ch
Feedback
TMPC 1917

TMPC 1917

关闭频道
1 149
订阅者
无数据24 小时
-37
-1830
帖子存档
https://vm.tiktok.com/ZS9eB43Em1EPe-S0zPG/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቀድሞ የተፈሪ መኮንን ት/ቤት ማህበር የኢትዬጲያ ቻፕተር ስብሰባ አካሄደ ። 🇪🇹የካቲት 14/2018 ዓ.ም🇪🇹 በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስም ያለው የቀድሞው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት፣ የአሁኑ ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር የቦርድ ስብሰባውን በድምቀት አካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ በተለያዩ ዘመናት በትምህርት ቤቱ ያለፉ የቀድሞ ተማሪዎች፣ የማህበሩ አባላት እና የቦርድ መሪዎች ተገኝተዋል። የኮሌጅ ስልጠና አካ/ጉ/ም/ዲን እና ጊዚያዊ የኮሌጁ ዋና ዲን ተወካይ አቶ ደመላሽ ተስፋዬ መድረኩን የእንኳን ደና መጣችሁ መልክት አስተላልፈዋል ። የዕለቱ ዋነኛ ክንውን ላለፉት ዓመታት ማህበሩን በፕሬዘዳንትነት ሲመሩ የቆዩት የዶ/ር ብስራት አክሊሉ ስንብት እና የምስጋና ሽኝት ሲሆን ዶ/ር ብስራት ለማህበሩ እና ለተቋሙ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ቀርቦላቸዋል። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብስራትን በመተካት አቶ ደጀኔ ተዘራ የማህበሩ አዲስ የቦርድ ፕሬዘዳንት በመሆን በይፋ ስራ ጀምረዋል። አቶ ደጀኔ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ውስጥ በተማሪነትም ሆነ በአስተማሪነት ያገለገሉ አንጋፋ ባለሙያ ሲሆኑ፣ ባደረጉት ንግግር የቀድሞው ፕሬዘዳንት ለተቋሙ ላከናወኑት አመርቂ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በመድረኩም በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመገንባት በሂደት ላይ ለሚገኘው አዲስ ህንፃ ማስፈጸሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ተካሄዷል። ማህበሩ የጀመራቸው የልማት ስራዎች ከግብ እንዲደርሱ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ሁሉም የቀድሞ የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ለማህበሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉና ከማህበሩ ጎን በመቆም የታሪካዊውን ተቋም ክብርና ልማት እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ተላልፏል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://vm.tiktok.com https://t.me/EntotoPtc1917 https://youtube.com/@entototms https://www.facebook.com ከኮሚኒኬሽን ቡድን

photo content
+8

photo content
+3

+2

photo content

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የISO 21001:2025 ዓለም አቀፍ የጥራት ሰርተፍኬት  አገኘ፡፡ 🇪🇹  የካቲት  13 /2018 ዓ.ም🇪🇹 በሀገራችን የትምህርትና የሥልጠና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል  በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያውን የISO 21001:2025 (Educational Organizations Management System - EOMS እውቅና በማግኘት ቀዳሚው ተቋም ሆኗል። ይህ ዓለም አቀፍ ሰርተፍኬት ለማዕከሉ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል። የISO 21001:2025 እውቅና የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት የአሰራር ሥርዓት እና የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት የሚያሟሉበት መንገድ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ መመዘኛ ነው። የISO 21001:2025 ሰርተፍኬት ተቋሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሥልጠና ጥራት፣ የባለድርሻ አካላትን እርካታ ያረጋገጠ ተገልጋይ ተኮር አሰራር እና ቀጣይነት ያለው የማሻሻል ብቃት እንዳለው የሚያረጋግጥ   ነው። ስኬቱ ማዕከሉ ለሌሎች ተቋማት አርአያ በመሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራትና የልህቀት ማዕከልነቱን በተጨባጭ ለማስመስከር ያስችለዋል። ሰርተፍኬቱ ማዕከሉ ላለፉት ዓመታት በአሰራር፣ በሰው ኃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ሲያደርግ የቆየው ከፍተኛ ጥረት ውጤት ነው።  እውቅናው ተቋሙ ወደፊት ለሚሰጣቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች እንዲሁም ለኢንዱስትሪው የሚሰጠው የምርታማነት ማሻሻያ ድጋፍ ትልቅ የሞራልና የሙያ ስንቅ ይሆናል። ‹‹ከፍታን ማጽናት፤ነገን ማላቅ›› ተጨማሪ  መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ  👉 Tiktok https://www.tiktok.com/@bols20116?_t=ZM-8y9L28EOubG&_r=1 👉Facebook https://www.facebook.com/addisababatvetbureau 👉Telegram https://t.me/AABOLS 👉YouTube https://youtube.com/channel/UCvdSuxRP-cMVC7-lSv2fxag?si=YiWZURWWlmGDBPjv 👉website https://aabols.gov.et 👉ለቅሬታ፣ አስተያየትና ጥቆማ https://complain.aabols.gov.et 👉ለነፃ የስልክ ጥሪ 6524

