ሰዋስው ☘☘☘☘
前往频道在 Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
显示更多1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለደብረ ሊባኖስ ሁለተኛ መምህር (እጨጌ) ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍት በኋላ ለተሾሙ ለአቡነ እጨጌ ኤልሳዕ ለዕረፍት መታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ኤልሳዕ እጨጌ ዘተክለ ሃይማኖት፦ ሀገራቸው ሸዋ ነው። በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን የነበሩ ሲሆን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው ደብረ ሊባኖስ ገዳም በእጨጌነት የተሾሙ የመጀመሪያ ዕጨጌ ናቸው። አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከማረፋቸው በፊት "በእኔ መንበር ኤልሳዕ ይሾም ነገር ግን ዘመኑ ትንሽ ስለሆነ ከእርሱ ቀጥሎ ፊሊጶስን ትሾማላችሁ" ብለው ለቅዱሳን ተከታይ ሐዋርያቶቻቸው ተናግረው ነበር።
❤ በዚህም መሰረት አቡነ ኤልሳዕ ተሹመው ብዙም ሳይቆዩ አንድ ዲያቆን ሞተና ሊቀብሩት ሲወስዱት በመንገድ ላይ ሳለ ድንገት ከሞት ተነስቶ "አባቴ ተክለ ሃይማኖት ኤልሳዕ አሁን ወደ እኔ ስለሚመጣ ፊሊጶስን ሹሙት ብለህ ተናገር ብለውኝ ነው" ብሎ ከተናገረ በኋላ ተመልሶ ዐርፎ፡ ቀበረ። አቡነ ኤልሳዕም ወዲያው ዐርፈው አቡነ ፊሊጶስን 3ኛ ሆነው ተሾሙ
❤ አቡነ ኤልሳዕም ከተጋድሎአቸው ብዛት የተነሳ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ጎናቸውን አሳርፈው ተኝተው አያውቁም ነበር። ነገር ግን ማረፍ ሲኖርባቸው በወንበር ላይ ተደግፈው ትንሽ ብቻ ያርፋ፡ በር። አቡነ ኤልሳዕም በሞት ያረፉትም እንደልማዳቸው ጎናቸውን ሳያሳርፉ በወንበር ላይ እንደተደገፉ ነበር። አባታችን ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ እንዲህ ይሉ ነበር "ነፋስ ትጋትን ትወዳለች፣ ሥጋ ግን ይደክማል። ለመነኰሳትና፡ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ መኝታ ማብዛት አይገባቸውም መኝታ ማብዛት ህልምን ያመጣል ነፋስን ይጎዳል ሰውነትንም ያደክሜል"።
❤ አቡነ ኤልሳዕ በዘመናቸው ወንጌልን በማስተማርና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ይታወቁ ነበር። እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ እሳቸውም ሙት አስነስተዋል ባሕር እየከፈሉ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ያሻግሩ ነበር። በጸሎታቸው የዠማን ወንዝ ለሁለት የከፈሉ ታላቅ አባት ናቸው። ከአባታችን ከእጨጌ አቡነ ኤልሳዕ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን መጽሐፍና ቅዱሳት በዓላት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
"ምስጢረ ሜሮን ለምን?" ሼር ማያደርግ እንዳይኖሮ❗️
ይህቺ ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት? ይህችስ ሰዓት ምን ያህል የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት። ይህን መሥዋዕቱን የሚሰውርባትና የሚያከብርበት።
የእግዚአብሔር ሰላም ከእኔ እና ከእናንተ ጋር ይሆን ዘንድ ጸልዩ።
ሥርዓተ ቅዳሴ
እንኳን ለዚህች ቀን አደረሳችሁ ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለ፫ተኛ ጊዜ የቅብዓ ሜሮን ዝግጅት እና ሥርዓተ ጸሎት እየተከናወነ ይገኛል።
ስለ ዝግጅቱ ከመጻፌ በፊት በአንዳንዶቻችሁ ላይ ግርታን ስለፈጠረ ግልጽ አድርጌ ልለፍ። ብዙዎች እንደጠየቃችሁኝ ይህ ምስጢረ ሜሮን ነው ታድያ ምስጢር ከሆነ ለምን አዘገጃጀቱን አስተላለፉ የሚል ነው አያይዤ ልመልስ።
ምስጢረ ሜሮን -ከ፯ቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ሲሆን አፈጻጸሙም ከማይደገሙ ሥርዓቶች አንዱ ነው። ሜሮን ማለት የግሪክ ቃል ሲሆን "ቅብዕ" ማለት ነው።
ታድያ ምስጢር ከተባለ ለምን በግልጽ ይታያል የሚል ጥያቄ ሊፈጥርብን ይችላል ነገሩ እንዲህ ነው ሁለት አይነት ምስጢር አለ የሚታይ ምስጢር እና የማይታይ ምስጢር።
-የሚታይ ምስጢር ማለት ስርዓቱ የሚታይ ነገርግን አፈጻጸሙ ምስጢር የሆነ ማለት ነው ይህም ማለት ለምሳሌ - ምስጢረ ጥምቀትን ብንወስድ የጥምቀት ሥርዓቱ በገሃድ የሚታይ ነው አፈጻጸሙ ግን ምስጢር ነው ። ምስጢረ ተክሊልን ብናይ ሥርዓቱ ግልጥ ነው አፈጻጸሙ ግን ምስጢር ነው። ምስጢረ ሜሮንም እንደዛው ብዙዎቹን መጥቀስ ይቻላል ምስጢር ያሰኛቸው አፈጻጸማቸው ነው ያም ማለት ወደ ቅድስና በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚለወጥ አይታወቅም እረቂቅ ነው ለማለት ነው መለወጡን በዓይነ ሥጋ ልናይ አንችለም የቅድስና ደረጃዎችን ይፈልጋል ማለት ነው ታድያ ይህም ዛሬ የተከናወነው ምስጢር ልክ እንደጠቀስኩት ነው።
