ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋

الذهاب إلى القناة على Telegram

亗 ꧁﷽꧂ 亗 🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ ✔Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊 ➻Islamic teachings💛 ➻Current information🤗 ➻Hadiths and Qurans 🤩 CROSS🔄 @Waver_boy1

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋

تُعد قناة 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 (@hafu_posts) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 17 802 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 597 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 019 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 17 802 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 18 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 226، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 21، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 11.82‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 8.67‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 2 105 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 545 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 53.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“亗 ꧁﷽꧂ 亗 🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ ✔Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊 ➻Islamic teachings💛 ➻Current information🤗 ➻Hadiths and Qurans 🤩 CROSS🔄 @Waver_boy1”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 19 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

17 802
المشتركون
+2124 ساعات
+2267 أيام
+22630 أيام
أرشيف المشاركات
ብቸኝነት ከ አላህ ጋር ሲሆን እጂግ ደስ ይላለል።😊

ዱኒያ ላይ የኛ የሆነ ነገር የለም::

🛍 ኦንላይን መገበያየት ቀላል ሆኗል! የሚፈልጉትን በቀላሉ ያግኙ። ▶️ ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ አዳዲስ እቃዎችን ይከታተሉ! 🌙ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው🌙
🛍 ኦንላይን መገበያየት ቀላል ሆኗል! የሚፈልጉትን በቀላሉ ያግኙ።  ▶️ ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ አዳዲስ እቃዎችን ይከታተሉ! 🌙ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው🌙

