ch
Feedback
Psychology

Psychology

前往频道在 Telegram
194
订阅者
无数据24 小时
无数据7
-630
帖子存档
whenever i go shopping, it’s the faces i see. is you patient enough to handle my indecisiveness? or are you gonna stand over there and መገላመጥ me like you’re the one paying? የእንጀራ ጉዳይ ሆኖ እንጂ most of the people working in customer service are not supposed to be working there. ሲሆን ሲሆን according to their personality they don’t even like interacting with people. ያሳዝኑኛል ሲመናቀሩ and i try to laugh it off. their lack of common decency is not justifiable but some part of me believes they’d be good at their jobs if they were working in a field they liked. i don’t believe in working a job that i don’t like or one i wouldn’t grow into enjoying, i’m actually so serious about this. ”የት ነው የምትኖሪው Deborah?🙂” እንዳትሉኝ። i’m very well aware of the reality most people live in and i have this opinion because i’m probably privileged enough to have it. life is taxing enough as it is let alone finding yourself day in and day out in an environment that you hate. ቢሆንልን i wish for people to earn a living from the things they love and care about, ህልም አይከለከል።

It took me years of wandering through oceans of friendships and connections to realise that my belief in me being unlovable came from the exposure to people who were not kind, people who projected so much of their insecurities and anger towards me and not because I was cursed. Learning to accept that I’m lovable, people enjoy my company and look forward to our conversations has been the most bittersweet experience I’ve had. I had to unlearn the pattern of always looking for that hint of disgust, jealousy and competitiveness in the eyes of people. I’m grateful to have learned that there are days where I have been the problem but that’s not always the case. For I write this from a place of knowing whatever unkindness, negativity and spite thrown at me has nothing to do with who I am as a human being. And I will not make the mistake of believing it determines how I speak and think about myself again. This statement stays even if you someday find yourself to be the problem too.

ሁለት ልጆች እየሮጡ መጡ። ስድስት አመታቸው ነው። አንደኛዋ ለመክሰስ አንደኛዋ ራሷን ለመከላከል ቸኩለዋል። በቅድሚያ ክሱን ሰማሁ። እንደኔ "ሚስተር" የሆነን ሌላ ሰውዬ ሲይዛትና ሲያቅፋት እንቢ ብላ 'Disrespect' ብጤ አሳይታ እንደመጣች ነገረችኝ። ቶሎ ተካሳሽ ቀበል አድርጋ አጥብቆ ይዟት እንደሆነ የመከላከያ ሀሳብ አነሳች። ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ የምላቸውን በጉጉት ጠብቀዋል። ባለ ስልጣን ሚፈልገውን ያለ ጥያቄ በማድረግ "Good Girl" ሽልማቷን ማግኘት የለመደችው ከሳሽም፤ ያደረገችው ትክክል እንደሆነ የምታውቀው ነገር ግን እንደ ጥፋት የተቃጠረባት ተከሳሽም ጽድቋን ለመስማት ተጨንቃለች። ከሳሽ ውስጥ የሆነች Trad Wife አየሁ። ገዢውን ስርአት በማስደሰት የሴትነት ጥበብ ምሳሌ ተደርጋ መታየትና ስርአቱ የሚያቀርበውን ጥቅማ ጥቅም ለመቋደስ የተንሰፈሰፈች። ተከሳሽ ጋር ጥሩ ተስፋ አየሁ። ራሷንና ፍላጎቷን፣ ትክክልና ስህተትን ታውቃለች። ድንበሯን ታሰምራለች። ድምጿንም ታሰማለች። እህቶቿን Under the Bus የምትወረውር ሴት ቅድምያ ራሷን የጣለች ናት። ይቺ ልጅ ጥሩ መስመር ላይ ናት። የወላጅ አያያዝ ልዩነት አየሁባቸው። አንደኛዋ ታላቆቿን ለማስደሰት፣ ራሷን ለመርሳት፣ "ለምን" ሳትል ለመገዛት ሕይወት Condition እየተደረገች ነው።  ሌላኛዋ "ለምን" ብላ ስትጠይቅ ተገቢ መልስ እየተሰጣት ውሳኔዋና ምቾቷም እየተከበረላት Parent እየተደረገች ነው። እኔ የማደርገው አንድ ተግባር ፋይዳው ኢምንት ቢሆንም በሚጠቅማት እንጂ በሚሰብራት አቅጣጫ መሆን የለበትም። ያ Creepy ሰውዬ ትልቅ ሆነም አልሆነም ካልተመቻት እንኳን ጨምቆ አቅፏት፣ እጇን ብቻ ቢይዝ ራሱ እንቢ የማለት ሙሉ መብት እንዳላት ገለጽኩ። "ግንኮ "ሚስተር" ነው" አለችኝ። "ይሁን" አልኳት።

