DBU INSIDER
前往频道在 Telegram
Voice and ear of deberberhan university community. a channel where you can get fast and reliable information about deberberhan university.
显示更多6 507
订阅者
+1824 小时
+2427 天
+87530 天
帖子存档
6 507
#MoE
በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
@DBUINSIDER
@DBUINSIDER
6 507
🍔 ክሪስፒ እርጥብ ቤት🍹
ለእርጥብ አፍቃሪያን በሙሉ 🔥እነሆ ላለፉት 🤩 አመታት በጣፋጭ እርጥቡ ምታዉቁት ክሪስፒ እርጥብ ቤት በአዲሱ ዘመን በማራኪ አቀራረብ እና በልዩ ጣዕም በአዲስ መልክ ወደ እናንተ መመለሱን ስንገልፅ በ ታላቅ ደስታ ነዉ ።
✅Normal እርጥብ ፣
✅Special እርጥብ ፣
✅እርጥብ በካቻፕ ፣
✅እርጥብ በአቡካዶ፣
የፈለጉጥን በ ግሩም ጣዕም እኛ ጋር
ለ ካምፓሳችን ተማሪዎች ጥናቱን ትንሽ ገታ📖
አድርገዉ ከጓደኞቻችሁ ጋር ይምጡ ይገባበዙ
ከትሁት መስተንግዶ ጋር እንጠብቅዎታለን 🤝
" 🔥ክሪስፒ is Back🔥"
አድራሻችን :- ዩኒቨርሲቲ ታክሲ ተራ
እንደዚሁም ቀድመዉ ከስር በሚገኘዉ ስልክ ደዉለዉ ማዘዝ ይችላሉ
📞 +251 901633037
@DBUINSIDER
@DBUINSIDER
6 507
1 ምደባ ያላገኛችሁ ተማሪዎች ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 06 ሄዳችሁ በጸሑፍ ማመልከት አለባችሁ፡፡
2. በሕጉ መሰረት ምርጫ መርጣችሁ ቅሬታ ያለባችሁ ተማሪዎች በየኮሌጃችሁ በጸሑፍ እስከ ሰኞ 4፡00 ብቻ ማመልከት አለባችሁ፡፡
3. ሌሎች ምደባውን ያገኛችሁት ተማሪዎች ወደየ ትምህርት ክፍላችሁ ሄዳችሁ እንድትመዘገቡ እና ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን። መልካም የትምህርት ግዜ ይሁንላችሁ!!
6 507
For 1st year students ‼️
1 ምደባ ያላገኛችሁ ተማሪዎች ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 06 ሄዳችሁ በጸሑፍ ማመልከት አለባችሁ፡፡
2. በሕጉ መሰረት ምርጫ መርጣችሁ ቅሬታ ያለባችሁ ተማሪዎች በየኮሌጃችሁ በጸሑፍ ማመልከት አለባችሁ፡፡
ለምሳሌ .፡- የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ማሕበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ማመልከት አለባችሁ፡፡
6 507
ተመስግናቿል ‼️
የምስጋና እና የአክብሮት መግለጫ
ከ ተማሪ ነገሠ ይቻለዋል
በነበረብኝ ከባድ የኩላሊት ህመም ምክንያት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቀዶ ህክምና አድርጌ ሙሉ ጤንነቴን መልሼ ለዚህ ላበቃኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋናዬ ይድረስ። በመቀጠልም ህይወቴን ለማትረፍ በፀሎት፣ በሀሳብና በገንዘብ ከጎኔ ለቆማችሁ በሙሉ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በተለይም ህክምናዬ እንዲሳካ ላደረጉልኝ ከፍተኛ ድጋፍ ለሚከተሉት አካላት የላቀ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡-
🙏 ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስማረ እና ለፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ባዩ — ላሳዩት አባታዊ ድጋፍና ትኩረት፤