ማለፊያ (ፉአድ ሙና) ክፍል አራት *** ሴት ልጅ ከወደደች፣ ከተያዘ ነብሷ፣ የቤተሰብ ክብር፣ ጨዋታ ነው ለሷ፡፡ *** አብደሏህ ቤቱ እንደገባ ጫማውን በቁሙ ወርውሮ አልጋው ላይ በጀርባው ተዘረረ፡፡ ሰመረ ያለው ትዳር መንገራገጭ እንደገጠመው ተሰምቶታል፡፡ እንደ ሌባ መመርመር ያማርራል፡፡ ከመች ጀምሮ ነው ለትዳር ደግሞ እንደ ስራ ቅጥር የቃል ፈተና የተጀመረው? የወንድሟ መኮሳተር አማሮታል፡፡ ወደ ሻወር ቤት እየሄደ ስልኩ ሲጮህ ተሰማው፡፡ አነሳው … ድምፁን ቀንሶ ማውራት ጀመረ፡፡ ‹‹ኧ ሰውየው …›› ‹‹እሺ ሙሽራው … ቃለ መጠይቅ እንዴት ነበር?›› ጓደኛው ነበር፡፡ ‹‹ኧረ የቀብር አስመሰለው ወንድምየው ባክህ!›› ‹‹እና ጀነት ገባህ ወይስ ጀሀነም? ሀሀሀሀሀ›› ‹‹ገና ሚዛን ላይ አልደረስንም …›› ‹‹እንግዲህ አላህ ይሁንህ!›› የሚያወጉትን ሌላ አጀንዳ ሲጨርሱ ከጓደኛው ጋር ተሰነባብቶ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡ የገንዘብ ችግር የለበትም፡፡ ሲሀምን በደንብ መንከባከብ ይችላል፡፡ ገንዘቡ ብቻውን ሲሀምን የሱ ለማድረግ በቂ እንደሆነ ተሰምቶት ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ምናልባት የሲሀም ቤተሰቦች የገንዘብ አቅም ወረድ ያለ ቢሆን የእሱ ግምት ሊሰምር ይችል ነበር፡፡ ድህነት እምቢ የማለት አቅምን ይሰልባል … ይከራከሩበት በራስ መተማመን ይነጥቃል፡፡ *** የተጋለጠ ሰውነት … ተከፍቶ እንደማያውቅ የሚያስታውቅ እንቡጥ ገላ … ከክለቡ የውጪ በር መብራቶች ጋር ሲደመር ያዙኝ ያዙኝ … ንኩኝ ንኩኝ ይላል፡፡ ምህረት፣ ቤቲ እና አዲሷ ነፃ ወጪ ሲሀም በተራ ተራ መታወቂያቸውን እያሳዩ ወደ ክለቡ ዘለቁ፡፡ የሙዚቃው ድምፅ ታምቡር ይበጥሳል፡፡ የመብራቱ ቀለሞችና የብርሀን ስልታቸው ያልጠጣን ሰው ያሰክራል፡፡ ወደ ጭፈራ ቤቱ ገብተው በጥቁር ሌዘር የተሰራ አግዳሚ ሶፋ ያለበት ጠረጴዛ ጋ ተቀመጡ፡፡ አስተናጋጇ መጥታ ትዕዛዝ መቀበል ጀመረች፡፡ ሲሀም ልቧ በጣም ተረብሽዋል፡፡ እየሮጠች ብትወጣም ደስ ይላታል፡፡ ሰው ቢያየኝስ የሚለው ስጋት ፈሪ አድርጓታል፡፡ በእርግጥ የተቀመጡበት ቦታ ጨለማ ስለሆነ ለመታየት የተጋለጠ አይደለም፡፡ ቤቲና ምህረት የመረበሽ ስሜት ሊፈጠርባት እንደሚችል ያውቃሉ፡፡ በቻሉት መጠን ምቾት እንዲሰማት ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ የመጠጥ ምርጫ ስለሌላት እነሱ ይሆናታል ያሉትን መጠጥ አዘዙላት፡፡ ምርጫ የሚኖረው ምርጫ የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ ‹‹ያስፈራል!