1 326
订阅者
+224 小时
+67 天
+11030 天
帖子存档
በድሬደዋ አስተዳደር ከተለያዩ ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው አካላት የተወጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦም ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ የቀረበው ሪፖርት አቀራረቡንና የተከናወኑ ስራዎችን አድንቀው በቀጣይ ሊተኮርባቸውና ሊስተካከሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች ሀሳብና አስተያየቶች አክለው ለቢሮው ግብረመልስ የሚሰጡም ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 2/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ከሚያስተባብሩ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የፕሮግራም አስተባባሪዎች ጋር በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት የጋራ ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይትና ስምምነት አካሄደ፤
በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲኖሩ በዛሬው ዕለት ከቢሮው ጋር ስራዎቻቸውን በዕቅድ አናብበው ለመስራት የተስማሙት የመስራት ስራ ፈጣሪዎች ፕሮግራም፣ ጥላ ፕሮግራም፣ ሳፊ ፕሮግራም፣ መስመር ፕሮግራም እና ሲድ ፕሮግራም ናቸው፡፡
የመስራት ስራ ፈጣሪዎች ፕሮግራም : 5 ዓመት የሚቆይ ፕሮግራም ሲሆን፣ 100 ጊግ ሞዴል ያላቸውን ቢዝነሶችን መርጦ ሁለገብ ድጋፍ ይሰጣል።
ጥላ ፕሮግራም ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የገጠር ወጣት ሴቶች ቀጣይነት ያለው የኑሮ መሻሻል እንዲፈጠር መነሻ ካፒታል የሚሆን የሶስት አመት ከዋስትና ነጻ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እና ቢዝነሶቹን በቅርበት ውጤታማነታቸውን በመከታተል መደገፍ ላይ የሚሰራ ነው።
ሳፊ ፕሮግራም ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራ ሲሆን መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ብድሮችን ያቀርባሉ በተለይ ለኢ-መደበኛ ተበዳሪዎች በመታወቂያ ብቻ ብድሮችን ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ በAI ታግዘው ብድሮችን ያመቻቻሉ፤በዚህም በዋናነት 80% ሴቶች፣ 10% ለአካል ጉዳተኞች እና 10% ለተፈናቃዮች ትኩረት አድርጎ ይሰራል።
መስመር ፕሮግራም የብድር አገልገሎት ሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና ሥራቸውን ለማስፋፋት የብድር አገልገሎት ይሰጣል አገልገሎቱ በአስተዳደራችን የሚገኙ በተለይም በወጣት ሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመጠነኛ ዋስትናና በአነስተኛ የወለድ መጠን እንዲሁም የሸሪአ መርህን የተከተለ ከወለድ ነጻ የብድር አገልገሎት ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ሲድ ፕሮግራም እንደ ኢትዮጵያ ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች እና ሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ይፈልጋል፡፡ አንድ መቶ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን በማጎልበት ለውጥ አምጭ የንግድ ሞዴሎችን በማስተዋወቅ፣ የንግድ መፈልፈያ ማዕከላትን በማቋቋምና ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ልማቶችን በማጎልበት የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራን ለመደገፍ በማለም የሚተገበር ነው፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ቢሮው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ አበይት ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች ላይ የአጋር አካላት ሚና ቀላል የማይባል መሆኑንና በቀጣይም ተቀራርቦ እና በየጊዜው ስራዎችን አቅዶ እየገመገሙ መሄድ አስፈላጊ በመሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት አቶ ሰኢድ አሊ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮግራሞችን ከዘርፉ እሳቤ ጋር የተቀናጀ እንዲሆኑ ለማስቻል ብሎም ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር በጋራ አቅዶ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ከሚያስተባብሩ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የፕሮግራም አስተባባሪዎች ጋር በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት የጋራ ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይትና ስምምነት አካሄደ፤
በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲኖሩ በዛሬው ዕለት ከቢሮው ጋር ስራዎቻቸውን በዕቅድ አናብበው ለመስራት የተስማሙት የመስራት ስራ ፈጣሪዎች ፕሮግራም፣ ሳፊ ፕሮግራም፣ መስመር ፕሮግራም እና ሲድ ፕሮግራም ናቸው፡፡
የመስራት ስራ ፈጣሪዎች ፕሮግራም : 5 ዓመት የሚቆይ ፕሮግራም ሲሆን፣ 100 ጊግ ሞዴል ያላቸውን ቢዝነሶችን መርጦ ሁለ ገብ ድጋፍ ይሰጣል፤
ሳፊ ፕሮግራም ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራ ሲሆን መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ብድሮችን ያቀርባሉ በተለይ ለኢ-መደበኛ ተበዳሪዎች በመታወቂያ ብቻ ብድሮችን ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ በAI ታግዘው ብድሮችን ያመቻቻሉ፤በዚህም በዋናነት 80% ሴቶች፣ 10% ለአካል ጉዳተኞች እና 10% ለተፈናቃዮች ትኩረት አድርጎ ይሰራል፤

የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሰልጣኝ ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሮክቶሬት በ2017 ዓ.ም የተዘጋጁ ከ75 በላይ በስራ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ ፤የስራ እድል የሚፈጠርባቸው የተለዩ አዳዲስ ገበያ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠና የሚሰጥባቸው ስርዓተ ትምህርቶች እና የማሰልጠኛ መሳሪያዎችን ለመንግስት ኮሌጆች ዲፓርትመንት ተጠሪዎች ፤ለግል ማሰልጠኛ ተቋማት እና ለድሬዳዋ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ማስተዋወቅና ማሰራጨት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ፡፡
