የጥበብ - መንገድ ™
前往频道在 Telegram
❝ Art is a step from nature toward the Infinite ~ Kahlil Gibran ™🌸📚 @abawassie ✉️
显示更多5 759
订阅者
-124 小时
-127 天
-6530 天
帖子存档
5 759
መስቃ
(በእውቀቱ ስዩም)
ተፈጥረን በጎግ ማጎግ ምድር
በሰላም ተኝተን አናድር፤
ሀውልታችችን የቃየን ድንጋይ
ስማችን ሽብሩ፤ ኢጄታ ፣ ገላጋይ
ነፍስ ሳናውቅ፤ ከነፍሰ ገዳይ ተዋውቀን
ከመርባታችን ተላልቀን
በጥይት ተገበያይተን
በፈንጅ ወረዳ፤ ሰኞ ማክሰኞ ተጫውተን፤
ጎልማሳው ከሚስቱ ፅዋ ፣ ተጎንጭቶ ሳይረካ
ከጫጉላ ወደ ጫካ
የወጣቱ፤ ለጋ ጣቱ፤ ከቃታ ጋር ተጣብቆ
የብር ቀለበት የት አውቆ፤
የጅራፋችን ድምጽ፤ በጥይት ድምጽ ተለውጦ
ሞፈራችን ተፈልጦ
ካረስነው ትልም በላይ፤ የቆፈርነው ምሽግ በልጦ
በሙሉ ልብ ለመሞት ፤ በግማሽ ልብ አኖራለን ፤
ደረት መትተን ጥለን፣ ገድለን፤ ደረት ደቅተን እንቀብራለን፤
ጎረቤቶቻችን ሁሉ፤ ያምባ ጉዋሮ ቤት ሆነው
መኖራችንን ተቀናቅነው፤
ቤት ለእምቦሳ ብንላቸው፤ ወይፈን ሆነው እያደሩ
ወደ ስስ ብልታችን ፣ ቀንዳቸውን እየወደሩ፤
እሳት አንጫጫር ብለው ገልና ፍም ተውሰው
በየለቱ ሲጋብዙን፤ እሳተ ጎመራ ጠንስሰው፤
የመላእክት ጭምብል ለብሰው
እንኩዋን ከሰው
ካውሬ ብሰው፤
5 759
Repost from Seblework Old Books Delivery ™📚
የታሪክ
የልቦለድ
መንፈሳዊ መጽሐፍ ት
እንገዛለን
ይደውሉልን ካሉበት መጥተን እንገዛለን
ስልክ ቁጥር ፦ 0946523397
@sebleold inbox 📚
5 759
እውነት የዓለም፣ ውበት የዘለዓለም ቋንቋ ናቸውና...
በፍም እሳት ማቃመስ፣
(ቅዱስ ውበት፣ እርኩስ እውነት)
ገጽ 154
.
.
.
እናስ መራመድ እንጂ ነጻ ያወጣኝ መመራመር ለምን በጀኝ? የብቻዬ ሀቅ እንደሌለኝ እያወቅሁት በእልፍ አግቦኞች መሃል መተራመሴ፣ ለዓመታት እውነትን ማሳደዴ ግማሽ ጎኑ የደረቀ ዛፍ ወደ መሆን አንደርድሮኝ አልነበረምን? ደግሞስ ለሚተናነቀኝ እርኩስ እውነት፣ ማርከሻውን ቅዱስ ውበት የተቀዳጀሁት ከጉዞዬ አይደለምን? አዎ መራመድ ግን ወደ ውበት፣ ወደ ገራም አውነት መራኝ፡፡ ውበትም እውነት፣ እምነት ሆነልኝ፡፡ ያ ውበት ከውስጤ ያስታወስኩት እንጂ የፈጠርኩት አልነበረም፡፡ እውነት የዓለም፣ ውበት የዘለዓለም ቋንቋ ናቸውና...
እነሆ መራመድ ግን ነጻ አወጣኝ፤ ከውበት አወዳጀኝ፡፡ ሄጄ ሄጄ ሁሉም ነገር ያረመመበት የተራራው ጫፍ ላይ ከቆምኩኝ ጉዞዬ (my odyssey) እዚያ ላይ ይገታል፡፡ በዙሪያ ገባው የተናኘውን ሰፊ ገጸ ምድር በሕልም ውስጥ እንዳለ ሕልም ፈዝዤ እመለከተዋለሁ፡፡ ከተራራው ጀርባ ሲረማመዱ የተመለከትኳቸው ሰዎች በማላውቃቸው ቋንቋዎች ሲነጋገሩ ልሰማቸው እችላለሁ፡፡ መልጎምጎማቸው ለነፍሴ ስክነት ይሆናታል፡፡
5 759
እውነት የዓለም፣ ውበት የዘለዓለም ቋንቋ ናቸውና...
