ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ግጥም

ግጥም

前往频道在 Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

显示更多
5 685
订阅者
+924 小时
+497 天
+13130 天
帖子存档
#ችክ_አትበልበት ስትወደው ከጠላህ ስትነግረዉ ካልሰማህ ስትሰጠዉ ፊትህን ከሰጠህ ጀርባዉን ፍፁም ካልተረዳዉ አስተሳሰብህን ችክ አትበልበት አትለማመጠው ወዳጅ አይሆንህም በግድ ያስጠጋኸው @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

አጥርሽ ገረገራ ውሻሽ ተናካሽ ተቋጥሬ ልግባ በመቀነትሽ። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

#ነገሽን_ስሪበት ነገ ከሚረግፈው ከዛሬው ውበትሽ ይዋል ተቀንሶ ለመቃብር ስምሽ ተግባርሽ በበጎ ዘወትር እንዲጠራ ውበትሽ ዛሬ ላይ የነገን ስም ይስራ ተዋቢ ግድየለም መልክሽ ይመርበት ከዛሬው ቀንሰሽ ነገሽን ስሪበት። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

አመለጠኝ ያልኩት የማይበጀኝ ነበር ለካስ ለዚህ ነበር ተው ያልከኝ እግዚአብሔር አብዝቼ ፈልጌ ያጣሁት የራቀኝ መጥፊያዬ ቢሆን ነው ጌታ የነፈገኝ። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

#ሰው_ከመሆን_አንሶ !!! ጠዋት የገቡት ቃል ማታ እየፈረሰ በወዳጁ ክህደት ስንቱ እያለቀሰ መተማመን ጠፍቶ መገፋፋት በዝቶ ገንዘብ ጣኦት ሆኖ ልብን እየገዛ ሰውነት ተናቀ እረክሶ እንደዋዛ ። የእግዚአብሔርን ዋጋ ለቄሳር ለግሶ የዘር ዛር ያነግሣል ሰው ከመሆን አንሶ ። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

ሰዎች ይሄን ቻናል እስካሁን ባለማሳየቴ በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ ደሞ እናንተም ይሄን የመሰለ የDraw Fixed Betting ሚለቀቅበት ቻናል ከሌላቹ ቤቲንግ አቆርጡም ማለት ነው እኔን እራሱ አስደመመኝ ደሞ በነፃ ነው ሁሉም ነገር FREE  ሚያጫውት ብቸኛው Source ነው እዛ ገብቶ ዝም ብሎ መብላት ነው join በማለት ቤቲንግን እንደ Business ይጠቀሙ !!

ቤተሰብ እንዴት ናችሁ? በ 1 Task 25 Birr መስራት የሚፈልግ 5 preparatory Level And Above Level ተማሪ እፈልጋለሁ ❗️Remember ❗️:- በቀን 20 ብትሰሩ 500 Birr ማለት ነው "ስኬት ከትንሽ ይጀምራል" የመስራት ፋላጎቱ ያላችሁ አናግሩኝ phone 📞 0924169863 Telegram:-@Special_waver

እኔስ ናፍቀሽኛል አልናፈቅኩሽም ወይ መራራቁ ቀርቶ አንገናኝም ወይ @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

#የነጠፈ_ብዕር ብዕር ወዙን አጥቶ ቀለሙ ነጠፈ ጥበብ ማማጥ ትቶ በዘር ተለከፈ ቅኔን አፍልቅ ቢሉት ደም እየሰበከ ከመንደር ሳይወጣ ግፍ እየታከከ ወረቀቱን ሁሉ በክሎ ጨረሰው ባለቅኔ መጥቶ እንዳይጠቀመው የነጠፈ ብዕር ድርቀት ያደረቀው ቢጽፍ አያምርበት ጽፎ መደለዝ ነው። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

ተወት በማድረግ ካልታለፈ ነገር በሆነው ልክማ ማን ችሎ ሊናገር። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

#እየመጣዉ_ነበር በቀጠሮ ሰአት ከነገርኩሽ ቦታ🕙 በርሬ እየመጣዉ እንዳትቆሚ ላፍታ🏃‍♂️ አበባ ባንድ እጄ ቀለበት በኪሴ🌹💍 ሽቅርቅር ብዬ ከእግር እስከ ራሴ🕺 እየመጣዉ ነበር እያልኩ ፈራ ተባ ቀለበቱ ይቅደም ወይንስ የእጄ አበባ እያልኩኝ ለራሴ ባሳብ ስብሰለሰል ካንዱ ወዳንዱ ሳሎጣ ሳማሰል ድንገት አረረና የሀሳቡ ፍሬ ከቀልቤ እርቄበት እየመራኝ እግሬ ካሳቤ ስወጣ ከተዘፈኩበት መሀል አስፓልት ነዉ ለካ የቆምኩበት @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

