𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋
前往频道在 Telegram
亗 ꧁﷽꧂ 亗 🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ ✔Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊 ➻Islamic teachings💛 ➻Current information🤗 ➻Hadiths and Qurans 🤩 CROSS🔄 @Waver_boy1
显示更多📈 Telegram 频道 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 的分析概览
频道 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 (@hafu_posts) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 17 779 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 4 598,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 017 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 17 779 名订阅者。
根据 19 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 225,过去 24 小时变化为 -8,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 11.69%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.58% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 080 次浏览,首日通常累积 1 526 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 53。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“亗 ꧁﷽꧂ 亗
🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ
✔Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊
➻Islamic teachings💛
➻Current information🤗
➻Hadiths and Qurans 🤩
CROSS🔄 @Waver_boy1”
凭借高频更新(最新数据采集于 20 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
17 779
订阅者
-824 小时
+2227 天
+22530 天
帖子存档
17 779
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋:
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 336❵ #hadith336
"አቡ ጁሐይፋህ ወሀብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦
"ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሰልማንን እና አቡ ደርዳዕን (ረ.ዐ) በወንድማማችነት አቆራኙ። ሰልማን አቡ ደርዳዕን ለመጉብኘት ሲሄድ ኡሙ ደርዳዕ ራሷን ጥላ ተመለከታት፥ "ምን አገኘሽ?" ሲል ጠየቃት። "ወንድምህ አቡ ደርዳዕ ለዚች ዓለም ቅንጣት ያህል ግድ የለውም" አለችው። አቡ ደርዳዕ መጣ። ምግብ አዘፋጀለትና "ብላ እኔ ፆመኛ ነኝ" አለው። "አንተ ካልተመገብክ አልመገብም" አለ ሰልማን። ተመገበ-አቡ ደርዳዕ ። አመሻሽ ላይ አቡ ደርዳዕ የሌሊት ሶላት ለመስገድ ተዘጋጀ። "ተኛ" አለው። ተኛ። እንደገና ለሶላት ተነሳ።"ተኛ" አለው። በሌሊቱ መጨረሻ ላይ "አሁን ተነስ" አለው። ሁለቱም ሰገዱ። ሰልማን እንዲህ አለ "ጌታህ በአንተ ላይ መብት አለው፥ ነፍስህ በአንተ ላይ መብት አላት፥ ቤተሰቦችህም በአንተ ላይ መብት አላቸው፥ ለእያንዳንዱ ባለመብት መብቱን አድርስ።" ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና ይህንኑ አወሳላቸው፡፡ "ሰልማን እውነቱን ነው" አሉ መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ)፡፡"
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/19366
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
17 779
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️
🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር
📖🎧 #ቁርኣን || PART ❸❻❺
⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™ || SHARE 😊
17 779
🛍 ኦንላይን መገበያየት ቀላል ሆኗል! የሚፈልጉትን በቀላሉ ያግኙ።
▶️ ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ አዳዲስ እቃዎችን ይከታተሉ!
