ch
Feedback
Ethio Space (ኢትዮ ጠፈር)

Ethio Space (ኢትዮ ጠፈር)

关闭频道

ሰለ ሌሎች ዓለማላቶች እና አስትሮኖሚ ሳይንስ ስታስብ በሰዎች መካከል ያሉት የጎሳ ,የብሔር ,የሐይማኖት ልዩነቶች እንዲውም የአገር ልዩነቶች ለአንት ተራ ነገሮች ይሆናሉ ምክንያቱም እራስክን የምታነፃፅረው በሌሎች አለማት ላይ ይኖራሉ ተብለው ከሚታሰቡ ልዩ ፍጥሮች ጋር ይሆናል ሰለዚህ አንት ሰው ከሆነክ በቂ ነው ምክንያቱም ሰው መሆንክ በራሱ በቂ ማንነት.. @unverseand 👈ለcross

显示更多
1 981
订阅者
无数据24 小时
-127 天
-4330 天
帖子存档
አፅናፍ አለም እንዴት ተፈጠር ? | የሳይንቲስቶች ወዝግብ እና እንቆቅልሽ የሆነው ዩኒቨረስ👇👇👇👇👇 https://youtu.be/TUFmcQa3oMI?si=qk-PeVaNgjpoEaCB

የውሃው አለም (the water world) "The water world" ወይም ሙሉ በሙሉ በውሃ የተሸፈነው ፕላኔት ወይም በሳይንትፊክ ስሙ  Gj 1214B ይባላል። የኛ ፕላኔት(ፈለከ) ወይም የኛ አለም 75% ፕርሰነተ በውሃ  የተሸፈነ ሲሆን 25% ደግሞ በውሃ ያልተሸፈነ ምድር ነው ይሄም ማለት ሰባቱ አህጉሮች አፍሪካን ጨምሮ የመሬትን 25% ብቻ ነው የሚሸፍኑት እንደማለት ሲሆን ቀሪው 75% በዊቂያኖሶች እና በተለያዩ የውሃ አካላቶች የተሸፈነ ነው ይሄ በእራሱ የኛን መሬት አስደናቂ እና በውሃ ያሸበረቀች አለም ሊያስብላት ይችላል ነገረ ግን ይሄ Gj1214B የተሰኘው ፕላኔት ደግሞ ይበልጡን ያስደምመናል ከስሙ እንደምነረዳው ይሄ የውሃው አለም 100% በውሃ የተሸፈነ ሲሆን እዚህ አለም ላይ መኖር የሚችሉት መዋኘት የሚችሉ ፍጡሮች ብቻ ናቸው ተብሎ ይታሰባል የውሃው አለም ላይ የሚገኘውን ውሃ ብንመዝነው 10% የሚሆነውን የፕላኔቱን ክብደት መሸፈን ይችላል ነገረ ግን መሬት ላይ የሚገኘውን ውሃ ብንመዝነው 0.05% ብቻ የመሬትን ክብደት ቢሸፍን ነው   የውሃው አለም ከኛ ፕላኔት 40 የብርሃን አመታትን ይርቃል ይሄም ማለት በብርሃን ፍጥነት ብንጓዝ እንኳን  ወደዚህ አለም ለመድርስ 40 አመት ይፈጅብናል እንደማለት ነው ብርሃን 40 የሚፈጅበት በሰከንድ 300,000km እየተጓዘ ነው በአሁኑ ዘመን እጅግ ፈጣን በሚባለው  "NASA solar probe" እስፔስ ክራፍት ብንጓዝ ደግሞ ወደዚህ አለም ለመድረስ ያለማቋረጠ 700,000 አመታትን መጓዝ አለብን አስተውሉ ይሄ እስፔስ ክራፍት በሰሀት እስከ 394,000km ይጓዛል ይሄ በራሱ አስደናቂ ፍጥነት ነው ይሄ አለም የተገኘው እንደ ኢትዮፒያኑ አቆጣጠር በ2001 ሲሆን በክብደት ከመሬት 6 እጥፍ የሚተልቅ ፕላኔት ነው ኔፕቱን ከተሰኘቹ ፕላኔት ግን እንደሚያንስ ይገመታል የውሃው አለም የሚዞረው ኮከብ ደግሞ "Gliese 1214" ተብሎ ይጠራል ይሄ ኮከብ "red dwarf " ተብለው ከሚጠሩ ኮከቦች ስር ይመደባል ይሄ ኮከብ ከፀሐይ አንፃር ትንሽዬ ሲሆን የፀሐይን 16 በ 100 ክብደት ብቻ ነው መሸፈን የሚችለው ሙቀቱ ከፍተኛ ቢሆንም ልዩ ፍጡሮች ሊኖሩበት