›› ‹‹አይዞሽ ሲሁዬ … ማንም አይደርስብሽም ሁሉም በራሱ ዓለም ላይ ነው፡፡›› ‹‹ቤቱ ውድ ቤት ስለሆነ ወጠጤ አይገባበትም፡፡ ክላስ ክላስ የሆነ ሰው ነው ያለው! እነርሱ ደግሞ በራሳቸው ዓለም ናቸው፡፡›› ዘፋኞቹ እየተቀያየሩ ይዘፍናሉ፡፡ ሞቅ ያላቸው ወንዶች ዘፋኞቹ ጋ እየሄዱ ገንዘብ ይበትናሉ፡፡ የሲሀምና ወዳጆቿ ጠረጴዛ ላይ ያዘዙት መጠጥ ቀረበ፡፡ ብርጭቆው ሲታይ … ስትሮ ተደርጎበት ሲቀርብ … የሚያሰክር መጠጥ አይመስልም፡፡ ሲሀም ስትመለከተው አስካሪ መጠጥ አልመሰላትም፡፡ መጠጥ ቤት ውስጥ የሚጠጣ የሚመስላት ጠርሙስ ተደርድሮ … ቢራ ከፍ ካለም በጠርሙስ የሚቀርቡት ከፍ ያሉ መጠጦች ናቸው፡፡ ለእነርሱ የቀረበላቸውን ስትመለከተው ባህር ዳርቻ ላይ ተቀምጣ ጁስ እየጠጣች ያለች ዓይነት ስሜት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ምህረትና ቤቲ መጠጣቸውን አነሱ፡፡ በአይናቸው እሷንም እንድታነሳ ጋበዟት፡፡ ብርጭቆዋን አንስታ ‹‹ቺርስ ለነፃነታችን!›› አለች፡፡ ምህረት ፈገግ እያለች ‹‹ቺርስ ለሲሁ ነፃነት!›› አለች፡፡ ብርጭቆዎች ተገጫጩ፡፡ መጠጡን ስትስበው ትንሽ ከበድ አላት፡፡ ስኳር ስኳር አይልም፡፡ ትንሽ ትንሽ ለመጠጣት ሞከረች፡፡ ምህረትና ቤቲ ወድያው ጨርሰውት ሌላ አስመጡ፡፡ መጠጡ ሲደጋገም ሞቅ ስላላቸው ተነስተው እየጨፈሩ ነው፡፡ ጨዋታ ጨምረዋል … ጮክ ብለው ይስቃሉ፡፡ ክለቡ ውስጥ ያሉ ወንዶች ዓይን ወደ እነሱ መሳብ ጀምሯል፡፡ ሲሀም ብዥ ብሎባታል፡፡ ምክንያታዊው እሷነቷ ትቷት እየበነነ ነው፡፡ ወንዶቹ ደግሞ ከምህረትና ቤቲ ገላ በላይ የእሷ ሰውነት ስቧቸዋል፡፡ ሁለት ወንድ ጓደኛማቾች መጠጣቸውን እንደ ያዙ ወደ ጠረጴዛቸው ቀረቡ፡፡ አንዱ የምህረትን እጅ ይዞ ቀለል ያለ ዳንስ መደነስ ጀመረ፡፡ ሌላኛው ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ሲሀምን ያወራታል፡፡ ‹‹ስማ … እሷን እንዳትነዘንዛት … ነግሬሀለሁ!›› ‹‹ኧረ ጨዋታ ነው የያዝነው!›› ‹‹ሲሁዬ ምቾት ከነሳሽ ንገሪኝ … እናስነሳዋለን!›› ‹‹ችግር የለውም … አልነሳኝም፡፡›› ‹‹የት ነው የምትኖሩት … የሸገር ልጆች ናችሁ?›› ልጁ የሲሀምን ቁጥር ለመቀበል መንገድ መጀመሩ ነው፡፡ ‹‹እኔ አዎ! ቤቲ የመቀለ ልጅ ናት፡፡ እሷ ደግሞ የአዳማ!›› ‹‹የግቢ ልጆች ናችሁ ማለት ነው አይደል?›› ‹‹አዎ … ግን እንዴት ገመትክ?›› ‹‹ከብሔር ብሔረሰብ የተዋቀረ ወዳጅነት ካምፓስ ላይ ነው የሚኖረው ብዬ ነው፡፡›› ሳቀ፡፡ ‹‹ስምሽ ግን ማነው?›› ‹‹ሲሀም …›› ‹‹ሲሀም?›› ‹‹አዎ ምነው?›› ‹‹ማለቴ ሲሀም … ምንኛ ነው?›› ሊል የነበረውን ዋጠው፡፡ ‹‹አረብኛ ነው፡፡ ሰምተህ አታውቅም?›› ‹‹አውቃለሁ … ግን ሙስሊም አልመሰልሽኝም ነበር፡፡›› ‹‹ለምን?›› ‹‹እኔንጃ … ብዙም ስለማይገጥሙኝ መሰለኝ! በተለይ ደግሞ ሙስሊም ሴት …›› ወሬው ቀዘቀዘ፡፡ አብሯት የማደር ፍላጎቱ ደግሞ እጅጉን ጨመረ፡፡  ‹‹እና ስልክሽን ስጪኝና እናውራ›› ‹‹ይቅርታ እጮኛ አለኝ …›› ‹‹ታዲያ ምናባሽ ትሰሪያለሽ እዚ … ድሮም ሙስሊሞች ኮተታችሁ ይበዛል፡፡ … ሙስሊም ሆነሽ ክለብ ለክለብ ምን ያዞርሻል!