It took me years of wandering through oceans of friendships and connections to realise that my belief in me being unlovable came from the exposure to people who were not kind, people who projected so much of their insecurities and anger towards me and not because I was cursed. Learning to accept that I’m lovable, people enjoy my company and look forward to our conversations has been the most bittersweet experience I’ve had. I had to unlearn the pattern of always looking for that hint of disgust, jealousy and competitiveness in the eyes of people. I’m grateful to have learned that there are days where I have been the problem but that’s not always the case. For I write this from a place of knowing whatever unkindness, negativity and spite thrown at me has nothing to do with who I am as a human being. And I will not make the mistake of believing it determines how I speak and think about myself again. This statement stays even if you someday find yourself to be the problem too.

ራስን ማሳደግ በቀጣይ ሕይወትህን ለማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው። ከታች ቀላል የሆኑ ነገር ግን ለውጥ የሚያመጡ መንገዶች፦ 1. ግብ አዘጋጅ የምትፈልገውን ግብ ግልጽ አድርግ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ግቦችን አስቀምጥ 2. ንባብን ልማድ አድርግ በየቀኑ ቢያንስ 10-20 ደቂቃ አንብብ 👉 ርዕሶች: ስነ-ልቦና, ስኬት, መንፈሳዊ 3. አዎንታዊ አስተሳሰብ ያዝ “እችላለሁ” በል በራስህ ተማመን 4. የጊዜ አጠቃቀምን ተማር አስፈላጊ ነገሮችን አስቀድመህ አድርግ 👉 To-do list ይጠቀሙ 👉not to-do list ይጠቀሙ 5. ጤናህን ጠብቅ እንቅስቃሴ: ጤናማ ምግብ: በቂ እንቅልፍ 6. አዲስ ነገር ሁልጊዜ ተማር ችሎታ (skills) አሳድግ 👉 ምሳሌ: ኮምፒውተር, ቋንቋ, ቴክኖሎጂ 7. መንፈሳዊ እድገት ጸሎት ማሰብ (meditation) 8. ከአዎንታዊ ሰዎች ጋር ጊዜ ይኑርህ 9. ራስህን ገምግም የዕለት ግምገማ አድርግ 👉 “ዛሬ ምን ተማርኩ?” 10. ትዕግሥት ይኑርህ ራስን ማሳደግ ጊዜ ይወስዳል በቀጣይነት  ነገሮችን መከወን 👍ትንሽ ትንሽ እያደግክ ትልቅ ሰው ትሆናለህ!