-ሁለተኛው የማይታይ ምስጢር ሲሆን ይህም ምስጢረ ክህነትን የሚጠይቅ የተሰወረ የተሸሸገ አስፈሪ ለተመረጡ ብቻ የተፈቀደ ሰማያዊ ሥርዓት ህግ እና ስጦታ ነው በከፊል ለማመልከት ያህል በመቅደስ ተከልሎ ይኖራል።
ልብ በሉ ይህ ምስጢረ ሜሮን እጅግ ከባድ ይህም ሥርዓቱ መፈጸም የሚችለው በቤተክርስቲያን እና በካህናት ብቻና ብቻ ነው ዲያቆኑም ቢሆን አይደለም መንካት ማስቀመጫውን መያዝም አይችልም ማያዝም ሆነ መንካት መቀባት የሚችሉት ከዲቁና ማዕረግ ከፍ ያሉ ናቸው።
አዘገጃጀቱም ልክ እንደዛው ነው በሊቃነ ጳጳሳት በብጹአን አባቶች በቤተክርስቲያን እና በቤተክርስቲያን ብቻና ብቻ ነው ይህም የራሱ የሆነ ሱባኤ እና ጸሎተ ሜሮን አለው ብጹአን አበው በመሰብሰብ ተከፋፍለው ጸሎት ያደርጋሉ ዕጣን ያጥናሉ ምህላ ያደርሳሉ ሌሎቹ የዝግጅት ሂደቱን ይፈጽማሉ ልብ በሉ ሁሉም ደረጃ እና ቅደም ተከተል አለው እንደየ ጸሎቱ ይከናወናል ወደ ሁሉም አብያተክርስቲያናት ይላካል። ይህ ሥርዓት ነው ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለ፫ተኛ ጊዜ የተከናወነው ከዚህ ቀደም ይህ ከግብፅ ተዘጋጅቶ ይመጣ የነበረ ሲሆን ለሃገራችን በረከት እና ሰላም እንዲልክልን ብጹዕ አባታችን በገለጡት መልዕክት ምዕመናን እና ካህናት ጨምሮ ለ፯ ተከታታይ ቀናት በጸሎት እንዲተባበሩ ከተደረገ በኋላ ማለዳ ፲ ሰዓት ላይ ሥርዓቱ ተጀምሯል።
የቅብዐ ሜሮን አገልግሎት
- በቤተክርስቲያን የተለያዩ አዳዲስ ንዋየቅድሳት ሲመጡ /መስቀል ጻሕል ጽዋ ጽርፈ መስቀል መሶበ ወርቅ የመሳሰሉት በጸሎተ ሜሮን ተቀብተው ይከብራሉ።
- አዲስ ቤተክርስቲያን ታንጾ ሲያበቃ በጸሎት ተባርኮ ቅብዐ ሜሮን ይቀባል።
- አዲስ መንበር እና ታቦት ቅብዐ ሜሮን ተቀብተው ይከብራሉ።
- የጸጋ ልጅነት የሚያሰጥ ምስጢር ስለሆነ በጥምቀት ጊዜ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም የተጠመቁ ምዕመናን ሜሮን ሲቀቡ መንፈስቅዱስ ያድርባቸዋል።
ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሲሆን ለማጣቀሻነት ጥቂት ጥቅሶችን ልተውላችሁ። ፩ኛ ዮሐ ፪÷፳-፳፯ ዘጸ ፴÷፳፪-፳፭ ፩ኛ ሳሙ ፲÷፩ ፩ኛ ነገሥ ፲፱÷ ፲፭ ዘሌ ፰÷፲፪ መመልከት ይቻላል ይህቺ ቤተክርስቲያን የጸጋ ግምጃቤት ናት ሥርዓቷም ፍጹም ሰማያዊ ነው አምልኮቷም አንድ ነው። አምላከ ቅዱሳን በረቱን አያሳጣን ለሃገራችን ምህረት ይላክልን እያልኩ እኔ በዚህ ተሰናበትኩ።
በጸሎት የምንለምን እና የምንማልድ ሁላችንንም በሠላም በመንፈስ ይጠብቀን ፍቅርንም ይስጠን ዓይነ ልቡናችንንም ያብራልን...!
እዩ ዘአማኑኤል / #Eyu16_21
የጸሎት ሂደቱን ለማየት ኮሜንት ላይ ሊንክ አስቀምጫለሁ!
1 161
14/2/2015 ዓ.ም (፲፬/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ።
ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፡፡ መዝ. 18፥3
🕯 ትርጉም
ነገር የለም፤ መናገርም የለም፤ ድምፃቸውም አይሰማም።
ድምፃቸው በምድር ላይ ተሰማ።
ቃላቸውም ሁሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነ ለብልሁና ለጥበበኛው ለወንጌላዊው ለሐዋርያው ለቅዱስ ሉቃስ በንጉሥ ኔሮን ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለየዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ሉቃስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፋ ከአራት መቶ ሰባ ሰባት ሰዎች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤"ሰላም ለሉቃስ ወንጌላዊ ዘተናገረ ሐዲሰ ቃለ፤ እስከ አዳም ላዕለ"። ትርጉም፦ ትውልድን እስከ ላይኛው አዳም የቈጠረ፤ ዐዲስ ቃልን የተናገረ ለኾነ ለወንጌላዊ ሉቃስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ ሉቃስ ጠቢብ፡እምወንጌላውያን አሐዱ"። ትርጉም፦ ከወንጌላውያን አንዱ ዐዋቂ ሉቃስ በእጁ ለሣላት ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል። መልክአ ሥዕል።
+ + +
❤ ብልህ ጥበበኛ የሆነ ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ፦ ይህም ቅዱስ የከበረ ወንጌል ከመዘገባቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው። እርሱም ወንጌልን ስለማስተማር በሥራው ሀሉ ሐዋርያት ጴጥሮስንና ጳውሎስን የሚአገለግላቸው ሆነ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈ ሉቃስ ነው።
