ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

UAT Tutorial Official

UAT Tutorial Official

前往频道在 Telegram

The first and Leading UAT Tutoring Platform in Ethiopia. ከቆይታችን በጥቂጡ : @Inside_UAT_Classes Ask: @UATsupport Call : 0907667755 web: www.havanacademy.com APP: https://t.me/UATtutorialofficial/13234 Register for Tutorial: @UATtutorial_bot

显示更多

📈 Telegram 频道 UAT Tutorial Official 的分析概览

频道 UAT Tutorial Official (@uattutorialofficial) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 342 名订阅者,在 体育 类别中位列第 4 574,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 479 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 342 名订阅者。

根据 28 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -1 182,过去 24 小时变化为 -36,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 6.46%。内容发布后 24 小时内通常能获得 3.39% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 926 次浏览,首日通常累积 486 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 1。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“The first and Leading UAT Tutoring Platform in Ethiopia. ከቆይታችን በጥቂጡ : @Inside_UAT_Classes Ask: @UATsupport Call : 0907667755 web: www.havanacademy.com APP: https://t.me/UATtutorialofficial/13234 Register for Tutorial: @UATtutorial_bot”

凭借高频更新(最新数据采集于 29 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 体育 类别中的关键影响点。

14 342
订阅者
-3624 小时
-2297 天
-1 18230 天
帖子存档
🔥 ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የመረጃ ሳምንት፤ ከነሐሴ 8–16፣ 2018 ቦታ፡ ዋና ካምፓስ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ጉዞዎን ከመጀመርዎ በፊት የሚያስፈልግዎትን መመ
🔥 ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የመረጃ ሳምንት፤ ከነሐሴ 8–16፣ 2018 ቦታ፡ ዋና ካምፓስ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ጉዞዎን ከመጀመርዎ በፊት የሚያስፈልግዎትን መመሪያ ሁሉ የማግኘት እድልዎ ነው! በመረጃ ሳምንት ውስጥ፣ የሚከተሉትን መረጃ ያገኛሉ • የመግቢያ መስፈርቶች • የማመልከቻ ሂደቶች • የመጀመሪያ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (UAT) • የስኮላርሺፕ አማራጮች (መንግስት፣ በግልና፣ ፕሬዝዳንታዊ) • ስለ ምደባ መረጃ ለጓደኞቻችሁ share አርጉላቸው @UATTutorialofficial

Register : @UATtutorial_Bot
Register : @UATtutorial_Bot

ዛሬ በከፍተኛ ቁጥር እየተመዘገባችሁ ያላችሁ ተማሪዎች እስከ ማታ ድረስ ሁላችሁንም Approve የምናደርግ ይሆናል። ስለሆነም በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን። ​👉 ለመመዝገብ: @UATTutorial_bot 👉 ለተጨማሪ መረጃ: @UATsupport Share: @UATTutorialofficial ​ስለ ትብብራችሁ እናመሰግናለን! 🙏

