ሰዋስው ☘☘☘☘
前往频道在 Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
显示更多1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1 161
20/2/2013 ዓ.ም (፳/፪/፳፻፲፫ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
አርውዮ ለትለሚሃ።
ወአሥምሮ ለማዕረራ።
ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ። መዝ. 64፥10
🕯 ትርጉም
ትልሟን ታረካለህ።
ቦይዋንም ታስተካክላለህ።
በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 19:26-ፍ፡ም፡ "ወእምዝ አውሥአ ጴጥሮስ" - "ኢየሱስም፡እነርሱን፡ተመልክቶ፦ይህ፡በሰው፡ዘንድ፡አይቻልም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ግን፡ሁሉ፡
ይቻላል፡አላቸው። በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡መልሶ፦እንሆ፥እኛ፡ሁሉን፡ትተን፡ተከተልንህ፤ እንኪያስ፡ምን፡እናገኝ፡ይሆን? አለው። ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦እውነት፡እላችኋለሁ፥እናንተስ፡የተከተላችሁኝ፥በዳግመኛ፡ልደት፡የሰው፡ልጅ፡በክብሩ፡ዙፋን፡በሚቀመጥበት፡ጊዜ፥እናንተ፡ደግሞ፡በዐሥራ፡ሁለቱ፡የእስራኤል፡ነገድ፡ስትፈርዱ፡በዐሥራ፡ኹለት፡ዙፋን፡ትቀመጣላችሁ። ስለ፡ስሜም፡ቤቶችን፡ወይም፡ወንድሞችን፡ወይም፡እኅቶችን፡ወይም፡አባትን፡ወይም፡እናትን፡ወይም፡ሚስትን፡ወይም፡ልጆችን፡ወይም፡ዕርሻን፡የተወ፡ሁሉ፡መቶ፡ዕጥፍ፡ይቀበላል፡የዘለዓለምንም፡ሕይወት፡ይወርሳል። ነገር፡ግን፥ብዙዎቹ፡ፊተኛዎች፡ኋለኛዎች፥ኋለኛዎችም፡ፊተኛዎች፡ይሆናሉ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
20/2/2015 ዓ.ም (፳/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ምህረኒ እግዚኦ ፍኖተ ጽድቅከ።
ወአኅሥሣ በኲሉ ጊዜ፡፡
አለበወኒ ወእኅሥሥ ሕገከ። መዝ. 118፥33
🕯 ትርጉም
አቤቱ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ። ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።
ሕግህንም እፈልጋለሁ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
ተ ይህ አባ ዕገሌ ነው ብሎ አስረዳው ረድኡም መልአኩን እንዲህ ብሎ ጠየቀው "ይህ በፊታቸው ያለ ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚበራ ማን?" ነው መልአኩም "የመነኰሳቱ ሁሉ አባት አባ እንጦንስ ነው" ብሎ መለሰለት።
❤ ወደ በዓቱም ያ ረድእ በገባ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ እንዳረፈ አባ ዮሐንስን አገኘውና ታላቅ ልቅሶን በላዩ አለቀሰ ከዚያም በኋላ ወደ መነኰሳቱ መንደር ፈጥኖ በመሔድ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐፂር እንደ ዐረፈ ነገራቸው። እነዚያም መነኰሳት አክብረው ገንዘው ሥጋውን ተሸክመው ወስደው በቦታቸው አኖሩት። የደረቀ ዕንጨት ተክሎ በአበቀለበት ላይ በሠራት የራሱ በሆነች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልጆቹ ከዚህ አፍልሰው ወስደው እስከ አኖሩት ድረስ በዚያ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለኤልሳዕ ነቢይ ዘኀይለ ጸሎቱ ዐቢይ ዘዐቀመ ማየ ዮርዳኖስ ለፌ ወለፌ፤ በቅርፍተ ዕፅ እማይ ዘአወጽአ ማሕጼ፤ ዘረሰያ ሰማይ መሪር ጥዕምተ፤ መዊቶሂ ዘአንሥአ በድነ ምውተ"። ትርጉም፦ የጸሎቱ ኀይል ደገኛ የኾነ፤ የዮርዳኖስን ወንዝ ወዲያና ወዲኽ ያቆመ፤ በዕንጨት ቅርፊትም ከውሃ ውስጥ መጥረቢያን ያወጣ፤ መሪር ውሃን ጣፋጭን ያደረገ፤ ሙቶ ስንኳ የሙቱን በድን ላነሣው ለነቢዩ ለኤልሳዕ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤልሳዕ፦ የዚህም ነቢይ የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ ማለት ነው። እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል። የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን "ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ" አሉት ኤልሳዕም "ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ" አላቸው እነርሱም አመጡለት።