እንደሚችሉ ይገመታል የውሃው አለም ላይ የሚኖሩ ፍጡሮች ደግሞ መሬት ላይ ከሚኖሩ ፍጡሮች ፍፅሙ የተለዩ ሊሆኑ ይችላሉ  ምክንያቱም የውሃው አለም ላይ ከፍተኛ ሙቀት እና ከፍተኛ የውሃ መጠን አለ ሌላኛው ነገረ ደግሞ ከፍተኛ አትሞስፐሪክ ፕሬዠር መኖሩ ነው ሰለዚህ እዚህ አለም ላይ የሚኖሩ ፍጡሮች ሙቀቱን እና አትሞስፔሪክ ፕሬዠሩን መቋቋም የሚችሉ መሆን አለባቸው በተመሳሳይ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ደግሞ ጥሩ ዋናተኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል  የሰው ልጆች ግን በዚህ አለም ላይ መኖር አይችሉም ተብሎ ይታሰባል ምክንያቱም የሰው ልጆችም ሆን የኛ አለም ላይ የሚኖሩ ፉጡሮች planet earth ላይ ብቻ መኖር እንዲችሉ ተደርገው ነው የተፈጠሩት ሰለዚህ የውሃው አለም በሙቀት በከባቢ አየር እንዲውም በሌሎች ነገሮች የኛን አለም እስካልመሰለ ድረስ መኖር አይቻልም እዚህ አለም ላይ ወይም የተለይ ቴክኖሎጂን መጠቀም አለብን የሆነው ሁን የውሃው አለም 120 ድግሪ እስከ 280 ድግሪ ይሞቃል ተብሎ ይገመታል በተመሳሳይ ጠጣር ወይም ከፍ ያለ  ከባቢ አየረ አለው ይሄ ሙሉ በሙሉ በውሃ የተሸፈነው ፕላኔቱ የዊቂያኖሱ ጥልቀተ እስከ 15,000 km እንደሚሆን ይገመታል ይሄም ማለት ከአዲስ አበባ እስከ አስመራ ያለውን እርቀት 12 እጥፍ መሆኑ ይችላል  የኛ አለም ላይ የሚገኙት ዊቃኖሶች ደግሞ እስከ 11km ጥልቀት ቢኖራቸው ነው ይሄም ከውሃው አለም ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ሌላው ይሄንን ፕላኔት ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ  ደግሞ ፕላኔቱ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ኑሮት ፈሳሽ ውሃን መያዙ ነው እደሚታወቀዎ ወሃ ከ 100 ዲግሪ ሴሊሴሽ በላይ በፈሳሽ መልክ አይገኝም ወይም መትነነ ነበረበት ግን አልሆንም ምክንያቱም ውሃ በኛምድር ላይ ብቻ  ነው 100° ሴልሴሽ የሚፈላው ወይም ውሃ ለመፍላቲ ሙቀት ብቻ በቂ አደለም ከባቢ አየርም ይወስነዋል ከፍ ያለ "atmospheric pressure " የሚኖር ከሆነ ውሃ የሚፈላበት የሙቀት መጥን ከፍ ያለ ይሆና  በተመሳሳይ ዝቅተኛ "atmospheric pressure " የሚኖር ከሆነ ዝቅ ባለ ሙቀት ነው ውሃ የሚፈላው ለምሳሌ የአለማችን ትልቁ ተራራ የሆነው ኤቨረስት ላይ ውሃ የሚፈለው 70°ማ ሴልሴሽ አከባቢ ነው ምክንያቱም ዝቅተኛ የሆነ ከባቢ አየር ስላለው ነው ባጠቃላይ ውሃ 100° የሚፈላው 1 ATM ላይ ወይም 101000 Pascal  pressure ላይ ነው ቅድም  እንደገለፅነው ፕላኔቱ ከፍተኛ የሆነ ከባቢ አየር አለው ሰለዚህ ውሃ በዚህ ምድር ላይ በቀላሉ አይፈላም ማለት ነው ሰለ ውሃው አለም ቪድዮ ለማየት ይሄንን ሊንክ ተጠቀሙ👇👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1

