ሪሳለቱል ሂጃብمعرفة الحجاب☀️
前往频道在 Telegram
ስለ ሂጃብ እና መስፈርቶቹ ማወቅ ያለብን አስተማሪ ትምህርቶች የምንለቅበት ቻናል ነው ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ 👇 @Risaletulhijab_bot ኒቃቤን ስወዳት Join and Share 👇 @Risaletulhijab
显示更多7 930
订阅者
-424 小时
-347 天
-14930 天
帖子存档
~ያ ጀባር🍁
አንዳንድ ጊዜ በዙሪያህ የብቸኝነት ግንብ መገንባት አለብህ ፤ ይኸውም ሰዎችን ከአንተ ለማራቅ ሳይሆን፣ አንተን ለማየት ሲሉ ግንቡን አፍርሶ የሚመጣው ማን እንደሆነ ለማየት !»
መላኢካ ነው ያልነው
ስንት ሰው አለ ከቆይታ በኃላ ሸይጧን የሆነብን።🤲
ሰባህኩም ጀሚል 🤌
صباحكم جميل🤎
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
ለሴቶች ብቻ
ቁርዓን በግል በኦንላይን መቅራት የምትፈልጉ ካላችሁ በዚህ ስልክ ወይንም በቴሌግራም በዚህ አናግሩኝ ትለናለች እህታችን
ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ ሒፍዝ መቅራት የምትፈልጉ ካላችሁ እሷ ጋር እንድትማሩ እጠቁማችኋለው
በሳምንት 6 ቀን በሚመቻችሁ ሰዓት
የቴሌግራም አድራሻ @Umu_asiya65
🌿 የቁርአንን ሒፍዝ ለማጠናቀቅ ትዕግሥትና ትጋት ያስፈልጋል!
አንዳንድ ጊዜ የሒፍዝ ጉዞው ከባድ ይሆናል ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀላል ይሆናል። ይህ የጉዞው ተፈጥሯዊ ሁኔታ ነው።
ነገር ግን ጽናት የሚኖረው በጀመረው መንገድ እውነተኛና ቁርጠኛ ሰው ነው።
ከአላህ ጋር እውነተኛ የሆነ ሰው ቢሰናከልም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል በመጨረሻም በአላህ ፈቃድ ይደርሳል።
🤲 አላህ ከቁርአን ባለቤቶች ያድርገን!
°ዉጤት ስላላያችሁ ብቻ
ዱአ ማድረግ አታቁሙ
....አላህ በልባችሁ ዉስጥ ያለዉን
ሹክሹክታ፣እንባ፣ምኞት ይሰማል...ጊዜዉ
ሲደርስም በምስጋና በሱጁድ እንድትወድቁ የሚያደርግ ነገር ይሰጣችኋል....
INSHA ALLAH
አብሽሩ👈
ለሴቶች ብቻ
ቁርዓን በግል በኦንላይን መቅራት የምትፈልጉ ካላችሁ በዚህ ስልክ ወይንም በቴሌግራም በዚህ አናግሩኝ ትለናለች እህታችን
ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ ሒፍዝ መቅራት የምትፈልጉ ካላችሁ እሷ ጋር እንድትማሩ እጠቁማችኋለው
በሳምንት 6 ቀን በሚመቻችሁ ሰዓት
የቴሌግራም አድራሻ @Umu_asiya65
ስልክ ቁጥር 0979746685
እነዛ ከ الله በቀር ሰው ያላወቃቸው ስብራቶች ሁሉ በ الله ፍቃድ ይጠገናሉ፤ ቀናቸውን ጠብቀው ነፃነታቸውን ያውጃሉ።
ትንሽ صبر
ኢማናችን ድሮ እና ዘንድሮ...
ኢማናችን ደካማ ስለሆነጂ ድሮማ ለሌሊት ኢባዳ ቀስቃሽም አያስፈልጋቸው ነበር!
ዛሬኮ ሌሊት ለመነሳት አላራም ቀጥረን ሲጮኽ የምናጠፋ ህዝቦች ሆነናል !
የድካም ማሰረሻ እና የዱንያ ጀነት ማለት በፈገግታ የምትቀበልህ ምርጥየ ሚስትህ ናት !
