ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 321
订阅者
+124 小时
+67 天
+14830 天
帖子存档
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንት ከEDI ከመጡ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ:: የውይይት መድረኩ ኮሌጁ ከEntrepreneurship Development Institute(EDI)
+1
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንት ከEDI ከመጡ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ:: የውይይት መድረኩ ኮሌጁ ከEntrepreneurship Development Institute(EDI) ጋር በመተባበር ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ሲሰጥ በቆየው የኢንተርፕርነርሺፕ ስልጠና መሰረት በቀጣይ እንደ ተቋም ወደ ተግባር ለማስገባት ያለመ መሆኑም ተገልፇል:: በዚህም በማኔጅመት ደረጃ ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት አስመልክቶ የቀጣይ ትግበራ ዝርዝር እቅድ እዘገጃጀት ላይ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥም ተችሏል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዳር 08/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

ታላቅ ቅናሽ በእጀ ወርቆች የተመረተ ልዩ ልዩ ቦርሳዎችን፣ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ታገኛላችሁ ምርቶቻችን 💼 በቆዳ ውጤቶች የተማሪ ቦርሳ፣የላፕቶፕ ቦርሳ፣
ታላቅ ቅናሽ በእጀ ወርቆች የተመረተ ልዩ ልዩ ቦርሳዎችን፣ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ታገኛላችሁ ምርቶቻችን 💼 በቆዳ ውጤቶች የተማሪ ቦርሳ፣የላፕቶፕ ቦርሳ፣የሴቶች ቦርሳ፣ዋሌት፣ቀበቶ 👗 በአልባሳት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ጋውን፣የ ሰራተኞች ቱታ፣የባህል አልባሳት፣የስፖርት ቁምጣ እና ቲሸርት፣የህትመት ቲሸርቶች፣ስካርፕ እንዲሁም ዘመናዊ አልባሳትን በትእዛዝ እናመርታለን በቡድን ለሚመጡ ደንበኞች ልዩ ቅናሽ እናደርጋልን፡፡ጥራትና ቅልጥፍና መለያች ነው ይምጡ ይዘዙን አድራሻችን ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወደ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ላይ እንገኛለን

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የቢሮውን ሰራተኞች በማስተባበር የኦፊስ ካይዘን ትግበራ አካሄደ። በዚህም ትግበራው ከአስተዳደሩ የካይዘን ኢንስቲትዩት በመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ከዚህ ቀደም በቢሮው የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ግንዛቤ በተፈጠረላቸው መሠረት ውጤት ሊያስገኝ በሚችል መልኩ የተሰራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል። ቢሮው ለሪፎርም ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ መሆኑን አስታውሰው እነዚህም ስራዎች የሆነ ጊዜ ብቻ ተግባር አለመሆኑ በሚያሳይ መልኩ ኦፊስ ካይዘንን በሁሉም የቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ገልጸው ዘወትር አርብ የካይዘን ቀን ተብሎ መሰየሙንና ቀጣይነቱንም የማረጋገጥ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው በቢሮው የካይዘን ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሰላም ደሳለኝ አስረድተዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 8/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የቢሮውን ሰራተኞች በማስተባበር የኦፊስ ካይዘን ትግበራ አካሄደ። በዚህም ትግበራው ከአስተዳደሩ የካይዘን ኢንስቲትዩት በመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ከዚህ ቀደም  በቢሮው የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ግንዛቤ በተፈጠረላቸው መሠረት ውጤት ሊያስገኝ በሚችል መልኩ የተሰራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል። ቢሮው ለሪፎርም ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ መሆኑን አስታውሰው እነዚህም ስራዎች የሆነ ጊዜ ብቻ ተግባር አለመሆኑ በሚያሳይ መልኩ ኦፊስ ካይዘንን በሁሉም የቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ገልጸው ዘወትር አርብ የካይዘን ቀን ተብሎ መሰየሙንና ቀጣይነቱንም የማረጋገጥ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው በቢሮው የካይዘን ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሰላም ደሳለኝ አስረድተዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 8/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የቢሮውን ሰራተኞች በማስተባበር የኦፊስ ካይዘን ትግበራ አካሄደ። በዚህም ትግበራው ከአስተዳደሩ የካይዘን ኢንስቲትዩት በመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ከዚህ ቀደም  በቢሮው የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ግንዛቤ በተፈጠረላቸው መሠረት ውጤት ሊያስገኝ በሚችል መልኩ የተሰራ መሆኑን በቢሮው የካይዘን ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰላም ደሳለኝ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሰላም አክለው ቢሮው ለሪፎርም ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ መሆኑን አስታውሰው እነዚህም ስራዎች የሆነ ጊዜ ብቻ ተግባር አለመሆኑ በሚያሳይ መልኩ የዚህ ትግበራ አካል የሆነው ኦፊስ ካይዘንን በሁሉም የቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 8/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