Ufo(Aliens )እንዳሉ የሚያምኑ ሕዝቦች በብዛታ ያሉባቸው 3 አገራት England 52% Germen 56% America 54% subscribe🙏🙏🙏👇👇 https://youtube.com/chan
Ufo(Aliens )እንዳሉ የሚያምኑ ሕዝቦች በብዛታ ያሉባቸው 3 አገራት England 52% Germen 56% America 54% subscribe🙏🙏🙏👇👇 https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን ኢድ ሙባረክ ለማለት እንወዳለን ። መልካም በዓል ❤️
ለመላው  የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን ኢድ ሙባረክ ለማለት እንወዳለን ። መልካም በዓል ❤️

አልበርት አንስታይን ነገሮችን በቀላሉ የሚረሳ ዝንጉ ሰው ነበር " ጂንዬስ ነህ ማለት ጥቂት ፎርሙላ መሸምደድና ፈተና መድፈንህ አደለም! ይህ ያስታወስከውን ማራገፍ ነው የሚባለው። " ሳይንቲስቶች ባደረጉት ጥናት ተፅኖ መፍጠረ የሚችሉ እንደ አልበርት አንስታይን ያሉ ሰዎች ዝንጉ መሆናቸውን ማወቅ ችለዋለ ይሁን እንጂ  እንዚህ ሰዎች የሚወስኖቸው ውሳኔውች አስገራሚ ሲሆን የተሻለ የማሰብ ችሎታ እንዳላቸውም ሳይንቲስቶች ማረጋገጥ ችለዋል አልበርት አንስታይንም የማትሪክ ፈተናውን የወደቀው መሸምደድ ስለማይችል ነበር። በተለይም በማህበራዊ ትምህርት ዘርፎች ለምሳሌ በታሪክ ዝቅተኛ ውጤት ነበር ያመጣው ያለፉ ዘመናት ና የመጪውን ዘመናት ጨምሮ ታላቅ የሆነው የሂሳብ ሊቅ በተመሳሳይ ጥቂት ገንዘቦችን እንኳን መቁጠር ይሳነው ነበር። እርግጠኛ ለመሆንም በተደጋጋሚ ይቆጥር እንደነበር የታሪክ አጥኚዎቹ ይናገራሉ። በአንድ ወቅት አልበርት አንስታይን በአውቶቢስ ውስጥ እየተጓዘ ሳለ ለሂሳብ ተቀባዩ ገንዘብ ይሰጠዋል ሂሳብ ተቀባዩም መልሱን ይመልስለታል። አንስታይን አንድ ጊዜ ፣ ሁለት ጊዜ ፣ ሶስት ጊዜ ይቆጥረዋል። የብሩ መጠን የተለያየ ይሆንበታል። ስለሆነም ለአራተኛ ጊዜ መቁጠሩን ይጀምራል። ይህንን ያስተዋለው ገንዘብ ተቀባይ "ምንድነው ችግርህ? ቁጥሮችን አታውቅም?" ይለዋል አንስታይንም " አዎ ቁጥር ላይ ትንሽ ደካማ ነኝ"አለው ይህ ታላቁን ስሌት የሰራው ሰወጰገንዘብ መቁጠር ይቸገራል ቢባል ማን ያምናል። ሌላው አሰገራሚው ነገረ አልበርት አንስታይን መታጠቢያው ክፍል ውስጥ ገብቶ ለሰዓታት ያህል  ከመታጠቢያው ክፍል አይወጣም ነበር። ምክንያቱም ከመታጠቢያ ቤቱ ውስጥ መውጣት እንዳለበት ሰለሚረሳ ነው ከጓደኞቹ አንዱ (ram manoar .dr. ) እርሱን ለማግኘት ሄዶ ለ 6 ሰዓታት ነበር የጠበቀው። ምክንያቱም መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ሰለነበር እናም ሚስቱ ይሄን ሰው በተደጋጋሚ ይቅርታ ትጠይቅ ነበር በትግስት እንዲጠብቀው። ይህን ያህል ሰዓት መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መቆየቱ ያላናደደው ጓደኛው "ግን መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ይህን ያህል ሰዓት ምን ይሰራል?" ሲል በአግራሞት ይጠይቃታል ሚስቱም "ማንም ይህንን አያቅም ግን ብትረብሸው በጣም ይናደዳል ፤ ነገሮችን መወርወሩ ይቀጥላል! ግን ሁሌም ከመታጠቢያ ክፍል ውስጥ መውጣት እንዳለበት ይረሳል። ልክ ወደ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ሲገባ መውጣት ይረሳል። አሁን እስከሚወጣ ድረስ መጠበቅ ይኖርብናል። ሲርበው ወይንም ሲጠማው ከዚያ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መውጣት እንዳለበት ያስታውሳል ስትል መልሳ ነበር። የመፅሐፍት ቱሩፍት ከሚል የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ እና ተሻሽሎ የቀረበ።

