Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለተል ቀድር ዙሪያ
~
ለይለቱል ቀድር ማለት ትልቅ ደረጃ ያላት ሌሊት ማለት ነው። ከፊል ዓሊሞች ዘንድ ደግሞ ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ሌሊት ማለት ነው።
1. የለይለተል ቀድር ደረጃዎች፦
* ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ነች። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተል ቀድር አወረድነው”ብሏል። [አልቀድር፡ 1]
* በሷ ውስጥ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ሌሊቶች ምንዳው የበለጠ ነው። አላህ “የመወሰኛዋ ሌሊት ከሺህ ወር በላጭ ናት” ይላል። [አልቀድር፡ 3]
* በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ። ጌታችን “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ” ብሏል። [አልቀድር፡ 4]
* ሌሊቷ ዒባዳ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት። ጌታችን “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት” ብሏል። [አልቀድር፡ 5]
* የተባረከች ሌሊት ናት። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው” ብሏል። [ዱኻን፡ 3]
* በዚች ሌሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል። “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል” ብሏል አላህ። [ዱኻን፡ 4]
* በዚያች ሌሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው። [አልባኒይ ሐሰን ብለውታል]
* ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ሌሊት ነች። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተል ቀድርን አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ሌሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር። በ(ረመዳን) አስር ሌሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!)” [በዳኢዑል ፈዋኢድ፡ 1/55]
2. ለይለቱል ቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
የምትገኘው በረመዷን ብቻ ነው። ከረመዷንም በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ። ነብዩ ﷺ “ይቺን ሌሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ አለኝ” ማለታቸው ይህን ያስረግጣል።
ይቺ ታላቅ ሌሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል። ነብዩ ﷺ በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ሌሊት አለች። የሷን ኸይር የተነፈገ በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2247]
3. መቼ እንፈልጋት?
ይበልጥ የሚገመተው 27ኛዋ ሌሊት ናት። ይሁን እንጂ “ለይለተል ቀድርን በ23ኛዋ ሌሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም “ለይለተል ቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ሌሊቶች) ፈልጓት። ከተረታችሁ በመጨረሻዎቹ 7 ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተል ቀድር ሁሌ በአንድ ሌሊት ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል። በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው። ይህን አስመልክተው ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድርን ከረመዷን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ሌሊቶች) በዊትሮቹ ፈልጓት” ብለዋል። [ቡኻሪይና ሙስሊም]
ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሸፍዕ ለሊቶችም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ፈልጓት። ዘጠኝ ሲቀረው፣ ሰባት ሲቀረው፣ አምስት ሲቀረው” ብለዋልና። ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ ሲቆጠር ነው። ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው የሚሆኑት። ይህም ሸፍዕ ሌሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል። ቢሆንም ግን “ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ዊትሩ ላይ ይበልጥ ማተኮር ይገባል።
4. በለይለተል ቀድር ምን ይጠበቅብናል?
ዒባዳ ማብዛት። ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል” ይላሉ። [ቡኻሪና ሙስሊም] እናም በዚች ሌሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለታይታ፣ ለጉራና መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደ ሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው።
5. ምልክቶቿ
1. “በዚያን ቀን ማለዳ ላይ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች።” [ሙስሊም]
2. በዚያን ሌሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል። ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች። [ሶሒሑል ጃሚዕ]
እነዚህ ምልክቶች ግን አንፃራዊ ናቸው ይላሉ ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ። በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል። ስለሆነም በትክክል ለይለተል ቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው ሊኖር ይችላል።
6. ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!
የወር አበባ ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች፣ … የዚች ሌሊት ትሩፋት አያልፋቸውም። ማስረጃው ጠቅላይ ነውና። ባይሆን ከሶላት ውጭ ባሉ ዒባዳዎች ላይ ሊበራቱ ይገባል። በዚያች ሌሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው። እንዲያውም ሱፍያኑ ሠውሪይ ረሒመሁላህ “በሌሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ።
7. ለይለተል ቀድር በአይን ትታያለች?
አንዳንዶች በረመዷን የመጨረሻው አስር ሌሊት ላይ እግራቸውን ዘርግተው፣ እያወሩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ። የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው። እሱን ሲያዩ “አኑረን አክብረን” ብለው ይንጫጫሉ። ይሄ ባዶ እምነት ነው። ለይለተል ቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም። የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም። ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ሌሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም።
8. ለይለተል ቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?
