ch
Feedback
ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

前往频道在 Telegram

የአለም አቀፍ ( የአስመጪና ላኪነት) ንግድ Import Export 📝ሥልጠና 🖍Training 💼ማማከር 📒Consultancy 👷‍♀️ሙሉ ስራ 👷‍♂️Outsource ስለ ስልጠናችን ለማወቅ @sebeztrainingbot www.sebeztraining.com/courses www.sebeztraining.com

显示更多
2 724
订阅者
-224 小时
+57 天
+1630 天
帖子存档
ሰበዝ ስልጠና እና ማማከር ለመላው ቤተሰቦቹ እና ኢትዮጵያዊያን አዲሱ ዓመት 2019 የሰላም፣ የፍቅር ፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንለዎ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ሰበዝ ስልጠና እና ማማከር ለመላው ቤተሰቦቹ እና ኢትዮጵያዊያን አዲሱ ዓመት 2019 የሰላም፣ የፍቅር ፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንለዎ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያሳየችው ተሳትፎና የንግድ እንቅስቃሴ ስኬት ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያሳየችው ተሳትፎና የንግድ እንቅስቃሴ ስኬት። ​(አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም) የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት በአህጉሪቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ለማሳደግና የጋራ ገበያ ለመፍጠር አልሞ ወደ ትግበራ መግባቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሂደቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። ​ስምምነቱ በአጠቃላይ 54 አባል ሀገራትንና 1.3 ቢሊዮን ህዝቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፤ የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በእርስ ንግድን በ52 በመቶ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያም ይህንን ታሪካዊ ስምምነት በቀዳሚነት ከፈረሙ ሀገራት አንዷ ስትሆን፣ እ.ኤ.አ በ2019 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጽድቃ ወደ ተግባር ገብታለች። ​እስካሁን ባለው ሂደትም ስምንት ፕሮቶኮሎች ላይ ድርድሮች የተካሄዱ ሲሆን፣ በቅርቡ በተደረገው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የአእምሯዊ ንብረት መብትና የዲጂታል ንግድ ፕሮቶኮሎች መጽደቃቸው ለንግድ እንቅስቃሴው መጠናከር ትልቅ እመርታ ሆኖ ተመዝግቧል። ​በንግድ ትግበራው ረገድ ኢትዮጵያ የታሪፍ ሰንጠረዧንና የአገልግሎት ንግድ የቃል ኪዳን ሰነዷን አጠናቃ በማቅረብ ቴክኒካዊ ምርመራዎችን ያለፈች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 9 ቀን 2025 በይፋ ንግድ መጀመሯ ይታወሳል። ሙሉውን ለማንበብ

Ethiopia targets China trade gap with export drive By our staff reporter Ethiopia is stepping up efforts to narrow its wideni
Ethiopia targets China trade gap with export drive By our staff reporter Ethiopia is stepping up efforts to narrow its widening trade deficit with China by using new duty-free market access, domestic economic reforms and export-promotion initiatives to expand sales to the world’s second-largest economy. https://capitalethiopia.com/2026/08/23/ethiopia-targets-china-trade-gap-with-export-drive/

ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርትና ተያያዥ አገልግሎቶች 474 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ ++++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት፣ ከሀገር ውስጥ ዳታ ማይኒንግና ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሽያጭ 474 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለጋዜጣ ፕላስ እንዳስታወቁት፣ ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የሚሆነው በቀጥታ ለጎረቤት ሀገራት ከተደረገ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የተገኘ ነው። ቀሪው በሀገር ውስጥ ሆነው የውጭ ምንዛሬ ከሚከፍሉ የዳታ ማይኒንግና የቴክኖሎጂ ተቋማት የተሰበሰበ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስርን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዋና ተዋናይ ሆና እያገለገለች መሆኗን ያነሱት አቶ ሞገስ፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ጅቡቲና ኬንያ የሚደረገው የኃይል ኤክስፖርት በተሳካ ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ከኬንያ ጋር ያለው የኃይል ትስስር አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት እየታየበት እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። በሁለቱ ሀገራት ስምምነት መሠረት በከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ሰዓታት እስከ 200 ሜጋ ዋት እንዲሁም በዝቅተኛ የፍላጎት ሰዓታት ደግሞ 65 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እየቀረበ ይገኛል። የኃይል አቅርቦቱ የኬንያን የኤሌክትሪክ ሲስተም መረጋጋት ከማስጠበቅ ባሻገር፣ ሀገሪቱ ከውጭ ከምታስገባው ኢነርጂ እስከ 90 ከመቶ የሚሆነውን ከኢትዮጵያ እንድታገኝ አስችሏታል። በሌላ በኩል፣ ወደ ሱዳን ይደረግ የነበረው የኃይል ኤክስፖርት ሀገሪቱ በገባችበት የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፤ በጦርነቱ ምክንያት በሱዳን በኩል ያለው የኢነርጂ ተሸካሚና አስተላላፊ መሠረተ ልማቶች በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው የኃይል አቅርቦቱ ሊቆም ችሏል። ከሱዳን ጋር የተፈጠረው የኃይል መቋረጥ ከመሠረተ ልማት ጋር ብቻ የተያያዘ እንጂ ከቀደመ ክፍያ ወይም ከውዝፍ ዕዳ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑን አስታውቀዋል። የሀገር ውስጥ የኃይል ማመንጨት አቅምን በተመለከተ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከተያዘለት እቅድ ውስጥ 99 ነጥብ አምስት ከመቶ ያህሉን በማሳካት ከፍተኛ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። ሀገሪቱ ካመነጨችው አጠቃላይ 35 ቴራ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 51 ነጥብ አምስት ከመቶውን ወይም ከግማሽ በላይ የሚሆነው የተመረተው ከሕዳሴው ግድብ መሆኑንም አቶ ሞገስ ተናግረዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ባሻገር፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰጥቶ መቀበል መርኅ ላይ የተመሠረተ የኢኮኖሚና የሰላም ትስስር ለመፍጠር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የአፍሪካ ኅብረት የ“አጀንዳ 2063” አካል የሆነውን የፋሲሊቲዎችና የመሠረተ ልማት ትስስር ግብ ለማሳካት ኢትዮጵያ የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች መሆኗን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ ከኃይል ሽያጭ የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ በሀገር ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት አሁን ካለበት 54 ከመቶ ለማሳደግና አዳዲስ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግም ገልጸዋል። በዮርዳኖስ ፍቅሩ

በ"Export to China" መድረክ ከ340 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያስገኙ 33 የንግድ ለንግድ (B2B) ስምምነቶች ተፈራረሙ። የኢፌድሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ታሪካዊው የ"Export to China" መድረክ በይፋ ተጀምሯል። የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የቻይና አስመጪዎችና የሀገራችን ላኪዎች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፤ ይህ መድረክ የኢትዮጵያና የቻይናን ዘላቂና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ላቀ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር የሚያሸጋግር እንዲሁም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አገራዊ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ የማስተዋወቅ (የፕሮሞሽን) ሥራ ዋና አካል መሆኑ ገልፀዋል። የቻይና አስመጪዎች ጥራት ያላቸውን የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንን በስፋት እንዲገዙ ለማድረግ የሚያስችሉ የፕሮሞሽን ስራዎችን መከወናቸውን ገልጸዋል። ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም፣ በመድረኩ በተፈጠረው ምቹ የገበያ ትስስር ከ340 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው 33 የንግድ ለንግድ (B2B) የግብይት ኮንትራቶች መፈረማቸውን አብራርተዋል። እነዚህ ስምምነቶች የቡና፣ የሰሊጥ፣ የአኩሪ አተር፣ የጨርቃጨርቅ እና የማዕድን ምርቶችን ወደ ውጪ ለመላክ የሚያስችሉ ሲሆኑ፤ ይህም የሀገራችንን የወጪ ንግድ ገቢ ግኝት በእጅጉ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል ብለዋል። የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የንግድ ሚኒስቴር የውጭ ንግድ ዲፓርትመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቻንግ ሁይ (Mr. Chang Hui)፤ የቻይና መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር አጠናክሮ ለመቀጠል እና የገበያ ዕድል ይበልጥ ለማስፋፋት ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጸዋል። አክለውም የቻይና አስመጪዎች ጥራት ያላቸውን የኢትዮጵያ ምርቶች በስፋት ለመግዛትና ዘላቂ የንግድ ድልድይ ለመገንባት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