Pretty hurts ብድግ ብዬ እንደነገሩ አስይዤው የምሄደው ፀጉር፣ ቆንጆ የምለው ፊት እስኪመጣልኝ መዘጋጀት ባይኖርብኝ፣ መጥቶልኝም እስካምነው ድረስ መስታወት ፊት ባልሻጥ፣ ስንት እድሜ አተርፍ ነበር? ከተማ መወለድ ለብዙ ነገር ትርፋማ ቢያደርግም፣ ለመልክ ግን ገበያ ነው። ምን አይነ ግቡ ብንሆን የሚያወዳድሩብን በጣም የምታምር ደግሞ ሌላ አለች፣ እንደሷ ማማር ትችያለሽ የሚል ገንዘብ የሚያስበዘብዝ ማስታወቂያ በየስክሮሉ አለ። ቆንጆ መባል ጎበዝ ከመባል እስኪበልጥብን፣ ሳናምር መውጣት ጠልተን መገኘት ከአለብን ቦታዎች እስክንቀር? ገና እግራችን ሲያደከድክ፣ ከወፌ ቆመች ቀጥሎ ስለመልካችን አስተያየት አልሰማንም ወይ? “አፍንጫዋ ነው እንጂ፣ ጆሮዋ ባይተልቅ፣ ፀጉሯስ ሶስት ፍሬ ናት፣ ሴት ስትቀላ ነው እንጂ፣ ተረከዟ ምን ያክላል?” እየተባልን ቅንጥ ቅንጣችንን ተብለን እሳት እንደነካው ላስቲክ ያልተሰበሰብን አምስት እንሞላለን ወይ? አሁን ላይ “ግን እኮ ቆንጆ ነሽ ለምን እንዲህ ይሰማሻል?” የሚልን አስተያየት ለመስማት ጆሯችን እንደሚያመነታ፣ አይናችን መስታወት ላይ ያለ ምስላችንን ለማመን እድሜውን ደርድሮ በቦውሊንግ ኳስ እንደረመረመ ያለሀፍረት እንዴት ማስረዳት እንችላለን? ብንቆምም፣ ከገላችን ልክ አልቆም እያለ እንደ ሰፊ ውስጥ ልብስ ውልቅ ውልቅ የሚል ቅስም እንዳለን እንዴት ማውራት እንችላለን? “ልጅን ሲወዱ...” ብሎ የተረተ ሀገር መች ከነ ወደደን? ፍቅራቸው በአፍንጫችን ቅናት እና ማጎንበስ አልተወሰነም? ሀሳባችንን ለመሸጥ ስንዝር የማይሞላ ወገብ እንደማይጠበቅብን ሁሉ፣ እድሜያችን 14 ሳይሆን ውሀ ቻፒስቲክ የልጅ ከንፈራችን ላይ ስናፈስ “እሱን ትተሽ ትምህርትሽ ላይ አታተኩሪም?” ተብለናል። በተንኳሽ አለም ተተንኳሽ ይጠነቀቃል:) እኔን ትተህ ትምህርቴ ደጃፍ ላይ ተኮልኩለው የልጅነት ባቴን ከልጅነት ባቷ የሚያወዳድሩንን ጎረምሶች፣ ለገና ማርያምን ለመሆን ቅላት እንደሚያሰፈልግ የምታምነዋን አስተማሪ ተዪ፣ ተው አትልልኝም? አትሉልንም? እድሜ ዘመን የሚከተል ድምፅ እንደምትሰጡን አታውቁም? የውስጥ ድምፃችን የትንኮሳ ቃል እና አሽሙር መሆኑ አያሳዝናችሁም? ስራችሁ ፍሬ አፍርቶ በሌላችሁበትም ለስላሳ ድምፃችንን አሸንፎ የሚወጣው ሸካራ ድምፃችሁ ነው። የፀጉራችን ቴክስቸር ስንት ሚዶ በድዱ እንዳላስቀረ፤ በለስላሳ ሉጫ ፀጉር የሚሰራው ማስታወቂያ እኛን እንዳላየ አልፎን በየቲቪው የሰራጫል። በጥቁር ሀገር ቅላት ይሰበካል፣ ልጅ ያወጣው ፓውች ሁለት ሳምንት ከተቀመጠ የአእምሮ ጤናን የሚያናጋ አስተያየት በየመታጠፊያው እንደመንገድ አበባ ይቀጠፋል፣ በፀጉራችን መሆን ነውር እስኪመስል ድረስ የቀጠልን ለት በተውሶ ውበት በተለየ እንደነቃለን። መጀመሪያ ኢንሴኪዩሪቲው ይሸጣል፣ ያን ኢንሴኪዩሪቲ ተጫርተን ቦዲ ዲስሞርፊያ እንገዛለን፣ ከዛ ጊዜያዊ መፍትሄ በተጋነነ ዋጋ ይከተላል፣ ያቺንም እንደያቅማችን እንቃረጣለን። መፍትሄው አልዘልቅ ሲል ማየት ከምንፈራው መልክ፣ ባዶ ኪስ እና ድባቴ ጋ እንቀራለን። “በሰያፍ በኩል ስታይ ምን እመስል ይሆን?” ብላ በሶስት መስታወት ያንን አንግል ለማየት ያልሞከረች እንስት ለትምህርት እና ለሌላ የህይወት ቁምነገር በቂ የአእምሮ ቦታዋን ያልሰዋች እና መሽቶ በነጋ ቁጥር ለሚፈለፈሉ አሸን ኢንሴኪዩሪቲዎች ያልተሸነፈች ሴት ለኔ ጠንካራዋ እሷ ነች። አብዛኞቻችን ግን ለሲስተሙ እና ለማህበረሰቡ አይን ተሸንፈንለታል። ካፒታሊዝም የቀናው በሴቶች ራስ አለመተማመን ላይ ነው። ገበያውም የጦፈው በሚቀጠለው ፀጉር፣ ጥፍር፣ ሽፋሽፍት፣ የተለያዩ ውበት መጠበቂያ(ማፅናኚያ) ሸቀጦች ነው። ለሀበሻ ማስቀየም እንደንቀት ነው፣ how dare you look like this? Whats with the ድንች አፍንጫ? “ኧረ በመቤቴ ማሰብ ይሻላል?” ብንልም “ዱላ በማይመልሰዉ ነገር አንስማም” የሚለው ብዙ ነው። ደግሞ እኮ nose job, boob job, face lifting, tummy tuck? ካልን ኪሳችንም እንደማህበረሰቡ መሳለቁ አይቀሬ ነው። ይሄ ሁሉ ተደማምሮ ጢባጢቤዉን የሚጫወተው በራስ መተማመናችን ላይ ነው። ገና በልጅነታችን በራስ ያለመተማመን ከጉድሞርኒንግ ሻይ ጋር ነው የሚሸጥልን። "መሆን አለመሆን" የሚለው ጥያቄ የሚጀምረው እዛላይ ፒግቴል ያሲያዘችውን ቆንጆ ትንሽ ልጅ ስናይ ነው። እናማ የውበት ኢንደስትሪው በለጋ እድሜያችን ለበረዶ ባስቀመጥነው ሳንቲም ነው ፐርም(የፀጉር ማለስለሻ) የሚያስገዛን። ቀጭን ሆኖ መታየት፣ ሸንቃጣ መሆንን ያላለመች ሴት፣ በሆርሞን፣ በስራ፣ በኑሮ ምክንያት አልመች ብሏት ከገዛ ሰውነቷ ተኮራርፋ የምትኖረዋም፣ በተገኘው ለማስተካከልም ከጂም ጀምሮ የተለያዩ የሚጠጡ፣ የሚዋጡ ነገሮችንም ያልሞከረች ሴት ቤት ይቁጠራት። ብጉር፣ ማዲያት፣ ዲስከለሬሽን የመሳሰሉትን ለማጥፋት አለ በተባለው ፕሮዳክት ገንዘቧን ያልከሰከሰች ሴት መኖሯም አጠራጣሪ ነው። ስንት ብራ የልጅነት ቀናችን፣ ሮጦ መስሪያ ወጣትነታችን በነዚህ መነጫንጮች ያላግባብ አልፈዋል፣ ፊታችን ላይ ሀፍረት ተሸክመን ኖረናል። አንገታችን በውድድር ብዛት አጎንብሷል። አንዳንዶቻችን ድርድር ያላለ ወጣ ገባ ጥርሳችንን ጮክ ብለን “ሲያምር” ለማለት 34 አመት ፈጅቶብናል። Ain't got no doctor or pill that can take the pain away The pain's inside and nobody frees you from your body It's the soul, it's my soul that needs surgery (It's my soul that needs surgery) Plastic smiles and denial can only take you so far Then you break when the fake façade leaves you in the dark You're left with shattered mirrors and the shards of a beautiful past

