ASTU Network ®️
前往频道在 Telegram
🛜 ASTU Network ®️ ➲ Join us || @ASTU_Network || || @ASTU_Network_Group || 📚 Library: @ASTU_Network_Library 👁🗨 We are here to keep you updated! ➲ Admin 📩 👤 @NS_Nazu Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷] |➲| @ASTU_Network
显示更多4 862
订阅者
-524 小时
+487 天
+31530 天
帖子存档
4 861
+1
#ምርጫ2018
ምን ያህል የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመራጭነት ተመዘገቡ ?
በዩኒቨርስቲዎች በተከናወነ የመራጮች ምዝገባ 20,122 ተማሪዎች የመራጭነት ምዝገባ ማከናወናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ለሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ለመራጭነት የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነሱን ተመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለምን ? ሲል ለቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ጥያቄ አቅርቧል።
ሰብሳቢዋ ቁጥሩ አነስተኛ መሆኑን ገልጸው ሆኖም በአከባቢያቸው ባለ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ በርካታ ተማሪዎች በአከባቢያቸው ባለ የምርጫ ጣቢያ በመመዝገባቸው ቁጥሩ መቀነሱን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የለማው የመመዝገቢያ ፕላትፎርም ዘግይቶ ወደ ተግባር መግባቱን የገለጹት ሰብሳቢዋ ጉዳዩ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም በአጭሩ ግን በመደበኛ መኖሪያ ቦታቸው በመደበኛው የምዝገባ ሁኔታ የተመዘገቡ ብዙ አሉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም
@tikvahethiopia
4 861
#ስፖርት : በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ አርሴናልን በፍጹም መለያ ምት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ቻለ።
ፒኤስጂ አርሰናልን በመለያ ምት 4 ለ 3 ማሸነፍ ችሏል።
ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀው ተጨማሪ ደቂቃ ቢሰጣቸውም ሊሸናነፉ አልቻሉም። ይህን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተው ፒኤስጂ ማሸነፍ ችሏል።
ፒኤስጂ ለተከታታይ አመት ነው ዋንጫውን ማንሳት የቻለው።
ቲክቫህ ስፖርት / @tikvahethsport
ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
4 861
🚀 Tech With Hos
Joke aside — This channel is about building skills that actually open doors in tech.
👉 What you’ll find here:
➲ Core 💻 Computer Science & programming fundamentals.
➲ Competitive programming insights (ICPC 🧠 mindset)
➲ Real-world 🌐 software development tools, workflows, and projects
➲ Practical data analysis 📊 concepts
➲ Lessons inspired by ICPC finalists and top 🏆 competitive programmers
➲ Career guidance from seniors working in big tech
➲ Essential tech news 📰 and trends for serious students
For students who think long-term, build leverage early, and aim high.
Maintained by -👨💻 Mr. Hosam Adem 🔰Software Engineering student at ASTU, 🔰Competitive Programmer & A2SVian 📥 Contact hos - TelegramJoin Channel |➲| Tech with hos #techwithhos #technews #hos
4 861
#Update #CBE
ውድ ደንበኛችን:
*
የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ሲያዘምኑ 'Passphrase' ጠይቆዎት ከነበረ ወይም ማንኛውንም አይነት ድጋፍ ካስፈለገዎት ወደ አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን እንደገና በቀላሉ አስጀምረው መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ መተግበሪያውን እስኪያስተካከሉ ድረስ አገልግሎቱን በ USSD *889# በኩል እንዲጠቀሙ በአክብሮት እንገልፃለን።
በዚህ አጋጣሚ ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት የአሰራር ሂደት የሌለ መሆኑን በመረዳት እራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ።
ለማንኛውም አይነት መረጃ 951 በነፃ ይደውሉ!
*
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!!
©️ CBE
|➲| @ASTU_Network
4 861
#ENEC 🤝 #ASTU
Adama Science and Technology University Signs MoU with Ethiopian Nuclear Energy Commission
======================================
Adama Science and Technology University (ASTU) has signed a Memorandum of Understanding (MoU) with the Ethiopian Nuclear Energy Commission on May 29, 2026, at the Commission’s office in Addis Ababa.
The agreement aims to establish a strong and sustainable partnership between ASTU and ENEC in advancing national human capacity development, academic programs, research, and institutional collaboration in the peaceful application of nuclear science and technology, in line with Ethiopia’s national nuclear policy and International Atomic Energy Agency (IAEA) standards.
The collaboration will focus on curriculum design and academic development based on IAEA frameworks, education and training, research and development, practical training and internship opportunities, capacity building and knowledge management, as well as workshops and scientific events.
During the discussion, both institutions emphasized the importance of transforming the agreement into practical and impactful activities that contribute to national development and technological advancement.
The MoU was signed by Dr. Lemi Guta, President of ASTU, and Mr. Sandokan Debebe, Commissioner of ENEC.
ASTU, the very University for you!
