Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
〽️ እውነትም አልኖረች
እኛ ካሌለናት - ከጎኗ ከእውነት፤
በሷ እየኖርን - እኛ ካለደገፍናት፤
ሰውነታችን አምሮ - ካላሸበረቀንባት፤
ሁሌ እውነት ካላወራን - ምላስ ረስቶ ውሸት፤
መያዛችን አይቀርም - በአንድ ቀን ቁጭት፤
እየኖርን ሳለ - የመብረቅ ጋጋታ፤
አይናችን አንጋጠን - አምላኬ ይቅርታ፤
ይሀው አካላችን - በእውነት ተረታ፤
ምንም ብናስመስል - በደቂቃዎች ቆይታ፤
የምንሞት መስሎን - የያዘን ብዥታ፤
መፍራት ስንጀምር - የውሸታችን ኮታ፤
መቁጠርም ስንጀምር - የባጢላችን ብዛት፤
አውጥተን ስናሰላላስል - የውሸታችንን ይዘት፤
ለካስ ጎተራ ሞልቷል - የጥፋታችን ቅዠት፤
እውነትም አልኖርም በሚል - ከበቀለችበት ጠፋች፤
እናም በኛ ጥፋት - በቅፅበት በረገገች፤
ከአፍንጫየ ውጡ ብላን - ጎራዋን ቀየረች፣
የሚናገራትን ፍልለጋ - ከኛ ይሀው ራቀች።
--- ለካስ ነገሩ - እንዲህ ነው፤
እኛ ነን ያልገባን - ሁኔታውን ያልተረዳነው፤
የእውነትን እውነት - እኛነን ያላወቅነው፤
ለካስ ወገኖቼ ነገሩ ወዲህ ነው፤
እውነት ቤት ስትሰራ - ውሸት ላግዝ ካለች፤
ጭቃ ከረገጠች - ሚስማር ካቀበለች፤
ቤቱም አልተሰራ - እውነትም አልኖረች
ቤቱም አልተሰራ - እውነትም አልኖረች።
ግጥም:- በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
t.me/ReshadIbnuMuzemil
t.me/InspiresWorld
እውነት
⚙️ የእውነት ቅርንጫፎች ረጃጅሞች ናቸው፤ ስራቸው ደግሞ መሬት ስር። እዚህ ያለ ቅርጫፍ ጥላው ሌላም ቦታ ያካልላል።
🏷 እነዚህን ቅርጫፎች የሰው ልጆች ሊገነድሷቸው (ሊቆርጧቸው) ይታገላሉ ነገር ግን ቅርጫፎቹን የሚቆርጥ መሣሪያ ከቶውኑም አልተፈጠረም ወደፊትም አይፈጠርም።
➝ እኛ ቅርንጫፎቹን ለመቁረጥ ስንታገል መጥረቢያችን(🪓) የነካው ቦታ ሌላ ቅርጫፍ ያበቅላል።
🏷 መሬት ያሉትን የእውነት ስሮች የሰው ልጆች ሊነቅሏቸው ይታገላሉ ነገር ግን እነዚህ ስሮች ከመሬት የሚነቅላቸው ተዓምር ራሱ የለም።
➝ እኛ ስሮቹን ለመንቀል ስንታገል ስሮቹ ደግሞ ይበልጥ ስራቸውን ሰደው ምድርን ያካልሏታል።
ወንድምና እህቶቼ ስለ እውነት በጥቂት መስመሮች የምንገልፀው ነገር አደለም። ዬቱንም ያህል ዕውቀት ቢኖረን “እውነት እኮ ማለት” ብለን “እውነትን” ማብራራቱ አዳጋች ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ነገር ነው።
♦️ብዙ ፅሁፎቼ ላይ እንደምላችሁ ዛሬም እላችኋለሁ......
➻እውነትን የሚገልፀው ነገር ቢኖር ራሱ “እውነት” ብቻ ነው!
➻ እውነትን “እውነት” ነው ብሎ የሚለየው ነገር ቢኖር ራሱ “እውነት” ብቻ ነው!
➻ እውነትን “እውነት” ነው ብሎ የሚረዳውና የሚያውቀው ነገር ቢኖር ራሱ “እውነት” ብቻ ነው!
💬 ሰዎች እውነትን ለማጥፋት ወይም ከእውነት ለመሸሽ እድላቸውን ይሞክራሉ......
