ch
Feedback
ግጥም

ግጥም

前往频道在 Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

显示更多
4 810
订阅者
+1124 小时
+537
+23230
帖子存档
PAWS VERIFY ተደርጓል አዲስ TASK መቷል ገብታቹ ስሩት ያልጀመራችሁ አሁኑኑ ጀምሩ https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=YSpEVSvG
PAWS  VERIFY  ተደርጓል አዲስ  TASK  መቷል  ገብታቹ  ስሩት ያልጀመራችሁ አሁኑኑ ጀምሩ https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=YSpEVSvG

#ቀረሽ_እንደዋዛ እንደ ፡ ድመቶቹ... የትም ፡ እንደሚያድሩት እንደ ፡ ስልክ ፡ እንጨቶች፣ እንደ ፡ ዛፍ ፡ ሀረጎች እንደ ፡ ቤት ፡ ክዳኖቸ ብርድ ፡ አቆራመደኝ ~ ስጠብቅ ፡ ስጠብቅ ትመጫለሽ ፡ ብዬ... ሳይ ፡ ማዶ ፡ ሳይ ፡ ማዶ ፣ የልጅነት ፡ ዐይኔ ፡ ሟሟ ፡ እንደ ፡ በረዶ፣ ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ደቂቃ ፡ ስቆጥር፣ ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ባዝን ፡ ባንጎራጉር፣ ትወጫለሽ ፡ ብዬ ፡ በበራፍሽ ፡ ብዞር፣ ብርድ ፡ አቆራመደኝ፣ የመንገድ ፡ መብራቶች ፡ አይተው ፡ አፌዙብኝ፣ ውርጩ ፡ ቀለደብኝ፣ ጨለማው ፡ ሳቀብኝ። አለመምጣትሽን ፡ አውቀዋል ፡ ያውቃሉ፣ መስኮቶች ፡ ጨልመው፣ ቤቶች ፡ ተቆልፈው... ከተማው ፡ ሲተኛ ፡ አይተዋል ያያሉ፣ አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ

#እድሜ_ለሷ አየሁ ራቁቷን ውበቷን እሳቷን ልቤ በጣም ፈራ ድፍረቴ መከነ ከጭኖቼ መሐል ድንኳን ተደኮነ ና ትላለች ባይኗ ሚሳኤል ጡቶቿን ተፊቴ ደግና ፈራሁ ጠፋኝ አቅም ከራዲዮኔ ውጭ ጡት ጠምዝዤ አላውቅም። ከምኔው አቀፍኳት ከንፈሬስ እራሰ ቋሚው ብቻ ቀርቶ ድንኳኔ ፈረሰ ከምኔው እሳቷን አቀፍኩት እስክነድ እንዴት በዚህ ፍጥነት ተሰራሁ እንደወንድ በውበቷ ገዳም ገባሁኝ ምናኔ አጎንባሹ ቀናሁ ለቀሪ ዘመኔ ፍቅሯን በገሞራ ለውሳ ቀይጣ ወንድ አርጋ ሸኘችኝ ሰራችኝ አቅልጣ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

በፍጹም እንዳያመልጣችሁ እድሉን ተጠቀሙበት! NOTCOIN - DOGS - HAMSTER ከሶስቱ አንዱን የሰራችሁ ወይንም ሁሉንም የሰራችሁ ካላችሁ እንዲሁም በቴሌግራም እድሜ ነጥብ የሚሰጣችሁ  PAWS የተሰኘ የቴሌግራም ቦት ከሰአታት በፊት ተለቁአል!!! ይህን   Airdrop  ትኩስ ከመሆኑ የተነሳ ከ20ሺ  ሰው በላይ አልተቀላቀለም። https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=YSpEVSvG

#ቅደሙኝ_አልኳቸው ብዙ ሰው በዋይታ ጥቂቱ በእልልታ ዓለምን ተጋርተው ሳቅና እንባን አዝለው እየተገፋፉ መንገዱ ጠቧቸው ሁሉንም በግዜ ሞቱ ሲጠራቸው ተከትለን ሲሉኝ ቅደሙኝ አልኳቸው እኔ ከሞት ተራ የምቀር መስሏቸው።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#መዋሸክ ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ብልሹ መዋሸት ብቻ ነው ትልቁም ትንሹ       ባገራችን ባህል በአገራችን ልምድ       አስነዋሪ ነበር መዋሸክ መልመድ ግን የዘመኑ ሰው ልማድ ያደረገው ትንሹም ትልቁም ሰውን ማማትን ነው       ለዚች ላጭር ዕድሜ መቶ ለማትሞላ       እንዴት ሰው ይኖራል ሰውን እያጣላ? የመዋሽክና የሐሜት ዘይቤ አያስፈልገኝም ይራቅ ካጠገቤ      ብሎ የሚል ወጣት ወይም አረጋዊ      ምነዋ በኖረ በሐቅ ኢትዮጵያዊ @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ደራሲ ታደለ ብጡል