ከአራት ኪሎ እስከ ጥቁር አንበሳ—የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አጠቃላይ መረጃ! ​ህልማችሁ ያለበት ዲፓርትመንት የትኛው ግቢ እንደሚያስተናግደው አሁኑኑ እወቋቸው! 👇 ​🌤 የአየር ሁኔታ፦ የመጀመሪያዎቹ ወራት መጠነኛ ብርዳማ ሆኖ፣ ቀስ በቀስ ወደ ደስ የሚል ሞቃታማ አየር ይለወጣል። ​🏢 ዩኒቨርሲቲው በውስጡ ዋና ዋና ግቢዎች ያሉት ሲሆን፣ እያንዳንዱ ግቢ የተመደበበት የትምህርት ዘርፍ አለው፡ ​1. ስድስት ኪሎ (Main Campus) ➔ የማህበራዊ ሳይንስ ማዕከል (Social Sciences, Law, Education, Humanities & Journalism) ​ 2. አራት ኪሎ (College of Natural & Computational Sciences) ➔ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች (Computer Science, Mathematics, Physics, Biology, Chemistry, Geology) ​ 3. አምስት ኪሎ (AAiT - Addis Ababa Institute of Technology) ➔ የኢንጂነሪንግ ዘርፎች (Software, Electrical, Mechanical, Civil, Chemical, Biomedical Engineering...) ​ 4. ጥቁር አንበሳ (College of Health Sciences) ➔ የህክምና ትምህርት (Medicine, Dental Medicine) እና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ​ 5. ሰፈረ ሰላም ➔ የጤና ሳይንስ ዘርፎች (Pharmacy, Nursing, Public Health, Medical Laboratory, Anesthesia...) ​📍 6. ልደታ (EiABC) ➔ የህንፃና ከተማ ልማት ዘርፎች (Architecture, Construction Management, Urban & Regional Planning) ​7. ሜክሲኮ (School of Commerce) ➔ የንግድና ቢዝነስ ትምህርቶች (BAIS, Accounting, Marketing Management, Logistics, Management, Economics) ​8. ኤፍ.ቢ.ኢ / FBE Campus (ከ6 ኪሎ አቅራቢያ) ➔ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲግሪና ድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ​ 9. ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት (Yared School of Music) ➔ የሙዚቃ ጥበብ፣ ድርሰትና ቲዮሪ (Music Performance & Ethnomusicology) 10. አለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት (Alle School of Fine Arts) ➔  ቅርፃቅርፅ፣ ግራፊክስና አፕላይድ አርትስ ትምህርቶች ​ 11. ቢሾፍቱ ካምፓስ (ከአዲስ አበባ ውጭ - ቢሾፍቱ) ➔ የእንስሳት ህክምና እና እርሻ ሳይንስ (Veterinary Medicine & Agriculture) ​ ማስታወሻ፦ የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ኮርሶች በዋናነት በጋራ ካምፓሶች የሚሰጡ ሲሆን፣ ወደየተወሰኑት ካምፓሶች የምትዛወሩት ከፍሬሽማን በኋላ ዲፓርትመንት ስትመርጡ ይሆናል! ​ Join: @UATtutorialOfficial Tutorial : @UATtutorial_bot

🏆 የውድድሩ አሸናፊዎች የአርጀንቲና 🇦🇷 vs ስፔን 🇪🇸 የጨዋታውን ትክክለኛ ውጤት በትክክል ለገመታችሁ  ተማሪዎች እንኳን ደስላችሁ! ምንም እንኳን ለ 5 ተማሪዎች ሽልማት ያዘጋጀን ቢሆንም፣ ህጉን አሟልተው በትክክል የገመቱት 3 ተማሪዎች ብቻ በመሆናቸው አሸናፊ ሆነዋል! 📌የነጻ UAT Package አሸናፊዎች 1 @Dawa_29 2 @histrologist 3 @HenoK158 ሽልማታችሁን ለመቀበል contact us: @UATsupport ተሳትፏችሁ ላልተሳካላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣ ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን! ወደፊት ተጨማሪ አጓጊ ውድድሮች እና ሽልማቶች ስላሉን ይከታተሉን። 📚 join us: @UATtutorialOfficial

Due to a decrease of 10% in the price of tea per kg, Hermela buys 250 gm of tea more than before for 270 ETB. What is the original price of tea per kg? ኮመንት ላይ ይሄን የምመልስ ተማሪ? @UATtutorialOfficial

📌በUAT ፈተና ዕለት ምንም ነገር አዲስ እንዲሆንባችሁ አትፍቀዱ! ​በየዓመቱ በርካታ ተማሪዎች በUAT ፈተና የሚሸወዱት በዕውቀት ማነስ ሳይሆን ከኮምፒዩተር ሲስተሙ፣ ከሰዓት አቆጣጠሩ እና ከቴክኒክ
📌በUAT ፈተና ዕለት ምንም ነገር አዲስ እንዲሆንባችሁ አትፍቀዱ! ​በየዓመቱ በርካታ ተማሪዎች በUAT ፈተና የሚሸወዱት በዕውቀት ማነስ ሳይሆን ከኮምፒዩተር ሲስተሙ፣ ከሰዓት አቆጣጠሩ እና ከቴክኒክ አጠቃቀሙ ጋር በመታገላቸው ነው! ​ፈተናው ላይ ስትቀመጡ ሲስተሙ አዲስ ሆኖባችሁ ጊዜያችሁ እንዳያባክን፤ ከአሁኑ ተለማመዱ! 📍​UAT Simulation ምንድን ነው? ይህ ያለፉት 3 ዓመታት የUAT ፈተናዎችን እና አዳዲስ ጥያቄዎችን የያዘ ብቻ አይደለም! ልክ እንደ AAU Exam System የተሰራ እውነተኛ የፈተና Environment ነው! ​ከጥያቄዎቹ ባሻገር UAT Simulation ልዩ የሚያደርገው፡ ​📍 ትክክለኛውን የAAU Exam Interface: ልክ በፈተናው ዕለት የምታዩትን የስክሪን layout እና የጥያቄዎች አቀማመጥ አስቀድማችሁ እንድታውቁ ያደርጋል። 📍  በፈተናው ወቅት ሰዓትን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባችሁ ያስለምዳችዋል። 📍 የሲስተም ሕጎች: በፈተናው ወቅት ምን ማድረግ እንደምትችሉ እና እንደማትችሉ በግልጽ ያሳያቸዋል። ​ በUAT Simulation የተለማመደ ተማሪ በፈተናው ዕለት የፈተናው ሲስተም የለመደው፣ የጥያቄዎቹም Pattern አስቀድሞ የደጋገመው ይሆናል! 📋ለመመዝገብ 👉https://simulation.havanacademy.com ​📩 ለማንኛውም ጥያቄ👉@UATsupport ​📚 join us:@UATtutorialOfficial