We are dedicated to innovative knowledge!
|➲| @ASTU_Network
4 861
+9
#ENEC 🤝 #ASTU
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ኒውክሊየር ሀይል ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
======================================
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ከኢትዮጵያ ኒውክሊየር ሀይል ኮሚሽን (ENEC) ጋር ግንቦት 21/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በኮሚሽኑ ጽ/ ቤት የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርሟል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኒውክሊየር ፖሊሲ እና በዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) መስፈርቶች መሰረት በኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሰላማዊ አጠቃቀም ዘርፍ የሰው ኃይል ልማት፣ የትምህርት ፕሮግራሞች፣ ምርምር እና ተቋማዊ ትብብርን ለማጠናከር የተዋቀረና ዘላቂ የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ ነው።
ትብብሩ በIAEA ማዕቀፎች መሰረት የሥርዓተ ትምህርት ንድፍና የአካዳሚክ ልማት፣ ትምህርትና ስልጠና፣ ምርምርና ልማት፣ ተግባራዊ ስልጠናና የልምምድ ዕድሎች፣ የአቅም ግንባታና የዕውቀት አስተዳደር፣ እንዲሁም ወርክሾፖችና ሳይንሳዊ ዝግጅቶች ላይ ያተኩራል።
በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ተቋማት ስምምነቱን ለሀገራዊ ልማትና ቴክኖሎጂ ዕድገት የሚያበረክቱ ተግባራዊና ውጤታማ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የመግባቢያ ሰነዱን የአ.ሳ.ቴ.ዩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ እና የኢ.ኒ.ሀ.ኮ ኮሚሽነር አቶ ሳንዶካን ደበበ ተፈራርመዋል።
|➲| @ASTU_Network
4 861
#ENEC 🤝 #ASTU
የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን (ENEC) ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ጋር ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኒውክሊየር ፖሊሲ እና በዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) መስፈርቶች መሰረት በኒውክሊየር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሰላማዊ አጠቃቀም ዘርፍ የተቀናጀና ዘላቂ የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ ነው።
ትብብሩ በዋናነት በሰው ኃይል ልማት፣ በስርዓተ ትምህርት ንድፍና አካዳሚክ ልማት፣ በምርምርና ልማት፣ በተግባራዊ ስልጠና፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በሳይንሳዊ ዝግጅቶች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች ስምምነቱ ለሀገራዊ ልማትና ዕድገት ፋይዳው የላቀ መሆኑን በመግለጽ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የመግባቢያ ሰነዱን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ እና የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሳንዶካን ተፈራርመውበታል።
|➲| @ASTU_Network
4 861
YouTube trusted creators since 2024. Now it trusts machines.
For two years, creators were asked to label AI videos themselves.
Many simply did not do it.
So YouTube built a system that detects AI on its own.
Soon every AI video you watch will carry a visible label.
The marker now sits right below the video, not hidden away.
You will know what is real before you press play.
©️ The Next Web
|➲| @ASTU_Network
4 861
#ጥቆማ
የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን የነጻ ትምህርት ዕድል ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞች በሩሲያ የነጻ ትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ለ2026/27 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ብቁ አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።
የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች በኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነዚህን ዘርፎችንም ያካትታል ፡-
- Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc & MSc)
- Nuclear Physics and Technology (BSc)
- Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc)
- Heat Power Engineering (BSc)
- Management in Technological Systems (MA)
የመወዳደሪያ መስፈርቶች ?
• ለመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤታቸው 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ።
• ለሁለተኛ ዲግሪ (MSc/MA) ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ያልበለጠ እና በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ።
ሴት አመልካቾች ለዘርፉ እንዲበረታቱ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ enecinfo@enec.gov.et መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
4 861
Repost from 𝐀𝐒𝐓𝐔 𝐄𝐧𝐭𝐞𝐫𝐭𝐚𝐢𝐧𝐦𝐞𝐧𝐭 ™️
When you finally reach home and find them watching TV 📺😁
You guys still watch TV? 😅
4 861
ለክቡራን የባንካችን ደንበኞች፡
**********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎቱን ቀላል፣ ምቹ እና በማንኛውም ሰዓት ተደራሽ ለማድረግ ዲጂታል የአገልግሎት አማራጮችን በየጊዜው ለደንበኞቹ እንደሚያቀርብ ይታወቃል።
ከባንኩ ዲጂታል የአገልግሎት አማራጮች መካከል ደግሞ ደንበኞች ሂሳባቸውን በቀላሉ በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ በስልካቸው እንዲያንቀሳቅሱ ያስቻለው የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ዋነኛው ነው።
ባንካችን የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በየጊዜው አገልግሎቱን የሚያዘምን ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜም በርካታ አዳዲስ የአገልግሎት አማራጮችን በማካተት እና ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል በማድረግ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት መተግበሪያውን በአማራጭነት አሻሽሎ አቅርቧል።
