1 331
订阅者
+124 小时
+97 天
+8030 天
帖子存档
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+8
በኮሌጁ የተጀመሩ የሪፎርም እና የመደበኛ ሥራዎች ተግባራዊነትን ለመከታተልና ለመደገፍ ባለመውና ከሥራና ክህሎት ሚንስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጣ ልኡክ ቡድን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፋዊ የክዋኔ ኦዲት እና የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት አከናወነ::
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን በውይይቱ ወቅት ሲገልጹ በባለፉት ግዜያት በኮሌጁ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተለይም የትምህርትና ስልጠና፣የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ልማትና የኢንዱስትሪዎችን የተለዋጭ ምርት ማምረት ላይ ኮሌጁ ያለውን ተሞክሮ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ለልኡክ ቡድኑ በመስክ ምልከታ ወቅት እና በግብረመልስ ስብሰባ ወቅት በበቂ ሁኔት አስረድተዋል።
የመሰክ ምልከታውን መሰረት በማድረግም ልኡክ ቡድኑ ኮሌጁ ያለበትን ደረጃ በበቂ ሁኔታ መረዳት እንደቻሉ እንዲሁም ከትምህርትና ስልጠና፣ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ እዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ኮሌጁ ባለው ትስስር አመርቂ ውጤት እያስመዘገባ እንዳለ መረዳት ችለናል ይህን ተሞክሮ ደግሞ ለሌሎች ተቋማት ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የመስክ ምልከታው ዓላማ በዋናነት መልካም አፈፃፀሞችን ማስፋት፣ ማነቆዎችን መፍታት እና ድጋፍ የሚፈልጉ ሥራዎችን ለይቶ በመደገፍ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በክህሎት ልማት፣ ከቴክኖሎጂ ልማት እና የኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ መደላድል ለመፍጠር የሚያስችል የክዋኔ ኦዲት ማድረግ መሆኑን ልኡክ ቡድኑ አስታውቋል::
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ግንቦት 22/2016 ዓ.ም
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቤተል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ትኩረት አድርጎ እየሰራባቸው ከሚገኙ ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመግባታቸው አስቀድሞ ከት/ቤቶች ጋር በመተባበር ለተማሪዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ሲሆን በዛሬው እለትም በቤተል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ለተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማካሄድ ተችሏል::
በመድረኩ ተገኝተው የግንዛቤ ማስጭበጫውን ያካሄዱት የኮሌጃችን ዲኖች ሲሆኑ በመድረኩም ለተማሪዎቹ በቴክኒክና ሞያ ዘርፍ ያሉ ምቹ አጋጣሚዎችን በዝርዝር በማስቀመጥ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲጨርሱ በዘርፉ ሊያገኙ የሚችሉትን ወርቃማ እድል ከወዲሁ ተረድተውት ትክክለኛውን ውሳኔ እንዲወስኑ የሚረዳቸውን መረጃና ግንዛቤ ለተማሪዎች ማስጨበጥ ተችሏል::
ይህን መሰል መድረኮች ቀጣይነት የሚኖራቸው ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ግንዛቤ ከማስጨበት ባሻገር ወደ ኮሌጃችን በመጋበዝ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲሰለጥኑና ለቀጣይ ምዕራፋቸው መሰረት እዲጥሉ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 19/2016 ዓ.ም
በአስተዳደሩ የሚገኙ አገር በቀል እውቀቶችና ክህሎቶች ዙሪያ እየተደረገ ያለው ጥናት የደረሰበት ደረጃ ተገመገመ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ጠቃሚ አገር በቀል እውቀቶችና ክህሎቶች ዙሪያ በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ጥናት መጀመሩ ይታወሳል፤
በዚህም ጥናት በተለይ በበጀት አመቱ በባህላዊ ህክምና (መድሀኒት) እና እደ ጥበብ ላይ እየሰሩ የሚገኙ ባለሙያዎች ቦታቸው ድረስ በመሄድ እና ቃለመጠይቅ በማድረግ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን መሰብሰብ ተችሏል፤
ስለሆነም ጥናቱ ምን ደረጃ ላይ እንደ ደረሰ በዛሬው ዕለት የተገመገመ ሲሆን በቀጣይ ጥናቱ ሲጠናቀቅ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማለትም በመደበኛም ሆነ በአጫጭር ስልጠና ውስጥ እንዲካተት በማድረግ የስራ ዕድል ፈጠራውን በማገዙ ረገድ የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ እንደሚሆን የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ቡድን መሪ ወ/ሮ አለምፀሃይ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ግንቦት 19/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ስራ እምቅ አቅም ያላቸውን የኮሌጅ፣ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ኢንተርፕራይዞችን ያሳተፈ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በዘርፉ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን እና ባለሙያዎች እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡
ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ውድድር በማጠናቀቂያው የአሰልጣኝ መምህራንና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ለውድድሩ በተመረጡ ዳኞች ፊት ቴክኖሎጂዎቻቸውን በማቅረብ ተወዳድረዋል የቴክኖሎጂ ውድድሩን በበላይነት የሚያጠናቅቁ ተወዳዳሪዎችም በአስተዳደር ደረጃ እውቅና እና ማበረታቻ የሚደግላቸው ይሆናል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ግንቦት 15/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