Beeksisa! Namoota barnootaa fi leenjii ogummaa leenji'uu barbaaddan hundaaf. Bulchiinsa Diree Dawaattii giddu-gala gahoomina Afrikaa baahaa ta'uun tajaajilaa kan jiru koolleejiin pooliteeknika diree dawaa bara barnoota waggaa kanaattii ogumaallee gara garraattin barsiisota muxannoo fi gahumasa gahaa qabniin issiin leenjisuuf qopha'ee issiin eggaa jira. Dammeeleen barnoottaa fi leenjii ittii kenniinuu:- 1. Railway Technology 2. Manufacturing Technology 3. Automotive Technology 4. Electrical Electronics Technology 5. Information Communication Technology 6. Construction Technology 7. Textile Garment Fashion and Leather Technology 8. Surveying and Drafting Technology 9. Wood Work Technology 10. Business and Finance 11. Hotel and Tourism 12. Theater Art 13. Bio medical and HIT

ኤስ ኤን ቪ ኢትዮጵያ ፕሮግራም ከድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በአስተዳደሩ ለሚገኙ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በኢ ኮሜርስና ዲጂታል ገበያ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤ የዛሬው መድረክ ዋና አላማ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ወጣቶችና ሴቶች የሚመሯቸው ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የተሻለ የገበያ አማራጭ የሚያገኙበትን ግንዛቤ በማስጨበጥ በዚህም ዘመናዊ የሆነ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ የኢንተርኔት በይነ መረብን በመጠቀም የሚደረገውን ግብይት እንዲቀላቀሉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርላቸው መሆኑን የፕሮግራሙ ተወካይ አቶ ታጠቅ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡ በአብዛኛው ፕሮጀክቱ አዲስ አበባ ላይ ሲተገበር ቆይቶ አሁን ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ እያመቻቸ የሚገኝ ሲሆን በኢ ኮሜርስና በዲጂታል ገበያው ምን አይነት አማራጭ አለ? አሰራሩ ምን ይመስላል? እንዴትስ መጠቀም ይችላሉ? የሚሉትን ጉዳዮች ተደራራሽ አድርጓል፡፡ በኢ ኮሜርስና ዲጂታል ገበያው ላይ የሚንቀሳቀሱ አሸዋ፣ ሁድሁድ፣ አምራች እና ሉሲ ገበያ የተሰኙ በግል እና በመንግስት የለሙ ዲጂታል ስርዓቶች ኢንተርፕራይዞቹ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉባቸውን አማራጮች በሰፊው ገለጻ ቀርቦ ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ ባሉት አማራጮች እንዳመቻቸው ገብተው አገልግሎትና ምርታቸውን በማስተዋወቅና በመሸጥ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ የፈጠረ የአቅም ግንባታ መድረክ እንደነበር በቢሮው የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሀ/ማርያም ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 5/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአል መከበሩ በአገሪቱን ያለውን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለአገር እድገት በሚል መሪ ቃል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አክብሯል ኢትዮጵያዊ በርካታ ብሄር እና ብሄረሰቦች ለዘመናት በመቻቻል እና በአንድነት አብረው እየኖሩበት የምተገኝ አገር በመሆን ትታወቃለች። በ1987 የፌዴራል ህገመንግስት የፀደቀበትን ቀን መክንያት በማድረግ በየአመቱ የኢትዮጵያን ብሄሮች፣ብሄረሰቦች እና ህዘቦች ቀን በዓል እየተከበረ ይገኛል። ዘንድሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል አዘጋጅነት የሚከበረውን 20 ኹነት በማስመልከት የድሬዳዋ ስራና ከህሎት ቢሮ ስራተኞች በኢትዮ ጣሊያን እና ድሬደዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮልጅ አዳራሽ በዓሉን አከብረዋል። በዘግጀቱ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሀገራችን በርካታ ብሄሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ልዩነታቸውን የጥንካሬቸው ምንጭ በማድረግ በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር በመሆኗ ልዩ ያደረጋታል ብለዋል። የበዓሉ መከበር በሀገሪቱ ያለውን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ያሉት ወይዘሮ ፈጡም አንዳችን የሌላውን ባህል"፣ቋንቋ እና ወግ ማወቅ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ሲሉ ገለፀዋል። የሀገር አንድነትን ለማረጋገጥ የፓለቲካ ልዩነት አያግድም ያሉት ሀላፊዋ የዘንድሮው በዓል የታላቁ ህዳሴ ግድብን ያሳካንበት እና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት የሁሉም የሀገሪቱ ህዞቦች መሆኑ በተገለፀበት ወቅት መሆኑ የተለየ ያደረገዋል ሲሉ አስታውቀዋል ። በመድረኩ የኢትዮጵያ ብሄሮች እና የፌዴራል ሰርአትን የሚገልፅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ©️ DireTv

የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአል መከበሩ በአገሪቱን ያለውን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለአገር እድገት በሚል መሪ ቃል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አክብሯል ኢትዮጵያዊ በርካታ ብሄር እና ብሄረሰቦች ለዘመናት በመቻቻል እና በአንድነት አብረው እየኖሩበት የምተገኝ አገር በመሆን ትታወቃለች። በ1987 የፌዴራል ህገመንግስት የፀደቀበትን ቀን መክንያት በማድረግ በየአመቱ የኢትዮጵያን ብሄሮች፣ብሄረሰቦች እና ህዘቦች ቀን በዓል እየተከበረ ይገኛል። ዘንድሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል አዘጋጅነት የሚከበረውን 20 ኹነት በማስመልከት የድሬዳዋ ስራና ከህሎት ቢሮ ስራተኞች በኢትዮ ጣሊያን እና ድሬደዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮልጅ አዳራሽ በዓሉን አከብረዋል። በዘግጀቱ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሀገራችን በርካታ ብሄሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ልዩነታቸውን የጥንካሬቸው ምንጭ በማድረግ በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር በመሆኗ ልዩ ያደረጋታል ብለዋል። የበዓሉ መከበር በሀገሪቱ ያለውን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ያሉት ወይዘሮ ፈጡም አንዳችን የሌላውን ባህል"፣ቋንቋ እና ወግ ማወቅ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ሲሉ ገለፀዋል። የሀገር አንድነትን ለማረጋገጥ የፓለቲካ ልዩነት አያግድም ያሉት ሀላፊዋ የዘንድሮው በዓል የታላቁ ህዳሴ ግድብን ያሳካንበት እና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት የሁሉም የሀገሪቱ ህዞቦች መሆኑ በተገለፀበት ወቅት መሆኑ የተለየ ያደረገዋል ሲሉ አስታውቀዋል ። በመድረኩ የኢትዮጵያ ብሄሮች እና የፌዴራል ሰርአትን የሚገልፅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ©️ DireTv