#ዝምታም_ይጮኻል የምላስ ጋጋታ ጀሮን ባይጋርደው ይደመጥ ነበረ ዝምታም ቃል አለው በህሊና ከሳሽ በልብ ዳኝነት የዝምታ ችሎት የተሰየመ እለት ሁሉም ተናጋሪ ጸጥ! ቢል ላንድ አፍታ እመኑኝ ይጮሃል ድምጽ አለው ዝምታ የተፈጥሮ ችሎት በልብ ሚዛን ቢረግጥ ዓለም ለሴኮንዶች መናገርን ቢል ጸጥ ያኔ ይደመጣል ቃል አለው ዝምታ ገለል ሲልለት የምላስ ውካታ ጆሮ ባይጋረድ በቃላት ጋጋታ መጮኽ በጀመረ የስንቱ ዝምታ የሰው ልጅ ቢኖረው ስድስተኛ ህዋስ ይሰማው ነበረ ዝምታችን ሲፈስ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#አልቻልኩም (አብሮ መሰደድ) የልቤ ሰመመን የፍቅሬ ትዝታ የዓይኖቼ ብሌን የሕይወቴ አለኝታ       አኔን ከጠላሽኝ ከናቅሽ ፍቅሬን      ከመሔዴ በፊት ስሚማ እሮሮዬን ልዝብ አንደበትሽ ታጋሽ ተፈጥሮሽ አስተዋይ አእምሮሽ ንጹሕ ልቦናሽ       ተባብሮ ከዓይኖችሽ ከውበትሽ ጋር       ልቤን ማርኮ ወስዶ አሰረው በፍቅር ኮኮብ ዓይኖችሽን ጉብል ጉንጮችሽን የቀጭኔ ጭራ መሳይ ጸጉሮችሽን        ለጋ ከንፈርሽን ወለላ እንደማር        ንብረቴ ለማድረግ ምኞቴ ነበር አይቻልም ካልሽኝ ማቀፍ ሽንጥሽን እኔ አልፈቅድም ካልሽኝ መሳም ከንፈርሽን        ፍቅሬን መግለጥ ካልቻልኩ የልቤን መንገር        በሰላም እናብቃው መጣላት ይቅር እንሰነባበት ነውና መጓዜ ጻፊልኝ ቢቻልሽ ትዝ ባልኩሽ ጊዜ        ስለተለበለብኩ በፍቅርሽ ንዳድ        አልቻልኩም ለመኖር አብሮ መሰደድ         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ደራሲ ታደለ ብጡል

ቤተሰብ ይኸን Airdrop ትኩረት ሰጥታችሁ ስሩት ትጠቀማላችሁ እንጅ አትጎዱም

ተቃቅፈን ስንሄድ ለሚያገላግሉ ጉንጭሽን ስስምሽ ነከሳት ለሚሉ ከፍቅራችን ይልቅ ጸብ ለናፈቃቸው ከራስሽ ተጣልተሽ... የወሬ ማድመቂያ ሰበብ አትሁኛቸው @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ገጣሚ አቤል ሽመልስ

#ምሥጢር ምሥጢር ነው ያልከውን ለሌላ ሰው መንገር መሆኑን ተረዳ በገዛጅ መታሰር          ግን ምሥጢር ለባዕድ እስካልተነገረ           ምሥጢርህ ምሥጢር ነው ባንተው ከታሠረ ምሥጢርህን ሌላ ሰው ካየና ከሰማው ያባከንከው ምሥጢር ላንተ ዘብጥያህ ነው          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ   ✍  ደሪሲ ታደለ ብጡል

sticker.webp0.16 KB

#መራራቅ ቅዠታም አዳሩን ጨፍጋጋ ውሎዉን ዝብርቅርቅ ተስፋውን ደረቅ ትዝታውን... በይሉኝታ ኮፈን እየጠቀለለ ከጥርሱ ሲጥለው ተቀባይ ይሻማል ሳቅ እየመሰለው። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ገጣሚ በረከት በላይነህ

አንድ ⭐️ እንኳን የሚሰጠኝ ሰው ጠፋ ቆይ ማልቀስ ይሻላል?

