Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
Repost from Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ዶ/ር ሐሰን ቡኻሪይ ከትናንት በፊት በጀመረው «መቃሲዱ-ል-ሐጅ» ደርሱ ላይ የኢብኑ ጀሪርን ንግግር ተመርኩዞ ሲናገር የሰማሁት፤ እነዚህ የዙልሒጃ 10 ቀናት ከሌሎች የየትኛውም የዓመቱ ቀናት በላጭ የሆኑት የዒባዳዎች እናት የሚባሉት ሁሉ አንድ ላይ ስለሚሰበሰቡበት ነው ብሏል።
ማለትም፤ ሶላት፣ ጾም፣ ዘካ፣ ሶደቃ፣ ዚክር… ወዘተ የመሳሰሉት ዒባዳዎች በሌሎች ጊዚያትም አሉ። ነገር ግን በነዚህ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት ከነዚህ ዒባዳዎች ባሻገር 5ኛው የእስልምና ምሰሶ የሆነው የሐጅ ተግባር ይጨመራል። ለዚያም ነው ቀናቶቹ ይበልጥ የሚለዩት። በተጨማሪም እንደ ጾም፣ ዘካ፣ ሶላትና ሶደቃ አይነቶቹ ዒባዳዎች በጊዜና በቦታ ሳይገደቡ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ይፈጸማሉ። ሐጅ ግን የሐጅ ወቅት ተጠብቆ በዓለም ላይ ብቸኛ በሆነው ቦታ በመካ ብቻ ይፈጸማል።
ስታርድ እዝነት ይኑርህ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ﴾
“አላህ ኢኽሳንን (ማሳመርን) በሁሉም ነገሮች ላይ ፅፏል። የገደላችሁ እንደሆነ አገዳደልን አሳምሩ። አንዳችሁ ባረደ ግዜ አስተራረዱን ያሳምር ማረጃውን ይሳል። የሚታረደውንም እንስሳም ያሳርፍ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1955
በሌላ ሀዲስ፦
﴿جاءَ رجلٌ إلى رسول الله ﷺ فقـال: يـا
رسـول الله إني لأذبحُ الشّـاةَ وأنـا أرحمها،
فقال ﷺ : والشاةُ إن رحِمتَها رحِمَك الله﴾
“አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ﷺ) በመምጣት እንዲህ አላቸው፦ ‘እኔ በጌን አርጄ ለሷም እዝነትን አድርጌ ነበር’ ረሱል (ﷺ) አሉት፦ ‘ለሷ ለበግህ እዝነትን እንዳደረክ አላህ ለአንተም ይዘንልህ።’”
📚 ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1081
©️ BuhariMuslimAmharic
t.me/ReshadIbnuMuzemil
🔰 የዘራናቸው ዘርች
⬛️ የዘራሃቸውን ዘሮች ዱካቸው ከጠፋህ ዝናቡ የት እንደዘራህ ይነግርሃል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
◆ የዘራናቸውን ዘሮች ዱካቸው ከጠፋን ዝናቡ የት እንደዘራን ይነግረናል። ➷➷▮▮
ልክ እንዲሁ መልካምነትን በየትኛውም ምድር፣ ከሰማዩ በታች፣ በምንም አይነት ሁኔታ እና ከማንም ጋር መዝራትን ልማዳችን ልናደርገው ግድ ይለናል .....
〽️ ምክንያቱም የዘራነው መልካምነት የት እንደምናገኘው እና መቼ እንደምናገኘው ግራ ቢገባን ዱካው ቢጠፋን ፈጣሪ በፈቀደው ጊዜ ወቅቱ ሲደርስ የዘራነው መልካምነት እራሱ መንገዱን ያቅጣጨናል።
▮ ስለዚህ በሄድንበት ሁሉ መልካም ነገር እንስራ።
የልባችንን ህመም ለመገላገል ከፈለግን የግድ በሌሎች እግር ስር የተሰካውን እሾህ መንቀል ይኖርብናል። የመልካምነትን ዘር ባገኘነው ማሳ ላይ እንዝራ መልሶ እኛውኑ ከመጥፎ ነገር ይጠብቀናል። ምላሽ ሳንጠብቅ ሰዎችን ስንደግፍም መጀመሪያ *የምንደገፈው* እኛው ነን!