በእንግልዘኛ የምንለቃቸውን የዩቲዩብ ቪድዮ ለማየት ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳይረሳ 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/CO8cCK30CiI

በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ የተገኙ እጅግ ድንቅ ፕላኔቶች በቀደም ተከተል👇👇 1. የፕላኔት ስም  "WASP-12b"  በራሱ ኮከብ ወይም ፀሐይ እየቀለጠ ነው በሚልዬንን ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ከዩንቨርስ ይጠፍል።   2. የፕላኔት ስም " pso j3185-22"  ምንም አይነት ኮከብ ሆን ሶላር ሲስተም የለውም ወይም ጠፈር ውስጥ ተንሳፎ የሚገኝ ፕላኔት ነው 3. የፕላኔት ስም "55 Cancri"  በዳይመንድ የተሰራ ፕላኔት ነው 4. የፕላኔት ስም  "TrES-2b"  ብርሃን የሚባል ነገረ አያውቅም ወይም የጨለማው ዓለም ልንለው እንችላለን 5. የፕላኔት ስም  "KELT-9b"  አጅግ ሞቃታማ ሲሆን የእሳት ዝናብ ይዘንብበታል በቅፅል ስሙ ደግሞ የገሀነሙ አለም ይባላል 6. የፕላኔቱ ስም  "HR 5183b"   አጅግ የተለጠጠ የእሽክርክሪት ኦርቢት አለው ፕላኔቱ በኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ የሚኖር ቢሆን ሰባቱ ፕላኔቶች የሚሽከረከሩበትን ኦርቢት ሙሉ ይሸከረከራል። 7. የፕላኔት ስም "K2-18b" የውሃ ዝናብ የሚዘንብበት ዓለም ነው እዚህ አለም ላይ ሕይወት ያለው ነገረ የመገኘት እድሉ ሰፊ ነው 8. የፕላኔት ስም " Gj1214b" ሙሉ ለሙሉ በውሃ የተሸፈን አለም ነው እዚህ አለም ላይ ለመኖር የግድ ዋናተኛ መሆነ አለብን በስፍት በዩቲውብ ይመልከቱ። https://youtu.be/pwzFlG4E4GU

ሰለ ቮያጀር እስፔስ ክራፍት ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋቹ ይሄንን ቪዲዮ ለማየት ሞክሩ የተብራራ ሐሳብ ነው subscribe እንዳይረሳ👇👇👇👇 https://youtu.be/tBewzZ6zJuw?si=3_BZMRf0uRjj4ZXM