#ዋ! ዓይኔ ወደደሽ ስልሽ አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት ምኞትሽ ሰመረ አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው እንደዘበት። ግን መች ተውሻለው በልቤ ብሩህ ዓይን ዛሬም አይሻለው። ደሞ እንደዚህ ስልሽ አትወጅኝምና ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሻለሁ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ገጣሚ በረከት በላይነህ

በጣም power ያለው በ Binance የሚደገፍ Airdrop ነው ሳያልፋችሁ ስሩት Listing Very soon https://t.me/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=JqFUJc

#ነጠብጣብ_ሀሳቦች ሰማይ ከሚመክን ይፀንስ መከራ ያርግፍ" ያርግፍ" ያርግፍ" መዓት እያፈራ የሣት ዛፍ ባለበት ሰደድ ላያስፈራ። ከሐምሌት ጋር ሞቷል ፣ የማመንታት ዓለም ከሆኑ በኋላ፣ አለመሆን የለም፤ ሸክም ፀጋ ሆኗል ፀጋህን አትግፋ በጠባብ ዓለም ውስጥ ትከሻህን አስፋ። አንድ ህልም እንደ ጠጅ፣ እየደጋገሙ ንግር፣ ትንቢት ሳይሆን ታሪክ እያለሙ ተኝቶ መነሳት አቤት ሲያቅለሸልሽ ጌታ ሆይ አትንሳት ነፍሴን እንቆቅልሽ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም

#አንቺ_ምን_አለብሽ ባልጠበቀ ስንኝ በላላ ቋጠሮ ውበትሽን ለመግለጽ ስጭር እንደ ዶሮ ቤት መታ ቤት ደፋ እያልኩኝ ለእራሴ ስደክም ስባክን ስትጨነቅ ነፍሴ አንቺ ምን አለብሽ ተኝተሽ አልሚ ክረምቱን በሙቀት ሳይበርድሽ ክረሚ ብዙ አድናቂ ያለሽ ሲጭር የሚያነጋ ውበትሽን አወዳሽ የገጣሚ መንጋ ቃላትን አዋቅሮ ይጭራል ይጽፋል ውበትሽን ለመግለጽ ስንኝ ይቋጥራል አንቺ ተኝተሻል አይገድሽ አይሞቅሽ ይብላኝ ለማይተኛው ቆሞ ለሚያልምሽ በክረምቱ ቆፈን ብርድ እያነዘረው ሲያስብሽ አዳሪው እልፍ አላፍ ጫሪ ነው          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ታማሁኝ_በፍቅር የዘንድሮማ ሰው ማውራት ያውቅበታል ልቡን ወስደዋለች ብሎ ያዋሽካል     ሐሜተኞች አሙኝ ደካማ ነው ብለው     መልካም ልጅ ባፈቅር ድካሜ እምን ላይ ነው ኃጢአት አደለም ወይ ወንጀል ማፍቀር እስቲ ተውኝ ሰዎች በሰላም ልኑር      ለኑሮ መዋተት መውጣትና መውረድ      መቺ አነሰኝና በፍቅር ልዋረድ ይኸ ሀሜታቸው እንዳይሆን እውነት ተይ አታንገላችኝ በፍቅርሽ አልሙት          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ   ✍  ደሪሲ ታደለ ብጡል

#በምናልባት_ኑሮ   አይቦዝን አንቀልባው    አይሞላም ጉድጓዱ ሺሆች ሞተው ቢያድሩ     ሺሆች ተወለዱ     ይመሻል ይነጋል     ያው እንደልማዱ፤ መሬት ባህር ሆኖ ፥ ድሃን ሰለቀጠው ትልልቁ ቪላ ፥ ትንሹን ቤት ዋጠው በመስታወት ጫካ ፥ በጡብ በብረት ደን አየሁ ባደባባይ ፥ ሰው በሰው ሲታደን፤    ማን በገላገለኝ ፥ የጄን ሰዓት ሰብሮ    በምናልባት አገር ፥ በምናልባት ኑሮ የመጣው ይምጣ እንጅ ፥ ማን ያቅዳል ደፍሮ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በእውቀቱ ስዩም