የፍቅረኛን ምራቅ መቅመስ (በመሳም ሂደት ውስጥ) ሰፊ የሳይንስና የፍቅር ትርጉም አለው። ​ጥቅሙ ​ ✅​የሆርሞን መለዋወጥ፡ በመሳም ወቅት ምራቅ ሲለዋወጥ ኦክሲቶሲን (Oxytocin) የተባለው የፍቅር ሆርሞን ይረጫል። ይህም በመካከላችሁ ያለውን መተማመንና ቅርበት ይጨምራል። ✅​ጭንቀትን መቀነስ፡ በምራቅ ንክኪ አማካኝነት ኮርቲሶል (Cortisol) የተባለው የጭንቀት ሆርሞን መጠን ይቀንሳል። ✅​የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity)፦ የሚገርመው ነገር፣ መጠነኛ የባክቴሪያ ልውውጥ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት አዳዲስ ጀርሞችን እንዲለምድና እንዲጠነክር ይረዳዋል ይባላል። ​ ✅ (Biological Matchmaking) ​ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ፣ በመሳም ወቅት የምራቅ መለዋወጥ ሳያውቁት የትዳር አጋርን ለመምረጥ ይረዳል። በምራቅ ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች "ይህ ሰው ለእኔ ይስማማል?" የሚል መልዕክት ለጭንቅላታችን ያስተላልፋሉ።