ቮያጀር የተሰኘው እስፔሴ ክራፍት ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ የሚደረገው ጉዞ ቀጥሎ ዛሬ እንሆ 47 ዓመቱን አስቆጥሯል። ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 46 ዓመት በ1977 የናሳ ተቋም "ቮያጀር አንድ" የተሰኘውን
ቮያጀር የተሰኘው እስፔሴ ክራፍት ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ የሚደረገው ጉዞ ቀጥሎ ዛሬ እንሆ 47 ዓመቱን አስቆጥሯል። ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 46 ዓመት በ1977 የናሳ ተቋም "ቮያጀር አንድ" የተሰኘውን እስፔስ ክራፍት ሰለ ሰው ልጆች ታሪክ ይዞ ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ እንዲወነጨፍ አድርጎት ነበር እስፔስ ክራፍቱ አሁንም ድርሰ ጉዞ ላይ ሲሆን 46 ዓመታትን በፈጀው ጉዞ ከ25 ቢልዬን በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጧል በ2037 ከሰው ልጆች ጋር ያላለውን ግኑኝነት ያቋርጣል ይሄም የሚሆነው ከሰው ልጆች በእጅጉን በመራቁ እና ሳይንቲስቶች ከርቀቱ አንፃር መረጃዎችን መለዋወጥ ሰለሚቸገሩ ነው። እስፔስ ክራፍቱ አላማው ሰለ ሰው ልጆች መረጃዎችን ይዞ ለሌሎች የተለዩ ፍጡሮች ማድረስ ነው ወይም የዚህ ዩንቨረስ ጥግ ላይ ድረስ ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል እስፔስ ክራፍቱ ከ 3000 ዓመት በዋላ ሙሉ ለሙሉ ከኛ ሶላር ሲስተም በመውጣት ወደ ሌላ ሶላር ሲስተም ወይም አዲስ አይነት ፀሐይ ጋር እና ፕላኔት ጋር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ከብዙ ሚልዬን ዓመታት በዋላ ደግሞ ከኛ ጋላክሲ በመውጣት ጉዞዎን ይቀጥላል በዚህን ጊዜ አደለም የሰው ልጅ መሬት በራሷ ጠፍታ ይሆናል። አለማችን ድምጥማጧ ቢጠፍ ፀሐይ ብትጠፍ የሰው ልጅ በዚህ አለም ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አይነት መረጃ ባይኖር እንኳን ቮያጀር የተሰኘው እስፔስ ክራፍት የሰው ልጆች አሻራቸውን ያሳረፉበት የመጨረሻው ነገረ ሁኖ በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ ይቀራል። አሁንም ጉዞ ላይ ነው ከሽህ ዓመታት በዋላም ጉዞ ላይ ነው ከሚልዬን ዓመታት በዋላም ጉዛ ላይ ነው ከቢልዬን ዓመታት በዋላም እስፔስ ክራፍቱ ጉዞ ላይ ነው ምክንያቱም እየኖረክ ያለከው መጨረሻው የት እንደሆን የማይታወቅ ዩንቨረስ ወይም ጠጉ የት እንደሆነ የማይታወቅ ጥልቅ ዩንቨረስ ውስጥ ሰለሆነ ነው። 🚀   @Ethio_tefer0

ይሄንን ያውቃሉ ? ቲቸር ዳኒ ምንም አይነት የፊዚክስ ዲግሪ ሳይኖራቸው ፊዚክስ ትምህርትን እጅግ ግልፅ በሆነ መንግድ ማስተማር ቻሉ መምሕር ናቸው። አለምን የቀየሩ ሳይንቲስቶችም ድግሪ ያላቸው ሳይሆኑ
ይሄንን ያውቃሉ ? ቲቸር ዳኒ ምንም አይነት የፊዚክስ ዲግሪ ሳይኖራቸው ፊዚክስ ትምህርትን እጅግ ግልፅ በሆነ መንግድ ማስተማር ቻሉ መምሕር ናቸው። አለምን የቀየሩ ሳይንቲስቶችም ድግሪ ያላቸው ሳይሆኑ እራሳቸውን በራሳቸው ያስተማሩ ነበሩ አለም ለዚህ ስልጣኔ እና ቴክኖሎጂ የደረሰቸው በእንዲ ባሉ ሰዎች ነው ልክ እንዲ ባለ መመህር ፊዚክስ ተምራቹ ከሆነ ዕድለኛ ናቹ ከትምህርት ቤት ባሻገር ተፈጥሮ እንዴት እንደምትሰራ የምትረዱት ትንሽ ቁምነገረ ይኖራችዋል ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇 @ethio_tefer0 @ethio_tefer0 🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽 https://t.me/ethio_tefer