በተለይ ደግሞ ሌሊቱ ለይለተል ቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አሏሁመ ኢነከ ዐፉውዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል] ስለዚህ ዋናው ትኩረታችን የአላህን ይቅርታ ለማግኘት ይሁን።
9. ግን ለምን አላህ ለይለተል ቀድርን ስውር አደረጋት?
ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዷን የመጨረሻ ሌሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ሌሊት ስውር ያደረጋት። እናም ለይለተል ቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ለዒባዳ ይተጋሉ። በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ። ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹ ሌሊቶች ላይ ይዘናጉ ነበር። እናም መሰወሯ ነብዩ ﷺ እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው። [ቡኻሪይ]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 29/2007)
#Ramadan
Join:-
tiktok.com/@secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
Israeli warplanes and artillery attack multiple locations in the vicinity of the Al Shifa Medical Complex in Gaza City.
ረመዳን ቀን 2️⃣1️⃣
ከእናታችን አዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦
﴿كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَجْتَهِدُ فِي الْعَشْرِ الْأَوَاخِرِ مَا لَا يَجْتَهِدُ فِي غَيْرِهِ.﴾
ነቢዩ (ﷺ) ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ (በዒባዳ) ላይ ይተጉ ነበር።
📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1175
➡️ በአላህ
እምላለሁ! አንድ ሰው ስጁድ ላይ በሚሆን ጊዜ ምን ያህል የአላህ እዝነት እንደሚሸፍነው ቢያውቅ ኖሮ ግምባሩ ከመሬት ባላነሳ ነበር።
➖ኢብኑል ቀይምTens of thousands of worshippers perform prayers at al-Aqsa Mosque despite Israeli restrictions in the occupied city of Jerusalem.
የተሀጁድ ሶላት
~
ተራዊሕ፣ ተሀጁድ እና የሌሊት ሶላት የሚባሉት ለተለያዩ ሶላቶች የተሰጡ የተለያዩ ስያሜዎች አይደሉም። ይሄ የኢስጢላሕ ጉዳይ ነው። ትኩረት ልንሰጥ የሚገባው ከቃሉ ይልቅ ጭብጡ ላይ ነው። የሌሊት ሶላት የሚለው ተሀጁድንም፣ ተራዊሕንም ይገልፃል። ተራዊሕ የሚለውን ቃል ዑለማኦች በረመዷን ወር ከዒሻእ በኋላ በጀማዐ የሚሰገደውን ሶላት ለመግለፅ ይጠቀሙታል። ልብ በሉ! ከአፈፃፀሙ በስተቀር አመቱን ሙሉ ካለው የሌሊት ሶላት የተለየ አይደለም።
ተሀጁድ ሰዎች ሌሊት ተነስተው የሚሰግዱት ሶላት ነው። የሌሊት ሶላት ወቅቱ ከዒሻእ ሶላት በኋላ ጀምሮ እስከ ፈጅር ድረስ መሆኑ ይታወቃል። ስለዚህ እነዚህ ሶስት ስያሜዎች (ተራዊሕ፣ ተሀጁድ እና የሌሊት ሶላት) የአንድ ሶላት መጠሪያዎች ናቸው ማለት ነው።
ይህንን ጉዳይ ማንሳት የፈለግኩት አመት ጠብቆ መነታሪኪያ ስለሚሆን ነው። ነጥቡን ለማጥራት ከመሞከሬ በፊት አንድ ቀዳሚ ነጥብ ላንሳ። እሱም በርእሱ ላይ የትኛውንም አቋም ብንይዝ ሃሳባችን ቢለያይ እንኳ በልክ እንሁን። ዑለማኦች የተለያዩበት ጉዳይ እንደሆነ አውቀን እነሱ በያዙት መጠን እንያዘው። ዑለማኦች ብቻ ሳይሆኑ ራሳችንም በጉዳዩ ላይ ያለን አቋም ሊቀያየር ይችላል። ከስሜት ነፃ እስከሆን ድረስ ይሄ የሚጎዳ አይደለም። ወደ ነጥቦቹ ልግባ፦