›› ተነስቶ ትቷት ሄደ፡፡ የፈለጋት ለዛሬ አዳር ነበር፡፡ ምህረት የጓደኛው ሰውነት ላይ ተለጥፋ እያስነኩት ነው፡፡ ዳንሱ ለመተሻሸት ሰበብ ይመስላል፡፡ መሸ … እኩለ ለሊት አለፈ፡፡ ቤቲም ምህረትም አብረን ካላደርን የሚሏቸው ወንዶች አግኝተዋል፡፡ እሷን ብቻዋን ወደ ዶርም መመለሱም ደብሯቸዋል፡፡ ከወንዶቹ ጋር ለሌላ ቀን ተቀጣጥረው በመከራ ተላቀቁ፡፡ ከክለብ እየወጡ ሲሀም ማስታወክ ጀመረች፡፡ ለማስታወክ ባጎነበሰችበት አንዱ መቀመጫዋን መቷት አለፈ፡፡ ፈሷ አመለጣት፡፡ ብቻውን ያመለጠም አይመስልም፡፡ የበላችው ሁሉ ተፈጭቶ በሁለት አቅጣጫ ተተፋ፡፡ ‹‹ኧረ አንቺ ቶሎ ውጪ!›› ጋርዱ አዋከባት፡፡ ምህረትና ቤቲ እንደ ምንም ተጋግዘው ይዘዋት ወጡ፡፡ የጠሩት ራይድ የሲሀምን ሽታ ችሎ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ተመልሰው ወደ ክለቡ ገብተው እንድትታጠብ አደረጉ፡፡ ታጥባ ልብሷን አውልቃ አባያዋን  ብቻ ለበሰች፡፡ ልብሷን በውሀ ቆሻሻውን አንስታ ፌስታል ውስጥ ካደረገችው በኋላ ወደ ቦርሳዋ ከተተችው፡፡ ሆዷ እንደተረበሸ ነው፡፡ ችላው ወደ ዶርማቸው ደረሱ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ሰዓት በኋላ እንደማያስገባቸው ያውቃሉ፡፡ በድንገተኛ ህክምና ክፍል በኩል እሷን ይዘው ገቡ፡፡ ድንገተኛ ህክምና ላይ የነበሩት የግቢው ሲኒየሮች ለመታከም የመጡ እንዲመስል አድርገው ወደ ዶርማቸው ሸኟቸው፡፡ ሲሀም የእስልምናን ጨቋኝነት አመለጠችው፡፡ ተዪ ያላትን ሰርታ እስልምናን … በጥቅሉ የሃይማኖት ጭቆናን ተበቀለችው፡፡ ተጎድቶ ይሆናል መቼስ! ዶርማቸው ገብተው ሲነጋ ራስ ምታቱ ከበዳት … አይኗን መግለጥ አልቻለችም፡፡ ፈጅር እንዳልሰገደች ትዝ አላት፡፡ ከአልጋዋ ላይ ተነስታ ተቀመጠች፡፡ ሀይድ ላይ መሆኗ ሲታወሳት ወደ አልጋዋ ተመለሰች፡፡ ከማታው ቆይታቸው አብዛኛው አይታወሳትም፡፡ የታመመችበት ግን አሁን እየሆነ ያለ ይመስል ፊቷ ላይ ይመላለሳል፡፡ ቤቲና ምህረት መነሳቷን ሲመለከቱ ወደ አልጋዋ መጡ፡፡ ‹‹እንዴት ነሽ? ህመሙ ለቀቀሽ?›› ቤቲ ጭንቅላቷን እየዳበሰች ጠየቀቻት፡፡ ‹‹ራሴን በጣም አሞኛል!›› ‹‹አይዞሽ ትንሽ ሲቆይ ይፈታሻል፡፡›› ‹‹ግን የማታው ኦቨር እንዴት ነበር? ወደድሽው?›› ‹‹ምኑ ነው ግን የሚያስደስታችሁ?›› ‹‹ማለት?›› ‹‹ስቃይ ነው እኮ! መከራ ነው፡፡ እስር ቤት ከባድ ወንጀለኛ ሊቀጣበት የሚገባ ነገር እኮ ነው፡፡  ጩኸቱ በሉ መብራቱ … ብቻ ሁሉም ነገር በጣም ነው ያሳቀቀኝ!›› ‹‹ስላለመድሽው ነው … ስትለምጂው ሁሉም ኖርማል ይሆንብሻል፡፡›› ‹‹አይ … ይኼን እንኳን ባለምደው ይሻላል፡፡ እዚህ ላይ ሃይማኖት ትክክል ነው፡፡›› ‹‹እመኚን ስትለምጂው ደስ ይልሻል፡፡›› ምህረት ለማሳመን ተደረበች፡፡ ‹‹ሌላ ነገር ፈልጉልኝ … በዚህ እንኳን አልፈልግም፡፡›› ‹‹what about sex without marriage? ሴት ልጅ ከባሏ ጋር ካልሆነ አትተኛ የሚለውን ትዕዛዝ ያስቀመጠው ሃይማኖት ነው፡፡›› ‹‹ዝሙት?