ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)

️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)

前往频道在 Telegram

እንኳን ወደ ፈለገ ጥበብ ሚዲያ የ 🅿🅷🅾🆃🅾🅶🆁🅰🅿🅷 ቻናላችን በደህና መጣቹ። ✔️በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤትም ይሁን በተለያዩ ደብራት የሚነሱ ፎቶግራፎችን በዚህ የፈለገ ጥበብ የፎቶ ማህደር ላይ ያኙታል። መልካም ጊዜ 📸📷📹💽

显示更多
731
订阅者
无数据24 小时
-67 天
-630 天
帖子存档
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የአድአ ወረዳ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በስሩ በሚገኙ 18 አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች አዲሱን የስርአተ ትምህርት የማስጀመሪያ
+9
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምስራቅ   ሸዋ ሀገረ ስብከት የአድአ ወረዳ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በስሩ በሚገኙ 18 አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች አዲሱን የስርአተ ትምህርት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናወነ። የፈለገ ጥበብ ሚዲያ (ፈ.ጥ.ሚ) ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት ተዘጋጅቶ ለሁሉም አህጉረ ስብከት በተሰራጨው ወጥ የሆነ ከ1ኛ- 12ኛ ክፍል ስርአተ ትምህርት የማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ መ/ሀዲስ ቆሞስ አባ ሀ/ገብርኤል የም/ሸዋ ሀገረስብከት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀላፊ መጋቢ ጥበብ መ/ር እውነቱ ጥላሁን የአድአ ወረዳ ቤ/ክ ዋና ፀሀፊ ዲ/ን ፍስሐ ታደሰ የሀገረስብከቱ አንድነት ም/ሰብሳቢ እና የወረዳው አንድነት ተቀዳሚ ም/ሰብሳቢ ወጣት ከተማ ደረጀ የሀገረስብከቱ አንድነት ዋና ፀሀፊ የወረዳው አንድነት የስራ አመራር ኮመቴ አባላት በተገኙበት በተመረጡ አጥቢያዎች የተከናወነ ሲሆን በሀገረስብከቱ እና በወረዳው አመራሮች የስርአተ ትምህርቱ እና የፈተናው አላማ ለተማሪዎች ግንዛቤ እንዲሁም አባታዊ መመሪያ እና የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል። በዛሬ መርሐግብር በከተማ 12 እና በገጠር 6 በድምሩ በ18 አጥቢያ ለ4ኛ እና ለ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የተሰጠ ሲሆን ፈተናው 1951 ተማሪዎች ተፈትነዋል ። ከነዚህም ውስጥ 502 ተፈታኞች በአፋን ኦሮሞ የተፈተኑ ናቸው። የወረዳው ሰ/ት/ቤቶች አንድነት እንደገለፀው ከሆነ በቀጣይነትም ህዳር 02/03/16 ዓ.ም በገጠር ሌሎች 8 አጥቢያዎችን ለማስጀመር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህ መርሐግብር መሰካት የወረዳው አንድነት ት/ት ክፍል የጎላ ድርሻ አንደነበረው ተገልጿል። ደብረዘይት/ቢሾፍቱ