ደስተኛ መሆን! ደስተኛ የመሆን ትልቁ ሚስጥር ገና የሚመጣውን ማሰብ ብቻ አይደለም፤ ወደ ህይወታችን የመጣውንም ማሰብ ነው። ወደ ህይወታችን ከመጣው ምርጥ ስጦታ አንዱ የዛሬው ቀን ነው። የዛሬዋን ቀን ከዚህ በፊት ቀድሞ ያየው አለ? የለም! አዲስ ስጦታ ነው። ለሀብታሙም ለደሀውም፣ ለትልቁም ለትንሹም፣ ለሴቱም ለወንዱም ከፈጣሪ የተሰጠ ልዩ ስጦታ! እየተነፈስክ ተደሰትና ፈጣሪህን አመስግን ወዳጄ።

አሁኑኑ ጀምር! አንተ የምትችለውን ሁሉ ስታደርግ ፈጣሪ ደግሞ የማትችለውን ሁሉ ያደርግልሀል፤ በተኛህበት ግን የሚመጣ እድል የለም! መሮጥና መጣር ስትጀምር ሰዎች እንኳን "ምን እናግዝ? ከጎንህ ነን!" ይሉሀል፤ ያልጠበከው ሲሳይ እጅህ ላይ ይወድቃል። ወዳጄ አንተ ብቻ ያሰብከውን አሁኑኑ ጀምር ሁሉም ምርጥ ሲሆን ታየዋለህ!