🙏ለተማሪዎች ክሊኒክ ሰራተኞች (ለዶክተር ነጋ) እና ለሀኪም ግዛው ሆስፒታል ሰራተኞች (ለዶክተር ዘመድ እና ዶክተር ዮሐንስ)፣ለኢትዮጵያ ጤና ተማሪዎች ማህበር EHPSA — ላደረጉልኝ የህክምና እንክብካቤ እና ትብብር፤
🙏ለተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት (በተለይም ለአቶ ጊዜው ፈጠነ) — ህክምናውን በጥሩ ሁኔታ እንድከታተል ላደረጉት ብርቱ ጥረት፤
🙏ለዩኒቨርሲቲው ሰላምና ደህንነት (ለሳጅን አበበ) — ላደረጉት ጥበቃና አጋርነት፤
🙏ለሴቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት (ለአድስ አስፍው ወሰን) — ስፖንሰር በማፈላለግ ላደረገችው ያልተጠበቀ effort፤
🙏ለ DBU Daily News፣ Ambashaw TV ፣ DBU Insider፣ DBU Students Voice፣ — መረጃ በማሰራጨትና ገንዘብ በማሰባሰብ ላደረጉት የጎላ አስተዋጽኦ።
🙏ለህግ ተማሪዎች ማኅበር፣ ተማሪ ፖሊስ፣ ተማሪዎች ህብረት እና በጎ አድራጎት ክበብ፤
🙏ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ለማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ፣ ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል እና ለደብረ ብርሃን ህዝብ — ላሳዩኝ ደግነትና አጋርነት፤
ምንጭ :- Dbu students voice
6 507
+3
☕️ አሀዱ ቁርስ ቤት 🍔
🎉 እንኳን ለ 2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት እና አዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ ፩ዱ ቁርስ ቤት 📖 አዲሱን የትምህርት ዘመን በጣፋጭ ቁርሳችን ይጀምሩ ይላችሁአል🍳
☕ ፩ ቁርስ ቤት አዲሱን ዓመትና አዲሱን የትምህርት ዘመን ምክንያት በማድረግ ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ Contrat ተጠቃሚዎቻችን በሙሉ በሁሉም የምግብ ዝርዝሮች ላይ
በ1️⃣0️⃣Birr🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩
ማስጠቀማችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነዉ።
ከዚህ ተጨማሪ አዲሱን እና ጣፋጩን
👉 እርጥብ በፍላፍላችንን በታላቅ ቅናሽ
✅ በ1⃣🤩🤩ብር ብቻ ማቅረባችን አይረሳ።
፩ዱ ቁርስ ቤት ☕️ 🌮
🍰🍴
አድራሻ :- ከግቢ በዋናዉ በር ወጣ እንዳላችሁ አደባባዩ ፊት ለ ፊት።
📞+251 946131419
አዲስ ዓመት፣ አዲስ የትምህርት ዘመን፣ አዲስ ጉልበት ፣ ልዩ ጣዕም ! ! 💪🍽️
@DBUINSIDER
@DBUINSIDER
6 507
Repost from Dbu students voice
የተማሪ ህብረት ምርጫ ሊደረግ እንደሆነ መረጃ እጃችን ላይ ገብቷል።
Students Voice የታገለችለት እና እየታገለችለት የሚገኘው የተማሪዎች የውክልና ጥያቄ መፍትሄ የሚያገኝበት እድል ከፊታችን እየመጣ ይመስላል።
የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን በትኩረት እየሰራበት እንደሆነም ደርሰንበታል።
ምርጫው ግልፅ እና ፍትሀዊ እንዲሆን ቻናላችን የበኩሏን እየተወጣች ትቀጥላለች።
በዚህ አጋጣሚ DBU insider በተማሪ ህብረት ዙሪያ ላደረጋቸው አስተዎፅኦ ምስጋና ሰጥተን ማለፍ እንፈልጋለን!
@dbudbu11
6 507
the most gorgeous girl in Debre Berhan University history ❓
Any ways To look at a masterpiece like this and not appreciate it is simply denying the Creator’s finest work.