›› ‹‹እንደሱ ብለው ያገዘፉት እነሱ ናቸው፡፡ መጥፎ ስም በመስጠት ማስፈራራት አመላቸው ነው፡፡ ያን ያህል አይደብርም፡፡ ከፈለግሽው ሰው ጋር ደስተኛ የምትሆኚበት መንገድ ነው፡፡›› ‹‹እጮኛ አለኝ እኮ!›› ‹‹ከሱ ጋር መሆን ይችላል፡፡ ሌላ ወንድ ጋ መሄድ አይጠበቅብሽም፡፡›› ‹‹እስኪ ፀባዩ ይታይና … ደግሞ ታውቃላችኋ ከዚህ በፊት የዚህ ነገር ምንም experience የለኝም፡፡›› ‹‹እናውቃለን፡፡ ከምትወጂው ሰው ጋር ቢሆን ቆንጆ ነው፡፡›› ሰሞኑን ፈተና መጨረሳቸው ነው … እረፍት ስለነበሩ ለማረፍ ወደ ቤቷ መሄድ እንዳለባት ተሰማት፡፡ ራስ ምታቱ ጋብ ሲልላት መኪና ጠርታ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ አባቷና እናቷ ሳሎን መጅሊሱ ላይ ተቀምጠው እያወጉ ነበር፡፡ ሂጃቧ ግጥም ማለቱና የአባያ አለባበሷ ትናንት ምሽት የነበረበትን ሁኔታ አያሳብቅም … ሆኖም ፈራች፡፡ ገላዋ አፍ አውጥቶ የሚናገር የሚናገር መሰላት፡፡ ያለመደባትን እናቷንና አባቷን ሳትስም ከሩቅ ብቻ ሰላም ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች፡፡ መኝታ ክፍሏ ውስጥ ሳለች ስልኳ ጮኸ፡፡ አብደሏህ ነበር፡፡ ‹‹ሄሎ … ›› ድምፁ ውስጥ ኩርፊያ ይነበባል፡፡ ‹‹አብዱዬ›› ‹‹ለምንድነው ስልክሽን የጠረቀምሽው?›› ‹‹አልተመቸኝም ነበር … ለማጥናት ፈልጌ ነው፡፡›› ‹‹አንቺ ለኔ ቦታ አለሽ ግን ከልብሽ?›› ‹‹አትቀባጥር! እዚህ ላንተ ብዬ እየተጋፈጥኩ ያለሁትን እኔ ነኝ የማውቀው!›› ‹‹ስልክሽን ስትዘጊው እኮ ነው፡፡›› ተለሳለሰ፡፡ ‹‹ቤተሰቦችሽ ምን አሉ? ቁርጡን አሳውቂኝ፡፡›› ‹‹እነግርሀለሁ … ትንሽ ታገስ!›› ከሱ ጋር ተሰነባብታ ሻወር ወሰደች፡፡ ልብሷን ቀያይራ ወደ ሳሎን አመራች፡፡ ‹‹አባ ማግባት እፈልጋለሁ፡፡ የኔ ፍላጎት መከበር ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በላይ እናንተን መታዘዝ አልችልም፡፡›› የሞት ሞቷን ከአፏ አወጣችው፡፡ ‹‹ታገቢያለሽ … ግን ልጅ ነሽ … ምን ያጣድፍሻል? በጊዜው ይደርሳል፡፡›› አባቷ ፈገግ ብለው ለመመለስ ሞከሩ፡፡ እናትየው በድንጋጤ እየተመለከቱ ነው፡፡ ‹‹እድሜዬ በቂ ነው፡፡ ከሪማን እያት … እኩያዬ ናት፡፡ እሷ ወልዳለች፡፡ ከጀማል ጋር የተጋባችው ራሱ ገና በ18 ዓመቷ ነው፡፡ ለኔ ሲሆን ነው እንዴ ልጅነት ትዝ የሚላችሁ?›› ‹‹ከሪማና አንቺ አንድ አይደላችሁም፡፡ አንቺ ዶክተር ለመሆን አራት አመት ብቻ ነው የቀረሽ … እሷ 12ኛ ክፍልም አላለፈችም፡፡›› አባቷ በስጨት አሉ፡፡ ‹‹እራሴ አግብቼ ብመጣ ግን እንዳይገርማችሁ እሺ!›› እየተነጫነጨች ወደ ክፍሏ ተመለሰች፡፡ ማዳመጫዋ የተዘጋ ይመስላል፡፡ ምናልባት ወዳጆችዋ እንደሚሉት አመፀኛ ሆናለች፡፡ ጀማል እንኳን ቀና ብሎ ለማውራት ከሚፈራቸው አባቷ ጋር መመላለስ ጀምራለች፡፡ ከሃይማኖት ጫና የመላቀቅ ዳዴ! ይቀጥላል! .