ነገር ግን ሰዎች ምንም ያህል እውነትን ለማጥፋት ቢሞክሩም፤ በያንዳንዱ ቅፅበት እውነት አዲስ መልክ ይዞ “እውነት” ሆኖ ይወለዳል።
🔑 ፍትህ ቀባሪዋን ስትቀብር፤ እውነት የሚወዳትን ትወዳለች የሚጠላትን ደግሞ ታዋርደዋለች ብቻ ሳይሆን ውድቀትን ታከናንበዋለችም‼️
Motivation by Reshad
t.me/ReshadIbnuMuzemil
t.me/InspiresWorld
ማስታወሻ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إذا رَأَيْتُمْ هِلالَ ذِي الحِجَّةِ، وأَرادَ أحَدُكُمْ أنْ يُضَحِّيَ، فَلْيُمْسِكْ عن شَعْرِهِ وأَظْفارِهِ.﴾
“የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያን ለማረድ ካቀደ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1977
ጆይን፦ @BuhariMuslimAmharic
t.me/ReshadIbnuMuzemil
አግራሞቴን በብዕር
📌 ህይወት አንድ ንግድ አደለችም፤ መቀበልና መስጠት ብቻ የሚካሄድባት። እና የኛ ተግባር ከንፁህ ልባችን ምንም ምላሽ ሳንጠብቅ መስጠት ብቻ ይሁን!!
▣ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን
▣ ወቀሳን ሳይሆን ሙገሳን
▣ ትችትን ሳይሆን ሐሳብን/መልካም ተግሳፅን
▣ ንቀትን ሳይሆን ክብርን እንስጥ
▣ ለኛ ይመስለናል መልካም መሆናችን የሚጎዳን....
💌 ነገሩ ግን ባለን ካልሰጠን የተሻለ ነገር ማግኘት አንችልም!!
➤ አይገርምህም ከተሰጠህ ነገር በጭልፋ እንኳን አልቀዳህም! ፈጣሪ የሰጠህማ ከባህር የሰፋ አቅም፣ ከውቅያኖስ የጠለቀ ቸርነት፣ ከፍቅር ከራሱ የበለጠ ፍቅር ነው፤ አመስግነህ ተጠቀምበት ወዳጄ!
📍እስቲ ወዳጆቼ መልካም እንስራ.....
ትንሽ እናተ ....ትንሽ ደግሞ እኛ!
በረሻድ ሙዘሚል
t.me/InspiresWorld
t.me/ReshadIbnuMuzemil
🔰 ዝምታ
► ከዝምታ ጀርባ ብዙ ግርምቶች አሉ፤ ብዙ ትዝብቶችም ጭምር!!
⚙️ ዝምታን ምርጫህ ባደረክ ጊዜ ሰዎች ጅል መስለህ ትታያቸዋለህ። እነሱ ያስባሉ፤ አንተ ምንም እንደ ማታቅ፣ ምንም እንዳልከፋህ፣ ምንም እንዳላዘንክ!!
Motivation By Reshad
t.me/InspiresWorld
የመልካም ስራዎች ቁንጮ ‘ላኢላአሃ ኢለላህ!’
ከአቡ ዘር አልገፋሪ (رضي ﷲ عنه)ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إذا عَمِلْتَ سيئةً فأتبِعْها حسنةً تَمحُها قالَ: قلتُ يا رسولَ اللهِ ! أمِنَ الحسَناتِ لا إلهَ إلّا اللهُ ! قالَ: هيَ أفضَلُ الحسَناتِ﴾
“ወንጀልን ከፈፀምክ መልካምን ስራ አስከትልበት ታሳብሰዋለችና። እንዲህ ተባሉ፦ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ‘ላኢላአሃ ኢለላህ’ ከመልካም ስራዎች ውስጥ ነውን? እንዲህ አሉ፦ አዎ! እንደውም እሱ በላጭ ከሆኑት ስራዎች ውስጥ ነው።”
📚 ሶሂህ አተርጊብ: 3162
ጆይን፦ @BuhariMuslimAmharic
t.me/ReshadIbnuMuzemil
👆አዓይናችን የመነፅር ቁጥር ማነስ
Text convetrs to Audio by Amharic (Ethiopia) to Speech Website.
