ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
925
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም የ2017/18 በጀት አመት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የመክፈቻ መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሀል አምባ ከተማ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመረሃ ግብሩ ላይ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሠን፣የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሠል ሀሠን፣የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ፣ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር፣የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሸሃቡ፣የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሴ በቀለ እና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዲሁም አስተባባሪ አካላት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል። በመረሃ ግብር ላይ የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪ አካል ጉዳተኛ ለሆኑት ወ/ሮ ሃዋ ረዲ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመር እና የችግኝ ተከላ ተካሄዷል። ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን!!!

ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ አፅንኦት ሠጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀው የወረዳው ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት የ4ኛ ሩብ ዓመት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው። የፅህፈት ቤቱ ልማት ዕቅድ ባለሙያ ወ/ሮ አበራሽ ታደሠ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በበጀት ዓመቱ ለሴክተሩ ከተያዘለት 8 ሚሊዮን 946 ሺህ ብር በጀት የተያዘለት ቢሆንም በአንፃሩ 10 ሚሊዮን 716 ሺህ 764 ብር ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ ስራ በማዋል አፈፃፀሙን ከዕቅድ በላይ ማሳካት ስለመቻሉ ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል። የውይይት መድረኩ መካሄድ ተቋሙ ከዚህ ቀደም በተሻለ ደረጃ የስራ ሁነቶችን መፍጠር የሚያስችለውን ግብዓትና አቅም ማጎልበት የሚያስችለው በመሆኑ መሰል መድረኮች መጎልበት እንዳለባቸው፣ ከመሠረተ-ልማት ዝርጋታ ጋር በተያያዘ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማጣት ችግር እየፈጠረ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ የመብራትና ጄኔሬተር ነዳጅ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ መሆኑን፣ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አቅርቦት አፈፃፀም የተሻለ ቢሆንም በዘርፉ ተጨማሪ ስራ መከናወን እንደሚገባው የተገለፀ ሲሆን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነቱን በበለጠ ሁኔታ ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተሳታፊዎች አንስተዋል። የወረዳው ውሃ ማዕድንና ኢንርጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጠይብ አስፍር ከተሳታፊዎች በኩል ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት መንግስት የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የመንግስት አቅምን፣ የባለሃብቱን እና የዜጎችን አቅም በመጠቀም በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማግኘት ስለመቻሉ አብራርተዋል። አክለውም ከውይይት መድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን አስመልክቶ በቀጣይ ዕቅድ በማካተት የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሠራ አስታዉቀዋል። አቶ ጠይብ አስፍር አያይዘውም የህዝቡን የውሃ ተደራሽነት ሽፋን አሁን ካለበት በበለጠ ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ የተጀመረዉ ርብርብ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ በመግለፅ ከማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የአየር ብክነትን መቀነስ ብሎም መቆጣጠር እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፍጆታን መቀነስ ዓላማው በመሆኑ የስራውን ሂደት አጠናክረዉው እንደሚያስቀጥሉት ገልፀዋል።  በመጨረሻም በስራ ዘመኑ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባለሙያዎች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው። ከሀምሌ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ይገኛል። በዕለቱ የፓርቲ ሰነዶችና መመሪያዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው። የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። #prosperity

ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም ወረዳዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ችግኝ ተከላ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመረሀ ግብሩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳን ጨምሮ ፣የወረዳው አስተባባሪ አካላትና አመራሮች እንዲሁም የከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ነዋሪዎች በስፍራው ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል። የገ/ጉ/ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ችግኝ መትከል የአካባቢና የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ፣ ብክለትን ለመቀነስና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል እንዲሁም ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ጠቀሜታ ለምግብነት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ ውብና ፅዱ የሆነ ወረዳና ሀገር ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቅሠው የአካባቢው ማህበረሠብ ችግኞችን በመንከባከብ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በገ/ጉ/ወለኔ ወረዳ ምክትል አስተዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ወረዳዊ የችግ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ መጀመሩን አንስተው የተጎዱ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ ለማድረግ፣ አካባቢን ለማስዋብና የተፈጥሮ ሚዛንን ለመጠበቅ ችግኝ መትከል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ከድር መርጋ አክለውም በዘንድሮ በጀት አመት ከ7.4 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው በዛሬው እለት በከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ልዩ ስሙ እንደብዮ ከ53 ሺህ በላይ ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ልዩ ስሙ እንደቢዮ ላይ በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር የወረዳው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ አርሶአደሮች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ታዳጊዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተክለዋል።

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም 👉🏼 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ የ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፍቃድ ሪፖርትና የ2017 ዓ.ም የክርምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ዕቅድ ገመገመ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼ጽዱ ቀበሌ ለመፍጠር የተጀመረው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ አሸነፈ በሞናኮ በተደረገው የወንዶች 5 ሺ ሜትር ዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአንደኝነት አጠናቋል። 👉🏼 በጉራጌ ዞንገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብ/ፓ/ፅ/ቤት የፓርቲ ተቋም ግንባታ ለላቀ እምርታ! በሚል መሪ ሀሳብ ለወረዳ ጠቅላላ አመራር አቅም ግንባታ ስልጠና ተሠጠ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼ሠራተኞች ይመዘናሉ እንጂ ከሥራ አይቀነሱም፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼አቶ ጀማል አሕመድ በደቡብ ካሎሪና ተወካዮች ም/ቤት እውቅና ተሰጣቸው ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘሬ ቀበሌ በበልግ የለማ የድንች ማሳ በምስል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች እና ለቀበሌ ሊቀ- መናብርቶች በማህበራዊ ፍርድ ቤት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን የወረዳው ፍርድ ቤት ገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም አመታዊ ግብር መክፈያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎ 👉🏼 የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉባዔ ተሳትፎ በአጠቃላይ ውጤታማ ነበር - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼 በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በኦቼና አንቀዲን ቀበሌ በበልግ የለማ የድንች ማሳ በምስል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋቦን ቀበሌ በከተማ የሚገኙ ተወላጆች ከአካባቢው ማህበረሰብ እና  ከወረዳ አመራሮች ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ዛሬ ማከናወናቸው ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ኦረንቴሽን እና ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሽኝት መርሃ-ግብር ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