በፍም እሳት ማቃመስ፣
(ቅዱስ ውበት፣ እርኩስ እውነት)
ገጽ 154
.
.
.
እናስ መራመድ እንጂ ነጻ ያወጣኝ መመራመር ለምን በጀኝ? የብቻዬ ሀቅ እንደሌለኝ እያወቅሁት በእልፍ አግቦኞች መሃል መተራመሴ፣ ለዓመታት እውነትን ማሳደዴ ግማሽ ጎኑ የደረቀ ዛፍ ወደ መሆን አንደርድሮኝ አልነበረምን? ደግሞስ ለሚተናነቀኝ እርኩስ እውነት፣ ማርከሻውን ቅዱስ ውበት የተቀዳጀሁት ከጉዞዬ አይደለምን? አዎ መራመድ ግን ወደ ውበት፣ ወደ ገራም አውነት መራኝ፡፡ ውበትም እውነት፣ እምነት ሆነልኝ፡፡ ያ ውበት ከውስጤ ያስታወስኩት እንጂ የፈጠርኩት አልነበረም፡፡ እውነት የዓለም፣ ውበት የዘለዓለም ቋንቋ ናቸውና...
እነሆ መራመድ ግን ነጻ አወጣኝ፤ ከውበት አወዳጀኝ፡፡ ሄጄ ሄጄ ሁሉም ነገር ያረመመበት የተራራው ጫፍ ላይ ከቆምኩኝ ጉዞዬ (my odyssey) እዚያ ላይ ይገታል፡፡ በዙሪያ ገባው የተናኘውን ሰፊ ገጸ ምድር በሕልም ውስጥ እንዳለ ሕልም ፈዝዤ እመለከተዋለሁ፡፡ ከተራራው ጀርባ ሲረማመዱ የተመለከትኳቸው ሰዎች በማላውቃቸው ቋንቋዎች ሲነጋገሩ ልሰማቸው እችላለሁ፡፡ መልጎምጎማቸው ለነፍሴ ስክነት ይሆናታል፡፡
5 759
"We choose not randomly each other. We meet only those who already exists in our subconscious."
― Sigmund Freud
5 759
“In many cases in psychiatry, the patient who comes to us has a story that is not told, and which as a rule no one knows of. To my mind, therapy only really begins after the investigation of that wholly personal story. It is the patient's secret, the rock against which he is shattered. If I know his secret story, I have a key to the treatment. The doctor's task is to find out how to gain that knowledge. In most cases exploration of the conscious material is insufficient. Sometimes an association test can open the way; so can the interpretation of dreams, or long and patient human contact with the individual. In therapy the problem is always the whole person, never the symptom alone. We must ask questions which challenge the whole personality."
— Carl Jung 🖤
Memories Dreams Reflections
5 759