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በሽሮሜዳ ካምፓስ ለሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ !! 🇪🇹የካቲት 13/2018 ዓ.ም🇪🇹 የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ለማሸጋገር ስልጠና በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በሽሮሜዳ ካምፓስ ለሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ ። ስልጠናው ለተከታታይ አምስት ቀናት የተሰጠ ሲሆን በዋናነት በንግድ ስራ ክህሎት፣ በንግድ እቅድ አዘገጃጀት እና በስራ ፍለጋ ስልቶች ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ሰልጣኞቹ በቆይታቸው የራሳቸውን የንግድ ስራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን መሰረታዊ እውቀት ያገኙ ሲሆን 245 ወንድ እና 1298 ሴት በድምሩ 1543 ሰልጣኞች ስልጠናውን አጠናቀዋል ። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://vm.tiktok.com https://t.me/EntotoPtc1917 https://youtube.com/@entototms https://www.facebook.com ከኮሚኒኬሽን ቡድን

photo content
+3

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኞች የክላስተር የክህሎት ውድድር ተካሄደ። 🇪🇹የካቲት 12/2018 ዓ.ም🇪🇹 በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2018 ዓ.ም የሚካሄደውን የክህሎት ውድድር አስመልክቶ፣ በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስተናጋጅነት የክላስተር የክህሎት ውድድር በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። በውድድሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር (ኢ/ኤ/ቴ/ሽ) ዲን አቶ ወንድም ሲያምረኝ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ለተወዳዳሪዎች ገለፃ (ኦረንቴሽን) በመስጠት ውድድሩን በይፋ አስጀምረዋል።አስጀምረዋል ተወዳዳሪ ሰልጣኞች በየዘርፎቻቸው የክህሎት ብቃታቸውን የሚያሳዩ የፈጠራ ስራዎችንና ተግባራዊ ስራዎችን ለታዛቢዎችና ለዳኞች አቅርበዋል። በውድድሩ ወቅትም ሰልጣኞች ከፍተኛ መነሳሳት የታየባቸው ሲሆን፣ በሁሉም የውድድር ዘርፎች ሙሉ ተሳትፎ ተደርጓል። ይህ የክላስተር ውድድር በዘርፉ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለመለየትና ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተሳታፊዎችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://vm.tiktok.com https://t.me/EntotoPtc1917 https://youtube.com/@entototms https://www.facebook.com ከኮሚኒኬሽን ቡድን

photo content
+4

photo content
+9

መልካም እድል!!
መልካም እድል!!

photo content

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በሽሮሜዳ ካምፓስ ለሁለተኛ ዙር ለ1580ሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተጀመረ !! 🇪🇹የካቲት 09/2018 ዓ.ም🇪🇹 የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ለማሸጋገር ስልጠና በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በሽሮሜዳ ካምፓስ መሰጠት ተጀመረ ። ይህ ስልጠና ዜጎች ከስራ አጥነት ወጥተው በራሳቸው አቅም የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የታለመ መሆኑ ተገልጿል። ስልጠናው ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሲሆን በዋናነት በንግድ ስራ ክህሎት፣ በንግድ እቅድ አዘገጃጀት እና በስራ ፍለጋ ስልቶች ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ሰልጣኞቹ በቆይታቸው የራሳቸውን የንግድ ስራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን መሰረታዊ እውቀትና ተወዳዳሪ ሆኖ የመቅረብ ክህሎት እንዲያዳብሩ አቅም ይፈጥራል።በዚህ የክህሎት ማበልጸጊያ መርሃ-ግብር ላይ የተሳተፉ በአጠቃላይ 1,580 ሰልጣኞች ከጉለሌ ክፍለ ከተማ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://vm.tiktok.com https://t.me/EntotoPtc1917 https://youtube.com/@entototms https://www.facebook.com ከኮሚኒኬሽን ቡድን

photo content
+9