❤ ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ "እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት አለ" አላቸው።
❤ ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ። የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል። የትንቢቱንም ወራት ፈጽሞ በሰላም ረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ሰላም እብሎ በሕቁ። ለዮሐንስ ሐፂር ዘነዊኅ ኂሩተ ጽድቁ። እምትርሲተ ዓለም ማሳኒ በዘይርኅቁ። ከመ ያለብዎሙ ለእለ ኃሠሡ ወጽሕቁ። ግብረ ምንኵስና ርእየ ቀዊሞ ዕራቁ። ትርጉም፦ የጽድቁ በጎነት የረዘመ ለኾነ ለዮሐንስ ሐፂር በእጅጉ (በአያሌው) ሰላም ሰላም እለዋለኍ፤ ከሚጠፋው ዓለም ጌጥ (ክብር) በሚርቁ ገንዘብ ለፈለጉና ለሹ ልብ እንዲያስደርጋቸው ራቊቱን ቆመ የምንኲስና ግብርን አየ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 20።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ምህረኒ እግዚኦ ፍኖተ ጽድቅከ። ወእኅሥሣ በኵሉ ጊዜ። አለብወኒ ወእኅሥሥ ሕገከ"። መዝ 118፥33-34። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥27-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "አርውዮ ለትለሚሃ። ወአሥምሮ ለማእረራ። ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ"። መዝ 64፥10። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥11-25፣ 1ኛ 4፥6-12 እና የሐዋ ሥራ 20፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥27-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የአባ ዮሐንስ ሐፂርና የዕረፍት በዓል፣ የነቢዩ የቅዱስ ኤልሳዕ የመታሰቢያ በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ ለትሕትናና ለትዕግስተኛው አባት ለክቡሩ፤ ለገናና ለሆነ ለአባ ዮሐንስ ሐጺር ለዕረፍት በዓልና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ ለሆነ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ኤልሳዕ ለልደቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ ሐጺር ትሩፈ ምግባር፤ ዘአጥረየ ትሕትና ወወረሰ ልዕልና"። ትርጉም፦ ትሕትናን ገንዘብ አድርጎ ልዕልናን የወረሰ መልካም ሥራው የበዛ ለኾነ ለዮሐንስ ሐጺር ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።
+ + +
❤ አባ ዮሐንስ ሐፂር፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ ከላይኛው ግብጽ ናቸው እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው ግን ከእርሱ በቀር ልጅ የላቸውም የዚህ ዓለምም ብልጽግና ቢሆን የላቸውም ነገር ግን በበጎ ሥራ ባለጸጎች ናቸው ይህንንም ቅዱስ እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት።
❤ የዚህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ሲሆነው የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሥታው የመላእክት የሆነ አስኬማን ይለብስ ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ ይኸውም የምንኵስና ልብስ ነው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ አባ ባይሞይ የሚባለውን አንዱን አረጋዊ አባት ተገናኘው ዮሐንስም ሰገደለትና ወደ እርሱ እንዲቀበለው ለመነው ሽማግሌውም አባት "ልጄ ሆይ ያንተ በዚህ መኖር ልክ አይደለም በዚች ገዳም የሚኖሩ በእጆቻቸው ይሠራሉ በቀንና በሌሊት ይጾማሉ ይጸልያሉ በሚተኙም ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ ይተኛሉ አንተ ወጣት ጎልማሳ ስለሆንክ ይህን ሁሉ ችግር አትችልም። ነገር ግን ወደ ዓለም ተመልሰህ እንደ ሰው ሁሉ በጎ አኗኗርን ትኖር ዘንድ ይሻልሃል የዚች ገዳም ኑሮ ጭንቅ ነውና" አለው።
