ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 327
订阅者
-124 小时
+67 天
+8830 天
帖子存档
"ከወጣቶች ጋር በመተባበር ሙስናን መከላከል የነገን ስብዕና ለመቅረጽ" 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረሙስና ቀን!" የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ "ከወጣቶች ጋር በመተባበር ሙስናን መከላከል የነገን ስብዕና ለመቅረጽ" በሚል በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ ከቢሮው ማህበረሰብ ጋር ተወያይቷል። የአስተዳደሩ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር በውይይቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የሙስና ምክንያት የሆነውን የስነ-ምግባር ዝቅጠትንና ስግብግብነትን ለማረም እና አይቶ እንዳላየ ማለፍን ለማስቆም የቢሮው ሰራተኞችና አመራሮች በተለይም ወጣቱ ሚናው ላቅ ያለ መሆኑን አስረድተዋል። የፀረ-ሙስና ትግሉ በቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ ዘንድ እንዲቀጣጠልና በዋናነት የስነ ምግባር ግንባታው የድርሻውን እንዲወጣ ወጣቱ ሙስናን የሚጠየፍ ብሎም በመከላከሉ ሂደት የድሻውን ተወጥቶ የሚታመንና የሚተማመን ሰራተኛና አመራር መፍጠር እንደሚገባ ተመላክቷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማት እና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ቢዝነስና  ሜዲካል  ኮሌጅ የስልጠና ጥራት ኦዲት በማከናወን የፈቃድ እድሳት እንዳደረገ ገለጸ፤ የፈቃድ እድሳቱን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ማለትም የኮሌጁን የሶስት አመት የስራ አፈጻጸም፤ የሰው ሃይል የስራ ፍላጎት የገበያ ጥናት ሰነድ፣ የአሰልጣኞች ፕሮፋይል፣:የህንጻ ውል፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት እና የመሳሰሉት ሰነዶች የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል በዚህም ዝቅተኛ የጥራት ስታንዳርድ ስለሟሟላቱ በተለይ በጤናው ዘርፍ ከጤና ቢሮ በተመደቡ ባለሙያዎች በፋርማሲ እና በነርሲንግ በኢትዮጵያ በቴ/ሙ/ት/ስ የስልጠና ዘርፍ በካሪኩለም መሠረት የስልጠና ግብአቶች ስለመሟላታቸው የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም በአምስት የስልጠና ፕሮግራሞች በአካውንቲንግ፣ በሰው ሃብት አስተዳደር፣ በማርኬቲንግ አስተዳደር፣ በነርሲንግ እና በፋርማሲ በግብአት፣ በአደረጃጀትና በአሰራር ብቁ ስለመሆኑ በባለሙያዎች ቡድን ተረጋግጦ ለቀጣይ ሶስት አመታት ስልጠናውን እንዲያካሂድ የፍቃድ እድሳት ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ውሳኔ ላይ መደረሱን የአሰልጣኝ ልማት እና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ምሩቅ ስራ ፈላጊዎች በድሬዳዋ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ለማሳየት ፍላጎትና ተነሳሽነታቸውን ከፍ የሚያደርግ ለዩኒቨርስቲ እና ኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሠጠ። ይህም ስልጠና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች የተወጣጡ ስራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ስራ ፈጣሪ ለማድረግ አቅማቸውን ለመገንባት ታስቦ በተከታታይ በመሰጠት ላይ ይገኛል። ቢሮው በአስተዳደሩ ትኩረት  የተሰጠውን የስራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የተጀመሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር በተፈጠረው መልካም ግንኙነት ተመራቂዎች ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራቱ ብዙዎች ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተናግረዋል። ዳይሬክቶሬቱ አክለው ተሳታፊ ምሩቃን ሥራ ፈላጊዎችም ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ይጠብቁ የነበሩበትን አመለካከት ከስልጠናው ባገኙት ግንዛቤ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለመስራት መነሳሳት እንደሚፈጥርባቸውና ይህን መሰል ስልጠናዎችንም ለወጣቶች ማዘጋጀት በአስተዳደሩ የተፈጠሩ የሥራ እድሎችን ለመጠቀም ያለው ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለመንግስትና ለግል ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን መስጠት ጀመረ፡፡ በዚህም በሞዴል ኢንተርፕራይዞች ላይ የካይዘን ትግበራ የሚደረግ ሲሆን ለኢንተርፕራይዞች ሠራተኞች የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ (ካይዘን) ትግበራ ስልጠና/ድጋፍ በመስጠት ማብቃት እና የመስሪያ/ ማምረቻ ወርክሾፖችን በካይዘን እንዲደራጁ በማድረግ ኮሌጆች ከኢንተርፕራይዞች ጋር የሚኖራቸዉን የስራ ትስስር ለማጠናከርና የኢንተርፕራይዞችን ሠራተኞች መሰረታዊ የካይዘን እዉቀትና ክህሎትን በኢንተርፕራይዙ ማምረቻ/የስራ ቦታ በመተግበር ደረጃዉን የጠበቀ ማምረቻ ቦታ ለመፍጠር እና በአጠቃላይ የካይዘን ፍልስፍናን በመተግበር የአሰልጣኝ መምህራኑን አቅም በመገንባት የኢንተርፕራይዞችን አላስፈላጊ ብክነቶችን በማስወገድ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል አቅም የሚፈጥር ስልጠና ይሆናል፡፡ ኤጀንሲው ከኮሌጆች ጋር በመሆን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ በመስጠት በአስተዳደሩ ጉልህ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን በተለይም በ4ቱ የድጋፍ ማእቀፎች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን  የምርትና ምራታማነት በማሻሻልና  ብቁ የሆነ የሰዉ ሃይል በማፍራትና የሥራ እድል እንዲፈጥሩ ለማድረግ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፤ በዚህም በአስተዳደሩ ዘጠኙም ወረዳዎች ለሚገኙ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ለሚደረግላቸው  ኢንተርፕራይዞች የድርጊት መርሀ ግብር በማዘጋጀት ከተለመደው 5ቱ ማዎች በተሻሻለው አድቫንስድ ካይዘን ትግበራ እንደሚደረግ የቢሮው ም/ኃላፊና የኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያላቸው ግንዛቤ ከሚፈለገው እኳያ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራንና የተማሪ ተወካዮችን የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሂዷል:: ፕሮጀክቱ በቀጣይ በሚኖረው የ5 አመት ትግበራ በኮሌጅ የሚሰጡ የሞያ ስልጠናዎች በእስተዳደሩ የሚገኙትን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎችን ማእከል ያደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች ስለ ዘርፉ በቂ ግንዛቤ መፍጠር ተቀዳሚው ተግባር በመሆኑ ይህ መድረክ መዘጋጀቱም ተገልፇል:: በመድረኩ ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ላይ ስለ ቴክኒክና ሙያ በቂ ግንዛቤ ባለመፈጠሩ ምክንያት ወጣቶቹ በዘርፉ የሚኖራቸውን ተጠቃሚነት ባለመገንዘብ ህይወታቸውን በማይለውጡ የትምህርት መስኮች ላይ እድሜያቸውን እያባከኑ እንደሚገኙ ገልፀው በስተመጨረሻም የተማሩትን ዲግሪ አስቀምጠው ሌሎች ስልጠናዎችን ለመውሰድ ወደ ኮሌጁ እንደሚመጡም አስታውሰዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም በአስተዳደሩ የሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከኮሌጁ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎቹ ላይ ተገቢውን የግንዛቤ የመፍጠር ስራ በመስራትና ተማሪዎቻቸው የ12 ክፍል መልቀቂ ፈተና ከመውስዳቸው አስቀድሞ ተማሪዎቹን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እሳቤ መቅረፅ የሁላችንም ድርሻ መሆን እንደሚግባውም አፅዕኖት ሰተው ተናግረዋል:: በኢንዱስትሪው ዘርፍ ሰፊ የክህሎት ክፍተት እንዳለ የተጠቀሰ ሲሆን በየፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ወጣቶችም ዝቅተኛ ክህሎቶች(Low skills) ላይ አየሰሩ ያሉ መሆናቸውም ተመላክቷል:: በመድረኩ የSTEM(Science,Technology, Engineering,Mathematics)ፅንሰ ሃሳብና ምንነት ዙሪያ በኮሌጁ ምክትል ዲን እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተሾመ ሸዋዬ በኩል ለመድረኩ ተሳታፊዎች ቀርቧል:: የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዘርፉ በሚፈለገው ልክ ውጤት እንዳይመጣ ተግዳሮት ሆነዋል ያሏቸውን ምክንያቶች በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን በቀጣይም ከኮሌጁ ጋር በቅንጅትና በባለቤትነት ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እንደሆኑና የሚታዩ ክፍተቶችንም በዘላቂነት መፈታት እንደሚሹ ሀሳብ አስተያየታቸውን ሰተዋል:: ኮሌጁ በቀጣይ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር የጋራ መግባብያ ሰነድ በመፈራረም ወደ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም

photo content
+8

photo content
+9

ለስራ ፈላጊ ዜጎች ተደራሽ እንዲሆን ሁላችንም ሼር በማድረግ እንረባረብ👈👈👈

"ወጣቱ በአስተዳደሩ የተለዩ ፀጋዎችን ተጠቅሞ በስራ እድል ፈጠራ የራሱንና የሌሎችን ህይወት ለመቀየር መሰማራት ይገባዋል!" አቶ ሰኢድ አሊ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳይሬክተሩ በኢ.ዲ.አይ(ኢስተርን ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቪ) እየተዘጋጀ በኤፍ ኤም ድሬ 106.1 የሚቀርብ #እኔ ሰላማዊ ነኝ# የተሰኝ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ በተጋባዥ እንግድነት ቀርበዋል። በዚህ መሰረት አቶ ሰኢድ አሊ በፕሮግራሙ  ላይ ቀርበው በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ በአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ✍️ አቶ ሰኢድ በአስተዳደሩ በርካታ የስራ እድል መፍጠር የሚቻልባቸው ዘርፎች መኖራቸው እሙን ነው ይሁን እንጂ ወጣቱ ያሉ አጋጣሚዎችን ተጠቅሞ ስራ ከመፍጠር አኳያ ክፍተቶች መኖራቸውን ገልፀዋል። ✍️ በመሆኑም የስራ ባህልን አሳድጎ ስራን በመፍጠር ብሎም ባሉ የስራ አማራጮች ላይ ስራን ሳይንቁ በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ አቶ ሰኢድ አብራርተዋል። ✍️ ድሬዳዋ በሰላምና አብሮ በመኖር በአገር አቀፍ ደረጃ ተሞክሮ መሆን እንደቻለች ይህንን ሰላም ለማስጠበቅና የአስተዳደሩን እድገት እውን ለማድረግ ወጣቱ እራሱን ስራ ፈጣሪና አምራች እንዲሆን መስራት እንደሚገባ አቶ ሰኢድ መልዕክት አስተላልፈዋል። ©️ ኤፍ ኤም ድሬ 106.1

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ የOSH( Occupational Safety & Health) የሙያ ደህንነት ስልጠና በኮሌጁ መስጠት ጀመረ:: ኮሌጁ እየሰጠ የሚገኘው ይህ የሙያ ደህንነትና ጤንነት አስተዳደር (OSH) ስልጠና በአስተዳደሩ ከየቀበሌው የተወጣጡ በኢንጂነሪንግ እና በጤናው ዘርፍ የመጀመርያ ዲግሪ ተመርቀው ስራ ያልያዙ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ሲሆን በመስፈርቱ መሰረት ተመልምለው የመጡ ወጣቶችንም ለማሰልጠንና ወደ ኢንዱስትሪው ለማሰማራት በማሰብ በመጀመርያ ዙር 31 ሰልጣኞችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ይገኛል:: ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው የLife skills ስልጠናን ጨምሮ በስራ ቦታ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን በመለየት እና በመቆጣጠር የሰውን ህይወት እንዲሁም ንብረትን ከአደጋ መጠበቅ የሚያስችሉትን የተግባር፣የንድፍ ሃሳብን ጨምሮ ኢንዱስትሪዎች ላይ የትብብር ስልጠናዎችን የሚወስዱ መሆኑም ተግልፇል:: የOSH( Occupational Safety & Health) ስልጠናው በአጫጭር ስልጠና መደብ የሚሰጥ ሲሆን ለቀጣዮቹ አንድ ወራትም የሚቆይ ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ፍትሃዊ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን የሚረጋገጡ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው ተገለፀ፤ **** የሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በሴቶች፣ በአካል ጉዳተኛ ለሚመሩ  ኢንተርፕራይዞች፣አንቀሳቃሾች እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ለሚያደርጉ ለግል ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ከድጋፍ ማእቀፍ አንዱና ዋነኛ  የሆነውን የንግድ ክህሎት እና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ላይ የኢንተርፕሩነርሺፕ ምንነትና የንግድ ክህሎታቸውን ሊያዳብሩ የሚችሉና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ጋር ያለባቸውን ክፍተት ከመሙላት አንጻር ያለው አስተዋፅኦ በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን ሰልጣኞች ከዚህ በፊት የነበራቸውን እውቀትና ግንዛቤ እንዲያሳድጉ የሚያስችል እድል የፈጠረላቸው ሆኗል፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ እርስ በእርስ ያላቸውን መስተጋብር ይበልጥ በማጠናከር የልምድ ልውውጥና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ያስቻለ ሲሆን  ለኢንተርፕራይዞች የተሻለ ትኩረት በማድረግ ውጤት ተኮር ተግባር ማስመዝገብ የሚቻለው ከጊዜው ጋር የዘመነ ስልጠና በመስጠት እንደሆነ  ተገልጿል፡፡ ከኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾቹ ጋር በስልጠናው የተሳተፉት የግል ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራን ኤጀንሲው ከግል ከኮሌጆቹ ጋር በደረሰው የጋራ መግባባት ለሚያደርጉት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን  የድጋፍ አይነቶች አቅማቸውን ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ታውቋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