▮▮እናም ለራሳችን ሀሴትና ተድላ ስንል ሰዎችን እንዲደላደሉ ቆሻሻ ያለበትን መንገድ እንድንጠርግላቸው ይገባናል። በሐዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ ከጎናቸው ሆነን ልናበረታቸው «አብሹሩ ከአላህ በታች እኛ ከጎናችሁ ነን» ልንላቸው ይገባናል‼️
▬▬ይችህ ዛሬ ላይ *በትንሽዬ ማሳ የዘራናት መልካምነት* *የነገ ቀን ዘሩ አድጎና በብዙ እጥፍ በርክቶ ሌላ ዘርን ይተካል*። *ያኔ ከኛ ጀምሮ ለብዙ ሰዎችም መትረፍ ይችላል*‼️
ስለዚህ ወገኖቼ መልካምነትን ባገኘነው ማሳ ላይ እንዝራ..... *ትንሽ እናተ* .... *ትንሽ ደግሞ እኛ* ፤ እነዚህ ሁለት ትንሾች ተደምረው ብዙ ይሆናሉና‼️
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
t.me/ReshadIbnuMuzemil
t.me/InspiresWorld
አላህ ሆይ እኛንም ወፍቀን‼️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በወቅታዊ ጉዳይ የማጋራቸው መልእክቶቼን ለማግኘት 〽️
t.me/ReshadIbnuMuzemil
ብዕር ከውስጥ ከስሜት ጋር የሚቦርቁበትን፤ በአላህ ፍቃድ ህይወትን የሚቀይሩ አነቃቂ ፅሑፎቼን ለማግኘት 〽️
t.me/InspiresWorld
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በ5 ማህበራዊ-ገፅ ትስስሮች ያገኙናል፤ ሁሉም የናተው መድረክ ነው‼️
1. Telegram
t.me/InspiresWorld
2. Facebook
fb.com/InspiresWorldWide
3. Instagram
Instagram.com/inspiresworldwide
4. Twitter
twitter.com/InspireWorldW
5. YouTube
https://www.youtube.com/@InspiresWorld
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ለየትኛውም ሀሳብ፣ አስታየት፣ ጥቆማ፣ ጥያቄና ድጋፍ
ቴሌግራም፦
t.me/ReshadMuzemil
ስልክ:- +251919728324
የናተው ወንድም:- ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል‼️
🔘(የልቦና ባለቤቶች ሆይ አስተውሉ)
"የሞቱ" ሰዎች ቀብራቸው ውስጥ ታግደው ባሳለፉት ነገር ይፀፀታሉ "በህይወት" ያሉት ደግሞ ቀብር ውስጥ ያሉት በሚፀፀቱበት ነገር ላይ ይገዳደላሉ
ወይ እነዚያ -የሞቱት- በህይወት ወዳሉት ሰዎች አይመለሱም በህይወት ያሉትም ቀብር ውስጥ ሆነው በሚፀፀቱ ሰዎች አይመከሩም
📂(ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ)
🔴 እነሆ እነዚህ አስሩ የዙልሒጃ ቀናት አሏህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሆኑ ቀናት ናቸው በእነዚህ ቀናትም ኸይር ስራዎችን በመስራት ተሽቀዳደሙ የሰማያትና የምድር ጌታ የሆነውን የአሏህን ውዴታ ለማግኘትም ጣሩ
አላህን ሱብሓነ ወተዓላ አልቁ የሱን ብቸኝነትም አውጁ አመስግኑት አወድሱትም እንደዚሁ ቀኑን ጹሙ የሌሊት ሶላትን ስገዱ ሰደቃም ስጡ አማኞች ሆይ ሁላችሁም ወደ አሏህ ተመለሱ ትድኑ ዘንድ
الله أكبر الله أكبر الله أكبر. لا إله إلا الله والله أكبر الله ولله الحمد
✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
©️ ዛዱልመዓድ
t.me/ReshadIbnuMuzemil
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
⏰ #አልስነይን 1 #ዙልሂጃ 1444 ሂ
በሳውዲ የዙልሂጃ ጨረቃ መበከሯን ታውጇል በዚህ መሰረት፦
➭ ዙልሂጃ ነገ ሰኞ 1 ብሎ ይጀመራል።
➭ ማክሰኞ ሰኔ 20 የአረፋ ቀን ይሆናል።
➭ እሮብ ሰኔ 21 የኢደል አድሃ ቀን ይሆናል።
©️BuhariMuslimAmharic
t.me/ReshadIbnuMuzemil
አስሩ ወርቃማ ቀናቶች!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشْرِ﴾
“በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆንባቸው ቀናት የሉም።”
📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል: 757
©️ BuhariMuslimAmharic
t.me/ReshadIbnuMuzemil
🔰 ለሰው ልጅ ፍቅርህንና አክብሮትህን የምትሰጠው ከገንዘብህ ወይም ከዕድሜህ ሳይሆን ከንፁህ ልብህ ነው!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬‼️‼️
ለሰው ልጅ ፍቅርህንና አክብሮትህን የምትሰጠው ከገንዘብህ ወይም ከዕድሜህ ሳይሆን ከንፁህ ልብህ ነው!!