✏️ የደራሲ ፉዓድ ሙና ማለፊያ የተሰኘ አዲስ ኢስላሚክ ታሪክ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ......ይቀጥላል ዝግጁ ናችሁ ወይ❔
✏️ የደራሲ ፉዓድ ሙና ማለፊያ የተሰኘ አዲስ ኢስላሚክ ታሪክ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ......ይቀጥላል ዝግጁ ናችሁ ወይ❔

🎙ወንድም አቡበከር '🤎' 📖 ይህ ወንድማችን ሞቷል፣ አላህ ይርሀመው። ቲላዋውን በማሰራጨት፣ ስንቁን እናብዛለት🌼.
☑️Sαlαh Responds😘

😀 👉 የኢስላሚክ ቻናል ባለቤቶች ቶሎ በሉ Wave መግባት የምትፈልጉ 😮 ✅ 2k-10k+ subscribers ✔️ ✅ 15k+ subscribers ✔️ ✅ 20k+ subscribers ✔️ ✅ 50k+ subscribers ✔️ ✅ 100k+ subscribers ✔️ ሁለተኛ ፎልደር ተዘጋጅቷል 5k+ ያላቹ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ! 🏃 Link ልካቹ Wave ብላቹ አስቀምጡልኝ 🔗 𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 ✉️ ◇ @Waver_boy1 📩

እኛ እንጥራለን — አላህ ይወስናል፤ እኛ እንመኛለን — አላህ ይለግሳል፤ እኛ እንተማመናለን — አላህ አያሳፍርም። »

If your only goal is to become rich, you will never achieve it." ብቸኛ ግብህ ሀብታም መሆን ብቻ ከሆነ፣ ፈጽሞ ልታሳካው አትችልም።

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋: ✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 335❵ #hadith335 "አቡ አብደላህ ጃቢር ኢብን ሰሙረት (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ "ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር እሰግድ ነበር፥ ሶላታቸውም ዲስኮራቸውም መካከለኛና ሚዛናዊ ነበር። (ሙስሊም ዘግበውታል) 📋ያለፈው ክፍል👇📋 https://t.me/Hafu_posts/19335 🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫

❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️ 🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር 📖🎧 #ቁርኣን  || PART ❸❻❹ ⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™ || SHARE 😊

/play quran reaction for 11 hours

/play evening adkhar tofik al habeshi

/play evening adkhar tofik al habeshi