🌙ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው🌙
17 779
ማለፊያ
(ፉአድ ሙና)
ክፍል አራት
***
ሴት ልጅ ከወደደች፣ ከተያዘ ነብሷ፣
የቤተሰብ ክብር፣ ጨዋታ ነው ለሷ፡፡
***
አብደሏህ ቤቱ እንደገባ ጫማውን በቁሙ ወርውሮ አልጋው ላይ በጀርባው ተዘረረ፡፡ ሰመረ ያለው ትዳር መንገራገጭ እንደገጠመው ተሰምቶታል፡፡ እንደ ሌባ መመርመር ያማርራል፡፡ ከመች ጀምሮ ነው ለትዳር ደግሞ እንደ ስራ ቅጥር የቃል ፈተና የተጀመረው? የወንድሟ መኮሳተር አማሮታል፡፡ ወደ ሻወር ቤት እየሄደ ስልኩ ሲጮህ ተሰማው፡፡ አነሳው … ድምፁን ቀንሶ ማውራት ጀመረ፡፡
‹‹ኧ ሰውየው …››
‹‹እሺ ሙሽራው … ቃለ መጠይቅ እንዴት ነበር?›› ጓደኛው ነበር፡፡
‹‹ኧረ የቀብር አስመሰለው ወንድምየው ባክህ!››
‹‹እና ጀነት ገባህ ወይስ ጀሀነም? ሀሀሀሀሀ››
‹‹ገና ሚዛን ላይ አልደረስንም …››
‹‹እንግዲህ አላህ ይሁንህ!››
የሚያወጉትን ሌላ አጀንዳ ሲጨርሱ ከጓደኛው ጋር ተሰነባብቶ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡ የገንዘብ ችግር የለበትም፡፡ ሲሀምን በደንብ መንከባከብ ይችላል፡፡ ገንዘቡ ብቻውን ሲሀምን የሱ ለማድረግ በቂ እንደሆነ ተሰምቶት ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ምናልባት የሲሀም ቤተሰቦች የገንዘብ አቅም ወረድ ያለ ቢሆን የእሱ ግምት ሊሰምር ይችል ነበር፡፡ ድህነት እምቢ የማለት አቅምን ይሰልባል … ይከራከሩበት በራስ መተማመን ይነጥቃል፡፡
***
የተጋለጠ ሰውነት … ተከፍቶ እንደማያውቅ የሚያስታውቅ እንቡጥ ገላ … ከክለቡ የውጪ በር መብራቶች ጋር ሲደመር ያዙኝ ያዙኝ … ንኩኝ ንኩኝ ይላል፡፡ ምህረት፣ ቤቲ እና አዲሷ ነፃ ወጪ ሲሀም በተራ ተራ መታወቂያቸውን እያሳዩ ወደ ክለቡ ዘለቁ፡፡ የሙዚቃው ድምፅ ታምቡር ይበጥሳል፡፡ የመብራቱ ቀለሞችና የብርሀን ስልታቸው ያልጠጣን ሰው ያሰክራል፡፡ ወደ ጭፈራ ቤቱ ገብተው በጥቁር ሌዘር የተሰራ አግዳሚ ሶፋ ያለበት ጠረጴዛ ጋ ተቀመጡ፡፡ አስተናጋጇ መጥታ ትዕዛዝ መቀበል ጀመረች፡፡ ሲሀም ልቧ በጣም ተረብሽዋል፡፡ እየሮጠች ብትወጣም ደስ ይላታል፡፡ ሰው ቢያየኝስ የሚለው ስጋት ፈሪ አድርጓታል፡፡ በእርግጥ የተቀመጡበት ቦታ ጨለማ ስለሆነ ለመታየት የተጋለጠ አይደለም፡፡ ቤቲና ምህረት የመረበሽ ስሜት ሊፈጠርባት እንደሚችል ያውቃሉ፡፡ በቻሉት መጠን ምቾት እንዲሰማት ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ የመጠጥ ምርጫ ስለሌላት እነሱ ይሆናታል ያሉትን መጠጥ አዘዙላት፡፡ ምርጫ የሚኖረው ምርጫ የሚያውቅ ሰው ነው፡፡