❤ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ስለዚህም ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ስለ ሐዋርያው ሉቃስ እንዲህ ብለው ጮኹ "ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው"። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።
❤ ሐዋርያ ቅዱስ ሉቃስም ከዚህ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ። በዚያም ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘ። መጻሕፍቱንና ደብዳቤዎቹን ሰጠው "ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱሃልና" እሊህን መጻሕፍት ጠብቃቸው አለው።
❤ በንጉሥ ኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ "በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው" አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ "ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም" ብሎ መለሰለት።
❤ ንጉሥ ኔሮንም ሁለተኛ እንዲህ አለው "እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ" ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ "ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ"። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። ከዚህም በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
❤ ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሉቃስን ሥጋ በማቅ አይበት ውስጥ አድርገው ወደ ባሕር ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ አንድ ደሴት ደረሰ። ምእመናንም አግኝተው ወስደው ገነዙት በአማረ ቦታም አኖሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያ ቅዱስ ሉቃስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 22 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለሉቃስ እንተ ረትዐ ልሳኑ። ወንጌለ መለኮት ይጽሐፍ እምእለ ብዙኃን ወጠኑ። ከመ ያርኢ ኀይለ ቅድመ ኔሮን ወተዐይኑ። አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ። እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ሥልጣኑ"። ትርጉም፦ ብዙዎች ሊጽፋት የዠመሩት ከመኾኑ የተነሣ የመለኮትን ወንጌልን ይጽፍ ዘንድ አንደበቱ ለቀና ለሉቃስ ሰላምታ ይገባል፤ በኔሮንና በሰራዊቱ ፊት ኀይልን ያሳይ ዘንድ የተቈረጠች ቀኝ እጁን ለያት መልሶም አጣበቃት በርሱ ላይ የክርስቶስ ሥልጣን ተጨምሯልና። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት22።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ይኩን ሰላም በኃይልከ። ወትፍሥሕት ውስተ ማኅደረ ክበዲከ። በእንተ አኀውየ ወቢጽየ። መዝ 121፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቈላ 4፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥1-6። የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የወንጌላዊው የቅዱስ ሉቃስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
እንደ እግዚአብሔር መልአክ ያማረ ነበር። በሹመቱም ጥቂት ዘመናት ከኖረ በኋላ ከመንበረ ሢመቱ እስከ አራቀው ድረስ በላዩ ሰይጣን ምክንያትን አመጣ።
❤ ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ማርቆስ ዘመን በግዛቱ ውስጥ ያሉ እስላሞች ስለ ዐመፁበት የኢትዮጵያ ንጉሥ ፈጅቷቸው ነበርና ስለዚህ በግዛቱ ውስጥ በሚኖሩ እስላሞች ላይ ክፉ እንዳያደርግ ለኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክት እንዲልክ ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን የምስር ንጉሥ አዘዘው።
