1 325
订阅者
+224 小时
+67 天
+11030 天
帖子存档
በአገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ አስፈፃሚ ተቋማት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በታሰበው የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አተገባበር ዙሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለሚገኙ የቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የስልጠና መድረኩ በቢሮው የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በዚህም በቀጣይ የጀት አጠቃቀም ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም የሚፈጥሩ ሰፊ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ቀጥሎ የአውቶሞቲቭ አሰልጣኝ መምህራን በደረጃ አምስት አውቶሜካኒክስ ሙያ በመመዘን ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
#ዜና| በአስተዳደሩ የሚታየውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የድርጅት ባለቤቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ ::
#Diretv አማርኛ ሚያዚያ 24/2017
ከፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአለም ባንክ ድጋፍ በአስተዳደሩ የሚተገበረው ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የ3ተኛው ዙር ትግበራ በፕሮጀክቱ ስር የታቀፉትን ወጣቶች ከድርጅት ባለቤቶች ጋር ለማስተሳሰር በሚያስችል ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል ::
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በወቅቱ ሲናገሩ ፕሮጀክቱ ለሦስተኛ ዙር እየተተገበረ እንዳለ ጠቅሰው ከዚህ በፊት በአንደኛውና በሁለተኛው ዙር በብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ በርካታ ወጣቶች ከስራ አጥነት ተላቀው የስራ ባለቤት እንደሆኑ አንስተዋል ::
አክለውም አሁንም በዚህ ሦስተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ከዘጠኝ መቶ ( ከ 900 ) በላይ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ወስደው ወደ ተግባር ልምምድ ለማሰማራት ዝግጅት ጨርሰናል ብለው አሁን ከእናንተ የድርጅት ባለቤቶች ጋር ልምምድ እንዲያደርጉና ሞያ ቀስመው ወይ እናንተው ጋር ተቀጥረው እንዲሰሩ አለያም ሌላ ቦታ ተቀጥረው የስራ ባለቤት ለማድረግ የተመቻቸ የውይይት መድረክ መሆኑን ለመድረኩ ተሳታፊ ባለሀብቶች ተናግረዋል።
ስለሆነም በአስተዳደሩ የሚታየውን የስራ አጥ ቁጥር ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ የእናንተ የድርጅት ባለቤቶች ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በወቅቱም ወጣቶቹ የተግባር ልምምድ በሚያደርጉበት ድርጅት ሲሄዱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከድርጅቱ ምን ይጠበቃል ፤ ከወጣቶችስ ምን ያስፈልጋል የሚሉና አጠቃላይ ይህ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ምንነት እና አስፈላጊነት ለመድረኩ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በመጨረሻም የአስተዳደሩ የስራና ክህሎት ቢሮ በሦስቱም ዙር የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ሲተገበር በራቸውን ከፍተው ወጣቶቹ የተግባር ስራ ልምምድ እንዲያደርጉ ትብብር ላደረጉ ባለሀብቶች ምስጋና አቅርቧል ::
ዘጋቢ ፦ ነጃት ተገኔ
ምስል:- ከቢሮው የህዝብ ግንኙነት
ለንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ተወዳዳሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም ለሚደረገው ብሩህ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር መወዳደር የሚፈልጉ እንዲመዘገቡ በማስታወቂያ አሳውቆ መመዝገቡ ይታወሳል በዚህም ለውድድሩ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን እና አሰራሮችን በማዘጋጀት የተወዳዳሪዎችን ሰነድ በመመርመርና በመለየት ስልጠና ሰጥቷል፤
ውድድሩ የሀሳብ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ከሀሳብ ደረጃ ወጥተው ዕውን የሚያደርጉበትን ብቃት እንዲያገኙ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ድጋፉም ማሰልጠን፣ መሸለምና ማብቃት በሚል ሶስት ደረጃዎችን ያልፋል፤ በመሆኑም በዋናነት በየዘርፉ የሚታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶችን መቅረፍ ላይ ያተኮሩ አዳዲስ የንግድ ፈጠራ ሀሳቦችን ማመንጨት የሚችሉበትን እና የአካባቢያቸውን ጸጋዎች ለይተው በፈጠራ ሀሳብ በመደገፍ ጥቅም ላይ ማዋልን እንዲያዳብሩ ስልጠናው መሰጠቱን የስራ ዕድል ፈጠራ ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ቤተልሔም ድንበሩ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ውድድሩ ተወዳዳሪዎች ከሀሳብ ደረጃ ወጥተው ዕውን የሚያደርጉበትን ብቃት እንዲያገኙ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ የሚያመቻች በመሆኑ አሸናፊ የሚሆኑ በቀጣይ በመሸለምና በማብቃት ሂደት ውስጥ የሚበረታቱ እንደሚሆን ገልጸዋል፤
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአገራችን ለ50ኛ ጊዜና በዓለማችን ለ136ኛ ጊዜ ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን ክብረ በዓል የሠራተኛና አሰሪዎች ማህበራት፣ ፌደሬሽን እና ኮንፌደሬሽን አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት ተከበረ፡፡
