ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS
前往频道在 Telegram
👉 "የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።" ሃርፐር ሊ Fiction (ልቦለድ), History (ታሪክ), Politics (ፖለቲካ), Psychology (ስነልቦና), Biography (ግለ-ታሪክ), Self-help(ራስ አገዝ),& Philosophy(ፍልስፍና) የሀገር ውስጥ & የውጪ ሀገር መጽሐፎችን ያገኛሉ!አስተያየትዎን እዚህ @Desutech_bot ያድርሱን
显示更多1 991
订阅者
-124 小时
-47 天
-5230 天
帖子存档
ለእናቴ
ሚስጥር ነው ሴትነት
እምቅ ሐያልነት ጥልቅ ረቂቅነት
በኅልዮ መዳፍ ወይ በገቢር ጥፍር
ደርሰው የማይነኩት ችሎ ማይቧጨር
የብርሐን ወስፌ የማለዳ ጨረር
ረቂቅ ምንጭነት የህይወት ዳና በር
ሴትነት ሐይል ነው ወሰንየለሽ ድንበር
አይኔን ያነቃሁ ለት
የተነፈስኩ እለት
ተማም ገጿን ያየሁ ክንፍ አልባ መልአክ
ያቺ ሴት በኔ አለም ሁለተኛ አምላክ
ጫንቃ ትከሻዋ በሸክም የማይጎዝል
ጫማ አልቦ እግሯ በህማም የማይዝል
ሴት ማለት ፣
የአፍታ ሽረት ናት ለዘለዓለም ቁስል ።
ህይወት አሸክማኝ ፥መከራና ደስታን፥እኩል እንደ አክርማ፤
ደስታውን ለኔ አርገሽ፥ እንባ መከራዬ፥ ባንቺ እየተቀማ።
አንቺ የምህረት ርስት ፥አንቺ የበረከት ጠል
አንቺ የስጦታ ምድር ፥ አንቺ የእምነት ጠለል
አንቺ የወይራ በትር ፥ አንቺ የወገን ኩራት
አንቺ ለጨለመ ዓለም፥ አንቺ የፋኖስ መብራት።
ለቡከን እግሬ መራመድ፥ እንዳይጠለፍ በእክል
እጄን ይዞ ያስቆጠረኝ ፥ጀግና ልብሽ ነው ትክክል።
ዝሁል አካልሽን ፥ለግፍ ባይለውም
ሰው ዝንጉ ፍጡር ነው፤
የፍጥረቱ ጌታ በቃሉ ያዘዘውን፥ በጀኝ አይለውም።
በሾተል አንደበት ፣በተርቡት ሰው ምላስ
አይተረተርም የልብሽ ጣቃነት፣
አለት ያንቺ መንፈስ።
ሴት እመ ብልሃት የዘዴ እናት አባቱ
ጥንትም መላ ካንቺ ነው ምንጩ ስር መሰረቱ
ብልሐትን እንደ ጠገራ፣ አገር ካንቺ ተውሶ
ለጠላት ሾህ የሆንበት ፣መሪር ልክ እንደ ኮሶ
በሽሮ በቆሎ ብቻ ፥ፋሲካ የምትደግሺ
በእፍኝሽ በያዝሽው ጥሬ፥ አገር የምትመልሺ።
በመናኛ በእራፊ ፥ገመና የምትሸፍኚ፥አገር የምታለብሺ
ሴት ማለት አንቺ ነሽ በቃ ሎሌ የምታነግሺ።
✍️©እስራኤል
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