Absolute perfection 👌 (Miss DBU 👸)
@DBUINSIDER
@DBUINSIDER
6 507
Urgent Notice
Dear other social Science, other Natural Science, Pre-Engineering, and Computing Science Students,
You are required to complete your department choices by tomorrow, 19/01/2019 E.C., at 11:30 LT. If you have any difficulties with your department choice, NG cases, or other related issues, please contact your respective college for assistance. If you need further support, please visit the Registrar's Office, Room F1, No. 6.
Thank you for your cooperation.
Source Dbu freshman 2018
6 507
Notice ‼️
1/ ከተመዘገባችሁበት ጊዜ ጀምሮ ክፍያ ስለሚፈፀም ካፌ መመገብ አትችሉም
2/ የመጀመርያ ወር ክፍያ ስለሚዘገይ የራሳችሁን ጥንቃቄ አድርጉ
3/ የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2:30 -5:00 ከሰዓት ከ 7:30 - 10:00 ነው ።
6 507
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይፋ ሆኗል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 950 ብር ሆኗል፤ 350 ብር ለምዝገባ እና ቀሪው በትምህርት አይነት የፈተና ክፍያ። ለውጪ ዜጋ 100 ዶላር።
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 2,000 ብር ተደርጓል። 500 ብር የምዝገባ እና 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ መሆኑ ተገልጿል። ለውጪ ዜጋ 100 ዶላር።
የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር የተደረገ ሲሆን፣ 500 ብር የምዝገባ እና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ መሆኑ ተመላክቷል። ለውጪ ዜጋ 100 ዶላር።
የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር ሲሆን፣ 1,000 ብር የምዝገባ እና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ መሆኑ ተገልጿል። ለውጪ ዜጋ 150 ዶላር።
ደንቡ ሌሎች ተቋሙ ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የክፍያ መጠንንም አስቀምጧል።
የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ለማግኘት
➻ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 115 ዶላር።
ምትክ ሰርተፊኬትና የማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት
➻ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 170 ዶላር።
በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል
➻ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 130 ዶላር።
የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት
➻ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 75 ዶላር።
ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለማስላክ
➻ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 50 ዶላር።
(የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
6 507
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማረ መለሰ
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት፣ በሴኔቱ እና በራሴ ስም ለመላው የእምነቱ ተከታዮች፣ ለተከበራችሁ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ ተመራማሪዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ።
የእቴጌ እሌኒ የእውነተኛውን መስቀል የመፈለግና የማግኘት ጉዞ፤ ጽናትን፣ ተስፋ አለመቁረጥን እና ትጋትን በተግባር ያስተማረን ታላቅ ክስተት ነው። ዩኒቨርሲቲያችንም እንደ ተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (Applied Science University) ለዕውቀት ሽግግርና ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚተጋ ተቋም እንደመሆኑ፣ ከዚህ በዓል ታላቅ መነሳሳትን በመውሰድ እውነትን፣ አካዳሚያዊ ልቀትን እና የፈጠራ ሥራዎችን የመፈለግ ጉዞውን አጠናክሮ ይቀጥላል።
የደመራ ማገዶ መብራት ጨለማን የሚገፍ የብርሃን ምልክት ነው። የደመራውን በዓል በጋራ ስናከብር ሁላችንም ለሚከተሉት እሴቶች ቃላችንን ልናድስ ይገባል፡-
፨ አንድነትና አብሮነት፡- በዩኒቨርሲቲያችን ግቢዎች ውስጥ በፍቅርና በትብብር በመስራት ልዩነቶችን ማጥበብ
፨ ሰላምና መረጋጋት፡- ዕውቀትና ምርምር የሚጎለምስበትን ሰላማዊ አካዳሚያዊ ከባቢ መፍጠር
፨ የተቋም እድገት፡- ለሀገራዊ ብልጽግና እና ለማኅበረሰብ ዘላቂ ጥቅም በጋራ ወደፊት መራመድ ነው።
ይህ የተቀደሰ በዓል ለእናንተና ለቤተሰባችሁ እንዲሁም ለሀገራችን የጤና፣ የሰላም፣ እና የደስታ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።
መልካም የደመራ እና የብርሃነ መስቀል በዓል!
ዶ/ር አስማረ መለሰ
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
@DBUINSIDER
@DBUINSIDER
