😒ትዝብት እና ብሶት😭
前往频道在 Telegram
232
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
ከኢትዮጵያ እስካሁን ያልወደቀው ላሊበላ ብቻ ነው
ተማሪው ሲወድቅ ዝም አልን
ህዝቡ ሲወድቅ ዝም አልን
ኑሮ ሲወድቅ እንደዛው
ይኸው አሁንማ መሬትም ካልወደኩ እያለችን ነው።
Btw ስልክ ላይ ተጥደን፣ በጭንቀት ተወጥረን፣ በሀሳብ ተውጠን የማንኖረውን መኪናና ቤት ስናልም ጊዜያችን ያልቅና ያለምነውን ኑሮ ሳንኖር እንሞታለን።
ማለም ሳይሆን መኖር እንጀምር!!!
ሠናይ ሠንበት🙏
@Tzibt
ገና ሀያዎቹን ሳንጀምር ተስፋ የቆረጠ ትውልድ መሆናችንን ስናውቅ እንዴት ልብ ይሠብራል😭 ... ተስፋ አንቁረጥ ሁሉም በጊዜው ነው የሚያበራው ጨረቃ በቀን ስትወጣ በፀሀይ ትሸፈናለች በሌሊት ስትወጣ ግን ሠው በብርሀኗ ብቻ ሳይሆን በውበቷም ይደሠታል አንዳንዱ የልብ ጓደኛውም ያደርጋታል። እኛም ጊዜያችን እስኪደርስ እየሠራን እንጠብቅ👍
@Tzibt
#የዘንድሮ_ፍቅር
አንቺ መቼ ገባሽ…!?
በኔ እንደበረታሽ
ወድሃለው ስትይ እኔም የማልልሽ
አፈቀርኩህ ስትይ መልሱን የማልነግርሽ
የስሜቴን ግለት አፍኜው በውስጤ
እንዳልተነካ ሰው አርፎ መቀመጤ
አይደለም በጭራሽ ሳልወድሽ ቀርቼ
የማልነግርሽማ ነው ገንዘብ አጥቼ
አፌን የለጎምኩት ስሜቴን ያነቅኳት
ላፍ መፍቻ የሚሆን ስለሌለኝ ነው ሀብት
በባዶ ሜዳ ላይ አፈቀርኩሽ ብልሽ
አውቃለው ጠንቅቄ ቅር ይለዋል ልብሽ
ለዚ እኮ ነው ውዴ…
ባንቺ መወደዱ ያላረገኝ ዘና
የዘንድሮ ፍቅር…
ገንዘብ ካልደገፈው ችሎ አይቆምምና
@Tzibt
#ህፃን_ሄቨን
ምነው ጋሞ ላይ የተናደው መሬት አንተን በቀበረ ነበር፣ የቦረናው ድርቅ አድርቆህ በነበር፣ የኤርታሌ እሳት በአፍህ ሲግቱህ ባሳየኝ🙏
ይቅርታ ይሄ ከህሊና በላይ ነው ምንም ማለት አልችልም፣ ፈጣሪ ምህረቱን ይላክልን!!!