❤ አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው እኔ በጥላህ ሥር ልኖር መጥቼአለሁና ስለ እግዚአብሔር ብለህ ተቀበለኝ እንጂ አትመልሰኝ ይህም አባ ባይሞይ እግዚአብሔርን ሳይጠይቅ ምንም ሥራ አይሠራምና በዚያን ጊዜ ሥራውን ይገልጥለት ዘንድ ስለ ዮሐንስ ሐፂር እግዚአብሔርን ለመነው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦለት "እርሱ የተመረጠ መሳሪያ ይሆናልና ተቀበለው ብሎሃል" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ሐፂርን ወስዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባው የምንኵስና ልብሶችንም አምጥቶ በላያቸው ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ጸለየ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾ በመስቀል ምልክት በልብሶቹ ላይ አማተበ ሽማግሌውም እነዚያን ልብሶች ለአባ ዮሐንስ አለበሰው።
❤ ከዚያቺም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ ተጋድሎንና አገልግሎትን ጀመረ አባ ባይሞይም ሊፈትነው ወደደ በአንዲትም ቀን ደብድቦ "ከአንተ ጋር መኖር አልሻም" ብሎ ከበዓቱ አስወጥቶ አባረረው የከበረ አባ ዮሐንስም ከሜዳ መካከል በውጭ ቆመ በየቀኑም በጥዋት እየወጣ "ከእዚህ ላይህ አልሻም" እያለ ይመታዋል እርሱ ግን "አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ" ብሎ ከእግሩ በታች ይሰግዳል። በሰባተኛዪቱም ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሔድ ሽማግሌው አባ ባይሞይ ወጣ አባ ዮሐንስንም ሰባት መላእክት ከበው አክሊላትን ሲያቀዳጁት አያቸው ከዚያንም ጊዜ ወዲህ መፈተኑን ተወው ወደ መኖሪያውም አስገባው።
❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ ዕንጨት አግኝቶ ወስዶ ለአባ ዮሐንስ ሰጠውና "ይህን ዕንጨት ትከለው እስከሚበቅልና እስከሚአፈራ ድረስ ውኃን አጠጣው" አለው። አባ ዮሐንስም ለአባቱ ታዛዥ በመሆን ተቀብሎ ወስዶ ተከለው በየቀኑም ሁለት ሁለት ጊዜ ያጠጣዋል ውኃውም ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል የራቀ ነው። ከሦስት ዓመትም በኋላ ያ ዕንጨት አቈጥቊጦ በቀለ ታላቅም ዛፍ ሁኖ አብቦ ጣፋጭ ፍሬን አፈራ። አባ ባይሞይም ከፍሬው ለቅዱሳን አረጋውያን ወሰደላቸውና "የታዛዡንና የትሑቱን ፍሬ እነሆ ብሉ" አላቸው እነርሱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው አደነቁ ለመምህሮቻቸው ለሚታዘዙ እንዲህ ያለ ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
❤ አባ ባይሞይም ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል በጽኑዕ ደዌ ውስጥ ተይዞ ኖረ አባ ዮሐንስም ያገለግለው ነበር አባ ዮሐንስን እንደፈተነው የተመረጠ መሥዋዕትን ይሆን ዘንድ በዚህ ደዌ እንዲፈተን እግዚአብሔር ፈቅዷልና። በሚሞትበትም ጊዜ አባ ባይሞይ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትን ሰበሰባቸውና አባ ዮሐንስንም እጁን ይዞ "እርሱ ሰው ያይደለ መልአክ ነውና ተቀብላችሁ ጠብቁት" ብሎ ሰጣቸው። እርሱንም ደግሞ እንዲህ አለው "ከዕረፍቴ በኋላ ያን ዕንጨት ወደ ተከልክበት ቦታ በዚያ ኑር እግዚአብሔር ላንተ ያዘጋጀልህ ነውና ብዙዎችም በአንተ እጅ ይድናሉ መታሰቢያህም በዚያ ጸንቶ ይኖራል ዜናህም በዓለም ሁሉ ይወጣል" ይህንንም ተናግሮ ዐረፈ አክብረውም ቀበሩት።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባ ዮሐንስ አረጋዊ አባቱ አባ ባይሞይ እንደነገረው ወደዚያ ቦታ ሒዶ ኖረ ዜናውም በዓለም ሁሉ እጅግ እስከ ተሰማ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። በራሱ ቤተ ክርስቲያንም አበ ምኔት ሁኖ ተሾመ በሹመቱም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ እጆቹን በራሱ ላይ ሲጭን "አክዮስ አክዮስ አክዮስ" የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ ይህም "ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል" ማለት ነው። የቊርባን ቅዳሴን በሚቀድስ ጊዜ ቅዱስ ቊርባንን መቀበል የማይገባቸውን ይለያቸዋል "ዛሬስ ሒዳችሁ ንስሓ ግቡ ከዚያም በኋላ ተመልሳችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ" ይላቸዋል።