❤ አባ ማርቆስም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ ስለሚላኩ ሰዎች ከመኳንንቱ ከኤጲስ ቆጶሳቱና ከሀገር ታላላቆች ሽማግሌዎች ጋር ተማክሮ እሊህን ብሩሀን ከዋክብት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስን የምስር ኤጲስቆጶስ አባ ሳዊሮስን በእውቀታቸው በአስተዋይነታቸውና በቅድስናቸው መረጡአቸው ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥም ይሔዱ ዘንድ ግድ አሏቸው።
❤ እነርሱም ታዛዦች ሁነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ የኢትዮጵያ ንጉሥም መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው እሊህንም ቅዱሳን አባቶች ይቀበሏቸው ዘንድ አሽከሮቹን በቅሎዎችን አስይዞ ላከ በመጡም ጊዜ በታላቅ ደስታ ሰላምታ አቀረበላቸው ከእርሳቸውም ቡራኬን ተቀበለ ታላቅ ክብርንም አከበራቸው ። እነርሱም የሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን ደብዳቤ ሰጡት እርሱም ተቀብሎ አንብቦ ለሊቀ ጳጳሳቱ ቃል ታዛዥ መሆኑን ገለጠላቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 21 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኪ ገነተ ሚዓ ወሰሊክ። ዘኢያይበሰኪ ነፋሰ መርቄ ወደደክ። እማእሠረ ጌጋይ ፍትሐኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክ። እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማእሠር ድሩክ። ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላእክ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት21።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10 ወይም 104፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57 ወይም ዮሐ 11፥38-46።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኀ። ወአንተ ገበርከ አድባረ ወምድረ ኵሎ። ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ"። መዝ 73፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 7፥1-14፣ ራዕ.ዮሐ 21፥21-ፍ.ም፣ የሐዋ.ሥራ 22፥1-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥25-34። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመታሰቢያ በዓል፤ የነቢዩ የቅዱስ ኢዩኤል የዕረፍት በዓል፣ የማኅሌተ ጽጌ አራተኛ ሳምንትና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ተአምራት አድርጋ ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስን ከእስራት ቤት ላአዳነችበት በዓል፣ ለነቢዩ ቅዱስ ኢዩኤል ለዕረፍት በዓል፣ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ካስነሣው ለቅዱስ አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር ወደ ቊስጥንጥንያ ለፈለሰበት፣ ለከበረች አገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት ለሆነ ለቅዱስ አባት ለአባ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከምትታሰበው፦ አምላክ ከወለደች ከቅድስት ድንግል ከእመቤታች ማርያም ከወራዊ በዓሏ መታሰቢ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፮ "በጊዜሁ ሐለፈ ክረምት ቆም በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጐታት ክርስቶስ ሠርዐ ሰንበት ነአኵቶ ለዘጸገወነ ሠናይቶ። ትርጉም፦ በጊዜው ክረምት አለፈ ተከተቸ፣ በረከት ተገኘ፣ እነሆ አበቦች አበቡ፣ በሽቱ ገነት ውስጥ ናርዶስ አፈራ፣ ሎሚ ከተርክ ጋር አፈራ፣ በጎውን የሰጠንን ሰንበትን የሰራውን ክርስቶስን እናመሰግነዋለን። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተአምራት አድርጋ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ማትያስን ከእሥራት ቤት እንዳዳነች፦ የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
❤ ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡
❤ ሐዋርያው ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ ጌታችንና ወደ እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡
❤ ሐዋርያውቅዱስ እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለሦስት ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና "በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ" በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡
❤ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡ ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት እመቤታችን ለእኛም ትለመነን!።
+ + +
❤ "ሰአሉ ለነ ነቢያት ስኩራነ መንፈስ ምሉኣን ሞገስ አቅርንተ ሥሉስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ የሥላሴ ነጋሪቶች (ዐዋጅ ነጋሪዎች) የምትኾኑ ክብርን የተመላችኊ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኛችኊ ነቢያት ለምኑልን ለእኛ አማልዱን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ላይ።
+ + +
❤ ነቢይ ቅዱስ ኢዩኤል፦ ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ።
"ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ"።
❤ ሁለተኛም እንዲህ አለ "ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል"።
❤ ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ "ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል"። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥቅምት 21 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ኢዩኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ከቆጵሮስ አገር ወደ ቊስጥንጥንያ መፍለስ፦ ከክርስቲያን ነገሥታትም አንዱ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቊስጥንጥንያ አፈለሰው። ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ውስጥ ሁኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ "ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው"።
❤ ይህንንም በአዩ ጊዜ ደስ ተሰኙበት ተሸክመውም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረ ቦታም አኖሩት በዚችም ቀን በዓልን አደረጉለት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አልዓዛር ጸሎት ይማረን።
+ + +
❤ ኢየሩሳሌም ሊቀ አገር ጳጳሳት አባ ዮሐንስ፦ ይህም አባት ያረፈው እግዚአብሔርን በሚወድ የንጉሥ ሰይፈ አርዕድ ደግሞ ቈስጠንጢኖስ ለሚባል ልጁ በሆነ በንጉሣችን በዳዊት ዘመን ነው።
❤ ይህም ቅዱስ ከምስር አገር ታላላቆች እግዚአብሔርን የሚፈሩ የክርስቲያኖች አባቶች ልጅ ነው። የዲቁና መዓረግንም ለመሾም እስከ ተገባው ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት። ከዚህም በኋላ በዲቁናው ሹመት አገልግሎቱን በአሳመረ ጊዜ የቅስና መዓረግ የሚገባው ሁኖ ቅስና ተሾመ።
❤ በጾም በጸሎት እግዚአብሔርንም በመፍራት የተጠመደ ሁኖ ድኆችንና ችግረኞችን የሚወዳቸው የሚረዳቸው ሆነ ያን ጊዜ የሐዋርያት የሆነች የጵጵስና ሹመት የምትገባው ሁና በከበረች አገር በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ ሕዝቡንም በፈሪሀ እግዚአብሔርና በትሕትና የሚያስተምራቸው ሆነ።
❤ እነርሱም ስለ ቅድስናው እጅግ የሚወዱት ሆኑ መልኩና የአንደበቱ አገላለጥ
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሉቃ. 4:27-33 "ወብዙኃን እለ ለምጽ ሀለው"- "በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም። በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህን ሰምተው ቍጣ ሞላባቸው፥ ተነሥተውም ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፥ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤ እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ። ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤ ቃሉ በሥልጣን ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ። በምኵራብም የርኵስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፥ በታላቅ ድምፅም ጮኾ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