‹‹ያስፈራል!››
‹‹አይዞሽ ሲሁዬ … ማንም አይደርስብሽም ሁሉም በራሱ ዓለም ላይ ነው፡፡››
‹‹ቤቱ ውድ ቤት ስለሆነ ወጠጤ አይገባበትም፡፡ ክላስ ክላስ የሆነ ሰው ነው ያለው! እነርሱ ደግሞ በራሳቸው ዓለም ናቸው፡፡››
ዘፋኞቹ እየተቀያየሩ ይዘፍናሉ፡፡ ሞቅ ያላቸው ወንዶች ዘፋኞቹ ጋ እየሄዱ ገንዘብ ይበትናሉ፡፡ የሲሀምና ወዳጆቿ ጠረጴዛ ላይ ያዘዙት መጠጥ ቀረበ፡፡ ብርጭቆው ሲታይ … ስትሮ ተደርጎበት ሲቀርብ … የሚያሰክር መጠጥ አይመስልም፡፡ ሲሀም ስትመለከተው አስካሪ መጠጥ አልመሰላትም፡፡ መጠጥ ቤት ውስጥ የሚጠጣ የሚመስላት ጠርሙስ ተደርድሮ … ቢራ ከፍ ካለም በጠርሙስ የሚቀርቡት ከፍ ያሉ መጠጦች ናቸው፡፡ ለእነርሱ የቀረበላቸውን ስትመለከተው ባህር ዳርቻ ላይ ተቀምጣ ጁስ እየጠጣች ያለች ዓይነት ስሜት የሚሰጡ ናቸው፡፡
ምህረትና ቤቲ መጠጣቸውን አነሱ፡፡ በአይናቸው እሷንም እንድታነሳ ጋበዟት፡፡ ብርጭቆዋን አንስታ ‹‹ቺርስ ለነፃነታችን!›› አለች፡፡ ምህረት ፈገግ እያለች ‹‹ቺርስ ለሲሁ ነፃነት!›› አለች፡፡ ብርጭቆዎች ተገጫጩ፡፡ መጠጡን ስትስበው ትንሽ ከበድ አላት፡፡ ስኳር ስኳር አይልም፡፡ ትንሽ ትንሽ ለመጠጣት ሞከረች፡፡ ምህረትና ቤቲ ወድያው ጨርሰውት ሌላ አስመጡ፡፡ መጠጡ ሲደጋገም ሞቅ ስላላቸው ተነስተው እየጨፈሩ ነው፡፡ ጨዋታ ጨምረዋል … ጮክ ብለው ይስቃሉ፡፡ ክለቡ ውስጥ ያሉ ወንዶች ዓይን ወደ እነሱ መሳብ ጀምሯል፡፡
ሲሀም ብዥ ብሎባታል፡፡ ምክንያታዊው እሷነቷ ትቷት እየበነነ ነው፡፡ ወንዶቹ ደግሞ ከምህረትና ቤቲ ገላ በላይ የእሷ ሰውነት ስቧቸዋል፡፡ ሁለት ወንድ ጓደኛማቾች መጠጣቸውን እንደ ያዙ ወደ ጠረጴዛቸው ቀረቡ፡፡ አንዱ የምህረትን እጅ ይዞ ቀለል ያለ ዳንስ መደነስ ጀመረ፡፡ ሌላኛው ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ሲሀምን ያወራታል፡፡
‹‹ስማ … እሷን እንዳትነዘንዛት … ነግሬሀለሁ!››
‹‹ኧረ ጨዋታ ነው የያዝነው!››
‹‹ሲሁዬ ምቾት ከነሳሽ ንገሪኝ … እናስነሳዋለን!››
‹‹ችግር የለውም … አልነሳኝም፡፡››
‹‹የት ነው የምትኖሩት … የሸገር ልጆች ናችሁ?›› ልጁ የሲሀምን ቁጥር ለመቀበል መንገድ መጀመሩ ነው፡፡
‹‹እኔ አዎ! ቤቲ የመቀለ ልጅ ናት፡፡ እሷ ደግሞ የአዳማ!››
