ch
Feedback
ግጥም

ግጥም

前往频道在 Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

显示更多
4 810
订阅者
+1124 小时
+537
+23230
帖子存档
#በሰው_ልብ_ከተማ ስቆ ማለፍ እንጅ ዘንድሮን ለከርሞ በፈገግታ ዜማ ብሶትን አስታሞ የሌለንን ትተን ባለን ካልተደሰትን ጊዜውስ ሞክሯል አዙሮ ሊጥለን የሳቃችን ሚዜ ሀዘናችን ሆኖ በጥርሳችን ጋቢ ከውስጥ ተከድኖ ሳቃችን ሙሽራ ሐዘናችን ሚዜ አብረው እየበሉ ሳቅና ትካዜ ጥርሳችን ቢስቅም ሐዘንን ሸሽጎ ጥርስ እየደመቀ መከራን ሚዜ አርጎ ደስታና ሐዘን አብረው እቁብ ጣሉ በሰው ልብ ድንኳን ድግስ እየበሉ በስቃይ ከተማ ድርሻቸውን ይዘው የፈረቃ ስልጣን ስፍራቸውን ወስደው ይፈራረቃሉ በሰው ልብ አዳራሽ ችሎትን ዘርግተው በሌለበት ከሳሽ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

///በሰው ልብ ከተማ/// ስቆ ማለፍ እንጅ ዘንድሮን ለከርሞ በፈገግታ ዜማ ብሶትን አስታሞ የሌለንን ትተን ባለን ካልተደሰትን ጊዜውስ ሞክሯል አዙሮ ሊጥለን የሳቃችን ሚዜ ሀዘናችን ሆኖ በጥርሳችን ጋቢ ከውስጥ ተከድኖ ሳቃችን ሙሽራ ሐዘናችን ሚዜ አብረው እየበሉ ሳቅና ትካዜ ጥርሳችን ቢስቅም ሐዘንን ሸሽጎ ጥርስ እየደመቀ መከራን ሚዜ አርጎ ደስታና ሐዘን አብረው እቁብ ጣሉ በሰው ልብ ድንኳን ድግስ እየበሉ በስቃይ ከተማ ድርሻቸውን ይዘው የፈረቃ ስልጣን ስፍራቸውን ወስደው ይፈራረቃሉ በሰው ልብ አዳራሽ ችሎትን ዘርግተው በሌለበት ከሳሽ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ለሰውነቱ_ክብር ሰው ኑሮን ለመኖር ሌት ተቀን መዋተት መውጣት መውረድና እድሜ ሙሉ መልፋት ፍዳ ነው ፍዳ ነው የሰው ልጆች ሕይወት        ሲያገኙ መደሰት ሲያጡ መሸማቀቅ        ተለምዶ መሆኑ በገሀድ ሲታወቅ        ታድያ ዘመናይ ሰው ለምን ይንደላቀቅ? ይኸን ውጣ ውረድ የኑሮ ሚዛን ማሰብ መመራመር መረዳት ሐቁን ማስተካከል ያሻል በማመጣጠን        ይኸ የዓለም ጣጣ እንዲስተካከል        ምሁር መኃይሙ ሳይነጣጠል        ለሰውነቱ ክብር ሊሰጥ ይገባል          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ደራሲ ታደለ ብጡል

#ውሻሽን_እሰሪው አንችን ስመለከት እንቅፋት መትቶኛል መምጫሽን ስጠብቅ ፀሐይ አጥቁሮኛል ባጥር ላይሽ ብዬም ውሻችሁ ነክሶኛል           ያውም ክፉ ውሻ... መምጫው ሳይታወቅ አድብቶ ሚያጠቃ ገዳይ መሬት ጥሎ የሚለውስ ጭቃ እችን ስንጥር እግሬን ከአፉ አስገብቶ አንከባሎኝ ሄዷል እመሬት ጎትቶ       ውሻሽን እሰሪው... ይህን ሀይለኝነት ከማንስ ተማረ አሳዳጊው አንቺ አትንኩኝ የምትይ አመል የነፈገሽ ለሰው ማትመቺ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ       ✍ አቤል ሽመልስ

#ዝኑፋ_ወቀሳ         ይለኛል ታዛቢ... "በእኛ ተረማምዶ - ስኬቱን ሸመተ፤ ሲመቸው ፣ ሲደላው - ትቶን ሰነበተ!"          ይለኛል ታዛቢ... "አቅፈን አሳድገን - ከሰው መሐል ለየን፤ አለፈለትና - ዞር ብሎም አያዬን!"          እኔ ግን እላለሁ...        "ስህተት የለብኝም፤ ያለፍኩበት ሁሉ አላሻገረኝም፤ የረገጥኩት ሁሉ አልተሸከመኝም!"          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በረከት በላይነህ