ባለብዙ ተሰጥኦው የድሬው ወጣት ክፍል 2 https://youtube.com/watch?v=ACbHftthjpo&feature=shared

ባለብዙ ተሰጥኦው የድሬው ወጣት ክፍል 1 https://youtube.com/watch?v=qhHKBVvgjYE&feature=shared

በኮሌጁ ሰልጥነው ስልጠናቸውን የሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች ኢንዱስትሪውን እንዲያንቀሳቅሱ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ስራ ፈጥረው ኢኮኖሚው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሰልጣኞችን እያፈራ እንዳለ ገለጸ፡፡ #ዜና|የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከEDI ጋር በመተባበር ስልጠና ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች የስራ ፈጣሪነት ስልጠና በዛሬው እለት መስጠት ጀመረ፡፡ ቴክኒክና ሙያ ማለት ለመቀጠር ዝግጁ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ብቻ የሚያፈራ ሳይሆን የራሳቸውን ስራ ፈጥረው ለሌሎችም የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ወጣቶች የሚፈሩበት ትልቅ ተቋም ነው ያሉት በስልጠናው ማስጀመሪያ እለት በመገኘት ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ኢ/ኤ/ቴ/ሽግግር ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ ም/ዲኗ አያይዘውም በኮሌጁ ሰልጥነው ስልጠናቸውን የሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች ኢንዱስትሪውን እንዲያንቀሳቅሱ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ስራ ፈጥረው ኢኮኖሚው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሰልጣኞችን እያፈራ ያለ ትልቅ ኮሌጅ ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም ይህን ስልጠና የወሰዳችሁ ሰልጣኞች በቀጣይ ጊዜያችሁ የራሳችሁን ስራ እንዴት እንደምትፈጥሩ ግንዛቤ የሚፈጥርላችሁ ስልጠና ነው፡፡ስልዚህ ስልጠናውን በአግባቡ እንድትከታተሉ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡ በመጨረሻም በተለያዩ ሙያ እየሰለጠናችሁ እንደመሆኑ መጠን ኮሌጁ በሚያዘጋጃቸው እንዲሁም የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት በሚያዘጋጁት የተለያዩ የስራ ፈጠራ ውድድሮች ላይ እየተሳተፋችሁ በማሸነፍ የራሳችሁን ስራ የምትፈጥሩበትን የገንዘብ ድጋፍ እንድታገኙ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡ ይህ በዛሬው እለት የተጀመረው ስልጠና ከEntrepreneurship Development Institute(EDI) በመጡ አሰልጣኞች እንዲሁም በኮሌጁ በሚገኙ ብቁ አሰልጣኞች አማካኝነት እየተሰጠ ያለ ሲሆን በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ለኮሌጁ ሰልጣኝ ተማሪዎች በየጊዜው እንደሚዘጋጅም ለማወቅ ተችሏል:: የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ህዳር 4/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ ለወቅታዊ ትኩስ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መረጃ You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: t.me/Dire Dawa Polytechnic College TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege Facebook (https://web.facebook.com/Dire)

የፅሁፍ ፈተና ጥሪ!! ከዚህ ቀደም የኢትዮዽያ አየር መንገድ ባወጣው የስራ ማስታወቂያ የተወዳደራችሁ በሙሉ ለፅሁፍ ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝር ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት ቅዳሜ ህዳር 6/2018
+2
የፅሁፍ ፈተና ጥሪ!! ከዚህ ቀደም የኢትዮዽያ አየር መንገድ ባወጣው የስራ ማስታወቂያ የተወዳደራችሁ በሙሉ ለፅሁፍ ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝር ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት ቅዳሜ ህዳር 6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ላይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን። መረጃውን ሼር በማድረግ ይተባበሩ

በአስተዳደሩ የተጀመረው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ቀጥሎ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ በሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አዲስ በተከለሰው የሙያ ደረጃና የሆልስቲክ ምዘና አሰጣጥ ስርዓት የሙያ ምዘና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። በዚህም ከኮሌጆቹ የተወጣጡ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና Practical እና Knowledge Test በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ዲፓርትመንቶች ያልተመዘኑ አሰልጣኝ መምህራን በተመሳሳይ የሚመዘኑ መሆኑን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኃላፊ እና የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 3/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