ከረጅም ስራና ከውጭው ዓለም ውጥረት በኋላ ደክሞህ ወደ ቤት ስትመጣ ፤ ከትከሻህ ላይ ያለው ከባድ ሸክም የሚያራግፈው በሚስትህ ፈገግታ ነው።
ይህቺ ድንቅ አጋር ስትቀበለው ከላይ ሳቅ ብቻ አይደለም የምትለግሰው ። በፈገግታዋ ውስጥ የማይሰለች ደስ የሚል ፍቅር በልቧ ይዛ ነው።
በውጭው ዓለም የደከመውን አዕምሮህን እንድትረሳ ታደርግሀለች ። ቤትህንም ከቤትነት በላይ ወደ ውብ ማረፊያ ትቀይርልሀለች ። እንዲህ ያለች ምርጥ ሚስት ያለችበት ቤት እውነተኛው የዱንያ ጀነት ነው ።
እስልምናም ለትዳር አጋር መልካምነትና ለዚህ የቤት ውስጥ ሰላም ትልቅ ቦታ ይሰጣል። ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል ።
الدُّنْيَا مَتَاعٌ، وَخَيْرُ مَتَاعِ الدُّنْيَا الْمَرْأَةُ الصَّالِحَةُ
ዱንያ መጠቃቀሚያ ናት፤ ከመጠቃሚያ ሁሉ በላጩ ደግሞ መልካም ሚስት ናት።
ሙስሊም ዘግበውታል ።
ከስራ ሲመለሱ በፈገግታና በመልካም ውበት የምትቀበል፣ የባልዋን ልብ የምታስደስት እንዲህ ያለች ምርጥ ሚስት ካለችህ በእርግጥም የዘመኑ እድለኛ ነህና አላህን አመስግን!
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
= https://t.me/Risaletulhijab
አንድ ነገር በሕይወት አትርሱ…
ሰዎችን በመልካም ያዙ፤ ምክንያቱም ሁሉም ከሚታየው በላይ የተደበቀ ታሪክ አለው።
አንዳንዱ ፈገግ ይላል፣ በውስጡ ግን ያዝናል። አንዳንዱ ዝም ይላል፣ ግን ብዙ ነገር በልቡ ይሸከማል። አንዳንዱ ከሰዎች ይርቃል፣ ምናልባት ሰላሙን ለመጠበቅ ይሆናል።
ስለዚህ ሰዎችን በመልካቸው አትፍረዱ፤ በሀብታቸው አትለኳቸው፤ በስህተታቸውም ብቻ አትገምቷቸው።
መልካም ቃል ተናገሩ፣ ማንንም አትናቁ፣ ይቅር ማለትን ተማሩ፣ ለሌሎችም በምትችሉት ልክ መልካም ነገር አድርጉ።
የሰው ትልቅነት በሚያወራው ብዛት ሳይሆን፣ በሚያሳየው #ሥነ ምግባር ይለካል።
ተውባ | توبة
ተውባ ማለት፦ አላህን ከመታዘዝ በመውጣት ከኃጢአት ወደ መታዘዝ መመለስ ማለት ነው።
ተውባ ተቀባይነት እንዲኖረዉ፦
ኃጢአቱን መተው ያስፈልጋል።
በተፈጸመው ኃጢአት
መጸጸት ያስፈልጋል።
ወደዚያ ኃጢአት ላለመመለስ በቁርጠኝነት መወሰን ያስፈልጋል።
የአላህ ምሕረት ሰፊ ነው። ከወንጀል ከጥፍት ለመመለስ አትቆይ ወደ አላህ ቶሎ በመመለስ ተዉበት አድርግ።
እስኪ አንድ መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ…
አሁን እያነበብኩት ያለሁት ይህን መጽሐፍ ነው። እውነት ለመናገር፣ መጽሐፉን እያነበብኩ ስሄድ የበለጠ ለማንበብ እንድጓጓ እያደረገኝ ነው።
ስለ ረሱል ﷺ የተጻፈ ብቻ አይደለም…
የረሱል ﷺ ስነ-ምግባርና ባህሪ
አስተምህሮታቸው
ስለእሳቸው የተነገሩ የተዛቡ አስተሳሰቦችና ምላሾቻቸው
ስለእሳቸው ﷺ የተነገሩ አስገራሚ ትንቢቶች
እና ከእኛ ዘመን ጋር የሚያገናኙ ጉዳዮችንም ይዳስሳል።
የሚገርመው ደግሞ አቀራረቡ ነው…
በጣም ሳቢ፣ ቀላል እና አንድ ገጽ ካነበብክ ቀጣዩን ገጽ ለማየት የሚያጓጓ አዘገጃጀት ነው።
እናንተም ስለ ረሱል ﷺ ማወቅ፣ መማር እና ማንበብ የምትወዱ ከሆነ፣ ይህን መጽሐፍ እንድታዩት እጋብዛችኋለሁ።
📌 መጽሐፉ፦ [ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ]
✍️ ደራሲ፦ [ኡስማን ሙስጠፋ]
📞0912027023/0921390122
Telegram @Usmanoman
Telegram channel👇 https://t.me/usmanic_psychology
ደግሞ ምን አግኝታ ሳቀች እንጂ ...ምን አታ ከፋት የሚልሽ የለም🙌
የሆድሽን ብሶት ለአሏህ እየነገርሽ ዝም ብለሽ ፈገግ በይ #ፈገግ🤗🌸