‹‹የግቢ ልጆች ናችሁ ማለት ነው አይደል?››
‹‹አዎ … ግን እንዴት ገመትክ?››
‹‹ከብሔር ብሔረሰብ የተዋቀረ ወዳጅነት ካምፓስ ላይ ነው የሚኖረው ብዬ ነው፡፡›› ሳቀ፡፡
‹‹ስምሽ ግን ማነው?››
‹‹ሲሀም …››
‹‹ሲሀም?››
‹‹አዎ ምነው?››
‹‹ማለቴ ሲሀም … ምንኛ ነው?›› ሊል የነበረውን ዋጠው፡፡
‹‹አረብኛ ነው፡፡ ሰምተህ አታውቅም?››
‹‹አውቃለሁ … ግን ሙስሊም አልመሰልሽኝም ነበር፡፡››
‹‹ለምን?››
‹‹እኔንጃ … ብዙም ስለማይገጥሙኝ መሰለኝ! በተለይ ደግሞ ሙስሊም ሴት …›› ወሬው ቀዘቀዘ፡፡ አብሯት የማደር ፍላጎቱ ደግሞ እጅጉን ጨመረ፡፡
‹‹እና ስልክሽን ስጪኝና እናውራ››
‹‹ይቅርታ እጮኛ አለኝ …››
‹‹ታዲያ ምናባሽ ትሰሪያለሽ እዚ … ድሮም ሙስሊሞች ኮተታችሁ ይበዛል፡፡ … ሙስሊም ሆነሽ ክለብ ለክለብ ምን ያዞርሻል!›› ተነስቶ ትቷት ሄደ፡፡ የፈለጋት ለዛሬ አዳር ነበር፡፡ ምህረት የጓደኛው ሰውነት ላይ ተለጥፋ እያስነኩት ነው፡፡ ዳንሱ ለመተሻሸት ሰበብ ይመስላል፡፡ መሸ … እኩለ ለሊት አለፈ፡፡ ቤቲም ምህረትም አብረን ካላደርን የሚሏቸው ወንዶች አግኝተዋል፡፡ እሷን ብቻዋን ወደ ዶርም መመለሱም ደብሯቸዋል፡፡ ከወንዶቹ ጋር ለሌላ ቀን ተቀጣጥረው በመከራ ተላቀቁ፡፡ ከክለብ እየወጡ ሲሀም ማስታወክ ጀመረች፡፡ ለማስታወክ ባጎነበሰችበት አንዱ መቀመጫዋን መቷት አለፈ፡፡ ፈሷ አመለጣት፡፡ ብቻውን ያመለጠም አይመስልም፡፡ የበላችው ሁሉ ተፈጭቶ በሁለት አቅጣጫ ተተፋ፡፡
‹‹ኧረ አንቺ ቶሎ ውጪ!›› ጋርዱ አዋከባት፡፡ ምህረትና ቤቲ እንደ ምንም ተጋግዘው ይዘዋት ወጡ፡፡
የጠሩት ራይድ የሲሀምን ሽታ ችሎ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ተመልሰው ወደ ክለቡ ገብተው እንድትታጠብ አደረጉ፡፡ ታጥባ ልብሷን አውልቃ አባያዋን ብቻ ለበሰች፡፡ ልብሷን በውሀ ቆሻሻውን አንስታ ፌስታል ውስጥ ካደረገችው በኋላ ወደ ቦርሳዋ ከተተችው፡፡ ሆዷ እንደተረበሸ ነው፡፡ ችላው ወደ ዶርማቸው ደረሱ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ሰዓት በኋላ እንደማያስገባቸው ያውቃሉ፡፡ በድንገተኛ ህክምና ክፍል በኩል እሷን ይዘው ገቡ፡፡ ድንገተኛ ህክምና ላይ የነበሩት የግቢው ሲኒየሮች ለመታከም የመጡ እንዲመስል አድርገው ወደ ዶርማቸው ሸኟቸው፡፡ ሲሀም የእስልምናን ጨቋኝነት አመለጠችው፡፡ ተዪ ያላትን ሰርታ እስልምናን … በጥቅሉ የሃይማኖት ጭቆናን ተበቀለችው፡፡ ተጎድቶ ይሆናል መቼስ!