#በረሻድ_ኢብኑ_ሙዘሚል
🔰 አዓይናችን የመነፅር ቁጥር ማነስ
● ብዙ እብዶች ባሉበት ቦታ አንድ ጤነኛ ቢኖር እንደ እብድ የሚታየው ጤነኛው ነው።
▮ልክ እንደዚሁ ብዙ የደከመና የዘቀጠ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች መካከል አንድ ጠንካራ አስተሳሰብ ያለው ሰው ቢኖር፤ ይህ ሰው ነው የደከመ አስተሳሰብ ያለው የሚመስለው።
📒 አዎ ለነገሮች ያለን ምልከታ ከብዙ ሰዎች የተለየ ከሆነ፤ ምልከታችን ትክክል እንኳን ቢሆን ለሰዎች ግን ስህተት መስሎ ይታያቸዋል። ምክንያቱም የዕይታቸው አድማስ ጠቧል፣ የአይናቸው የመነፅር ቁጥር አናሳ ነው!!
ይህ በሆነበት ሁኔታ መልካም ስብዕናና ያለ ምላሽ ሰዎች ማገዝ በጣም ከባድ ይሆንብናል። ከጎናችን ያሉ ሰዎች እኛን መረዳት ስለማይችሉ የሚያግዘንም ሆነ የሚያበረታታን ሰው አናገኝም።
ያኔ ይህን ልንል እንገደድ ይሆናል....
📒 በቃ እኔም እንደ ሌሎቹ ሰዎች ህልም የሌለው፣ መለወጥ የማይፈልግ፣
▪ሰዎች ሲኖሩ አይቶ የሚኖር፣ ሰዎች ሲሮጡ አይቶ የሚሮጥ፣
▪ሰዎች ሲስቁ አይቶ የሚስቅ እንዲሁም ሲያለቅሱ አይቶ የሚያለቅስ፣
▪ወደዚህች ምድር የተገኘበት አላማ 🎯 ምን እንደሆነ ሳያውቅ ዝም ብሎ በዘፈቀደ እንደሚኖር ሰው ልሁን።
⚙️ ግን ወዳጆቼ እንደዚህ ያለ ዓላማ 🎯 የሌላው እርባና-ቢስ ከመሆን በጥንካሬዎቻችን የተነሳ የሚደርሱብንን በደልና ግፎች ይሻሉናል። አዎ እነዚህን እንቅፍቶች መቋቋም ይሻለናል‼️
➤ ሰዎች የሚቀረኑን ለዚህ ነው፤ የኛን ጥንካሬና ፍንክች-ልንክች የሌለበት አቋማችን አስፈርቷቸው።
➤ ብዙዎች የማይደግፉን ለዚህ ነው፤ ከኛ እኩል በስኬት ጎዳና ላይ መራመድ ስላቃታቸው።
➤ ብዙዎች በቅናት የተነሳ በደል የሚፈፅሙብን ለዚህ ነው፤ ከኛ እኩል ከፍ ብለው መብረር ስለማይችሉ።
🔚 የኛን የእይታ አድማስ ምን ያክል እንደሰፋ ለማወቅ ይጓጓሉ ነገር ግን የነሱ ጠባብ ስለሆነ የኛን መለካት አይችሉም። ስለዚህ እነሱን ችላ እንበላቸውና ልክ እንደ ወፍ እንኑር... ለሚሰማት ሰውና ለአስታያየቱ ቦታ ሳትሰጥ እንደ ምትዘምረዋ ወፍ።
Motivation By Reshad
t.me/InspiresWorld
〽️ እንኖራለን በሀሴት
ኢንዲ ስትል ፃፈች - ያረገዘችው ብዕሬ
ለእጄ እንዳይከብደኝ - ክዳኗን ወርውሬ
እናም መፃፍ ጀመርኩ - እንዲህ ስል ጀምሬ
ግን ገንፍላለችና - ቀለሟ እንዳያልቅ
እውነቱ ላውጣው - ልቤ እንዳይጨነቅ
በሀቅ ትደሰት - ብዕሬ ትቦርቅ።
እስቲ ልሞነጫጭር - ሀሳቤን ልግለጥ
ግን አልችልም - ውብ ቃሎችን መምረጥ
አጣዳፊ ነውና - ያረገዘቺው ብዕሬ ምጥ።
