ch
Feedback
Bashewam Primary & Junior School 1-8

Bashewam Primary & Junior School 1-8

前往频道在 Telegram

Bashewam School Grade 1-8

显示更多
2 759
订阅者
+124 小时
+117
+5830
帖子存档
መፅሐፍ ያልደረሳችሁ ውድ ወላጆች ከ1ኛ-6ኛ ክፍል መፅሐፍ ስለመጣ ዛሬ ሰኞ ጀምሮ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።

ባሸዋም ትምህርት ቤት የ2015 ዓም የ 12ኛ ክፍል ተፈታኞችን እያስመረቀ ይገኛል ፡ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ። Congratulations! Congratulations on graduating and here's to your next adventure! You're a class act! Best of luck on your new beginnings! You did it, Graduate!

አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት የተማሪዎች ምዘና እና የክፍል ዝውውር መመሪያ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 50% እና በላይ ያገኘ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ይዛዋወራል፡፡ ከ1ኛ - 3ኛ ክፍል ላሉ ተከታታይ ምዘና ከ70% ወስደው የማጠቃለያ ምዘና (ፈተና) ከ30 % እንዲወስዱ ያዛል። ያላለፉ ተማሪዎች በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ድጋፍ አግኝተው የሚዘጋጀውን ፈተና ተፈትነው እንዲገቡ ይደረጋል። ከ4ኛ - 5ኛ ላሉ ደግሞ ተከታታይ ምዘና ከ60% ወስደው የማጠቃለያ ምዘና (ፈተና) ከ40 % እንዲወስዱ ያስቀምጣል። በእነዚህ ክፍሎች ተማሪዎች ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማግኘት አለባቸው። ከ7ኛ ወደ 8ኛ እንዲሁም ከ8ኛ ወደ 9ኛ ለሚሸጋገሩ ደግሞ 40% ተከታታይ ምዘና 60% ደግሞ የማጠቃለያ ምዘና እንደሚወስዱ ያስቀምጣል። ለማለፍም 50 ከመቶ በላይ ማስመዝገብ አለባቸው። ከ9-11ኛ ክፍል ሂሳብ (Maths) እና እንግሊዘኛ (English) ትምህርት ከ50% በታች ያመጣ ተማሪ እንዲሁም 1-7ኛ ክፍል 6ኛን ሳይጨምር Maths እና የማስተማሪያ ቋንቋውን ከ50% በታች ካመጣ ወደቀጣይ ክፍል መዛወር የማይችል እንደሆነ ተጠቅሷል። በመመሪያው አንኳር የትምህርት ዓይነት ተብለው የተለዩ የትምህርት አይነቶች ሲቀመጡ ለአንደኛ እና ለመካከለኛ ደረጃ የትምህርት እርከኖች ትምህርቱ የሚሰጥበት ቋንቋ እና የሒሳብ ትምህርት ዓይነቶች እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና የሒሳብ ትምህርት  አንኳር ዓይነቶች ሆነው ተለይተዋል። በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍሎች ላይ በሚሰጡ ፈተናዎች የማለፊያ ነጥብ ካላገኘ ለአንድ ጊዜ በትምህርት ቤቱ በመደበኛነት ትምህርት እንዲከታተል ይደረጋል። ነገር ግን ከ9ኛ_11ኛ ክፍል ተማሪ በአንድ ክፍል ከ2 ጊዜ በላይ ከደገመ ወይም በተከታታይ ክፍሎች ከደገመ ከትምህርት ዓለም ይሰናበታል። በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 50% እና በላይ ያገኘ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ይዛዋወራል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ከ1-5 እና 6ኛ የክፍል ክፍል ዝውውር የራሱ የዝውውር አፈፃፀም እንደሚኖረው ሲጠቀስ በተመሳሳይ ፥ የመሀከለኛ ደረጃ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል የተማሪዎች ምዘና እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዘና እና የክፍል ክፍል ዝውውር አተገባበር የየራሳቸው ዝርዝር መመሪያ ወጥቶላቸዋል። አስራ አራት አመት የሚወስደውን አጠቃላይ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች በአንድ የሥራና የተግባር ትምህርት መስክ ጥናት ማጠናቀቃቸውንና በዚያም መስክ መመረቃቸውን ለማረጋገጥ የሚካሄድ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ይኖራል። መመሪያው ተግባራዊ የሚደረገው ከቅድመ አንደኛ ደረጃ አስከ 12ኛ ክፍል በመደበኛ እንዲሁም በማታውና በርቀት መርሃ ግብሮች ትምህርት በሚሰጡ ተቋማት ሲሆን ከዓለም አቀፍና ከውጭ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግስትና በሌሎች በሁሉም አይነት ትምህርት ቤቶች/ተቋማት/ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ለተማሪ ወላጆች፡ ፡ የአሸዋ ሜዳ ፡ ቀርሳ ፡ ፍሊዶሮ የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት የትራንስፖርት ሰርቪስ ተጠቃሚዎች ፡ የሰርቪስ ክፍያ 600 ብር ሲሆን መጠቀም የምትፈልጉ የተማሪ ወላጆች ቅድሚያ የትምህርት ቤቱ ፋይናንስ በመምጣት መመዝገብ እና በመክፈል አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

📔🔟የንባብ ጥቅሞች 1️⃣መጽሐፍት ማንበብ የበለጠ ጠቢብ ያደርጋል 2️⃣አንባቢዎች ከፍተኛ የውስጥ ሰላም አላቸው 3️⃣መጽሐፍት ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳሉ 4️⃣ መጻሕፍትን ማንበብ የንባብ ቅልጥፍናን ይገነባል 5️⃣ማንበብ እውቀትዎን ያሳድጋል እርስዎ የተሻለ የውይይት ባለሙያ ያደርጎታል 6️⃣ማንበብ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባርን ይጠብቃል 7️⃣ማንበብ የአልዛይመር በሽታን ይከላከላል 8️⃣ማንበብ የበለጠ ሳቢ ያደርግልዎታል 9️⃣ማንበብ ውስጣዊ ሃይሎን ያነቃቃል 🔟 ትኩረትዎን እንዲያሻሽሉ ይረዳል መልካም ንባብ !