ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

前往频道在 Telegram
924
订阅者
-124 小时
-27 天
+730 天
帖子存档
ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በዘንድሮ የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራዎች ቁጥራቸዉ ከ805 ሺህ 268 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማስጠቀም ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዞን ዓቀፍ የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ እወጃ መርሃ-ግብር ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው። በመርሃ-ግብሩም የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪ አካል ጉዳተኛ ለሆኑት ወ/ሮ ሃዋ ረዲ ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚፈጅ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በይፋ ተጀምሯል። በዚህ ወቅትም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት እያከናወናቸው ባሉ ሠው ተኮር ስራዎች በሃገር ዓቀፍ እና በወረዳ ደረጃ በርካታ ዜጎችን ማስጠቀም እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት እና መልካም ፈቃድ በህብረተሰቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፍ ነፃ አገልግሎት የሚያበረክቱበት ተግባር ሲሆን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እድሜና ፆታ ሳይገድበው ሰብዓዊነት መርህን ብቻ መሰረት በማድረግ የሚሰጠን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በዘንድሮ በጀት አመት በዞኑ 395 ሺህ 183 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በ14 የስምሪት መስኮች በማሰማራት፣ 805 ሺህ 268 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እና 386 ሚሊዮን 267 ሺህ 475 ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት ግብ መያዙን ያወሱት አቶ ሙራድ ረሻድ በአጠቃላይ በዞን ደረጃ በዘንድሮው የበጎ አድራጎት ተግባር ውስጥ መጠለያ ቤት ለሌላቸው አቅመ-ደካማ ዜጎች ከ295 በላይ አዲስ ቤት ለመገንባት መታቀዱን ጠቅሰው የዚህ አንድ አካል የሆነው የወይዘሮ ሀዋ ረዲ አዲስ መኖሪያ ቤት ግንባታ በዋናነት ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸው ለቤት ግንባታው ወጪ የጉራጌ ዞን መንግስት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የሚሸፈን ሲሆን 150 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት የወረዳው መንግስት በነፃ ማቅረቡን አስታውቀዋል። የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሠን እንደገለፁት በጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የጀመሩት የበጎ አድራጎት ተግባር አሁን ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና መተሳሰብ ባህል ማጎልበት ያስቻለ ስለመሆኑ ጠቁመው በበጎ ተግባራት አማካኝነትም በዞናችን በርካታ የማህበራዊ ችግር ያለባቸውንና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ማስጠቀም እንደተቻለ በማንሳት በዞን ዓቀፍም ሆነ በወረዳው የተያዙ የበጎ ስራዎች ተግባራት ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የሚደረገውን ርብርብ ወጣቶችና ህብረተሰቡ ማገዝ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በዕለቱ ለአቅመ ደካማና አካል ጉዳተኛ የሆኑት ወ/ሮ ሀዋ ረዲ የአዲስ መኖሪያ ቤት ማስጀመር ስራ እና በመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናውኗል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም የ2017/18 በጀት አመት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የመክፈቻ መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሀል አምባ ከተማ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመረሃ ግብሩ ላይ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሠን፣የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሠል ሀሠን፣የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ፣ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር፣የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሸሃቡ፣የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሴ በቀለ እና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዲሁም አስተባባሪ አካላት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል። በመረሃ ግብር ላይ የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪ አካል ጉዳተኛ ለሆኑት ወ/ሮ ሃዋ ረዲ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመር እና የችግኝ ተከላ ተካሄዷል። ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን!!!

ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ አፅንኦት ሠጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀው የወረዳው ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት የ4ኛ ሩብ ዓመት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው። የፅህፈት ቤቱ ልማት ዕቅድ ባለሙያ ወ/ሮ አበራሽ ታደሠ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በበጀት ዓመቱ ለሴክተሩ ከተያዘለት 8 ሚሊዮን 946 ሺህ ብር በጀት የተያዘለት ቢሆንም በአንፃሩ 10 ሚሊዮን 716 ሺህ 764 ብር ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ ስራ በማዋል አፈፃፀሙን ከዕቅድ በላይ ማሳካት ስለመቻሉ ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል። የውይይት መድረኩ መካሄድ ተቋሙ ከዚህ ቀደም በተሻለ ደረጃ የስራ ሁነቶችን መፍጠር የሚያስችለውን ግብዓትና አቅም ማጎልበት የሚያስችለው በመሆኑ መሰል መድረኮች መጎልበት እንዳለባቸው፣ ከመሠረተ-ልማት ዝርጋታ ጋር በተያያዘ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማጣት ችግር እየፈጠረ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ የመብራትና ጄኔሬተር ነዳጅ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ መሆኑን፣ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አቅርቦት አፈፃፀም የተሻለ ቢሆንም በዘርፉ ተጨማሪ ስራ መከናወን እንደሚገባው የተገለፀ ሲሆን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነቱን በበለጠ ሁኔታ ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተሳታፊዎች አንስተዋል። የወረዳው ውሃ ማዕድንና ኢንርጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጠይብ አስፍር ከተሳታፊዎች በኩል ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት መንግስት የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የመንግስት አቅምን፣ የባለሃብቱን እና የዜጎችን አቅም በመጠቀም በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማግኘት ስለመቻሉ አብራርተዋል። አክለውም ከውይይት መድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን አስመልክቶ በቀጣይ ዕቅድ በማካተት የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሠራ አስታዉቀዋል። አቶ ጠይብ አስፍር አያይዘውም የህዝቡን የውሃ ተደራሽነት ሽፋን አሁን ካለበት በበለጠ ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ የተጀመረዉ ርብርብ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ በመግለፅ ከማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የአየር ብክነትን መቀነስ ብሎም መቆጣጠር እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፍጆታን መቀነስ ዓላማው በመሆኑ የስራውን ሂደት አጠናክረዉው እንደሚያስቀጥሉት ገልፀዋል።  በመጨረሻም በስራ ዘመኑ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባለሙያዎች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው። ከሀምሌ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ይገኛል። በዕለቱ የፓርቲ ሰነዶችና መመሪያዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው። የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። #prosperity