በመድረኩ የኢሰማኮ የምስራቅ ኢትዮጵያ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንዳለ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ማህበራዊ ፍትህ ቅድሚያ በመስጠት ኢኮኖሚያዊ ደረጃቸው ምንም ይሁን ምን ሁሉም ሰራተኞች የተከበረ እና አስተማማኝ ህይወት እንዲኖራቸው ማድረግ ትችላለች፤ መንግስት ከዚህ በፊ ያነሳናቸውን ጥያቄዎቻችንን ተገቢነት ተቀብሎ ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ሰጥቶ እንደነበር አስታውሰው ምላሽ ያገኙ ጉዳዮች መኖራቸው የሚያስመሰግነው ሆኖ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ታይተው ምላሽ ይሰጠን ዘንድ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
አክለውም አለም ዓቀፍ የሰራተኞች ቀን ሜይ ዴይ በሚከበርበት ዕለት ለመንግስት ምላሽ እንዲሰጥባቸው ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ የሥራ ግብር ምጣኔ እንዲስተካከል፤ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም፤ በተቋማት የስራ ደህንነትና ጤንነትን በተመለከተ ክትትሉ እና ቁጥጥሩ ሊጠናከር እንደሚገባ በማሳሰብ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮቻችንን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሠላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን ጥረት መላው ሰራተኛ እንዲደግፍ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የዘንድሮው ሜይዴይ የሚከበረው በዓለም አቀፍ ደረጃ “በአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምቹ የሥራ ሁኔታ ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ቃል ቢሮው ሰላማዊ እንዱስትሪና የኢንዱስትሪ ባህል ግንባታ እንዲረጋገጥ፣ ምቹ የስራ ቦታ እንዲፈጠርና ሠራተኛው እና አሰሪው በነጻነት የመደራጀት መብት በማረጋገጥ ሰራተኛው ከአሰሪው ጋር የመመካከር እንዲሁም እንዲደራደርና ግዴታውን እየተወጣ መብትና ጥቅሙ እንዲከበር የምክክር ባህል እንዲጎለብት ከምስራቅ ኢትዮጵያ ኢሠማኮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በጋራ በማቀድ እና ሰራዎችን በመገምገም እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በተለይ በአስተዳደሩ በሚገኙ የማምረቻ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚገኙ ሠራተኞች በማህበር እንዲደራጁ ቢሮው ከምስራቅ ኢትዮጵያ ኢሠማኮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከዚሁ ጎን ለጎን የሥራ ቦታ ደህንነትና ጤንነትን በማስጠበቅ ረገድ የወጡ የሕግ ማዕቀፎችን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ በሁሉም እንዱስትሪዎችና ድርጅቶች ጥምር የሙያ ድህንነት እና ጤንነት ኮሚቴ እንዲደራጅ ከማድረግ ጅምሮ በዘርፉ የባለሙያ እጥረትን ለመቅርፍ ባለፈው አንድ ዓመት በአጫጭር ስልጠና 31 የሚሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉን አስታውሰው በትብብር ለመሠራት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በድሬዳዋ አስተዳደር የተጀመሩ የከተማዋን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ተግባራት እንዲሳኩ ሠራተኛው ተገቢውን አስተዋጽኦ እንዲያደረግ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለ4ኛው አገር ዓቀፍ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ ስራዎች እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድሮች በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ለተሳተፉና ላለፉ ተወዳዳሪዎች የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራ ክህሎት ቢሮ የውድድርና የተነሳሽነት ስሜትን በመፍጠር በክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማቱ ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን እና አሰልጣኞችን ባለሙያዎችን ለማፍራት በማለም የ2017 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ ስራዎች እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድሮች ማካሄዱ ይታወሳል፤
በዛሬው ዕለት በተካሄደው በዚህ የዕውቅና ፕሮግራም ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደገለጹት፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት በዋናነት በአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር በሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በተለይም ከኢንዱስተሪዎችና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍን የላቀ ሚና ለማጎልበት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ እና በዚህም አበረታች ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑንና ይህም መርሃግብር አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ከተጣለበት ከፍተኛ ኃላፊነት አንዱ በሙያ ክህሎቱ የበለጸገ የሰው ሀይል ማፍራትና ቴክኖሎጂን የመቅዳት፣ የማሻሻል እና የማሸጋገር ስራ ዋነኛው መሆኑን ገልጸው፡፡ በሙያ ክህሎታቸው የበቁ ቴክኖሎጂስቶችና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ለሚሰሩ አሰልጣኞች፤ ሰልጣኞች፤ ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እንዲሁም ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መምህራንና ተማሪዎች ውድድሮችን በማዘጋጀት ማትጋቱ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት ቢሮው ይህን ኃላፊነት በመውሰድ ውድድሮችን በማዘጋጀት ዕውቅናና ሽልማት መርሃግብር ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ መርሃ ግብር በሁሉም ውድድሮች ለተሳተፉና ውጤት ላስመዘገቡ የሰርተፍኬትና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በቀጣይ ድሬዳዋን ወክለው በፌደራል ደረጃ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምቹ የሥራ ሁኔታ ለማህበራዊ ፍትህ በሚል መሪ ሀሳብ 136 ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በዛሬው እለት በድሬዳዋ ደረጃ በድምቀት ተከብሯል ።