ሕይወት አጭርና ውድ ስጦታ ናት። በጉዞህ ላይ ጠቃሚ ይሆናሉ የምላቸውን ጥቂት ነጥቦች እነሆ፦ 1. ራስህን ሁን ሌሎችን ለመምሰል በመሞከር የራስህን ማንነት አታጥፋ። ያንተ ልዩ መሆን ለዚህች ዓለም የሚያስፈልግ ቀለም ነው። በራስህ ማንነት ላይ መተማመንን አዳብር። 2. በሂደት እመን ሕይወት በአንድ ጀምበር የምትቀየር አይደለችም። ትልልቅ ውጤቶች የሚመጡት በየቀኑ ከምታደርጋቸው ትናንሽ ጥራቶች ነው። ስህተት ስትሰራ ተስፋ አትቁረጥ፤ ይልቁንም እንደ ትምህርት ተመልከተው። 3. ለሰዎች ደግ ሁን ደግነት ዋጋ አይጠይቅም፤ ነገር ግን ትልቅ ዋጋ አለው። ለሰዎች የምታሳየው አክብሮትና ፍቅር ወደ አንተ በሌላ መልክ ተመልሶ ይመጣል። ሆኖም ግን፣ የራስህን ሰላም የሚነጥቁ ሰዎችን መለየትና ርቀትህን መጠበቅም ብልህነት ነው። 4. ዛሬን ኑር ስላለፈው መቆጨት ወይም ስለወደፊቱ ከልክ በላይ መጨነቅ የዛሬን ደስታ ይነጥቅሃል። አሁን ያለህበትን ቅጽበት በአግባቡ ተጠቀምበት። 5. ምስጋና ይኑርህ ባለህ ነገር መርካትና ማመስገን የውስጥ ሰላም ይሰጥሃል። ምስጋና በሌለበት ልብ ውስጥ ደስታ ቦታ የለውም። አጭር ማጠቃለያ፦ ሕይወት የምትለካው በኖርክባቸው ዓመታት ብዛት ሳይሆን፣ በኖርክባቸው ጥራትና ለሌሎች በሰጠኸው ብርሃን ነው። ይህ ምክር ካለህበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ይገናኛል? በሆነ የተለየ የሕይወት ዘርፍ (ለምሳሌ ሥራ፣ ትምህርት ወይም ግንኙነት) ላይ በደንብ በመስራት መለወጥ ትፈልጋለህ?? ከሆነ

ሳራ (we were neighbours) had this ቴፕ መሳይ phone, and every time I had no school መዝሙር ክፈቺ እያልኩ እጨቀጭቃት ነበር። Sara, who introduced me to the beauty of Afaan Oromo songs. We were around the same age, she was a little older but if you stared a little bit longer you could see the lines of aging without her will drawn on her face. ልቧ እስኪጠፋ ነበር መዝሙሮቹን የምትዘምራቸው፣ እያለቀሰች ምናምን። እኔ መዝሙሮቹ ስለሚያምሩኝ ነበር ክፈቺ የምላት፣ the raw emotions I can hear in their voices and the melodies magical ስለነበሩ። She barely understood Amharic and I with no knowledge of her language. ረጅም ሰዓት አብረን እንድንቀመጥ የሚያደርጉን መዝሙሮቹ ብቻ ነበሩ። Every time I come across an Afaan Oromo song, she’s all I can remember. ዛሬም ቋንቋው ሳይገባኝ፣ just the beauty making me float እሰማለሁ።

የስኬታማ ቀን ቀመር፦ ቀኑን በእጅህ፣ ሕይወትህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ! ብዙዎቻችን ቀናችንን የምንጀምረው በግርግር፣ በስልክ ንክኪና በድንገቴ ነገሮች ነው። ነገር ግን እውነተኛ ስኬት የሚመጣው ቀኑን አስቀድሞ በመቆጣጠርና በራስህ ቀመር በመምራት ነው። ቀኑን በእጅህ ካደረግክ፣ ሕይወትህን መቆጣጠር ትችላለህ። ✨ ቀኑን ለመቆጣጠር የሚረዱ 3 ወርቃማ መርሆች፦ 🔵 #ቀንህን በምስጋና እና በጸሎት ጀምር፦ ማንኛውም ስኬታማ ቀን የሚጀምረው ከውስጥ ሰላም ነው። ጠዋት ስትነሳ ለተሰጠህ አዲስ ቀን ፈጣሪን በማመስገንና በጸሎት መንፈስህን በማደስ ጀምር። ይህ ለቀኑ የሚያስፈልግህን አዎንታዊ ኃይል ይሰጥሃል። 🔵 የጥሞና ጊዜ ይኑርህ፦ ከግርግሩ በፊት ለጥቂት ደቂቃዎች ቆም ብለህ ራስህን የምታዳምጥበት የጥሞና ጊዜ ይኑርህ። ይህ ጊዜ አእምሮህ እንዲረጋጋ፣ ሐሳቦችህ እንዲጠሩና ለቀኑ ውሳኔዎችህ ጥንካሬ እንድታገኝ ይረዳሃል። ጸጥታ የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ናት። 🔵 በእቅድ መመራት፦ ከምስጋናና ከጸሎት በመቀጠል፣ ቀኑን እንዴት እንደምትውል ግልጽ እቅድ ይኑርህ። "ዛሬ ምን ልሥራ?" ብለህ በማሰብ ጊዜ ከማባከን ይልቅ፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ወደ ሥራ ግባ። 🔵 የራስህን ደንቦች አውጣ፦ ሕይወትህን የሚመሩ ጽኑ ደንቦች ይኑሩህ። ለምሳሌ፦ "ጠዋት እንደተነሳሁ ለተወሰነ ጊዜ ስልክ አልነካም" ወይም "የጠዋት ጊዜዬን ለዕድገቴ ቅድሚያ ለሚሰጡ ተግባራት ብቻ አውላለሁ" የሚሉ ግላዊ መመሪያዎች ለስኬትህ ዋስትና ናቸው። የዕለቱ ልዩ መልእክት አእምሮህ ትኩረት በሚሰጥባቸው ነገሮች ልክ ሕይወትህ ቅርጽ ይይዛል። ጠዋትህን በምስጋና ስትከፍት ለበረከት ትዘጋጃለህ፣ በጸሎትና በጥሞና ስትበረታ የውስጥ ጥንካሬ ታገኛለህ፣ በእቅድ ስትጓዝ ደግሞ ግብህ ላይ ትደርሳለህ። ስኬት በአጋጣሚ የሚመጣ ሳይሆን በየቀኑ በምታደርጋቸው በእነዚህ ትናንሽ ውሳኔዎች ድምር ውጤት ነው። የዕለቱ ጥያቄ፦ የራስህን ቀን ለመቆጣጠር ዛሬ ጠዋት የጀመርከው ወይም ነገ ለመጀመር ያሰብከው አዲስ ልምድ ምንድነው? መልካምና ውጤታማ ቀን ይሁንላችሁ!

በዓሉ ግርማ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢላባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት አጠናቀዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የ ቢ.ኤ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ደራሲ በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ። ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር» የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ሪፑብሊኮች ኅብረት ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ፤ ሙያቸውንም ያስከበሩ ደራሲ ነበሩ። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዜጣ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ረፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጦችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያቸው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሠርተዋል። ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «ኦሮማይ» በመባል ይታወቃል። ይኼውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም. ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል።

ሐቁ ለምን ግን እንደ ወንዶቹ ፥ ግጥም አትፅፍልኝም? ወንዶቹ ግጥም ይፅፉልሽ ነበር? ታዲያሳ። ቀላል ሰው አርገኸኛል... ጥሩ ግጥም? የእውነት አሪፍ? ግጥም ቢሉህ ግጥም ነው? ክንፍ የቀጠሉልኝ አሉ። ሰማያዊ ምንጣፍ የሸለሙኝ አሉ። የደመና ካባ ያጐናፀፉኝ አሉ። ከገነት ሜዳ ላይ ፥ ቆርሰው የሰጡኝ አሉ። እንትን ራሱ... የሆኑ ሰይጣኖችን ይሁኑ ምናምን ፥ ያስቦኩልኝ አሉ። በግጥም ብቻ ይኸውልህ። አይ ጥሩ ምነው ቅር አለህ? አይ ምን ቅር ይለኛል? ወንዶቹ በጣም ይወዱሽ ነበር ስል አሰብኩ በጣም! እኔ ምልሽ? እ አይገርምሽም? ምኑ? ከእኔ ጋር መሆንሽ። እኚያን ሁሉ ወዳጅ ወንዶችሽን መሸኘትሽ። ምን ማለት ነው? አንተ አትወደኝም? እወድሻለሁ እንጂ አይመስለኝም እንዴት አይመስለኝም? እኔንጃ... ምን እንደ ወንዶቹ በግጥም ልግለፅልሽ? ተው። ተው።