#የቴሌግራም ፕሪሚየም በጣም ተወዷል ይሄ ግን ምርጥ ቦት  ነው አትሞኙ አይሰራም ብላቹ። ሰዎች ቶሎ በዚ ሊንክ ገብታቹ ሶስቱን ቻናል ብቻ ተቀላቅላቹ ቴሌግራም ፕሪሚየም ውሰዱ እውነቴን ነው እየቀለድኩ አይደለም እንዳያመልጣቹ። ሊንኩ 👇👇👇👇 https://t.me/TgPremiumRoBot?start=Bot16703940 ጊዜው ከማለፉ በፊት ተጠቀሙበት ❤️

ህሊና ታውሮ ዐይን እያፈጠጠ ሀሰት ቀና ስትል እውነት ግን ጎበጠ። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

#መኖር_የተካኑ በመከራ ሆነው ተመስገን የሚሉ እንዴት መታደል ነው ቢገባቸው ቃሉ ዓለም በፈተና ጠፍራ ይዛቸው ተመስገን ይላሉ በመታደላቸው ሲወድቁም ሲነሱ የሚያመሰግኑ በተስፋው ብርሀን መኖር የተካኑ ያስቀኑኛል እኔን ከደላቸው በላይ በችግር ውሰጥ ሆነው የሚያዩ ወደላይ አምላክን ተማምነው ፈተናን ያልፈሩ በመራብ ውስጥ ሆነው ፍሬን የሚያፈሩ ካላቸው ቀንሰው ሌላን የሚያጎርሱ በስውር ሸሽገው ሳይተርፍ የሚያለብሱ እንዲህ ነው መታደል ቃሉን ልተረዱ አምላክን ፍለጋ ልብን ያሰናዱ። @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

Follow this page 👏👏👏👏👏👏 https://www.facebook.com/profile.php?id=61556302110644

በሰው ሀሳብ ቢሆን በምድራዊ ስሜት መቼ እንኖር ነበር ዛሬንስ ለማየት እግዚአብሔር ፈቅዶ እንጂ ሰጥቶን ትልቅ ዋጋ በምቾት ያለነው እንደ ባለጸጋ!!! ሳይኖረን ያኖረን እኛን ክርስቶስ ነው እንደኛማ ቢሆን ህይወት አዙሪት ነው @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