ለግጥም አፍቃሪዎች 😍 ፧ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን  ቻናሉን join ብለው እንዲቀላቀሉ እጋብዛለሁ። በብዙ ይዝናኑበታል ያተርፉበታልም። 😍 join/ጆይን /👇👇👇 @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm

#በእንባ_የራሰ_ፍትፍት ቀበሌ ሂድና ፥ ድህነት አስመስክር ይላል አሉ ሃብታም ፥ መፅውቶ ሲሰክር እማኝ ጥራ ይላል ፤ ቀበሌ በተራው እማኙ ሲመጣ ፤ ይንዛዛል ወረፋው            አሹቅ ከጨበጠ... ከነዳይ መዳፋ ላይ ፥ ሹም እየዘገነ "ድሃ!" መባል እንኳን ፥ ገንዘብ ላለው ሆነ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በርናባስ ከበደ

#ጀሮ_ባጣ_ሀገር አድማጭ በሌለበት በነጠፈ ጀሮ በስንኝ ቋጠሮ የሚያሰሙ እሮሮ ዜማው ቢሽሞነሞን ቃላቱ ተመርጦ ክራሩ ቢሰደር በዋሽንት አጊጦ አድማጭ በሌለበት ብሶት ቢደረደር ጀሮ ዋጋ ላይሰጥ ምላስ ቢቀባጥር ቅኔ ምን ሊፈይድ ዜማስ ምን አባቱ!!! ሰሚ በሌለው ቤት መባከን ነው ከንቱ ከበሮ ቢደለቅ መሰንቆ ቢያነባ ዋሽንት እህ እህ ቢል የስንኝ ቋጠሮ ከዜማው ቃል ቢጥል ሁሉም ተዋህደው ተስማምተው ቢገጥሙ ጀሮ ባጣ ሀገር ትርፉ ነው ድካሙ ❤         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ፖለቲካ_አልባ_ስንኝ ዳሌሽ ያንቺ ነው? ንገሪኝ በሞቴ ሰው ሰራሽ ከሆነ እንዳትገቢ ቤቴ ከደረትሽ ገዝፈው የተወደሩቱ ከጦር በላይ ሾለው የተቀሰሩቱ ሁለቱ መንትዮች እውነት ያንቺ ናቸው? ንገሪኝ ሳትፈሪ ዘመኑ ፎርጅድ ነው። ከዐይኖችሽ ሽፋሽፍት የተንጨባረሩት ከከንፈርሽ ዳርዳር ደምቀው የሚታዩት ጸጉርሽን አስንቀው የሚንዘናፈሉት ውዴ የማናቸው? እውነቱን እናውራ ከተፈጥሮ በላይ ምን አለ ሚያኮራ? አትመሪ አልልም መድመቅሽን አልጠላም የማን እንደሆኑ ማወቅ ግን አይከፋም። ተፈጥሮን አስንቀው ባንቺ የነገሡ ማንነት ያስናቁ ማን ናቸው? እነርሱ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

ለግጥም አፍቃሪዎች🥰🥰 ፧ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቻናሉን join ብለው እንዲቀላቀሉ እጋብዛለሁ። በብዙ ይዝናኑበታል ያተርፉበታልም። join👇👇👇 @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm

#ተራ_ነሽ_ለልቤ እንደ ዛሬው ሳትሆኝ ክፋት ሳትማሪ አውቄያለሁ ብለሽ ዘርንም ሳትቆጥሪ በንጹሕ ልቦናሽ ሰው በመሆን ቅኔ እወድሽ ነበረ አልወደሽም እኔ። ስልጣኔ መስሎሽ እርቃን እውቀት ይዘሽ ልብሽ ሲደነድን ክብርሽም ሲሟሽሽ ጠላሁሽ ከልቤ በርካሽ ጸባይሽ ተራ ነሽ ለልቤ የልቤን ልንገርሽ ያኔ! ግን በእውነቱ ልብሽ የከበረ ሰው የማክበር ዜማሽ ሰውነት ነበረ አንደበትሽ ማርማር ለእግዚአብሔር ያደረ ያ " ሁሉ ቀረና ዘምኛለሁ ብለሽ ቅሉም ተሰበረ አሁን አልወድሽም የለሽም ከሆዴ ስልጣኔሽ ሁሉ የቂል ሆኗል ውዴ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ባልተቋጨ_ፍቅር ያልረሳውን እውነት የረሳ ለመምሰል ስንቱ ይታገላል ትዝታን ለማቅለል በልቡ ማህደር ፍቅርን ተሸክሞ በውሸት ፈገግታ እራሱን አስታሞ ዛሬን አስመስሎ ለትላንት የሚኖር ብዙ አለ ታማሚ ባልተቋጨ ፍቅር በልቡ እያነባ በጥርሱ እየሳቀ ደስተኛ መስሎ ግን የተጨነቀ ምዕራፍ ባጣ ታሪክ እልባት በሌለው በትላንት ትዝታ ዛሬን የሚኖረው በውሸት ፈገግታ የሚወዛወዘው ስንት አለ ባለበት እሱን ቤት ይቁጠረው።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#እባካችሁ_ተውኝ!!! እንኳን የሰው ሀጢአት ደርቤ ሊቀለኝ የእራሴንም አልቻልኩ እያንገዳገደኝ የእኔ ነውር በዝቶ ከብዶኝ እያያችሁ የሌላውን ሸክም ደርብ ማለታችሁ በየትኛው አቅሜ ችዬ ልሸከመው ሁሉም የስራውን በግሉ ይቻለው ሰው የእራሱን በደል እያለባበሰ የሌላውን ሀጢአት ቆሞ እየቀደሰ ሲበርደው ይኖራል ፀጋውን ተገፎ በሰው ጉዳይ ገብቶ እያደር ወፍፎ እባካችሁ ተውኝ የእኔም አቅቶኛል ከአቅሜ በላይ በዝቶ ዘንድሮስ ከብዶኛል          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ተራርቆ_ከእውነት ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ቡራኬ_ነው_እጇ #ገጣሚ_ኤልያስ_ሽታሁን የገጣሚ ኤልያስ ሽታኹን እና የሌሎች እውቅ ገጣሚያን ግጥሞች በፅሑፍ ፣ በ Vedio እና በ Audio የሚቀርብበት ምርጥ የቴሌግራም ቻናል❤❤❤❤❤❤ ቻናሉን ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇👇👇 💚💛❤💤💤💚❤💛 Share  ለወዳጆ ያጋሩ https://t.me/eliyasshitahun https://t.me/eliyasshitahun