1. የተራዊሕ ሶላት "መልካም" ቢድዐ ሳይሆን በቀጥታ ከነብዩ ﷺ የተገኘ ሱና ነው። [ቡኻሪይ፡ 872] [ሙስሊም፡ 1271] ከዚያም በአንድ ጀማዐ መስገዱ ተቋርጦ ከፊሉ በጥቂት በጥቂት ተከፋፍሎ ከፊሉ ደግሞ በተናጠል ሲሰግድ ከቆየ በኋ ልክ በነብዩ ﷺ ኢማምነት ተጀምሮ እንደነበረው በአንድ ጀማዐ በዑመር ተሰብስቧል። [ቡኻሪይ፡ 2010]
2. ቁጥሩ ከነብዩ ﷺ በተግባር የተገኘው እስከ 11 ረከዐ ድረስ ነው። ይህንን ይዘው ጭማሪው ቢድዐ ነው ብለው የገለፁ አሉ። የብዙሃን ዑለማእ ምርጫ ባይሆንም። የነብዩን ﷺ ቃላዊ መረጃዎች እና የቀደምቶችን አፈፃፀም ለተመለከተ ግን ጉዳዩ በቢድዐ ለመግለፅ የሚያስደፍር አይደለም። ስለዚህ ከአንድ አቅጣጫ ጥናት በመውጣት ጠለቅ ብሎ በማየት ጥንቃቄ ቢኖረን ይመረጣል። ከመሆኑም ጋር አፈፃፀማችንን ከነብዩ ﷺ ተግባራዊ አፈፃፀም ማለትም 11 ረከዐ ጋር ብናጣጥም የበለጠ ነው፣ ወላሁ አዕለም።
3. የረመዷን የመጨረሻው 10 ላይ ሌሊት ላይ ተነስቶ መስገዱ ቢድዐ ይደርሳል? በፍፁም!
3.1. ከጊዜ አንፃር፦ ሙሉ ሌሊቱ የሶላት ወቅት ነው። እንዲያውም ለሚችል ሰው የሌሊቱ መጨረሻ ከመጀመሪያው በላጭ ነው። በላጭ በሆነ ወቅት ላይ መሰባሰቡ ከቢድዐ ጋር የሚገናኝበት ነጥብ የለም።
3.2. አፈፃፀም፦ በጀማዐ መስገድም ቢሆን ተጨባጭ መረጃ የመጣበት ስለሆነ በዚህም በኩል ክፍተት የለም።
3.3. በመጨረሻው አስር ላይ ትጋት መጨመሩ፦ ተጨባጭ መረጃዎች የመጡበት ነው። አንድ ሁለት ልጥቀስ፦
ከእናታችን ዓኢሻ ተይዞ እንዲህ ብላለች፦
كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا دخل العشر أحيا الليل، وأيقظ أهله، وجدَّ وشدَّ المئزر
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ የመጨረሻው አስር ሲገባ ጊዜ ሌሊቱን በንቃት ያሳልፉ፣ ቤተሰባቸውን ያነቁ፣ በእጅጉ ይጣጣሩና ትጥቃቸውን ያጠብቁ ነበር።" [ቡኻሪይ፡ 2024] [ሙስሊም፡ 1174]
* ሌሊቱን በንቃት ያሳልፉ ነበር ማለት በዒባዳ ንቁ ሆነው ማለት ነው።
* ቤተሰባቸውን ያነቁ ነበር ማለት ለሌሊት ሶላት ነው።
* ትጥቃቸውን ያጠብቁ ነበር ማለት ከሴት ያገሉ ወይም ዒባዳ ላይ ያላቸውን ትጋት ከቀደመው ይጨምሩ ነበር ማለት ነው። [ፈትሑልባሪ፡ 4/316]
በሌላም መረጃ እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ብላለች፦
كان رسول الله صلى الله عليه وسلم يجتهد في العشر الآخر ما لا يجتهد في غيره
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ በመጨረሻው አስር ላይ በሌላው ላይ የማይተጉትን በተለየ ይተጉ ነበር።" [ሙስሊም፡ 1175]
3.4. ቁጥሩ፦ ከ11 በላይ መስገድ ይቻላል የሚል ሰው እዚህ ላይ ጥያቄ ሊያነሳ አይገባም። አይቻልም ለሚል አካል ግን ዐምር ብኑ ዐበሰህ ረዲየላሁ ዐንሁ "የትኛው የሌሊቱ ክፍል ነው ይበልጥ ለዱዓእ ተቀባይነት በላጭ የሆነው?" ብለው ሲጠይቋቸው ነብዩ ﷺ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
فصلِّ ما شئتَ فإنَّ الصَّلاةَ مشْهودةٌ مَكتوبةٌ حتّى تصلِّيَ الصُّبحَ
"ያሻህን ስገድ። በዚህ ጊዜ የሚሰገድ ሶላት መላእክት የሚጣዱባት ነችና። ፈጅር እስከምትሰግድ ድረስ።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1277]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
صلاة الليل مثنى مثنى فإذا خشي أحدكم الصبح صلى واحدة توتر له ماقد صلى.