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከዕቅድ በላይ ሕዋ ላይ ለቆዩት ጠፈርተኞች "ከኪሴም ቢሆን እከፍላቸዋለሁ" አሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጠፈር ተመራማሪዎቹ ሱኒታ ዊልያምስ እና ባሪ ዊልሞር ከዕቅድ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከዕቅድ በላይ ሕዋ ላይ ለቆዩት ጠፈርተኞች "ከኪሴም ቢሆን እከፍላቸዋለሁ" አሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጠፈር ተመራማሪዎቹ ሱኒታ ዊልያምስ እና ባሪ ዊልሞር ከዕቅድ በላይ ሕዋ ላይ ለቆዩበት ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያውን በግላቸው ሊከፍሏቸው እንደሚችሉ ተናገሩ። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ሁለቱ ተመራማሪዎች ከዕቅድ ውጪ በጠፈር ላይ ለቆዩባቸው ተጨማሪ 286 ቀናት በቀን 5 ዶላር፣ በድምሩም 1 ሺህ 430 ዶላር ብቻ እንደሚከፈላቸው በተገለጸላቸው ጊዜ ነው። "እስካሁን ጉዳዩን ያነሳልኝ ማንም የለም፤ ማድረግ ካለብኝ፣ ከራሴ ኪስም ቢሆን እከፍላቸዋልሁ፤ ከደረሰባቸው እንግልት አንፃር ይህ ብዙ አይደለም" ብለዋል ትራምፕ። ለ8 ቀናት ቆይታ ብቻ ወደ ሕዋ ተልከው የነበሩት ሁለቱ የጠፈር ተመራማሪዎች በቴክኒክ ችግር ሳቢያ ከ286 ተጨማሪ ቀናት ቆይታ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ምድር መመለሳቸው ይታወሳል። የናሳ ቃል አቀባይ ጂሚ ሩሴል፥ በተቋሙ የአሰራር ደንብ መሰረት ከ5 ዶላሩ በቀር ለጠፈርተኞቹ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ክፍያ እንደማይከፈላቸው አሳውቀዋል። ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇 @ethio_tefer0 @ethio_tefer0 🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽 https://t.me/ethio_tefer

ዝንብለን ወደታች ብንቆፍር የት እንደርሳለን እሰከ የትስ መቆፈር ትችሏል ? ሁላቹም ልታዩት የሚገባ ቪድዮ👇👇👇👇 https://youtu.be/l9D3yiv-SlU?si=CO5DrVOZfX04EQJ1

ከሁሉም ፕላኔቶች የቱ ፕላኔት ያስገርምካል ? የቻትጂፒት መልስ "ከሁሉም ፕላኔቶች ውስጥ ምናልባትም በጣም የሚያስገርመኝ ፕላኔት ሳተርን (Saturn) ነው። ምክንያቱም የእሱ የውጭ ቀለበቶች (ring
ከሁሉም ፕላኔቶች የቱ ፕላኔት ያስገርምካል ? የቻትጂፒት መልስ "ከሁሉም ፕላኔቶች ውስጥ ምናልባትም በጣም የሚያስገርመኝ ፕላኔት ሳተርን (Saturn) ነው። ምክንያቱም የእሱ የውጭ ቀለበቶች (rings) እጅግ በጣም የሚያምሩ እና የሚያስደንቁ ናቸው። እነዚህ ቀለበቶች በዋነኝነት ከበረዶ፣ ከድንጋይ እና ከአቧራ የተሰሩ ናቸው፣ እና በፕላኔቷ ዙሪያ በተወሰነ ርቀት ይገኛሉ። ይህ ልዩ መልክ ሳተርን በፀሐይ ስርአት ውስጥ በጣም አስደናቂ እና ልህ ያለ ፕላኔት ያደርጋታል። ከዚህ በተጨማሪ፣ የሳተርን ሎጂካል አወቃቀር (hexagonal storm) በስሜን ምዕራብ ወሰን ላይ ያለው አስደናቂ ዩፒተር ያስገርማል። ይህ ቅርጽ በፕላኔቷ ላይ ለረጅም ጊዜ የቆየ ነው እናም ሳይንሳዊ ጥናት የሚያስደስት ነው። እርስዎስ የቱን ፕላኔት ያስደስትዎታል? 😊 " ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇 @ethio_tefer0 @ethio_tefer0 🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽 https://t.me/ethio_tefer