በዚህ መሠረት የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በርካታ ደንበኞች እየተጠቀሙበት ሲሆን፣ አዲስ በመሆኑ ምክንያት በተወሰኑ ደንበኞች ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል እንዳጋጠመ ተረድተናል። ባንካችን ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቀ፣ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን እና ችግሩ እንደተፈታም ለደንበኞቻችን እንደምናሳውቅ ለመግለፅ እንወዳለን።
ከተሻሻለው መተግበሪያ ጋር በተገናኘ ችግር ያጋጠማችሁ ደንበኞቻችን ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት፤ ወደ 951 ነፃ የደንበኞች የጥሪ ማዕከል በመደወል ወይም በባንካችን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በመግባት ድጋፍ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
https://chat.whatsapp.com/BFR1h7SrAti091qznFEP4u
4 861
#ጥቆማ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በስሩ በሚገኙ የኢንጂነሪንግ፣ የጤና እና የቢዝነስና ማኅበራዊ ጥናት ኮሌጆች በ2019 ዓ.ም በተለያዩ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብሮች ተማሪዎችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ለማስተማር ይፈልጋል።
የምዝገባ መስፈርቶች
➫ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ
➫ በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን የመግቢያ ነጥብ የሚያሟሉ
➫ ሙሉ ጤነኛና ለጤና ምርመራ ፈቃደኛ የሆኑ
➫ ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑ
➫ የመከላከያ ምልመላ መስፈርቶችን የሚያሟሉ
በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች 1ኛ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የምትማሩ ተማሪዎች በዝውውር 2ኛ ዓመት መቀጠል ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
የትምህርት መስኮች
➫ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ፕሮግራሞች (Bachelor of Technology)
➫ የቢዝነስና ማኅበራዊ ጥናት ኮሌጅ ፕሮግራሞች (BA)
➫ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፕሮግራሞች (BSc)
የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ሰኔ 05/2018 ዓ.ም
የመመዝገቢያ አማራጮች
➫ በአካል በተቋሙ የምዝገባ ማዕከላት
➫ በኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://www.etdu.edu.et/admission/register
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
➫ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
➫ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት
➫ ኦርጂናል ሰነዶች ከሁለት ኮፒ ጋር
➫ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
ለበለጠ መረጃ 👇
ዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር፦ 0114308408
@tikvahuniverity
4 861
🌙 Eid Mubarak to the ASTU Family! ✨
As the beautiful days of Eid al-Adha begin, we extend our warmest wishes to all our Muslim students, staff, and general members.
May this blessed festival of sacrifice bring immense joy, peace, and prosperity to your lives. Let us embrace the spirit of unity, sharing, and compassion within our campus community and beyond.
Wishing you and your loved ones a wonderful celebration filled with love, laughter, and delicious food!
Happy Eid al-Adha!
|➲| @ASTU_Network
4 861
ከሲኒየር ካፌ አጠገብ ያሉት ስቴሺኔሪዎች ጋር ይህን 10 ብር የጣለ ፣ ብሩ የቱጋር የተቀደደ ቦታ እንዳለው በመናገር መውሰድ ይችላል 😅
.
4 861
+1
አስቱ ሙስሊም ጀማዓ በደስታ እና በክብር በOBN TV ላይ በዒድ አል-አድሓ ረቡዕ የሚደረግ ልዩ ቃለ መጠይቅ ለመሳተፍ ተጋብዟል 🎉
በዚህ ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ሕይወታችንን፣ የዒድ ትዝታዎቻችንን እና የተማሪ ልምዶቻችንን እንካፈላለን ✨
በጣም በደስታ እንጠብቃለን፣ እና OBN TV ከአስቱ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር ዒድን መካፈሉ ልዩ ክብር ነው 🤍
ተከታተሉን! 📺🌙
4 861
#ዜና
ባለፈው ግንቦት 14 ፣ 2018 ዓ.ም በዩኒቨርስቲያችን ኦዳ ናቤ አዳራሽ የተደረገ ስብሰባ ነበር። ይህ ስብሰባ በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እና በዩኒቨርስቲው እንዲሁም በሀገሪቱ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተደረገ ነበር።
ከዩኒቨርስቲያችን ፕሬዚዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከመንግሥት ባለስልጣናት ደግሞ የመከላከያ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እንዲሁም ከፍተኛ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጄነራሎች ተገኝተዋል።
የተደረገው ውይይት እጅግ ገንቢ የሚባል ሲሆን ፣ በዋናነት በቅርቡ በሀገር ደረጃ ስለተመሰረተው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ መግለጽና ፣ ስለ ተቋሙ ህዝቡ በተለይም ተማሪዎች ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ እና ማስፋት ላይ ያተኮረ ነበር።
በውይይቱም ተማሪዎች ስለ ዩኒቨርስቲው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተደረገ ሲሆን ፣ የተለያዩ አካላት ፣ በተለይ በቀጣይ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚቀላቀሉ ወጣቶችን ጨምሮ ሌሎችም ተቋሙን እንዲቀላቀሉ ግንዛቤው የተሰጣቸው ተማሪዎች ግንዛቤ እንዲሰጡ እና የተቋሙን ራዕይ እንዲደግፉ ሀገራዊ ጥሪ ቀርቧል።
ከዚህ በፊትም የተከበሩ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ተገኝተው ስለ ኢፌዴሪ አየር ሀይል ግንዛቤ ከሰጡ በኋላ ፣ ፍላጎቱ እና ተሰጥኦ ያላቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሀገራቸውን ለማገልገል ተቋሙን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
📰 ዘገባው የASTU Network ነው!
|➲| @ASTU_Network
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