Ethiopia's Horticulture Exports Generate $490 Million, Sector Targets $575 Million Next Fiscal Year #EBR_News Jul 24, 2026 Ethiopia's horticulture sector generated $490 million in export earnings during the 2025/26 fiscal year, with the government setting a target to increase revenues to $575 million in the coming fiscal year as it seeks to strengthen the country's foreign exchange earnings through higher-value agricultural exports. According to the Ministry of Agriculture, flower exports accounted for $412 million of the total revenue, while vegetables generated $57 million and fruit exports contributed $21 million. For the 2026/27 fiscal year, the Ministry plans to export 357,457 tones of flowers, vegetables and fruits to achieve the $575 million revenue target, representing an increase of about 17% over this year's . Source ETHIOPIAN BUSINESS REVIEW NEWS

አሜሪካ ሀገር የሚካሄደውን ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንስ በአሜሪካን ሀገር ሚያሚ ከተማ 30ኛው የምግብ እና መጠጥ የንግድ ትርኢና ኮንፈረንስ እ.ኤ.አ ከመስከረም 10-15 ቀን 2026 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምከር ቤት ንግድ ትርዒት እና ኤክስፖ በማስተባበርየቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሜሪካን ሀገር በሚካሄደው የንግድ ትርዒትና ኮንፈረንስ ላይ የሚሳተፉ ዘርፎች ቡና ላኪዎች፣ የምግብ እና መጠጥ አስመጪ እና ላኪዎች፣ የግብርና ውጤቶች አምራች እና ላኪ ፣ አግሮ ኢንዱስትሪ እና የምግብ ማቀነባበሪያ አምራች እና ላኪ፣ አልኮል እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች አምራች እና ላኪ፣ አትከልቶች እና ፍራፍሬዎች አምራች እና ላኪ፣ ኦርጋኒከ ምግብ አምራች እና ላኪ፣ ጣፋጭ ምግቦች አምራች እና ላኪ፣ ቅመማ ቅመም አምራች እና ላኪ ፣ኢንጀራ እና ባህላትና ውጤቶች እና በተመሳሳይ ዘርፎች የተሰማሩ የሀገራችን ባለሃብቶች እንድትሳተፉ እየገለጽን ለመሳተፍ ፍለጉት ያላችሁ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች፡- 1. የተሳትፎ ፎርሙን በጥንቃቄ መሙላት 2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ 3. የታደሰ ንግድ ምዝገባ ኮፒ 4. የፓስፖርት ኮፒ 5. ከሚሰሩበት ድርጅት የድጋፍ ደብዳቤ 6. የድርጅቱ ተቀጣሪ ከሆኑ ከገቢዎች ቢሮ የደመወዝ ግብር መከፈላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 709፣ 716 በአካል በመቅረብ ወይም በኢሜይል ethiochamberevent@gmail.com በመላከ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ድረስ ይመዝገቡ፡፡ #Ankuaru

ከንግድ ሚኒስቴር ማበራዊ መገናኛ ያገኘነው መረጃ፡- • የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ በወጪ ንግድ ዘርፍ ከ10.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማስገኘት የዕቅዱን 114 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ የወጪ ንግድ ታሪክ አዲስ ሪከርድ በመስበር ከፍተኛው የገቢ መጠን ሆኖ መመዝገቡን • የኢትዮ-ኬንያ የጠረፍ ንግድ መመሪያ ጸድቆ በይፋ ሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑና በጠረፍ ንግድ ሥርዓቱ ውስጥ ሊገበያዩ የሚችሉት 50 አይነት ምርቶች ሲሆኑ ግብይቱ ሊፈጸም የሚችለው ከኢትዮጵያ እና ከኬንያ የድንበር በር ጀምሮ በኢትዮጵያ በኩል 50 ኪሎ ሜትር፤ በኬንያ በኩል ደግሞ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ባሉ የጠረፍ አካባቢዎች እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

አሜሪካ ከኢትዮጵያ በሚገቡ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ መሣሪያዎች ላይ ምርመራ መጀመሯ ተገለፀ ሲል አዲስ ሰታንዳርድ ዘገበ:: የአሜሪካ የንግድ መምሪያ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የሲሊኮን የፀሐይ ኃይል ማመንጫ መሣሪያዎች ላይ ሀገር አቀፍ ምርመራ መጀመሩን የፀሐይ ኃይል ኢንዱስትሪ መረጃ ምንጭ የሆነው ሶላር ፓወር ወርልድ ዘገበ። ምርመራው የተጀመረው ስምንት የአሜሪካ የሶላር አምራቾች በቻይና የተመረቱ የሶላር ምርቶች በአሜሪካ የተጣለባቸውን ታሪፍ ለማለፍ በኢትዮጵያ በኩል ኤክስፖርት እየተደረጉ ነው የሚል ቅሬታ መቅረባቸውን ተከትሎ ነው። ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ቶዮ (Toyo) እና ኦሪጅን ሶላር (Origin Solar) የተሰኙ ሁለት አምራቾች፣ ከቻይና የሚመጡ ግብዓቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይል መሣሪያዎችን እንደሚያመርቱና ከዚያም በኢትዮጵያ ወይም በቬትናም ተገጣጥመው ወደ አሜሪካ እንደሚላኩ ገልጸዋል። ሙሉውን ከአዲስ ሰታንዳርድ ለማንበብ https://addisstandard.com/Amharic/?p=13450