የዕድሜችን ጉዞ ሽሽት
የተስፋችን ቅዠት
የመኖራችን ሚስጥር
የህይወት ቁም ነገር
የኑሮ ስንክሳር
እንጨነቃለን ኢሀው - ምንም ላንፈጥር
በሆነ ጊዜና - ስትጠልቅ ጀምበር
ድቅድቁ አይሎ - ጨለማው ሲደራ
እኛም ረስተን - ሰባዓዊ ፉጥርነታችንን
ፍንትው ብሎ ወጣ - ኢሀው ጭካኔያችን
ልብሳችን ሸፍኖት - ያን ትምኪት አንደበት
ስንኖር አምሮብን - ኑሮን የውሸት
ሰው መች ይህነ አወቀ - እኛነታችንን እውነት
ፀሃይ ማብራት ስትጀምር - ለሰው ልጅ በተራ
ፍርድም ሲጓደል - እውነት ሲሆን ተራ
ከፋፍለን ስንጨርስ - ሰዎችን በጎራ
እናም አስተዛዘበን - የአስተሳሰባችን ስፍራ።
ጌዜም ሚስጥር ሆነ - እንደ ስልክ ኮድ
ሚከፍተው ያለ አይመስልም - አወይ የኛስ ጉድ
ወይስ በኮፒ እንክፈተው - በአርተፊሻል ፓስዎርድ
ቀኑ ቶሎ መሸ - ለሊቱ ረዘመ
ልባችን ታመመ - እኛን እያከመ
ሀሴት መበፈለግ - ውስጣችን ከሰመ
እንቅፋት በዝቶበት - ደስታን ሚቀማ
ግራ ገብቶን አለን - የጭቀት አላማ።
ሰኞን እየጠበቅን - ማክሰኞ ደረሰ
እሮብ አለፈ - ሀሙስ ተጋመሰ
ጨለማው ረዝሞ - ብርሃን ታመሰ
ደስታም እንደ ቤት - ተሰርቶ ፈረሰ
ቀኑ 24 ሰዓት - እኛ ግን ዜሮ
ማሳለፍ ለምደን - ጭንቀትን በጓሮ
ለውጥ ላናመጣ - አሰማን ሮሮ
ኢሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ
ኢሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ።
ደግነት ይፃፍበት - በጥላቻ ሰነድ
እውነት ይስፈርበት - በጨለማው መንገድ
እስቲ ደግ እንሁን - በቃ ሰው እንውደድ
በቃ ሰው እናክብር- ውስጣችን እንዳይናድ
ለውዴታችን ግን - ምላሽ አንጠብቅ
በሚመስጥ ትህትና - ከእውነት እንታረቅ
ተስማምተው ከሄዱ - እምነትና ተስፋ
ሃቅ ገኃድ ከወጣ - የሰው ልጅ ካልከፋ
እውነት ሚስጥር ካልሆነ - ካወጣነው ኢፋ
ይሄኔማ ሰው እንሆናለን - ደግነት ያቀፈ
ሁሉም ለበጎ ይሆናል - ይጠፋል ብስጭት
መመኘት እንጀምራለን - እውነተኛ ምኞት
በደስታ ያበበ - ውብ ማራኪ ጊዜያት
እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት
እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት።
በረሻድ ሙዘሚል
ቀን፦ ነሃሴ 18/2011[Aug 24/2019]
t.me/ReshadIbnuMuzemil
t.me/InspiresWorld
A man walked from India to Saudi Arabia (8500km) to perform Hajj. Allahu Akbar. May Allah accept his journey.
#Hajj2023
እንኳን ኒቃብ መልበስ መገላለጥም መብት ተደርጓል‼
ፍትሕ ለጉንችሬዋ እህቴ‼
#ጉንችሬ #ኒቃብ #ትምህርት
t.me/ReshadIbnuMuzemil
Inshallah sin argaa Yaa Rasulallaahi(ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም)
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
〽️ አንቺ፣ አንተና እኔ በዱኒያ ጥማት፣ በማንአለብኝነትና እኔ ብቻ ነኝ ትክክል በሚል የዘቀጠ አመለካከት ሰክረናል። ህፃኑን ግን ያስለቀሰው _⁉️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬‼️
©️ ኢንሻአላህ እናያችኋለን የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም)
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬‼️
t.me/ReshadIbnuMuzemil
#እኔና ሂጃቤ
ያለሷ አያምርብኝ፣ያለኔ አያምርባት፣
አቤት ያለኝ ውበት፤ሂጃቤን ስለብሳት፣
እኔና ሂጃቤን፤ምቀኞች ቢጠሉን፣
ሗላ ቀር እያሉ ቢያገሉኝ፤በእሳት ቢያቃጥሉን፣
እኛ አንለያይም፤እንዋደዳለን፣
እስከመጨረሻ፤አብረን እንኖራለን፣
እርቃኔን እንድሄድ፤ሂጃቤን ሊቀሙኝ፣
የማያዋጡኝን፤ከ አላህ ሊያጣሉኝ፣
እኔ ግን አልሄድም፤ሂጃቤን አውልቄ፣
ጥቅምና ጉዳቱን፤አውቃለሁ ጠንቅቄ፣
እባካችሁ ተውኝ፣ሰላም ልኑርበት፣
ሂጃብ ውበቴ ነው፤ልከናነብበት፣
ከ /ትቤት ብባረር፤ከሀገር ብወጣ፣
ሂጃቤን አልተውም፤የመጣው ቢመጣ፣
ስንት ዘዴ አመጡ፤ሂጃቤን እንድተው፣
ደካማ ናት ብለው፤ሴትነቴን አይተው፣
ብትመቱኝ ብትቆርጡኝ፣ብትቀጡኝ እንደ ጠላት
እኔ ግን አልተውም፤ሂጃብ ውበቴ ናት፣
እኔ እሷን አልተውም፤እያለሁ በሂወት፣
እከናነባለሁ፤ ባለኝ ላይ ደርቤ፣
ልዩ ፍቅር አለኝ፤እኔ ለሂጃቤ፣
ከሀራም ጠብቃ፤ውበት በሰጠችኝ፣
አውልቂ ምትሉት፤ምን አደረገችኝ?፣
ፅሁፌን ልጨርስ፤ባያልቅም ሀሳቤ፣
በቃ አንለያይም፤እኔና ሂጃቤ፡፡
Copy
•°•… ከእንስቶቻችን አንደበት …•°•
አምላኬ አላህ ሆይ !
የተሸፈንኩበትን ልብሴን
ስርዓቱን የጠበቀውን ሂጃቤን
ራሴን ከውድቀት የማድንበት
ከዋልጌያን የምጠበቅበት
ፈታኝ ከመሆንም የምድንበት
አይናፋርነቴን ይፋ የማረግበት
ያንተን ትዕዛዝ መቀበሌን ማጎላበት
መልዕክተኛህን መውደዴን ማሳይበት
ዟሂሬን እንዳሳመርክልኝ
ፅናቱን ስጠኝ
ልቤን ከኒፋቅ ተግባሬን ከእዩልኝ
አቂዳዬን ከውድቅ እምነት ጠብቅልኝ
🌴 🌴
ያ………………… ረብ
የምእመናን እናቶችን በመውደዴ
በነሱ ፈለግ በመሄዴ
ተግባር እምነታቸውን ለመያዝ በመጣሬ
አፅናኝ አበርታኝ ኣቁመኝ በሁለት እግሬ
በጥቡቅነቴ የምኮራበት
ሰሃቢያትን መከተሌን የማስመሰክርበት
ከዱንያ ፊትናዎች መሸሸግያ
ስሜትን ከመከተል መደበቂያ
ኣድርግልኝ
🌴 🌴
ያ………… ኢላሂ
ከማይቀረው ቅጣት የምድንበት
ከአሳማሚው እሳት የምተርፍበት
ከአላዋቂያን ጎራ የምርቅበት
ከሷሊህ እንስቶች የምመደብበት
ከሰሃቢያት ጋር የምቀሰቀስበት
ለጀነት ሙሽራነት የምታጭበት
ለክብሬ እንደኖርኩ
ነገም የምከበርበት
ላንተ ስል ፈተናዎቹን ሁሉ
የተቋቋምኩበት
የሸሮች ሁሉ መሸፈኛ
የኸይራት ሁሉ ማግኛ
የእዝነትህ ሰበብ ኣድርግልኝ
🌴 🌴
አላህ ሆይ `
ይህን ሂጃቤን በዱንያም ከክፉ ነገሮች
መጠበቂያ ሂጃብ ፤
በኣኺራም ከእሳቱ የምሰተርበት
ሂጃብ ኣድርግልኝ ።
آمين
__
📝abufewzan15Jan 14
•> 24 Rabi'e al-awal 1436 <•