኘት፦
👇👇👇👇👇👇👇👇
🔗 ĐESU TECH TIPS
📚ትምህርታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔗 GENIUS ACADEMY
📖መጽሐፍቶችን በ PDF ለማግኘት፦
👇👇👇👇👇👇👇
🔗 ET~ BOOKS
📚ርዕስ:- የተውኔት ድርሰት አፃፃፍ ዘዴ
📝ደራሲ:- ፋንታሁን እንግዳ
📖ገፅ ብዛት:- 236
📆ዓ.ም:- 2005
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
📚ርዕስ - የኦዴሳ ማህደር ( ፋይሎች )
📝ደራሲ - ፍሪድሪክ ፎርሲዝ
👤ተርጓሚ - ጋሽዬ ማሞ ውድነህ
📜ዘውግ - እውነተኛ ታሪክ | Espoinage |
📅የህትመት ዘመን - 1970
📖የገፅ ብዛት - 299
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
✨((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))
➽ በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣
➽ አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥፥
➽ አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥
➽ ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥
➽ አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣
➽ በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣
➽ ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣
➽ ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ
➽ እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል
➽ በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣
➽ የአንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣
➽ ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣
➽ ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣
,
…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል
➽ አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ፣
➽ እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥
ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣
➽ 5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …
➽ ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣
➽ ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣
➽ የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣
➽"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥
➽ ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣
➽ በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ ፣
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
"ስንቴ ወደክ "
ጠፋኝ ቁጥር..
"እንዴት ወደክ?"
በሰዉ ሻጥር.....
"እያወከዉ"
ምኑን???.....
"አጣጣሉን...?"
ባዉቀዉማ መችች ወድቃለዉ
ልጠለፍ ስል እነቃለዉ......
"እና እንዴት ነዉ..."
በፈግታ እያዋዙ
መልካም ወሬ እየነዙ
እምነት ስጥል በላያቸዉ
ይጠልፉኛል በሴራቸዉ...
"ያማል አይደል??"
አዋን በጣም
እምነት ሲጎል
ስብራቱ ቶሎ አይወጣም
"አይዞህ ...''
ህህ ለሁላችን....
ስለወደድኩት አጋራዋችሁ!
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1📚ርዕስ:- ዳና (the sky is falling )
📝ደራሲ:- ሲድኒ ሽልደን
👤ትርጉም :- አ.ሠ.ተ.
📜ይዘት:- ልቦለድ
📖የገፅ ብዛት:- 334
📆ዓ. ም:- 2000
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
#የተሳሳተ_ቁልፍ_ነው_የሰጠኸኝ
የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎ ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና “በአራት ቀናት ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈተው እና እሷ ያንተ ነች" አለው።
ፈረሱ ላይ ወጣና ወደ ጦር ሜዳ ጋለበ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው ደመና የመሰለ አቧራ አየ። ቆም ብሎ ሲመለከት ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየጋለበ ሲመጣ አየው።
"ምንድነው ችግሩ?" ንጉሱን ጠየቀው። ሙሳም ትንፋሹ እየቆራረጠ
“የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ” ሲል መለሰለት።
ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለ4 ቀናት ይቅርና ለ1ሰአት እንኳን አልጠበቀም።
እንደ “ጓደኞችህ” ከምትቆጥራቸው ሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ላይ ተጠንቀቅ። በትጋት ለምታገኘው ሃብት አደራ ልትሰጣቸው ትችላለህ - እነሱ ግን በቅርቡ እንድትሞት እየተመኙልህ ሊሆን ይችላልና እራስህን ከጓደኛህም ቢሆን መጠበቅህን አትዘንጋ።
መጽሐፉን ለማግኘት ይህን Link ይጠቀሙ 👉 ሰዎችን የማንበብ ጥበብ እንድታነብ ተጋብዘሀል።
ሠናይ ቀን!➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ 👉 @et_books1 👉 @et_books1
📚ርዕስ የፍቅርና የፍልስፍና አባባሎች
📝ደራሲ ሀይለማርያም አብዲሳ
📜ይዘት አባባሎች
📆ዓ. ም 2005
📖የገፅ ብዛት 162
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 @et_books1
👉 @et_books1
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