ታሪክ በ1907 ዓ.ም የተፈጠሩ ሁነቶች " አዶ ከብሬ " የተባለ የዛር ዓይነት በሽታ በሽዋ ባላገር ላይ ተናኝቶ ሴቱንም ወንዱንም ያስጨፍረዉ ጀመር ። በሽታዉ ከትግሬ የመጣ ነዉ ስለሚባል በሽተኛዉ የትግረኛ ዓይነት እየተናገረ ይቀባጥራል ። በሽታዉንም ለመሸኘት ድግስ መደገስ ስለሚያስፈልግ ድሕዉ ህዝብ ባለጣጣ ሆነ ።
እንዲሁም "ሞያሌ" የተባለ በእግር ላይ የሚገባ ቁንጫ ዓይነት በሽታ በዚሁ ዘመን ስለ መጣ የሁሉም እግር በወረንጦ ሲዘንጠል ይዉል ጀመር ። ስሙ ሞያሌ መባሉ በሽታዉ የመጣዉ በቦረና ዉስጥ ካለዉ ሞያሌ ከተባለዉ ስፍራ በመሆኑ ነዉ እየተባለ ይነገር ነበር ።
"ጣጣቴ " የተባለ በሽታ ደግሞ በዚሁ ዘመን መጣ ። የትኩሳት በሽታ ነዉ የዣንጥላ መገተሪያ ብረት በእሳት አግሎ የበሽተኛዉን ገላ በተኮሱት ጊዜ ይንጣጣ ነበርና ከዚህ የተነሳ የበሽታዉ ስም ጣጣቴ ተባለ ።
እንዲሁም ደግሞ ዕጣን እየተጨሰ ቡና የመጠጣት ልማድ በሽዋ ባላገር ዘንድ የተጀመረዉ በዚሁ ጊዜ ነዉ ። ከዚያ በፊት ግን ይህ ዓይነት ልማድ የሚታየዉ በነጋዴዎች እና በእስላሞች በተለይም በቃልቾች ዘንድ ነበር ። በበርሃ ስፍራ የሚኖሩ ነፍጠኞችም የዚሁ የቡና ሱስ አለባቸዉ ። እነዚያ ነፍጠኞች ወይም ነጋዴዎች ወደ አገር ቤት በተመለሱ ጊዜ ዕጣን እያጨሱ ቡና ይጠጡ ነበርና ሌላዉ ሰዉ እነርሱን አይቶ ተከተለ ። ይልቁንም የየመንደሩ ሴቶች የቡና ወንፈል ( ተራ ) እያበጁ እና ተራ በተራ እየተጠራሩ ቡና ሲያፈሉና ሲጠጡ መዋል ጀመሩ ። ይህ ልማድ በባላገር ሆነ በከተማ እየተስፋፋ ስለ ሄደ ብዙ ሰዉ የቡና ሱሰኛ ሆነ ። የቤተ ክህነት ሰዎችም በቤተ ክርስቲያን የሚጨሰዉን ዕጣን ለቡና ማጨስ አምልኮ ባዕድ ነዉ እያሉ ተቃዉመዉት ነበር ። የሆነ ሆኖ ዉሎ አድሮ እየተለመደ ሄደ ።
"የሐያኛዉ ክፍለ ዘመን መባቻ "መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ እንደፃፈዉ ✍️
5 759
አምላኬን አግኝቼ እንደት በነገርኩት
ፈጣሪን አግኝቼ እንደት በነገርኩት
የደላኝ መሰለው ተመስገን ስላልኩት!
_
(ጤዛ ፊልም- ስነ ቃል)
ፕሮፌሰር - ኀይሌ ገሪማ
5 759
Repost from N/a
ከልባችን መቃብር የተቀበረው የእውነት መስቀልስ መቼ ይገኝ ይሆን? በዓላት በመጡ ቁጥር በጥያቄ ጎርፍ የምጥለቀለቅ ሰው ነኝ። ወዲህ በአሁናዊ የሕይወት መልካችን እና መሆን በነበረበት መካከል ያለው ገደል ስፋት ወዲያ ሀገርና ማኅበረሰብ የተቸነከረበት የጉስቁልና ችንካር ያላጉኛል። ሰላም የታወጀበት ፣እርቅ የተፈጸመበት ፣ ነጻነት የተገኘበት መስቀልን በ"ደማቅ" ሥነ ስርዓት የምናከብር ባለ መስቀሎች ሰላም እንደ ሰማይ ርቆናል። ጥላቻ እንደ አረም ወሮናል። በሚያስደነግጥ ባርነት ተቀፍድደናል። ይህ ተቃርኖ ታዲያ አያሳስብም? በዓሉ አይከበር ማለቴ አይደለም። የሆነ የእውነት ሐዲድ እንደሳትን፣ ሸርተት ያልነው ነገር እንዳለ ስለሚሰማኝ ነው።
እና ከልባችን ተራራ የጠፋው የእውነትና የክርስትና መስቀልስ መቼ ይገኝ ይሆን?
እንኳን ለቅዱስ መስቀሉ በዓል አደረሳችሁ
5 759
¶ የህይወት ድካም ከረታው ጨፍጋጋ ፊት ላይ በሙዚቃ እና በግጥም የሚጽናና ስሱ ልብ አለ !