"የሌሊት ስግደት ጥንድ ጥንድ ነው። አንዳችሁ ንጋትን ከሰጋ የሰገደውን ዊትር ታደርግ ዘንድ አንድ ረከዐ ትሰግዳለህ።" [ቡኻሪይ፡ 472] [ሙስሊም፡ 749
ስለዚህ ማታ ለሰገደም ይሁን ላልሰገደ ሌሊት ላይ በጀማዐም ይሁን ለብቻ መስገድ ይችላል። ከዊትር በኋላ መስገድም መረጃ መጥቶበታል። ባይሆን ሁለት ጊዜ ዊትር አይሰገድም። "በአንድ ሌሊት ሁለት ዊትር የለምና።" [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7567]
ወላሁ አዕለም!
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
ሁሉም ነገር በግንባር ተደፍቶ ሱጁድ ላይ በማልቀስ ይመጣል … ሁሉም ነገር በአላህ ተዐምር ይከሰታል…
ምንም እንኳን በጣም ከባድ እና መቼም ሊሆን የማይችል ህልም አድርገን ብናስበውም…ወላሂ ሁሉም ነገር ከአላህ ጋር ባለን ቅርበት ልክ ወደኛ ይመጣል …
https://t.me/tolehaahmed
This gateway to the Ka'bah is known as Bab Al-Fath (Door of Victory). It was from here that the Prophet (ﷺ) entered during the conquest of Makkah.
Israeli airstrikes on southern Lebanon destroyed a residential house in the town of Shihin moments ago.
*ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? *
እናታችን ዓኢሻ ረዲየ ‐አላሁ ዓንሀ እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለይለተል-ቀድርን ባገኝ (ያቺ ለሊት ለይለተል-ቀድር መሆኖን ባውቅ) ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ብዬ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም:- "አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው ፈዕፉ ዓኒ " በይ አሉኝ:: ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ ) ማለት ነው። (ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል::)
ሸይኽ አልባኒም ሀዲሱን ሰሂህ ከማለታቸውም ባሻገር በአንዳንድ የቲርሚዚይ ኪታብ ህትመቶች ላይ የሚታየው "ከሪሙን" የሚለው ቃል ጭማሪ ከአንዳንድ ፀሀፊዎች ወይም አታሚዎች ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል:: (ሲልሲለቱ አል-አሀዲስ አሰሂሃ)
©: ጣሃ አሕመድ ረመዿን 1442
ይህን ሰምቶ ለይለቱል ቀድርን ለማግኘት የማይጓጓ የለም!
አላህ ለዚያን ቀን ከወፈቃችሁ ይህን ሚስኪን ወንድማችሁን በመልካም ዱዓችሁ አትርሱት
አላህ ለመልካም ነገሮች ሁሉ ይወፍቀን
© Toleha Ahmed
150,000 worshipers perform the Taraweeh prayer inside Al-Aqsa Mosque today, despite Israeli restrictions in occupied Jerusalem.
At least 125,000 Muslims performed Friday prayers today at #AlAqsa_Masjid despite Israeli restrictions.
#Ramadan
#Palestine
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
🇵🇸 No one can break their faith. 🇵🇸
ማንም እምነታቸውን መስበር አይችልም። ቆይ ማን መሰሉህ ሙስሊምና ፈለስጢኖች እኮ ናቸው‼️
ረቢግፊርሊ!
ሉቅማን አል‐ሀኪም ለልጃቸው እንዲህ አሉት፦
﴿يا بني عود لسانك رب اغفر لي فإن لله ساعات لا يرد فيها سائل﴾
“ልጄ ሆይ! ምላስህ ረቢግፊርሊ ‘ጌታዬ ሆይ ምህረትን ለግሰኝ’ በማለት ላይ የሙጥኝ ይበል፤ የላቀው አላህ የጠያቂዎችን ጥያቄ መልስ የማይመልስበት (የሚቀበልበት) ወቅት አለና።”
[ሹዕበል ዒማን: 1120]