#ዜና | የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ፥ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፥ 'ብሩህ' የተሰኘ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር አካሄደ።
ውድድሩ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች፥ ሀሳባቸውን ወደ ተግባር መለወጥ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው ተብሏል።
የድሬዳዋ ስራ፥ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ ቢሮው የአስተዳደሩን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ ለዜጎች የስራ እድል የመፍጠርና የማመቻቸት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፥ በዚህ ውድድሩ የተሳተፉ ወጣቶችን በሀሳብ ከመደገፍ በተጨማሪ ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በቢሮው የስራ እድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰኢድ አሊ በበኩላቸው፥ በውድድሩ የተሻለ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ መኖሩን ከማሳየት ባሻገር፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ የሚሆኑ የድሬዳዋ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች እንደሚወጡ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ፥ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባዘጋጀው ውድድር ላይ የተሳተፉ ተወዳዳሪዎች ፥ ፕላስቲክን መልሶ የመጠቀም ቴክኖሎጂ፥ የዲጂታል ህክምና አገልግሎት እና የአልባሳት ንድፍ ሥራን ጨምሮ በርካታ የፈጠራ ሀሳቦችን ማቅረባቸው ታውቋል።
©️ ድሬ ቲቪ
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት በድሬዳዋ አስተዳደር የሁለተኛ ዙር ትግበራ የህይወት ክህሎት ስልጠና ወስደው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ኢንደስትሪዎች ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የስራ ልምምድ እንዲያደርጉ ገለጻ ስለ ተቋሞቻቸው በማብራራት ወደ ስራ የማስገባት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ራስዎን ከህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች እና አጭበርባሪዎች ይጠብቁ!
ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረግ የሥራ ሥምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ክብር የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ የታገዘ የምዝገባ ሥርዓት አልምቶ ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
በዚሁ ሥርዓት ላይ ተመዝግበው መስፈርቱን ያሟሉ በርካታ ዜችን ህጋዊ መንገድን በመከተል በተለያዩ መዳረሻ አገሮች ለሥራ ማሰማራት ተችሏል፤
ይሁን እንጂ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ስም የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ምዝገባ እናካሄዳለን በማለት ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል፡፡ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በህግ እንዲጠየቁ ተገቢውን ክትትል እያደረግን እንገኛለን፡፡
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎቱን ለማግኘት ዜጎች ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቁ መሆኑን አውቀው ከህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ እናሳስባለን።
በአንፃሩ ክፍያ የሚጠይቁ አካላትን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥቆማ መሰጫ ስርዓት https://pfs.mols.gov.et/ ወይም በስልክ ቁጥር +251116671356 እንዲሁም በተዋረድ ላለው የዘርፉ መዋቅር ወይም በአቅራቢያችሁ ለሚገኙ የሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንድትሰቱን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በውጭ ሀገር ሥራ ሥራ ስምሪቱ ለመጠቀም ፍላጎት ያላችሁ ዜጎች ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ( https://lmis.gov.et/ ) መመዝገብ እና አስፈላጊውን ሙያዊ ስልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚህ ውጭ በሆነ ህገ-ወጥ መንገድ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረግ ጉዞ የከፋ ችግር ውስጥ የሚጥል መሆኑን በመገንዘብ ዜጎች ህጋዊ አማራጮችን ብቻ እንዲጠቀሙ እናሳስባለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በአካባቢችሁ ወደሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢዎች ወይም የሥራና ክህሎት ፅ/ቤቶች በመሄድ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ስርዓተ ስልጠናዎች(ስርኣተ ትምህርቶች)፤ ማስልጠኛ መርጃ መሳሪያዎች እና የአሰልጣኙ መምሪያዎች እንዲሁም በአሰስመንት ፓኬጆች ላይ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያ ቤት ማዕከል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም አሰልጣኞች እና ስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፤
ይህም ስልጠና በዋናነት በማረሚያ ቤቱ በተለይም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንቅስቃሴን ለመደገፍ ቢሮውና በስሩ የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ሲያደርጉ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ በማስቀጠል የተቋሙ አሰልጣኝ መምህራን እና የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ጊዜው የሚጠይቀውን እና የሚፈልገውን ክህሎት ተላብሰው ተልዕኮ መፈጸም እንዲችሉ ታስቦ በአጠቃላይ ስልጠና አሰጣጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ግንቦት14/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