#ልብና_መስታወት አንዳችም ሳይጨምር ፥ አንዳችም ሳይቀንስ፤ በተሰጠው መጠን ለሁሉም ሲመልስ፤     ከትዝታ ገጹ ምንም ሳይጽፍበት፤ መስታወት ብቻ ነው ኑሮን ያወቀበት።         ልብ ግን አቃተው! በመጣው ሲደሰት በሄደው ሲከፋ፤ ውለታ ሲደምር ቅያሜ ሲያጠፋ፤ ከሚስጥር ሆድ እቃው ነገር ሲያመሰኳ፤ ቀለም አልባ ሆነ- ይቅርታችን መልኳ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በረከት በላይነህ

Are you single

#ልቤ_ክፍት_ይሰንብት ከራሚ ጠፋ እንጅ ከልባችን ጓዳ ገብቶ ወጭስ አለ የማያድር እንግዳ ሳይጠራ ገብቶ ሳይሸኝ ይሄዳል በዚህ ዘመን ከልብ ማን ይሰነብታል ገብተው እየወጡ የልቤ በር ሰፍቷል እያደር ማገሩ የጠበቀው ላልቷል! እኔን የናፈቀኝ ከራሚ ሰው ነበር ቃሉ የሚፀና የሚያድር ለፍቅር ገብታችሁ አትውጡ አይባል ሰው በግድ ሳይጋበዝ መጥቶ ሳይሸኙት ለሚሄድ ለካስ ይከብድ ነበር ከልብ ሰው ማልመድ ከማይዘልቅ ተጓዥ ጋር ከንቱ ነው መዋደድ ድግስ አትደግሱ አብዝታችሁ ለሰው ቁርስ በልቶ ምሳ ውሎ ለማይደግመው አይዘጋ በሩ ልቤስ ክፍት ይሰንብት አንድ ቀን ከመጣ ከራሚ ሰው ድንገት ይመላለሱበት አይዘጋም በሩ ቢወጡም ቸኩለው ቢጓዙ ሳያድሩ ድንገት እንዳያጣኝ ከራሚ ሲመጣ ልቤ ክፍት ክረም ሁሉም ገብቶ ይውጣ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

" #ይገለባበጣል " ጠላቴ አትደሰት ለእኔ ተራ መውደቅ መነሳቴ አይቀርም ነግ ለኔ በል ይልቅ ይገለባበጣል ጊዜ ቋሚ አይደለም ሳይወድቅ የኖረ ሰው እስከዛሬ የለም የወደቀው ቆሞ የቆመው ይወድቃል ይልቅ መደጋገፍ ለሁሉም ይበጃል!!!          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#የኔነሽ የምጠረጥረው ፥ የማልጠረጥረው ቄሱ መነኮሱ ፥ ወታደር ደብተራው            ያም የኔነሽ ሲላት፤            ያም የኔነሽ ሲላት፤   ለበለበኝ ፍቅር አቃጠለኝ ቅናት ወይ ጠንካራ ክንዴ ፥ ጉልበቴ አያስቀራት!    እንዴት የብቻዬ ፥ የግሌ ላድርጋት? ሰው በጠራት ቁጥር ፥ ባልነቴ ሟሟ የሰማኒያ ሚስቴ ፥ የኔነሽ ነው ስሟ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ደራሲ ይስማዕክ ወርቁ