◉ ግን ብዙዎቻችን ከገነዘባችንና ከዕድሜያችን ቀንሰን የምንሰጥ ይመስለንና ለሰው ልጅ.......
➨ ፍቅርን፣ አክብሮትን፣ ታማኝነትን፣ ይቅር ባይነትን፣ መርዳትንና መደገፍን እንዲሁም ምክርንና ተግሳፅን እንሰስታለን፤ አረ አንደውም ይባስ ብለን እንደአውሬ «እኔ ብቻ» በሚል ሱስ ተለክፈን መኖርን ልማዳችን እናደርገዋለን‼️
⇒ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፣ የዋህነትና ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ⁉️
〽️ እየተጠሉ መወደድ፤
〽️ እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤
〽️ በጥላቻ መንፈስ እየታዩ ፍቅርን መስጠት
〽️ እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል።
⛔ ትዕግስት እንደ ፍርሃት፣ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፣ አክብሮት እንደማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን ከመልካም ስብዕና እየራቅን ነው።
⇒ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን።
⇒ ደግነት ማለት ማየት ለማይችሉ አይን፤ መስማት ለማይችሉ ጆሮ ሆኖ የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑን ማን በነገረን!!!
ደግነት የሚጀመረው ደግሞ በልባችን ስንመራ፣
o እንደራሳችን ቆጥረን ስለሌሎች ስንጨነቅ፣
o ዉለታን ሳንፈልግ ስናገለግል፣
o ሰው ስንቀን እኛ ግን ስናከብር፣
o ምላሽ ሳንጠብቅ መስጠት ስንጀምር ነው‼️
⇒ ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፣ እራሳችንን ማስቀደም ብልህነት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን።
⇒ እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፣ ሌሎችን እደማክበር፤ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ⁉
በመጨረሻም፦
⬛️ ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው ካልተጠቀምንበት ይቆርጠናል!!
➤ እናም በዚህ ጎራዴ በሆነው ጊዜያችን ከመባላትና ከመጠላላት ይልቅ አብረን ተዋደን፣ ተከባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንዳችን አንዳችንን መክረን ወይም ገስፀን በሰላምና በፍቅር እንኑር።
● ካልሆነ ግን በጥላቻና በተንኮል ያሳለፍነው ጊዜ እራሳችንን ቆርጦ ይጥለናል።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን:- ቅዳሜ/ ሰኔ 10/2015 E.C [June 17 2023 G.]
t.me/ReshadIbnuMuzemil
t.me/InspiresWorld
«𑁍አዲስ አፕልኬሽን𑁍
𑁍ተለቀቀ𑁍
“ስለ ረሱል ምን ያህል እናውቃለን?”
﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌
በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነብያችን (ﷺ) ላይ ይውረድ።
እያንዳዱ ሙስሊም ሊያውቃቸው ግድ ከሚሉት ነገራቶች መካከል ወደሱ የተላኩትን ነብይ ማወቅ አንዱ ነው።
ከአነስ ብኑ ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ በተላለፈው ሐዲስ የአሏህ መልክተኛ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) "እኔ አንዳችሁ ዘንድ ከወላጆቹ፣ ከልጆቹ እና ከሰዎች በሙሉ በላይ እርሱ ዘንድ ይበልጥ እስካልተወደድኩ ድረስ አላመነም" ብለዋል።
ነብዩን (ﷺ) ለመውደድ ስለእነሱ ማወቅ አስፈላጊ ስለሆነ በዚህ የሙባይል አፕልኬሽን የነብያችንንﷺ የህይወት ታሪክ አጠር ባለ መልኩ ለመዳሰስ ተሞክሮዋል።
ስለ ነብዩ (ﷺ) እና ቤተሰቦቻቸው የበለጠ እንድንማር እና የበለጠ እንድንወዳቸው አላህ ይርዳን።
እርሶም ከአጅሩ ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ አንብበው ለሌሎችም ያጋሩ።
𑁍መተግበሪያውን በሚከተለው ሊንክ ይጫኑ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ProphetMuhammed.Hudasoft
በአላህ ፍቃድ ሌሎች ጠቃሚ አፖችን አዘጋጅተን በቀጣይ እናደርሳችኃለን።
ዝግጅት፡ አብዱ ሙሰማ ሀሰን
አፕልኬሽን ስራ፡ ሁዳ ሶፍት||HUDA SOFT»
©: ሁዳ ሶፍት
t.me/ReshadIbnuMuzemil
Hijaab is not a Barrier between you and the people.
It is the Barrier between you and the evil of the people.
Dr.Zakir Naik
t.me/ReshadIbnuMuzemil