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ወደ አውሮፓ የሚገባ ቡና ከደን ጭፍጨፋ ነጻ ኾኖ እንዲመረት በሚያስገድደው ሕጉ ውስጥ የሚሟሟ ወይም የሚነከር ቡናን አካተተ። ኮሚሽኑ ከሦስት ዓመታት በፊት ባወጣው የደን ጭፍጨፋ ሕጉ ያካተተው፣ አረንጓዴ ወይም የተቆላ ቡናን ብቻ ነበር። የአውሮፓ ቡና ፌደሬሽን፣ በአውሮፓ የቡና አስመጪዎች መካከል ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር የሚሟሟ ቡና በሕጉ ውስጥ እንዲካተት ግፊት ሲያደርግ ነበር። ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመትታት ወዲህ ወደ ውጭ የምትልከውን የሚሟሟ ቡና መጠን ጨምራለች።ዋዜማ

መግለጫ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎች እና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት (ESW)በኩል እንዲያገኙ ፈቀደ
መግለጫ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎች እና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት (ESW)በኩል እንዲያገኙ ፈቀደ

Sebez Training Import Export Procedures and Documentation Training For Beginners የአስመጪ እና ላኪነት ስልጠና ለጀማሪዎች Reserve your spot
+1
Sebez Training Import Export Procedures and Documentation Training For Beginners የአስመጪ እና ላኪነት ስልጠና ለጀማሪዎች Reserve your spot for the upcoming training • Weekend Group Class • Monday- Friday Mini Group • VIP/Personal • Online Our Program will start on • Weekend Sat July 14, 2026 • Weekday Mini Group July 14, 2026 • VIP/ Personal any time • Online July 27, 2026 Main Training Contents • Export Import License process • Export Import licensing institutions and their responsibility • Export Import Documentation • Transportation and Logistics • Payment Methods • Export Import Procedures • Ethiopian Single window System • Ethiopian customs procedures Mobile 0923753535 0908097709 Email:- sebeztraining@gmail.com Telegram:- @sebeztraining Website:- sebeztraining.com Physical Address:- Megengna around Diaspora square Lion Ethiopia bldg. 3rd floor 306

ለጥራጥሬ እና ቅባት እህል ላኪዎች የ2019 በጀት ዓመት የስራ እቅድ( Business Plan) ፎርማት

ለአስመጪና ላኪዎች መልካም ዜና በብሔራዊ ባንክ ገዢ ዛሬ ሀምሌ 6/2018 መገለጫ የተሰጠበት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባደረገው ሰብሰባ ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክረ ሃሳብ እንዳቀረብ እና ተቀባይነት አግኝተው ከፀደቁ ውስደጥደ ለአስመጪ እና ላኪዎ ጠቃ የሚባሉ 3 ለውጦች ውስጥ 1. ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘም ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ኮሚሽንን ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ ዝቅ አድርጓል። 2. ላኪዎች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ለባንክ የመሸጥ ግዴታ (Surrender requirement) ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ በማድረግ 3. ቀድሞ የነበርው የባንኮች የማበደር ጣሪያ ( credit cap) ተነስቷል https://www.tiktok.com/@sebeztraining/video/7662066940067826964?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7658108297735980560

ጋዜጣዊ መግለጫ | የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባ ቁ.7
+3
ጋዜጣዊ መግለጫ | የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባ ቁ.7

ኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ ስጋ መላክ ጀመረች የሚል ሰፊ ዜና እየተነገር ቢሆንም የግብርና ሚኒስቴር ምንም አይነት የስጋ ምርት ኢምፖርት ህጋዊ ፍቃድ አልሰጠሁም ብሏል ሲል ካፒታል ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