ዶርማቸው ገብተው ሲነጋ ራስ ምታቱ ከበዳት … አይኗን መግለጥ አልቻለችም፡፡ ፈጅር እንዳልሰገደች ትዝ አላት፡፡ ከአልጋዋ ላይ ተነስታ ተቀመጠች፡፡ ሀይድ ላይ መሆኗ ሲታወሳት ወደ አልጋዋ ተመለሰች፡፡ ከማታው ቆይታቸው አብዛኛው አይታወሳትም፡፡ የታመመችበት ግን አሁን እየሆነ ያለ ይመስል ፊቷ ላይ ይመላለሳል፡፡ ቤቲና ምህረት መነሳቷን ሲመለከቱ ወደ አልጋዋ መጡ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ? ህመሙ ለቀቀሽ?›› ቤቲ ጭንቅላቷን እየዳበሰች ጠየቀቻት፡፡
‹‹ራሴን በጣም አሞኛል!››
‹‹አይዞሽ ትንሽ ሲቆይ ይፈታሻል፡፡››
‹‹ግን የማታው ኦቨር እንዴት ነበር? ወደድሽው?››
‹‹ምኑ ነው ግን የሚያስደስታችሁ?››
‹‹ማለት?››
‹‹ስቃይ ነው እኮ! መከራ ነው፡፡ እስር ቤት ከባድ ወንጀለኛ ሊቀጣበት የሚገባ ነገር እኮ ነው፡፡ ጩኸቱ በሉ መብራቱ … ብቻ ሁሉም ነገር በጣም ነው ያሳቀቀኝ!››
‹‹ስላለመድሽው ነው … ስትለምጂው ሁሉም ኖርማል ይሆንብሻል፡፡››
‹‹አይ … ይኼን እንኳን ባለምደው ይሻላል፡፡ እዚህ ላይ ሃይማኖት ትክክል ነው፡፡››
‹‹እመኚን ስትለምጂው ደስ ይልሻል፡፡›› ምህረት ለማሳመን ተደረበች፡፡
‹‹ሌላ ነገር ፈልጉልኝ … በዚህ እንኳን አልፈልግም፡፡››
‹‹what about sex without marriage? ሴት ልጅ ከባሏ ጋር ካልሆነ አትተኛ የሚለውን ትዕዛዝ ያስቀመጠው ሃይማኖት ነው፡፡››
‹‹ዝሙት?››
‹‹እንደሱ ብለው ያገዘፉት እነሱ ናቸው፡፡ መጥፎ ስም በመስጠት ማስፈራራት አመላቸው ነው፡፡ ያን ያህል አይደብርም፡፡ ከፈለግሽው ሰው ጋር ደስተኛ የምትሆኚበት መንገድ ነው፡፡››
‹‹እጮኛ አለኝ እኮ!››
‹‹ከሱ ጋር መሆን ይችላል፡፡ ሌላ ወንድ ጋ መሄድ አይጠበቅብሽም፡፡››
‹‹እስኪ ፀባዩ ይታይና … ደግሞ ታውቃላችኋ ከዚህ በፊት የዚህ ነገር ምንም experience የለኝም፡፡››
‹‹እናውቃለን፡፡ ከምትወጂው ሰው ጋር ቢሆን ቆንጆ ነው፡፡››
ሰሞኑን ፈተና መጨረሳቸው ነው … እረፍት ስለነበሩ ለማረፍ ወደ ቤቷ መሄድ እንዳለባት ተሰማት፡፡ ራስ ምታቱ ጋብ ሲልላት መኪና ጠርታ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ አባቷና እናቷ ሳሎን መጅሊሱ ላይ ተቀምጠው እያወጉ ነበር፡፡ ሂጃቧ ግጥም ማለቱና የአባያ አለባበሷ ትናንት ምሽት የነበረበትን ሁኔታ አያሳብቅም … ሆኖም ፈራች፡፡ ገላዋ አፍ አውጥቶ የሚናገር የሚናገር መሰላት፡፡ ያለመደባትን እናቷንና አባቷን ሳትስም ከሩቅ ብቻ ሰላም ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች፡፡
መኝታ ክፍሏ ውስጥ ሳለች ስልኳ ጮኸ፡፡ አብደሏህ ነበር፡፡
‹‹ሄሎ … ›› ድምፁ ውስጥ ኩርፊያ ይነበባል፡፡
‹‹አብዱዬ››
‹‹ለምንድነው ስልክሽን የጠረቀምሽው?››
‹‹አልተመቸኝም ነበር … ለማጥናት ፈልጌ ነው፡፡››
‹‹አንቺ ለኔ ቦታ አለሽ ግን ከልብሽ?››
‹‹አትቀባጥር! እዚህ ላንተ ብዬ እየተጋፈጥኩ ያለሁትን እኔ ነኝ የማውቀው!››
‹‹ስልክሽን ስትዘጊው እኮ ነው፡፡›› ተለሳለሰ፡፡
‹‹ቤተሰቦችሽ ምን አሉ? ቁርጡን አሳውቂኝ፡፡››
‹‹እነግርሀለሁ … ትንሽ ታገስ!››
ከሱ ጋር ተሰነባብታ ሻወር ወሰደች፡፡ ልብሷን ቀያይራ ወደ ሳሎን አመራች፡፡
‹‹አባ ማግባት እፈልጋለሁ፡፡ የኔ ፍላጎት መከበር ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በላይ እናንተን መታዘዝ አልችልም፡፡›› የሞት ሞቷን ከአፏ አወጣችው፡፡