#ዜና /አለምአቀፉ የሰራተኞች ቀን በናሽናል ስሚንቶ ፋብሪካ በልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች በድምቀት ተከበረ
#DGC ሚያዚያ 22/2017
የናሽናል ስሚንቶ አ/ማ ከድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር "በአምራች ኢንዱስትሪው እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምቹ የስራ ሁኔታ ለማህበራዊ ፍትህ" በሚል መሪ ሀሳብ አለምአቀፉ የሰራተኞች ቀን በልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች በድምቀት ተከብሯል።
በመርሀ ግብሩም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው አለም አቀፉ የሰራተኞች ቀን ስናከብር ኢንደስትሪዎችን የሚገነቡ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ኢኮኖሚያችንን የሚያንጹ እጆችን እናከብራለን ብለዋል።
በአለም ለ136ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀን ሲከበር ያለፈውን ትግሎች ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ የስራ ቦታዎችን ለሰራተኞች ክብር እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ላይ ግልጽ አላማ ይዘን በአንድነት እንድንቆም የሚያደርገን ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።
የናሽናል ሲሚንቶ አ/ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሊዮ የሰራተኞች ቀን ሲከበርም የናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ድርጅትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ምርት ና ምርታማነትን በማሳደግ በቁርጠኝነት ስራቸውን እየፈጸሙ ለሚገኙት ሰራተኞች ምስጋና እና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
በዓሉ በተቋሙ ሲከበርም የኢትዮጵያ እና የቻይና ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብርን ይበልጥ በማቀራረብ በኩል ጎልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በመርሀ ግቡሩም በተቋሙ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ ቆይተው በጡረታ ለተሰናበቱ እና ጥሩ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የስጦታ ና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
በመርሀ ግብሩም የናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር ተጠሪ ክብርት ወ/ሮ ቢፍቱ መሀመድ፣የናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ከፍተኛ አመራሮች እና በርካታ ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
©️ DDGC
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በአጠቃላይ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ https://lmis.gov.et የሚከናወነው ምዝገባ እንቅስቃሴን አስመልክቶ ከወረዳ የአንድ ማዕከል አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በዋናነት ምዝገባ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እሰከ አሁን የተመዝጋቢዎች ቁጥር የደረሰበት ደረጃ ተገምግሟል፤ በተለይም ስራ ፈላጊ፣ ስራ ያላቸው እና ኢንተርፕራይዞችን ምዝገባ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የታየ ሲሆን በዚህም ሂደት የተመላከቱ ክፍተቶችን ለማስተካከልና በቀጣይ በሁሉም የወረዳ አንድ ማዕከላት ደረጃ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ያለውን አፈጻጸም ለማሻሻል እንዲሁም ቁጥሩንም ከፍ ለማድረግ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የአክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራር አባላትን የያዘ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ እያሳየ በሚገኘው ከፍተኛ አፈፃፀም ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ኮሌጆች ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማችን እየመጡ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለትም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚገኘው የአክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋማችን የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርጏል::
ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የአፈፃፀም ሂደት በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በተለያዩ ተግባራት እያከናወናቸው የሚገኙ የለውጥ ስራዎችም በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገልፃ ተደርጎላቸዋል::
ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ ባደረገው ምልከታና የተደረገላቸው ገለፃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው የጋራ ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች መደነቃቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ በአጭር ጊዜ እያሳየ ያለው የላቀ አፈፃፀም ለሌሎች አቻ ተቋማትም ሞዴል ተደርጎ መወሰድ የሚችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሀሳባቸውን ገልፀዋል::
በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲሁም ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኟቸውን በርካታ ልምዶችንም ቀምረው በመጡበት ኮሌጅ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም
