ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 318
订阅者
+324 小时
+207 天
+15030 天
帖子存档
#የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ይቀላቀሉ እውቀትና ክህሎትዎን ያሳድጉ የስራ ፈጣሪነትዎን በእኛ ኮሌጅ እውን ያድርጉ።
#የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ይቀላቀሉ እውቀትና ክህሎትዎን ያሳድጉ የስራ ፈጣሪነትዎን በእኛ ኮሌጅ እውን ያድርጉ።

የድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፈ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመትን አስመልክቶ ለመላው የድሬዳዋ ሕዝ
+1
የድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፈ   የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመትን አስመልክቶ ለመላው የድሬዳዋ ሕዝብ፣ ለወጣቶች፣ ለሥራ ፈላጊዎች፣ ለሥራ ፈጣሪዎች፣ ለአሰሪዎችና ለቢሮው አጋር አካላት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።   የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመልዕክታቸው፣ 2019 ዓ.ም. ለድሬዳዋ ሕዝብ የሰላም፣ የአንድነት፣ የብልጽግናና የስኬት ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።   አቶ ሮቤል ጌታቸው አዲሱ ዓመት ወጣቶች በክህሎታቸው ተጠቅመው የሥራ ዕድል የሚያገኙበት፣ ሥራ ፈጣሪዎች የሚበረታቱበት፣ አሰሪና ሠራተኛ በተሻለ ሁኔታ የሚገናኙበትና የድሬዳዋን የሥራ ገበያ የበለጠ ውጤታማ የሚያደርግ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።   በተጨማሪም ቢሮው በአዲሱ ዓመት የሥራና ክህሎት ዘርፍ የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋፋት፣ የወጣቶችን ክህሎት በማሳደግና የሥራ ገበያውን በማጠናከር ለድሬዳዋ የተሻለ የልማት አቅጣጫ ለመፍጠር በትጋት እንደሚሠራ ኃላፊው ገልጸዋል።   “2019 ዓ.ም. የአዲስ ተስፋ፣ የአዲስ ዕድል፣ የሥራና የስኬት ዓመት ይሁን!” በማለት አቶ ሮቤል ጌታቸው ለመላው የድሬዳዋ ሕዝብ ከልብ የሆነ የአዲስ ዓመት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።   መልካም አዲስ ዓመት! አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

የነገው ቀን ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን
የነገው ቀን ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል። በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራት ያበስራል! #DigitalEthiopia2030

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አዲስ አመትን አስመክክቶ በተቋሙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞቹ ማዕድ የማጋርት መርሃ-ግብር አካሄደ:: #EIPC ጳጉሜ 4.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ማኔጅመንት አባላት ጳግሜ 4 የሚከበረውን "የህብር ቀን" ምክንያት በማድረግ በኮሌጁ ዝቅተኛ ደመወዝ ለሚያገኙ ሰራተኞች ለአዲስ አመት ማዕድ አጋርተዋል:: በማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብሩ ላይ ለአዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለሰራተኛው ያስተለለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በዛሬው እለት ጳጉሜ 4 የሚከበረውን "የህብር ቀን" አስመልክቶ ይህ ድጋፍ ለማድረግ ስናስብ አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስ መጀመር እንዲያስችለን በቂም ባይሆን ተቋሙ እናንተን ሰራተኞቹን እንደሚያስባችሁ ለማሳየትና በሚችለው አቅም ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም ተቋሙ ላከፋት ወራት መሰል ሰው ተኮር የክረምት በጎ ስራዎች ላይ በሰፊው መንቀሳቀሱን አስታውሰው በዚህም የችግኝ ተከላ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ፣ ለወጣቶች ነፃ የክረምት ሙያ ስልጠና ማሰልጠን የመሳሰሉ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን መቻሉንም ገልዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የኅብር ቀንን በመካፈል፦ የሰው ተኮር አመራር በተግባር ለ118 አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች የበዓል ድጋፍ ተደረገ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት “የኅብር” ቀንን ምክንያት በማድረግ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የቢሮው እና የኮሌጅ ሠራተኞች የማዕድ ማጋራትና የበዓል ድጋፍ ፕሮግራም አካሂደዋል። የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡምሙስጠፋ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት፣ የኅብር ቀን መከበር በዓልን ከማክበር ባሻገር በሥራ ቦታ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና የአብሮነት ባህልን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ነው። ሠራተኞች የተቋማቱ ትልቁ ኃይል በመሆናቸው፣ በተለይም የድጋፍ ፍላጎት ያላቸውን በመደገፍ ሰው-ተኮር የሥራ አካባቢን መገንባት የተቋሙ ትኩረት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት 118 አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች የበዓል ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 346,700 ብር (ሦስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ብር) የበዓል የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ተሰጥቷል። ድጋፉም መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል በጋራ በደስታ ለማክበር ያለመ ሆኗል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም. | ድሬዳዋ

የጅጅጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ #EIPC ጳጉሜ 4.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የጅጅጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ ማካሄድ ችለዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ የEASE ፕሮጀክት ትግበራን ጨምሮ ጠቅላላ በተቋም የተመዘገቡ የአፈፃፀም ውጤቶችን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁ በEASE ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህም በቀጣይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከኮሌጁ ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ጨምሮ ከኮሌጁ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

‹‹ በህብር ቀን ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ ትቀርጻለች›› የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በክረምቱ የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር መሰረት በ
+4
‹‹ በህብር ቀን  ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ ትቀርጻለች›› የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በክረምቱ የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር መሰረት በኮሌጁ ለሚገኙ ዝቅተኛ ደሞዝ ላላቸው ሰራተኞች የማእር ማጋርተ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህ ተገባሩም የማኅበራዊ ኃላፊነት ተሳትፎን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የኮሌጁ ማህበረሰብ  የአብሮነትና የህብረት ማሳያ ነው፡፡ይህ ተግባርም በቀጣይ ጊዜያት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡   የዛሬ በጎነት ለነገ ህይወት መሰረት ነው   የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ነሀሴ 4/2018 ድሬዳዋ

የኅብር ቀን ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች! በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር
የኅብር ቀን ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች! በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል። እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን። በአንድነት ወደ ብልጽግና ጉዟችን እንቀጥላለን። አንድ ህዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ! #EthiopiaPrevails

አቶ ሰኢድ አሊ፦ “የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክቱ ወጣቶችን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነትና ወደ ተግባራዊ የሥራ ዓለም የሚያሸጋግር ድልድይ ነው”   የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስለ ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት አተገባበር የወረዳ አመራርና ባለሞያዎች ስላለባቸው ኃላፊነት የማሳወቂያ መድረክ አካሄደ።   በዚህ መድረክ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ እንደተናገሩት “ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክትን በቁጥር ብቻ ለመፈጸም አንፈልግም። ዋናው ዓላማችን ወጣቶች ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር እንዲፈትኑ፣ የሥራ ልምድ እንዲያገኙና በራሳቸው አቅም ወደ ሥራ ዓለም እንዲገቡ የሚያስችል ዕድል መፍጠር ነው።   በዚህ ሂደት የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ኃላፊነት ትልቅ ነው። ወጣቶችን ቦታ ላይ መመደብ ብቻ በቂ አይደለም፤ የተመደቡበት የሥራ ቦታ ትክክለኛ የልምምድ ዕድል እየሰጠ መሆኑን፣ ወጣቶቹ ክህሎት እያዳበሩ መሆናቸውንና በሂደቱ የሚያጋጥሙ ችግሮች በፍጥነት እየተፈቱ መሆኑን በተግባር መከታተል ይጠበቅብናል።   የሥራ ላይ ልምምድ የሚጠናቀቀው ወጣቱ የልምምድ ጊዜውን ሲጨርስ ሳይሆን፣ ያገኘውን ክህሎት ተጠቅሞ ወደ ቋሚ ሥራ፣ ወደ ሥራ ፈጠራ ወይም ወደ ተሻለ የሙያ ዕድል ሲሸጋገር ነው። ስለዚህ ከምደባ እስከ ክትትል፣ ከልምምድ እስከ ውጤት ድረስ ያለውን ሂደት በተጠያቂነትና በቅንጅት ማስፈጸም ይገባል።   በቀጣይ የምንሠራው ሥራ የወጣቶችን ቁጥር በመጨመር ብቻ አይወሰንም፤ የምንፈጥረው የሥራ ዕድል ጥራት ያለው፣ ውጤት የሚያመጣና ወጣቱን ወደ ዘላቂ የሥራ ዕድል የሚያሸጋግር መሆን አለበት። ይህንን ለማሳካት ቢሮው፣ ወረዳዎች፣ ባለሙያዎችና የሥራ አሰሪ ተቋማት በአንድ የሥራ ሰንሰለት ውስጥ በቅንጅት መሥራት አለብን ብለዋል። ከግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ጎን ለጎን በተጨማሪ የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ለወረዳ የሥራ ማዕከላት ማውረድና ማናበብ የተቻለ ሲሆን ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት በመስጠት ተወያይተውበታል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. | ድሬዳዋ