አንድ ቀን መቃብር ሲቆፍር የነበረን ሰው እንዲህ ብዬ ጠየቅኩት፡- "ለምንድነው ይህንን ጉድጓድ የምትቆፍረው?" እርሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፡- "የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር ነው።" እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ በእውነት የምትቀብረው በሥጋ የሞቱትን ብቻ ነውን? ወይስ ነፍሳቸው በሕይወት እያሉ የሞቱትን ጭምር? ብዙ ሰዎች በምድር ላይ ይራመዳሉ፣ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፤ ነገር ግን በውስጣቸው ናፍቆትና ፍቅር የለም። እነዚህ ሰዎች ከመቃብር ውስጥ ካሉት በምን ይለያሉ? እውነተኛው ሞት ትንፋሽ መቆም ሳይሆን፣ በልብ ውስጥ ያለው የጥበብና የፍቅር እሳት መጥፋት ነው።

✅መርሳት ጸጋ ነው 💠 አስቡት እስኪ ከተወለዳችሁ ጀምሮ ያስቀየማችሁን ቃል የተጣለችሁን ሰው፣ ሃዘናችሁን፣ ተስፋ መቁረጣችሁን፣ እንባና ለቅሷችሁን፣ የጎዷችሁን ሰዎች፣ ያጋጠማችሁን አደጋ፣ የምትወዷቸው ሲለያችሁ ያለው ስሜት፣ በስራ የከሰራችሁበት፣ የፍቅር ግንኙነታችሁ እንደ ደረቀ አበባ የሆነበትን ቀን፣ የነፍሳችሁን ክፋይ አፈር ውስጥ የዶላችሁበት ቀን፣ ብቻ በአጠቃላይ ክፉ፣ መጥፎ ቀናችንን መርሳት ባንችል መንፈሳችን ተሰብሮ ፣ ክው ብለን በቅጽበት አንሞትም ነበር?! አያችሁ! መርሳት ጸጋ ነው!!! መዋሸት ጸጋ ነው 💠 አስቡት እስኪ! ሁሌ ለሰዎች እውነቱን ብቻ ብንነግር! አንቺ አስቀያሚ! አንተ ደደብ! ብንል። መርጠን ለሰዎች መናገር የማንችለው ቢኖር'! ወንፊት-አፍ ብንሆን፦ጆሮ አይደማም?! ነፍስ አይቆስልም?! አያችሁ እውነት የክት ናት። ሁሌ አትነገርም። እውነት ለመናገር ግዜ፣ ቦታ፣ አውድ ጠብቆ ነው። ታዲያ መዋሸት ሲባል የሚያስቀስፍ ከባድ ውሸት ለማለት አይደላም። ማንንም የማይጎዳ ጠቃሚ ውሸት እንጂ! አያችሁ! መዋሸት ጸጋ ነው!!! Lying is a blessing. So is forgetting!

"ዝምታ ወርቅ ነው" የሚለው ተረት በገሃዱ አለም አይሰራም። በቢዝነስም ሆነ በግንኙነት አለም፣ ካልተናገርክ እንደሌለህ ትቆጠራለህ። ዝምታህ እንደ ብስለት ሳይሆን እንደ ባዶነት ሊተረጎም ይችላል። ሰዎች ሃሳብህን እንዲገምቱ መጠበቅ የለብህም። የማርኬቲንግ ህግ እንደሚለው፤ "ያልተዋወቀ ምርት አይሸጥም"። እውቀት እያለህ ዝም ካልክና መድረኩን ለአላዋቂዎች ከለቀቅክ፣ በነሱ ስር ለመገዛት ወስነሃል ማለት ነው።

‘የታለ ደስታ አምጡት ይቀዳ የት አለ ሀዘን ወዲያ ይደፋ’ አሉና ሰዎች በከንቱ ዋሉ ማልቀስ ሳያውቁ መሳቅ ላይችሉ።

አውቃለሁ ጊዜ ይሰጣል ጀርባ ሳር ይመስልና ይሆናል ጉድባ የትኛውም ሰው ማገዶ አይፈጅም ሞት ብቻ አይደክምም ሞት ብቻ አያረጅም የመቃብሬ ጥቅስ፦ ህይወት በጣም አጭር እኔ በጣም ረጅም 👍🏾