‹‹ታገቢያለሽ … ግን ልጅ ነሽ … ምን ያጣድፍሻል? በጊዜው ይደርሳል፡፡›› አባቷ ፈገግ ብለው ለመመለስ ሞከሩ፡፡ እናትየው በድንጋጤ እየተመለከቱ ነው፡፡
‹‹እድሜዬ በቂ ነው፡፡ ከሪማን እያት … እኩያዬ ናት፡፡ እሷ ወልዳለች፡፡ ከጀማል ጋር የተጋባችው ራሱ ገና በ18 ዓመቷ ነው፡፡ ለኔ ሲሆን ነው እንዴ ልጅነት ትዝ የሚላችሁ?››
‹‹ከሪማና አንቺ አንድ አይደላችሁም፡፡ አንቺ ዶክተር ለመሆን አራት አመት ብቻ ነው የቀረሽ … እሷ 12ኛ ክፍልም አላለፈችም፡፡›› አባቷ በስጨት አሉ፡፡
‹‹እራሴ አግብቼ ብመጣ ግን እንዳይገርማችሁ እሺ!›› እየተነጫነጨች ወደ ክፍሏ ተመለሰች፡፡
ማዳመጫዋ የተዘጋ ይመስላል፡፡ ምናልባት ወዳጆችዋ እንደሚሉት አመፀኛ ሆናለች፡፡ ጀማል እንኳን ቀና ብሎ ለማውራት ከሚፈራቸው አባቷ ጋር መመላለስ ጀምራለች፡፡ ከሃይማኖት ጫና የመላቀቅ ዳዴ!
ይቀጥላል!
.
17 779
Repost from 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋
✏️ የደራሲ ፉዓድ ሙና ማለፊያ የተሰኘ አዲስ ኢስላሚክ ታሪክ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ......ይቀጥላል
ዝግጁ ናችሁ ወይ❔
17 779
Repost from Sαlαh Responds ࿈
🎙ወንድም አቡበከር '🤎'
📖 ይህ ወንድማችን ሞቷል፣ አላህ ይርሀመው። ቲላዋውን በማሰራጨት፣ ስንቁን እናብዛለት🌼.
☑️Sαlαh Responds😘
17 779
😀 👉 የኢስላሚክ ቻናል ባለቤቶች ቶሎ በሉ Wave መግባት የምትፈልጉ 😮
✅ 2k-10k+ subscribers ✔️
✅ 15k+ subscribers ✔️
✅ 20k+ subscribers ✔️
✅ 50k+ subscribers ✔️
✅ 100k+ subscribers ✔️
ሁለተኛ ፎልደር ተዘጋጅቷል 5k+ ያላቹ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ! 🏃
Link ልካቹ Wave ብላቹ አስቀምጡልኝ 🔗
𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 ✉️ ◇ @Waver_boy1 📩
17 779
If your only goal is to become rich, you will never achieve it."
ብቸኛ ግብህ ሀብታም መሆን ብቻ ከሆነ፣ ፈጽሞ ልታሳካው አትችልም።
17 779
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋:
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 335❵ #hadith335
"አቡ አብደላህ ጃቢር ኢብን ሰሙረት (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦
"ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር እሰግድ ነበር፥ ሶላታቸውም ዲስኮራቸውም መካከለኛና ሚዛናዊ ነበር።
(ሙስሊም ዘግበውታል)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/19335
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
17 779
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️
🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር
📖🎧 #ቁርኣን || PART ❸❻❹
⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™ || SHARE 😊