71.8 ሚሊዮን ብር የፋይናንስ ድጋፍ ለገጠር ኢንተርፕራይዞች ተደረገ 55 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው 671 ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከቆላማ አካባቢዎች ኑሮ መሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት (LLRP II) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም. በገጠር አካባቢዎች የሥራ ዕድል ፈጠራንና የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀትን ለማጠናከር ሰፊ የሥልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ። በዕቅዱ መሠረት በግብርና፣ በንግድና በአገልግሎት ዘርፎች የተሰማሩ 55 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው የሥልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ አግኝተዋል። በዚህም 671 ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸው ታውቋል። ከኢንተርፕራይዞቹ አባላት የተሰበሰበው የቁጠባ ሀብት 6.43 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ከፕሮጀክቱ የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ 71.8 ሚሊዮን ብር መሆኑ ተገልጿል። በዚህም በአጠቃላይ 78.23 ሚሊዮን ብር የቁጠባና የድጋፍ ሀብት መመዝገቡ ታውቋል። የተደረገው ድጋፍ በተለይ የገጠር ነዋሪዎችን በሥራ ፈጠራ ለማሳተፍ፣ የፋይናንስ እጥረትን ለመቅረፍ፣ የኢንተርፕራይዞችን የሥራ አቅም ለማሳደግና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ጉልህ አስተዋፅዖ ማድረጉ ተጠቁሟል። አቶ ሮቤል፦ “ድጋፋችን ከፋይናንስ በላይ የሥራ ፈጠራ አቅምን ለመገንባት ነው” የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የገጠር ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር የሥራ ዕድልን ከመፍጠር ባለፈ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስና የማህበረሰቡን የገቢ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
“የምንሰጠው ድጋፍ የፋይናንስ ሀብት ብቻ አይደለም፤ ተጠቃሚዎች ራሳቸውን ችለው የሚሰሩበትን፣ ገቢ የሚያመነጩበትንና ለሌሎችም የሥራ ዕድል የሚፈጥሩበትን አቅም መገንባት ነው። የገጠር ኢንተርፕራይዞች በተለይ በሥራ ፈጠራና በአካባቢያዊ ሀብት አጠቃቀም ረገድ ትልቅ አቅም አላቸው።”
አቶ ሮቤል አክለውም፣ የተሰጠው ድጋፍ በተጨባጭ የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ እንዲሆን ቢሮው ከፕሮጀክቱ ጋር በመተባበር የክትትል፣ የምክርና የድጋፍ ሥራዎችን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።
“አንድ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅቶ ድጋፍ ማግኘቱ የሥራው መጨረሻ አይደለም። ዋናው ውጤት ድጋፉን በአግባቡ ተጠቅሞ ወደ ምርት፣ ወደ ገቢና ወደ ተጨማሪ የሥራ ዕድል መቀየር ነው። ስለዚህ በቀጣይ የክትትልና የድጋፍ ሥራችንን የበለጠ እናጠናክራለን።”
የ2019 ዓ.ም. ትኩረት፦ 58 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች በቀጣይ ወደ ሥራ ያልገቡ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሥራ ማስገባት፣ የክትትልና የድጋፍ ሥራን ማጠናከር እንዲሁም በ2019 ዓ.ም. 58 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ማደራጀት የቢሮው ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ተገልጿል። የቢሮ ኃላፊው በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎች በቁጥር ላይ ብቻ ሳይሆን በኢንተርፕራይዞች ዘላቂነት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገቢ ማስገኘትና በአካባቢያዊ ሀብት ውጤታማ አጠቃቀም ላይ እንዲመሠረቱ አፅንዖት ሰጥተዋል።
“የ2019 ዓ.ም. ዕቅዳችን ቁጥር ለመሙላት ብቻ አይደለም። የምንደራጃቸው ኢንተርፕራይዞች ዘላቂ ሆነው እንዲቆዩ፣ ሥራ እንዲፈጥሩ፣ ገቢ እንዲያመነጩና በገጠር አካባቢ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን እንዲያፋጥኑ በውጤት ላይ ያተኮረ አሠራር እንከተላለን።”
በዛሬው ዕለት የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም. የትኩረት አቅጣጫ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢሳም ሁሴን፣ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸም በመገምገም በ2019 ዓ.ም. የሚፈጸሙ ተግባራት ላይ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. | ድሬዳዋ