✍መልእክቱ✍ ለወትሮው ያለምክንያት ሳንቲም የማያወጣው ሰውዬ አሁን አዲስ የእርዳታ ተቋም ተከፈተ በተባለ ቁጥር እየሄደ እጁ ላይ ያለውን ብር በሙሉ ይሰጣቸዋል። መለገሱ ደግ መሆኑ አልበረም የከነከነኝ በአንድ ግዜ ለጋስ መሆኑ እኮ ነው ያጠራጠረኝ። "የተፈጠረ ነገር አለ አይደል?" አልኩት ሌላ የእርዳታ ድርጅት እየሄድን "ሰውን ለመርዳት የሆነ ነገር መፈጠር?" አለበት አለ አይኔን እየሸሸ።ይሄኔ የደበቀኝ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ሆንኩ። "ንገረኝ ችግር የለውም" አልኩት ምናልባት የሚያናድድኝ ነገር ከሆነ ብዬ "አይ ጥፋት እንኳን አይደለም" አለ ወደ መስኮት ዞሮ አይኖቹ እንባ አቅርረዋል ይሄኔ ልቤ መሸበር ጀመረ። "ምንድንው ቢኒዬ? እያስጨነከኝ ነው" አልኩት "ሳልነግርሽ ቀኑ ተሸርሽሮ ቢያልቅ ደስ ይለኝ ነበረ... ግን አልቻልኩም... አይኖችሽን እያየሁ በየቀኑ መደበቅ አቃተኝ" "እንዴ የምን ቀን ነው የሚሸረሸረው?? ምንድነው ያልነገርከኝ?" አልኩት እንባውን ከፊቱ ላይ እየጠረግኩ። "ግፋ ቢል አምስት ወር ነው የቀረህ ብለውኛል..." "ለምኑ? ፕሮሰሱ ተሳካ እንዴ?" አልኩት ሰፍ ብዬ "የጉበት እጢ ነበረህ... እና አሁን ወደ ካንሰር ተቀይሯል ያለህ ጊዜ ከ አምስት እና ስድስት ወር አይበልጥም አሉኝ።" ሰውነቴ ቅዝቅዝ ሲል ተሰማኝ። እነዛ ፊልም ላይ እንዳሉት፤ ወይ ታሪካቸው እንደሚወራላቸው ሰዎች ጠንካራ አልነበርኩም። ላስታምመው እና የመጨረሻዎቹን ወራቶች በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፍ አላደረግኩም። ወይ ማድረግ አልሞከርኩም ራሱ። የዛን ለታ ከተለያየን በኋላ፤ መጀመርያ ቤቴ ገብቼ ማሰብ ጀመርኩ 'እሱስ መሞቱ አይቀርም እኔ ግን እንዴት ነው ሀዘኑን የምችለው ከወዲሁ መለማመድ አለብኝ' አልኩና እሱ የሚያውቀውን ሲም ካርድ አውጥቼ በሌላ ቀየርኩት ከዛ በሳምንቱ ሌላ ሰፈር ሄጄ ተከራየሁ ደብዛዬን አጠፋሁበት። ያው እየፈለገኝ መሆኑ አይቀርም ብዬ ነው። ህይወት ከቀጠለ፤ ያለሱ መኖርን ከለመድኩት ከብዙ ወራት በኋላ፤ ለስራ ጉዳይ አንድ ፋይል በድሮ ስልክ ቁጥሬ ላኩልኝ እና እሱን ለማየት ሲም ካርዴን መልሼ ስከተው ከሰባት ወራት በፊት የእሱን አርባ ምናምን መልክት ከሀምሳ ሶስት ሚስድ ኮል ጋር አየሁ። አልገረመኝም ይሄንኑ ሽሽት አይደል እንዴ የጠፋሁት። 'ይሄኔ እኮ ሞቶ ይሆናል' አለኝ ጭንቅላቴ። "ነፍስህን በገነት ያኑረው" ብዬ አንሾካሸኩ። ከዛ ግን አንድ መልእክት ቀልቤን ያዘችው። የተላከው ከሌሎቹ አንፃር በቅርብ ነው። ከሶስት ሳምንት በፊት ይላል መልዕክቱም፦ "አየሽ እንዳንዴ የሰውን እውነተኛ ማንነት ለማወቅ የትንሸ ደቂቃ ትወና በቂ ነበረ። ይገርምሻል ካንሰር አልያዘኝም ። ገና ለገና ሊሞት ነው ብለሽ ግን በአንድ ቀን ትተይኛለሽ ብዬ አላሰብኩም ነበረ። ምናልባት ደንግጣ ይሆናል፤ ራሷን እስክታረጋጋ ነው እያልኩ እስክትደውዪ እስክትመጪ ስጠብቅ ነበረ። አንቺ ግን የራስወዳድነትን ጥግ አሳየሺኝ። ይሄ ሁሉ ትወና ለምን ካልሺኝ ቀለበት ገዝቼልሽ ነበረ። በኔ ቤት propose ላደርግ እኮ ነው። ከዛ ግን ምን ሹክ እንዳለኝ አላውቅም ያደረኩትን አድርጌ ማንነትሽን አየሁበት። ደግሞ ግምትሽ ትክክል ነበረ ፕሮሰሱ አልቋል ይህን ስፅፍ ሻንጣዬን እያስፈተሽኩ ነው። በይ ደህና ሁኚ" ይላል ከዛ ብቻ ብዥዥ ሲልብኝ ይታወቀኛል...ስልኬ ከእጄ ላይ ሲወድቅ... የቤቴ ጣራ ሰያፍ ሲንሻፍፍ... የቆሞኩበት ሲከዳኝ ይታወቀኛል... ብቻ ከስብርባሪ ሰከንዶች በኋላ ጉልበቴ ሲከዳኝ.... ተንሸራትቼ ስወድቅ አጠገቤ የነበረው ጠረጴዛ ማጅራቴን ሲመታኝ አንድ ሆነ....እያየሁት ደሜ ፈሰሰ። ✍አበቃ✍ https://t.me/justhoughtsss

Imstagram ላይ በወሩ መጨረሻ photo dump እያላቹ ምትላላጡ ወንድሞቻችን: ለወሊድ መከላከያ ደግሞ ክንዳችሁ ስር ሉኘ አስቀብሩ🙂

#ዛሬም_ካንቺ_ጋር_ነኝ በትዝታ ፈረስ የኋሊት ተጉዤ ፍቅርሽን ላስታዉስ ከስሩ መዝዤ ካፍንጫዬ ሲደርስ የ ፍቅርሽ ሽዉታ ጆሮዬ ሲገባ ድምጽሽ በሹክሹክታ ያ ዉብ ኣካላትሽ ከፊቴ ተስሎ ምላሴ ሲፈታ አነ ጽጌ ብሎ ኣሁን ግን ሲወራ ሰማሁኝ የለቺም ተብሎ አቺን የቀማኝን ባገኘው ምን አለ እጠይቀው ነበር ምን አንዳስጨከነው አይቻት ሳልጠግብ ቀስሜያት ሳልረካ የልቤን ላይ ፅጌ ከኔ የነጠለው እሱ ባይነግረኝም ባይመልስልኝም ዛሬም ካንቺ ጋር ነኝ ምን ጊዜም ኣልቀርም ጨረቃን ከሰማይ እመለከትና በ ጊዮርጊስ ፈረስ ሽቅብ ጋልብና የዝናቡ ሃይል ዉርጩ ቢያይልብኝ የሳጥናኤል ጭፍሮች መንገድ ላይ ቢይዙኝ ከቶ እንዳታስቢ እንዳትጨነቂ እመጣልሻለው የኔ ተናፋቂ @gitm_post ♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ #መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶

https://t.me/notcoin_bot?start=r_581063_14978408 🎁 +2.5k Notcoin as a first-time gift 🎁🎁🎁 +50k Notcoin if you have Telegram Premium @PremiumBot