በዚህም የአዲሱ የTVET ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ላይ ተመስርተው የተዘጋጁና የተከለሱ በቀጥታ የስራ እድል የሚፈጠርባቸው የተለዩ አዳዲስ የአጫጭር ስልጠና የሚሰጥባቸው በገበያ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ከክህሎት ስልጠና እና ከስራ ጋር የተቆራኙ በኢንዱስትሪው መስክ ፤በቴክኖሎጂ እድገት ምክኒያት በየጊዜው እየተለወጠ የመጣውን ተፈላጊ የሆኑ ችሎታዎች እንዲኖሯቸው የሚያስችሉ የሚፈለገውን ክህሎት የሚያጎሉ ሙያዎች እና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት እና ማስፋፋት ፍላጎትን ለማሟላት የሚስችሉ በጣም አስፈላጊ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ተዘጋጅተው ሲሰራጩ መቆየታቸውን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን የገለጹ ሲሆን የስርዓተ-ስልጠና እና የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ስርጭትን አስመልክቶ በነባራዊ ሁኔታ የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ ውይይት በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 1/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ለትራንስፖርት ማህበራትና በኢንዱስትሪዎች ለሚገኙ ለአሰሪና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ።
የስልጠና መድረኩ የሥራ ቦታ ማህበራዊ ምክክር በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 በሕብረት ድርድር ዙሪያ ሲሆን በይበልጥ ትኩረቱን በሥራ ቦታ ማህበራዊ ምክክር ያደረገና በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቀርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሥራ ቦታ ማሕበራዊ ምክክር የሚጫወተውን ሚና ለማስገንዘብ ያለመ ነው።
አዋጁን በመረዳትም የአሰሪውንና ሰራተኛውን ግንዛቤ ማሳደግ ዓላማው አድርጎ ከዚህ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪውን ሰላም በማረጋገጥ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚኖሩ አለመግባባቶችን በመቀነስ የስራ ክርክሮችን በምክክር መፍታት የሚያስችላቸው ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 1/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ለተመረጡ አሰልጣኝ መምህራን አቅም የሚገነባ ስልጠና ተሰጠ፤
የሙያ ስነ-ምግባር /PROFESSIONAL WORK ETHICS, MORALITY AND PATRIOTISM በሚሉ የስልጠና ርእሶች ላይ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል እጩ ፕሮፌሰር በሆኑ መምህር ለሶስት ተከታታይ ቀናት መስጠት ተችሏል፤
በዚህም ስልጠና አእምሮን፣ ልብን እና እጅን በተግባር ማገናኘት የሚችሉ፤ ሁለንተናዊ ብቃትን የተላበሱ የአስተሳሰብ፤ የአመለካከት እና የስነ- ምግባር ባህሪ ለውጥ የሚያመጡ ስልጠና አጠናቃቂ ሰልጣኞችን ለማፍራት ሰው ተኮር ልል ክህሎትን መሰረት ያደረገ ሃገር ወዳድነት እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ለማላበስ በሙያ ደረጃው ውስጥ የተካተቱትን ብቃት አሃዶች እና ኮርሶችን ያካተተ ሆኗል፤
በመሆኑም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶበት እየሰራ ካለባቸው የክህሎት ልማት ጉዳዮች ውስጥ ወቅቱ የሚጠይቀን የአርበኝነት አይነት ግልፅ አላማ እና ተልእኮ ያለው ትውልድ የማፍራት በመሆኑ አሰልጣኙ ሲበቃ ብቁ ሰልጣኞችን የማፍራት እድሉ ከፍተኛ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልፀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 1/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ግራንድ ግሩፕ ከተባለ በድሬዳዋ የመጀመሪያው የሆነ በዲጂታል ማርኬቲንግ እና የበቃ የሰው ሀይል ለኢንዱስትሪዎች አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሄዱ።
ውይይቱ በዋናነት ከቢሮው ጋር በተቀናጀ እና በተናበበ አግባብ ከመስራት አንጻር ሰራተኞችን ከማስቀጠር ባሻገር ያሉ ጉዳዮችን በጥናት ላይ የተመሰረተ ችግር ፈቺ ስራዎችን ለመስራትና በአስተዳደሩ የሚገኙ ዜጎችና ተቋማት በዲጂታል ማርኬቲንጉ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ ስራዎችን ለማስፋት ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደገለጹት ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ማስቀጠር ላይ የሚቆም አለመሆኑና ዘላቂ የሆነ የሥራ ዕድል መፍጠር ላይ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፤ ለዚህም መሰል ኢንተርፕራይዞች በአስተዳደሩ መፈጠራቸውና ወደ ስራ መግባታቸው ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑና በቀጣይም ተቀራርበው የሚሰሩና አስፈላጊውን ድጋፍ ቢሮው የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 30/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ሶስተኛ ዙር ትግበራ በድሬዳዋ ሁለቱም የመንግስት ኮሌጆች ላይ ሰልጣኝ ወጣቶችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀመረ።
በዚህም ለሚቀጥሉት 12 ቀናት የህይወት ክህሎትና የሥራ አፈላለግ ስልጠና በኮሌጆቹ ውስጥ ይሚሰጣቸው ሲሆን ይህንንም ሲያጠናቅቁ በመረጡት የሙያ ዘርፍ በአስተዳደሩ በሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንደስትሪዎች ላይ የኪስ ገንዘብ እየታሰበላቸው በተግባር እየሰሩ እውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ ይሆናል።
በተከታታይ ዙሮች ሰልጣኞች በተመሳሳይ ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን በስልጠና ቆይታቸውም በኮሌጆቹ የህጻናት ማቆያ ቦታዎች ተዘጋጅተውላቸዋል በዚህም የልጅ እናት የሆኑ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ስልጠናውን ሳይስተጓጎሉ እንዲወስዱ የሚደረግ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 29/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