ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 329
订阅者
+324 小时
+87 天
+8330 天
帖子存档
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ለወጣቶች በተከታታይ ስድስት ዙር ሲደረግ የነበረው የአቻ ለአቻ ውይይት ተጠናቀቀ፤      ወጣቶቹ  በየወሩ የአቻ ለአቻ  ውይይት  በማድረግ  በየጊዜው ያገኙትን ዕውቀት  የገጠማቸውን ችግሮች  ለይተው የተወያዩበት መድረክ  ሲሆን ይህ  ለስድስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ እና የመጨረሻው  ውይይት የተደረገ ሲሆን የስራ ላይ ልምምዱን ሲያጠናቅቁ  በተቀጠሩበት ወይም በሚቀጠሩበት ድርጅቶች በሰለጠኑት ሞያ መሰረት የሚያገለግሉ ይሆናል፡፡      በአስተዳደሩ የፕሮግራሙ ሁለተኛ ዙር ትግበራ ከ1700 በላይ ሰልጣኞች ተመዝግበው 1500 በላይ የሚሆኑት የህይወት ክህሎት ሰልጠና ወስደው 972 የሚሆኑ ወጣቶች ተግባራዊ የሥራ ላይ ልምምድን የተቀላቀሉ ሲሆን በተለያዩ በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንደስትሪዎች ላይ ስድስት ወራት የሚፈጀውን ውጤታማ ቆይታ እያደረጉ ሲገኝ ከዚሁ ጎን ለጎን የአቻ ለአቻ ውይይቶችን በየወሩ ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡      በዚህም ውይይት ላይ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ተጠቃሚነታቸው በአመለካከት፣ በክህሎት እንዲሁም በዕውቀት ከዚህ በፊት ከነበሩበት የተሻለ ነገሮችን የመረዳትና የማድረግ አቅም ማዳበራቸውን የተናገሩ ሲሆን በተለይ እርስ በዕርስ በመነጋገር ችግሮችን የፈቱበትና የተሻለ ዕውቀት የቀሰሙበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በስድስተኛው ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ማጠቃለያ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ወጣቶች ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ጋር የጋራ መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት ማድረግ በሚገባቸው ነገሮች ላይ  መግባባት የፈጠሩበት ሆኗል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 7/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የቴክኖሎጂ እሴት ሰንሰለት ትንተና እና ሰነድ ዝግጅት ላይ ያኮረ ስልጠና ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ተሰጠ፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር በሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖለጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጥቃቅን፣ አነስተኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች በአዲሱ ዕሳቤ መሠረት ለኢንተርፕራረ አጫጭር የእሴት ሰንሰለት እንዲሰጥ ከሥራና ክህሎት ሚንስቴር በተላለፈው መመሪያ መሠረት የተሰጠ ነው። የዚህ ስልጠና ዋነኛው ዓላማ በሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ በ2017 ዓ.ም በተያዘው ዕቅድ መሰረት በአስተዳደሩ የሚገኙትን የዘርፉን እሴት ሰንሰለት ለማዘጋጀት በቅድሚያ በንዑስ ዘርፍ ተሰማርተው ለሚገኙ የጥቃቅን፤ አነስተኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች በአዲሱ እሳቤ መሰረት ለኢንተርፕራይዞቹ  በተመረጡ በስድስት ንዑስ ዘርፎች የእሴት ሰንሰለት ስልጠና እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ኢንተርፕራይዞቻችን በቀጣይ በሽግግር ወቅት እስከ ኤክስፖርት ስታንደርድ ሊያደርሳቸው የሚችል የዘርፉ የቴክኖሎጂ ክፍተቶች የሚለዩበትና የምርት/የአገልግሎት ችግሮቻቸውን  ሊፈታ የሚችል ቴክኖሎጂ በቀጣይ ጊዜያቶች በተቋም የሚሰራበትና የሚሸጋገርበትን እድል የሚፈጥር ይሆናል ፡፡ በዚሁም መሰረት በቀጣይ ለነዚህ ለተመረጡት ንዑስ ዘርፎች ከዘርፍ መ/ቤት፤ ከዩኒቨርሲቲና ከተቋሞቻችን በተመረጡ ባለሞያዎች/ኤክስፐርቶች የእሴት ሰንሰለቱ ትንተና የሚሰራ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

"ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት!" የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ። በዓሉ በፓናል ውይይት የተከበረ ሲሆን፣ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑን አውስተው፣ ሀገራዊ መግባባትን ለማጽናት ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ጥያቄዎችን በሰላማዊ አግባብ የሚያስተናግድ ሥርዓት መገንባትና የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ከዳር ደርሶ አንድነታችንን እንዲያጠናክር ቀዳሚ የመንግሥት ትኩረት እንደሆነ ተናግረዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት የተለያየ ዘርፍ ስር ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች አሰሪና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት በሙያ ደህንነትና ጤንነት ላይ ስልጠና ተሰጠ። በቢሮው የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት በዋናነት የሰራተኛውን ደህንነትና ጤና የማስጠበቅ ስራዎች ትኩረት የተሰጣቸው ሲሆኑ ይህም የኢንተርፕራይዞቹን ምርታማነት በማሳደግ የስራ ቦታቸውን ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የሚያስገኘው ውጤት ቀላል አይደለም። በዚህም በየኢንተርፕራዞቹ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አንዲደራጅና እንዲጠበቅ ድጋፍ በማድረግ ለኢንተርፕራይዞቹ አሰሪና ሰራተኞች በቀጣይ ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች በማስገንዘብ  በተለይ የሙያ ደህንነቱና ጤናው የተጠበቀ የስራ አካባቢን በመፍጠር የስራ ቦታቸውን ሰላም እና ደህንነት በማስጠበቁ ረገድ ያለው ሚና ከፍ ያለ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢብራሂም ተናግረዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት እና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ስራዎችን ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም ለኢንተርፕራይዞች በሚደረገው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፍ ዙሪያ የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት በኮሌጆች ተዘጋጅቶ ውይይት ተካሄደ። ዳይሬክቶሬቱ በተለያዩ ዘርፎች ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ አስተማማኝነትን ለማረጋገጥና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት በሚያስችል መልኩ ሰነድ ቀርቦ በተለያዩ ጉዳዮች  ዙሪያ የሚመለከታቸው የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት የጋራ ስምምነትና መግባባት የተፈጠረበት ውይይት ማካሄድ ተችሏል፡፡ በውይይቱ ላይ የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት የዛሬ መድረክ ዋና ዓላማ በአስተዳደሩ በተለያዩ ዘርፍ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎችን በቅንጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚከናወኑ ተግባራት በጋራ በማከናወን ኢንተርፕራይዞችን የሚጠቅሙና የሚያሳድጉ ስራዎችን ለመስራትና በዚህም ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንደሆነ ተናግረዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

“ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ኘሮጀክት ለተጠቃሚ ወጣቶች የሥራ አፈላለግ ክህሎት ስልጠና በኮሌጆች መሰጠት ጀመረ፤ በዚህም ወጣቶቹ ባለፉት ስድስት ወራት በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሥራ ላይ ልምምድ ማድረጋቸው ይታወቃል በቀጣይ ከሥራ ጋር ለመተሳሰር እንዲያስችላቸው ደግሞ ለተከታታይ አምስት ቀናት በሚወስዱት ስልጠና ሥራ የማፈላለግ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ ይሆናል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 QMS የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሸላሚ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 QMS የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሸላሚ::

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ የቀንና የማታ ተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሀግብር በኮሌጁ አዳራሽ አከናወነ፡፡ በመርሀግብሩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን  አቶ ሰልሀዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት በቅድሚያ በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል የሆነውን ኮሌጃችንን ስለመረጣቸሁ በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም አመሰግናለሁ ያሉ ሲሆን:: አያይዘውም ቴክኒክና ሙያ ማለት የወደቁ ተማሪዎች መሰብሰቢያ ሳይሆን ይልቁንም የእውቀት፣የክህሎትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የሚፈልጉ ወጣቶች የሚማሩበትና በእጃቸው ሰርተው በላባቸው ሀገራቸውን መቀየር የሚፈልጉ ወጣቶች የሚሰባሰቡበት ትልቅ የትምህርትና ስልጠና ማእከል ነው ብለዋል፡፡ ኮሌጃችን የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዘመኑን የሚመጥን የትምህርትና ስልጠና ዘዴዎችን እየተጠቀመ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ይታወቃል ስለዚህ በኮሌጁ ውስጥ በምትቆዩበት ወቅት ስራ ፈጣሪ ብሎም ኢንዱስትሪዎችን አንቀሳቃሽ እንድትሆኑ አድርገን ነው የምናሰለጥነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ድሬዳዋ ከተማች የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ነጻ የንግድ ቀጠና እንደመሆኗ መጠን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሰለጠኑ ወጣቶችን በብዛት ይፈለጋሉ ስለዚህ በኢንዱስትሪዎች ተቀጥሮ ለመስራት እንዲሁም የራስን ስራ ፈጥሮ ለመንቀሳቀስ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መሰልጠን ያስፈልጋል ብለዋል በማስቀጠልም በኮሌጁ ውስጥ የሚኖራችሁ ቆይታ እውቀት፣ክህሎት እንዲሁም መልካም አስተሳሰብ ያላችሁ ወጣቶች የምትሆኑበት እንዲሁም በምታገኙት እውቀትና ክህሎት ደግሞ ከተማችሁን ብሎም ሀገራችሁን የምትጠቅሙ ዜጎች እንደምትሆኑ  እተማመናለሁ ያሉ ሲሆን የስልጠና  ቆይታችሁም መልካም እንዲሆን መልካም መኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይ በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የትምህርት ክፍሎች ስለ ትምህርት ክፍሎቻቸው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከገለጻው በኋልም በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎችንና ማሰልጠኛ ወርክሾፖችን ጎብኝተዋ፡፡በቀጣዩ ቀንም የህይወት ክህሎትና የማይንድ ሴት ስልጠና እንደሚሰጥ በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ህዳር 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

“የግል ኮሌጆችን በኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ላይ መሳተፍ መጀመራቸው የግሉን ዘርፍ በማህበረሰብ ዓቀፍ አገልግሎት ውስጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ይሆናል።” ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ በተመላከተው መሰረት የግል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ለኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ መስጠት እንዲያስችላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በዛሬው ዕለት የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ከሁለቱ የመንግስትና የግል ኮሌጆች ተወካዮች ጋር የግል ኮሌጆች ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ማድረግ በሚችሉበት አግባብ ላይ ወደ ትግበራ እንዲገቡ የሥራ አቅጣጫ በመስጠት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ጋር በክላስተር በመክፈል በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን በማዳረስ ረገድ የተፈጠረውን ጫና የሚጋሩ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 3/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