Fully Funded scholarship opportunities at AAU with pocket money https://vt.tiktok.com/ZSXKeDbDN/

📖 Mathematics ASTU entrance exam 🏠ASTU ⏳2007 📚join:@UATtutorialofficial

📖 English ASTU entrance exam 🏠Astu  ⏳2007 📚join:@UATtutorialofficial

#Update version, please delete the previous one and Download this version የUAT ኮርስ መመዝገቢያ መመሪያ ✔️መጀመሪያ App-ውን ያውርዱ። ✔️Sign Up (መመዝገቢያ) የሚለውን ይጫኑ። ✔️ስማችሁን፣ ስልክ ቁጥራችሁን፣ ኢሜይላችሁን እና ሌሎች የሚጠየቁ መረጃዎችን በትክክል በመሙላት አካውንታችሁን ፍጠሩ። ✔️ከዚያ በኋላ በኢሜይላችሁ ወይም በስልክ ቁጥራችሁ Log In አድርጉ። ✔️በመነሻ ገጹ Explore Courses ወይም Explore Packages የሚለውን ምረጡ። ✔️UAT ወይም UAT Packages ብላችሁ ፈልጉ። ✔️የምትፈልጉትን ኮርስ ወይም ፓኬጅ ምረጡና Enroll አድርጉ። ምዝገባችሁ እስኪፀድቅ (Approved) ድረስ ጠብቁ። ✔️Learning ወደሚለው ገጽ ግቡ፤ እዚያም የUAT ቪዲዮ ትምህርቶች፣ ኖቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን በSmart Learning Environment ውስጥ ታገኛላችሁ። 🎓 አሁኑኑ ተመዝገቡና የUAT ዝግጅታችሁን ጀምሩ! @UATtutorialofficial

በ2017 ዓ.ም. UAT ወስዳ ፣ አሁን በኢትዮጵያ ታላቁ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲኒየር ተማሪ ናት። በዚህ Audio የUAT ጉዞዋን፣ ያጋጠሟትን ተግዳሮቶች እና የተማረችውን ልምድ ታካፍላለች። ተሞክሮዋ ለእናንተ ጠቃሚ እንደሚሆን እናምናለን። ለበለጠ መረጃ : @UATsupport 📞 0907667755 share : @UATtutorialOfficial

🔓 ሲሙሌሽን 1 አሁን በነፃ ተከፍቷል! ከአሁኑ ጀምሮ የUAT ጥያቄዎችን በነፃ መለማመድ ትችላላችሁ። የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተሉ፦ መጀመሪያ አካውንት ይፍጠሩ። ከዚያ ወደ አካውንታችሁ ይግቡ (Lo
+1
🔓 ሲሙሌሽን 1 አሁን በነፃ ተከፍቷል! ከአሁኑ ጀምሮ የUAT ጥያቄዎችን በነፃ መለማመድ ትችላላችሁ። የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተሉ፦ መጀመሪያ አካውንት ይፍጠሩ። ከዚያ ወደ አካውንታችሁ ይግቡ (Log in)። UAT Simulation ወደሚለው ክፍል ይሂዱ። በነፃ የተከፈተውን Simulation 1 በመጫን ወዲያውኑ መለማመድ ይጀምሩ። Simulation 1ን ከጨረሳችሁ በኋላ የውጤታችሁን (Screenshot) ላኩልን። ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሚቀጥሉትን Simulations በነፃ እንከፍትላችኋለን። ማስታወሻ: Simulation 9, 10, 11 እና 12 በቀጥታ ከቀደሙት ዓመታት የAAU UAT እውነተኛ ፈተና ጥያቄዎች የተዘጋጁ ናቸው። ስለዚህ ከእውነተኛው ፈተና በፊት የተሻለ ልምምድ እና ዝግጅት ያገኛሉ። 🎯 ዛሬውኑ ልምምድ ይጀምሩ፤ ለUAT ፈተና ያላችሁን ዝግጁነት ይፈትሹ! https://simulation.havanacademy.com @UATtutorialOfficial

የ2018 ብሔራዊ ፈተና ውጤት ምን ሊጠበቅ ይችላል? ካለፉት 4 ዓመታት የፈተና ውጤቶች አንድ ግልጽ ነገር ያሳያሉ፦ 2014: 3.3% 2015: 3.2% 2016: 5.4% 2017: 8.4% የማለፊያ መጠኑ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ መጥቷል። በተለይ በ2017 ዓ.ም. በኮምፒውተር (CBT) የተፈተኑ ተማሪዎች 21.7% ሲያልፉ፣ በወረቀት (PBT) የተፈተኑት ግን 4.4% ብቻ ነበሩ። ይህ ለ2018 ምን ማለት ነው? በዚህ ዓመት 300,000+ ተፈታኞች የሚሆኑት በCBT እንደሚፈተኑ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ፦ ✅ በካለፉት 3 ዓመታት የCBT ልምድ ተገኝቷል። ✅ የትምህርት ሚኒስቴር በመምህራን ስልጠና፣ በመሠረተ ልማት እና በፈተና ዝግጅት ላይ ብዙ ስራ ሰርቷል። ✅ የመማሪያ ፕሮግራሞች (Tutorial Programs) በእጅጉ ተስፋፍተዋል፣ ተማሪዎችም ከዚህ በበለጠ ዝግጁ ሆነው ወደ ፈተና ገብተዋል። ስለዚህ በ2018 ከዚህ በፊት ይልቅ ብዙ ተማሪዎች ሊያልፉ ይችላሉ ብሎ መጠበቅ ምክንያታዊ ነው። ግን ይህ ሌላ ፉክክር ያመጣል... ብዙ ተማሪዎች ካለፉ፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፉክክር ይጨምራል። በተለይ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) መግባት የሚፈልጉ ተማሪዎች የሚለያዩት ከእንግዲህ 12ኛ ክፍል ውጤት ብቻ አይሆንም፤ UAT ነው። 🎯 ማለፍ ብቻ አይበቃም፤ ከሌሎች በላይ መሆን ያስፈልጋል። UAT የሚያለያችሁ ፈተና ነው። ከዛሬ ጀምረው ይዘጋጁ! ለትቶሪያል ለመመዘገብ : @UATtutorial_bot lለመረጃ : @UATsupport

በ 1 ሚልዮን ብር ብቻ በ አዲስ አበባ ዩኒቨስቲ መዲስን እና ዴንታል መዲስን መማር እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?😂 https://vt.tiktok.com/ZSX7HJU3m/

የUAT ኮርስ መመዝገቢያ መመሪያ ✔️መጀመሪያ App-ውን ያውርዱ። ✔️Sign Up (መመዝገቢያ) የሚለውን ይጫኑ። ✔️ስማችሁን፣ ስልክ ቁጥራችሁን፣ ኢሜይላችሁን እና ሌሎች የሚጠየቁ መረጃዎችን በትክክል በመሙላት አካውንታችሁን ፍጠሩ። ✔️ከዚያ በኋላ በኢሜይላችሁ ወይም በስልክ ቁጥራችሁ Log In አድርጉ። ✔️በመነሻ ገጹ Explore Courses ወይም Explore Packages የሚለውን ምረጡ። ✔️UAT ወይም UAT Packages ብላችሁ ፈልጉ። ✔️የምትፈልጉትን ኮርስ ወይም ፓኬጅ ምረጡና Enroll አድርጉ። ምዝገባችሁ እስኪፀድቅ (Approved) ድረስ ጠብቁ። ✔️Learning ወደሚለው ገጽ ግቡ፤ እዚያም የUAT ቪዲዮ ትምህርቶች፣ ኖቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን በSmart Learning Environment ውስጥ ታገኛላችሁ። 🎓 አሁኑኑ ተመዝገቡና የUAT ዝግጅታችሁን ጀምሩ! @UATtutorialofficial

AAU 2018 entry Cut off point .pdf2.88 KB

የAAU የትምህርት ክፍያ (Tuition fee) እንዴት ይከፈላል? ብዙ ተማሪዎች "ትምህርት ክፍያው እንዴት ነው የሚከፈለው?" ብለው ይጠይቃሉ። እስቲ በቀላሉ እንመልከተው። ✅ 1. ክፍያው መቼ ነው የሚከፈለው? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) አብዛኛዎቹ ዲፓርትመንቶች የትምህርት ክፍያቸውን በየሴሚስተሩ ሁለት ጊዜ ይከፍላሉ። ይህ ማለት፦ 1ኛ ሴሚስተር ➜ 2 ጊዜ ክፍያ 2ኛ ሴሚስተር ➜ 2 ጊዜ ክፍያ በአጠቃላይ በአንድ ዓመት 4 ጊዜ ክፍያ ይፈጸማል። 📌 ልዩ ሁኔታ: Medicine (MD) እና Dental Medicine (DDM) በሞዱል (Modular) system ስለሚማሩ፣ የአንድ ዓመት ክፍያቸውን በሁለት ክፍያ ያጠናቅቃሉ። ✅ 2. ክፍያው እንዴት ይሰላል? AAU የትምህርት ክፍያን በECTS (European Credit Transfer and Accumulation System) መሰረት ያሰላል። በቀላሉ ለማለት፣ የወሰድካቸው የECTS ብዛት × የዲፓርትመንትህ የECTS ዋጋ = የሴሚስተሩ ክፍያ ✅ 3. ምሳሌ አንድ Software Engineering ተማሪ እንውሰድ። የSoftware Engineering 1 ECTS = 1,500 ብር ነው፣ በአንድ ሴሚስተር እነዚህን ኮርሶች ይወስዳል ብለን እናስብ፦ • Course 1 → 6 ECTS • Course 2 → 7 ECTS • Course 3 → 4 ECTS • Course 4 → 5 ECTS • Course 5 → 6 ECTS ጠቅላላ = 28 ECTS ስለዚህ፦ 28 × 1,500 = 42,000 ብር ይህ የሴሚስተሩ ጠቅላላ ክፍያ ነው። የሚከፈለው በሁለት ዙር ስለሆነ፣ ➡️ 21,000 ብር (1ኛ ክፍያ) ➡️ 21,000 ብር (2ኛ ክፍያ) ✅ 4. ሁሉም ዲፓርትመንቶች አንድ ክፍያ አይከፍሉም! የECTS ዋጋ ከዲፓርትመንት ወደ ዲፓርትመንት ይለያያል። ለምሳሌ፦ Software Engineering → 1,500 ብር / ECTS Electrical Engineering → 900 ብር / ECTS Economics → 700 ብር / ECTS Freshman → 600 ብር / ECTS MD/DDM → 2300 ብር/ECTS 📌 በአጠቃላይ ከSoftware Engineering በታች ያሉ አብዛኛዎቹ ዲፓርትመንቶች የECTS ክፍያቸው ዝቅተኛ ነው። ከሁሉም ከፍተኛ የECTS ክፍያ ያላቸው ዲፓርትመንቶች፦ 🥇 Medicine (MD) እና Dental Medicine (DDM) ከዚያ በመቀጠል፦ 🥈 Software Engineering 🥉 Law 🏛 Architecture ነው Notice: የክፍያ መጠኖች ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ ሊያሻሽላቸው ይችላል። ይሄ የአምና አሰራር ነው። ©️ UAT Tutorial Official Share and Join : @UATtutorialOfficial

🎯 15,000 ተማሪዎች ይፈተናሉ። ግን የሚገቡት 5,000 ብቻ ናቸው። ይህ ማለት ከ3 ተማሪዎች 1 ብቻ እድሉን ያገኛል። እዚህ ላይ የሚለየው IQ አይደለም። ዝግጅት ነው። አንተ ዛሬ "ቆይ በኋላ አነባለሁ" ስትል፣ ሌላ ተማሪ የUAT ጥያቄ እየሰራ፣ ስህተቱን እያረመ፣ ፍጥነቱን እያሻሻለ፣ ወደ ፊት እየተጓዘ ነው። UAT "ስንደርስበት እናያለን" የሚባል ፈተና አይደለም። "እዘጋጃለሁ እና አሸንፋለሁ" የሚባል ፈተና ነው። እያንዳንዱ የምትሰራው Practice ነገ የሚያስመዘግብልህ ውጤት ነው። ዛሬ የምታዘገየው ነገ ለመጸጸት ምክንያት ሊሆን ይችላል። ዛሬ የምትጀምረው ግን የህልምህን ዩኒቨርሲቲ በር ሊከፍትልህ ይችላል። በለላ አገላለጽ ⬇️ ✅ Around 2,500 ብቻ በGovernment Sponsored ✅ Around 2,500 ብቻ በSelf Sponsored በድምሩ 5,000 ተማሪዎች ብቻ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ። ይህ ማለት... አንተ ከ2,500 ምርጥ ተማሪዎች ውስጥ መሆን አለብህ። አለዚያ እድሉ በሌላ ሰው ይወሰዳል። ከ15,000 ተወዳዳሪዎች መካከል አንተ በ5,000ዎቹ ውስጥ መሆን ከፈለግህ... መወሰን ያለብህ ዛሬ ነው። መጀመር ያለብህም ዛሬ ነው። 📌ለትቶሪያል ለመመዝገብ : @UATtutorial_Bot

🎓 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውድድር የሚደረግባቸውን ዲፓርትመንቶች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) የሀገራችን ቀዳሚ የትምህርት ተቋም እንደመሆኑ መጠን፣ የተመደቡ ተማሪዎች ወደሚፈልጉት የትምህርት ዘርፍ ለመግባት የሚያደርጉት ውድድር እጅግ አታጋይ ነው። በተለይም በየዓመቱ ከፍተኛ GPA መቁረጫ ነጥብ የሚያስመዘግቡትን 4ቱን ቀዳሚ ዲፓርትመንቶች እና የውድድሩን ምክንያት እንመልከት 📌Medicine -የጤና ዘርፉ ያለውን ማህበራዊ ክብርና የተረጋጋ የሥራ ዕድል ተከትሎ፣ የፍሬሽማን ውጤታቸው ወደ 4.0 የተቃረበ እና የቅበላ ፈተናዎችን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ የሚቀላቀሉት ዘርፍ ነው። 📌Software engineering - በ AAiT ሥር ከሚሰጡት የኢንጂነሪንግ ዘርፎች መካከል በየዓመቱ ቀዳሚውን cut off point  ይይዛል። የቴክኖሎጂ ስታርትአፖች እና የዲጂታል ኢኮኖሚው መስፋፋት የብዙዎችን ቀልብስቧል። 📌Computer science -በቴክኖሎጂው ዘርፍ ባለው ከፍተኛ የሥራ ፍላጎት፣ የርቀት ሥራ (Remote Work) ዕድሎች እና በራሳቸው የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች መፍጠር የሚፈልጉ ተማሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ከፍተኛ GPA ይጠይቃል። 📌Law - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት በሀገሪቱ ረጅም ታሪክና ትልቅ ስም ያለው በመሆኑ፣ በማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቀዳሚ መዳረሻ ነው።      እነዚህ ዲፓርትመንቶች ከፍተኛ ውድድር የሚደረግባቸው በገበያው ላይ ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት፣ በውስጣቸው በሚይዙት የተማሪዎች መጠን ገደብ እና በሚሰጡት ሰፊ የሙያ ዕድል ምክንያት ነው። 📌 እነዚህ ዲፓርትመንቶች መግባት የሚወሰነው በፍሬሽማን ውጤታችሁ ነው። ስለዚህ ከአሁኑ በትክክል መዘጋጀት የህልማችሁን ዲፓርትመንት የመቀላቀል እድላችሁን በእጅጉ ያሳድጋል። Havan Academy ይህንን ጉዞ እንድታሳኩ ከጎናችሁ ነው። 📌ባለፉት ዓመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የህልማቸውን ዩኒቨርሲቲ እና የሚፈልጉትን ዲፓርትመንት እንዲቀላቀሉ ረድተናል። ሀቫን አካዳሚ : የፍሬሽማን ስኬት የሚጀምርበት ቦታ! የሌሎችን የምን ዩኒቨርሲቲ እንስራላችሁ፣ በኮመንት አሳውቁን ! 📚join Us: @havanacademyofficial