ተስፋ በቆረጠች የልጃገረድ እጅ ውስጥ እውድሻለሁ የምትል ብስራት ነጋሪ ፤ ቃል አለች ፡ ጤዛ ከቋጠረች የስጦታ አበባ ጋር በርሷ የልቧ መቅደስ ኃሴት ያደርጋል ፡ የመኖር ልምላሜ ይበክራታል ።
© የአባ ልጅ
5 759
"ምነው ተለየሽኝ" በሚለው ተወዳጅ ዜማው የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ እና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ አረፈ
*
"ምነው ተለየሽኝ..." እያለ በናፍቆትና በትካዜ ቅላጼው የበርካታ ትውልዶችን ልብ በፍቅር የገዛው፣ በለሰለሰ ድምፁ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ማማ ላይ ደምቆ የኖረው አንጋፋው ድምፃዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ በ83 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ድምጻዊ ግርማ በ1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ አራት ኪሎ "ፊት በር" ተብሎ በሚጠራው ታሪካዊ ሰፈር ከአባቱ አቶ ነጋሽ ወልደሥላሴ እና ከእናቱ ወይዘሮ አፀደ ውቤ ነው የተወለደው።
ትምህርቱን በሽመልስ ሀብቴ እና በኮከበ ጽባህ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከታትሏል።
ለቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ የሆነው አርቲስቱ፣ የሕይወት ጉዞው በብርቱ ሥራ ትጋት እና በፈተናዎች የተሞላ ነበር።
በሙዚቃው ዓለም ስሙ ገንኖ ከመውጣቱ አስቀድሞ በኮካ ኮላ ኩባንያ በሽያጭ ባለሙያነት፣ በ1959 ዓ.ም በማስታወቂያ ሚኒስቴር በሥነ ጽሑፍ ምርመራ ክፍል አና በመዝገብ ቤት ሠርቷል።
በመቀጠልም በኢትዮጵያ ሬዲዮ በሹፌርነት አገልግሏል። ከጊዜ በኋላም ከታዋቂዎቹ ጋዜጠኞች ደምሴ ዳምጤ እና ይንበርበሩ ምትኬ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ሬዲዮ የስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅ እና ጋዜጠኛ ሆኖ አገልግሏል።
ተፍጥሮ ባደለው የሙዚቃ ስጦታ በመሳቡም ገና በወጣትነቱ ወደ ኪነ ጥበቡ ዓለም በመቀላቀል በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ በድምፃዊነት ማገልገል ጀምሯል።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ተቀጥሮ በመሥራት ለረጅም ዓመታት ድምፃዊነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በተጨማሪም በራስ ሆቴል እና በግዮን ሆቴል የምሽት ክበቦች እንዲሁም በውጭ ሀገራት ሥራዎቹን በብቃት አቅርቧል።
አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከ60 ዓመታት በላይ ዕድሜን የተሻገሩ እና በሕዝብ ዘንድ አሁንም ድረስ በናፍቆት የሚደመጡ በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎችን አበርክቷል።
ከተወዳጅ ሙዚቃዎቹም መካከልም "ምነው ተለየሽኝ"፣ "ቀለሜዋ"፣ "እንገናኛለን"፣ "የኔ ሃሳብ"፣ "አልበቃኝም ገና" እና "የኔ ውብ ዓይናማ" የሚሉት ዜማዎቹ ይጠቀሳሉ።
ባለትዳር እና የሦስት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት የነበረው የአንጋፋው ከያኒ ሥርዓተ ቀብር ነገ መስከረም 14 ቀን ከረፋዱ 5 ሰዓት ቤተሰቦቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና በርካታ አድናቂዎቹ በተገኙበት መንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
© በሰለሞን ክፍሌ
5 759
ስለ ኢትዮጵያ የድሮ ሁናቴ አሁን ካለችበት ሁኔታ ጋር እያጣጣሙ ኢትዮጵያ ለምን አሁን ያለችበት ሆነች? በሚል እሳቤ ከተፃፉ መፅሐፍት መሀከል ያነበብኩት በ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የተፃፈውን መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ እና አዳፍኔ ፍርሀትና መክሸፍ የሳቸው ሲሆን በቅርብ አመታት ከተፃፉ ያዕቆብ ብርሀኑ በፍም እሳት ማቃመስ ናቸው።
እኚ መፅሐፎች ላይ ኢትዮጵያ ለምን ከሸፈች? ለምን ቁልቁል ተንደረደረችና ሳትለወጥ ቀረች የሚለውን ጥያቄ በማንሳት ያብራራሉ። በያዕቆብ መፅሐፍ ላይ ኢትዮጵያ ሥልጣኔዋን የጎተተው ገዢዎቿ ዘላን መሆናቸው እንደ ትልቅ ክሽፈት ያየዋል። የሀይማኖትንም ተፅዕኖ ይዳስሰዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን በበኩላቸው በሁለቱ መፅሐፎቻቸው ውስጥ ብዙ ሀሳቦችን ያነሳሉ። ለምን ስልጣኔያችን ከቦታ ቦታ የማይዛመት ሆነ? እነ አክሱም እነ ላሊበላ ሌሎችን ጥበብ ያረፈባቸውን ግንባታ ያነፅን ህዝቦች ከ አክሱም ከላሊበላ ሀውልት አጠገብ ያን የመሰለ ጥበብ ትተን የሳር ጎጆ ውስጥ መኖርን መረጥን? የራሳችን ፊደል ኖሮን ስለምን በስነፅሑፍ መራቀቅ አቃተን? የነ ኮንሶ የእርከን ስራ የነ ሐረር ግንብ አንዳንድ ቦታ ያለ የ እርሻ ጥበብ ስለምን ህዝቡ ሳያስፋፋው እዛችው ብቻ ቀረ? ለት/ት ወደ ውጭ የተላኩት ለምን ከሸፉ? የመንግስት ለውጦቻችንስ? የሚለውን እያነሱ ያጠይቃሉ።
በነዚህ መፅሐፎች ብዙ ነገሮችን ማግኘት ይቻላል። በ ፕሮፌሰር መስፍን መፅሐፍ ውስጥ ይበልጥ የሚጠየቁት ከሚደርሱብን ብዙ መከራና ስቃይ እንዴት መማር ቻልን? ለውጥን እንዴት አንሻም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።
አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ መንግስት ሲከበብና ራሱን ማጥፋቱን በራሱ ይጠይቃሉ። እንግሊዝ በዘመናዊ ጦር እንዲያ ስታርበደብደን እና የፈለገችውን አድርጋ ከሀገራችን ስትለቅ እኛ ግን ሴባስቶፖል እንኳ ሳይቆጨን የ አፄ ቴዎድሮስ ራዕይን ችላ በማለት እራሱን ማጥፋቱን ስናራግብ አፄ ዩሐንስን መሐዲስት እንዲያ ሲያደርጉት ጣልያን በ አድዋ ሲያፋጥጠን እኛ ግን በ አክሱም ጊዜ በነበረ አልተላቀቅንም ነበር። ጣሊያን ከ 40 አመታት በኋላ እራሱን አዘምኖ በቴክኖሎጂ ረቆ በአየር በምድር በማይጨው ሲመለስ እኛ ግን ጋሻና ጎራዴ እንደያዝን በአይሮፕላን ከሚወርድ ቦምብና ጋዝ አለቅን። የሚገርመው ይሄ ሁሉ እንኳ ሲሆንና ጣሊያን አምስት አመት እንዲያ ሲገዛን ሰንብቶ በውጪ እርዳታ ሲወጣ እኛ ግን ያንን ሁሉ መበለጥና ወደ ኋላ መቅረት ሳያንገበግበን እዛው ኑሮዋችን ተመለስን። የሚገርመው ስለ አድዋ ጣሊያንን ማሸነፋችንን እንጂ አሁን ላይ ጣሊያን ቢመጣ እናሸንፋለን ወይ የሚል ቁጭት የለንም። ሽንፈቶቻችን ውድቀቶቻችን ቆጭተውን አያውቅም ኋላ መቅረታችን አንገብግቦን እራሳችንን ለመቀየር የተነሳንበት ጊዜ የለም። ይሄ እንደ ሀገርና ህዝብ ምን አይነት ስነ ልቦና እንዳለን ግራ ያጋባል።
ሮም ለምን ወደቀች? የሚል ብዙ ጥናቶች ቢኖሩም። ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለምን ከዛ ገናናነት አሽቆለቆለች የሚል ጥናቶች የሉም። እንደ ህዝብ እንደ ሀገር ያለንን ስነ ልቦና የሚያጠናና የሚተነትን የለም። ታሪካችን ምንድነው? እንዴት እንለወጥ? እንዴት እንሻሻል? የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች መነሳታቸውና መወያየታችን አስፈላጊ ቢሆንም እኛ ግን ዛሬም አለም የትናይት ጥሎን መሄዱን አይተን አንደነግጥም ዝምታችን ያስፈራል።
ቡርሀን አዲስ በአንድ ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያውያን ትዝታ ላይ ነን ይላል። እሳቤው እውነትነት አለው። ኢትዮጲያውነት ትላንትና ላይ የቆመ የትላንቱን ብቻ ድል ተራኪ ሆነናል። ሁሉ ነገራችን ትላንት ስለነበረን ገናናነት ትልቅነት እንጂ ስለ ወደ ፊታችን ያለ የመለወጥ የመነሳሳትና አሁን ላይ እራሳችንን ስለመቀየር በጋራ አንድ የሚያደርጉን እሳቤዎች ስንመክር አይታይም። ይሄን ሳስተውል እውነትም ኢትዮጵያ መች ይሆን ከክሽፈቷ የምትነሳው? የሚለው የሁልጊዜ ጥያቄ ነው።
@ourrthought