❤ ይህን አባ ዮሐንስንም ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ የቅዱሳን የሠለስቱ ደቂቅን ሥጋቸውን እንዲአመጣለት ወደ ባቢሎን ልኮታል ይህም በግንቦት ወር በዐሥረኛው ቀን ተጽፎአል።
❤ በአንዲትም ዕለት አንድ መነኰስ ሊጎበኘው ወደ በዓቱ ቢመጣ አባ ዮሐንስን ተኝቶ አገኘው የእግዚአብሔርም መላእክት በላዩ ይጋፉ ክንፎቻቸውንም ያርገበግቡ ነበር አንዱም ሌላውን "ተወኝ ክንፌን በላዩ ላኑር ይለዋል" ይህንንም አይቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው ።
❤ ከዚህም በኋላ የመነኰሳቱን መንደር ሊበረብሩ የበርበር አረማውያን ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ አባ ዮሐንስም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ወደ ቁልዝም ሔደ በዚያም በአባ እንጦንስ ገዳም በጎኑ በአለ ቦታ ተቀመጠ እስከ ሚያርፍባትም ቀን ድረስ የሚያገለግለው አንድ የታመነ ሰውን እግዚአብሔር አመጣለት።
❤ ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ እግዚአብሔር ቅዱሳን ጻድቃኖቹን አባ እንጦንስን፣ አባ መቃርስን፣ አባ ጳኵሚስን ከእርሳቸውም ጋር መንፈሳዊ አባቱ አባ ባይሞይን ያረጋጉትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መለየቱን ይነግሩት ዘንድ ወደርሱ ላካቸው። እነርሱም እንዲህ ብለው አረጋጉት "ደስ ይበልህ እግዚአብሔር የማያልቅ ተድላ ደስታን አዘጋጅቶልሃልና" ክብር ይግባውና ጌታችንም እንዳዘዘ "በእሑድ ቀን ሁለተኛ ወዳንተ መጥተን ወደ ዘላለም ሕይወት እንወስድኻለን" ባርከውትም ከእርሱ ዘንድ ተመለ።
❤ በዐርብ ቀንም አገልጋዩን ወደ አንድ ቦታ ላከው ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ በእሑድም ቀን ሌሊት ዶሮ ሲጮህ እሊያ ቅዱሳን ከሁሉም ቅዱሳን ማኅበር ጋር መጡ የመላእክትም ሠራዊት ሁሉ ወደርሱ መጡ በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን ሰጠ መላእክትም እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ነፍሱን አሳረጓት በዚያንም ጊዜ ረድኡ መጣ ነፍሱንም ከበው እያመሰገኑ ሲያሳርጓት የጻድቃንና የመላእክትን ማኅበር አይቶ እያደነቀ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ። ከመላእክትም አንዱ ወደርሱ መጥቶ የቅዱሳንን ስማቸውን በመጥራት በጣቱ እያመለከ
1 161
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ማህሌተ ጽጌ ዘራብዕ ሳምንት
☘☘☘☘☘☘☘☘☘
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ (፪) እመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡
@EOTCW
@EOTCW
✴️ነግስ፦
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCW
🌱ዚቅ
ሃሌ ሉያ ይኬልልዋ መላእክት በውስጠ ውሳጤ መንጦላእት ለቅድስት ማርያም ነቢያት ወሐዋርያት ወሰማእትኒ ያሰምኩ ባቲ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ወማህደሩ ለልዑል
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ጽጌ
ናሁ ጸገየ ወወሀበ መአዛ፤ ተአምርኪ ናርዶስ ለቤተክርስቲያን ዘይሔውዛ፤እንዘ ታረውጽኒ ሊተ ማርያም በፍኖተ ሎዛ፤ አጕይዪኒ ከመ ወይጠል ወከመ ኃየል ወሬዛ፤እምገጸ ኃጢአት እኅተ አርዌ ዘይቀትል ሕምዛ
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ናሁ ጸገየ ወወሀበ መአዛ ናሁ ጸገየ/2/
ተአምርኪ ናርዶስ ለቤተክርስቲያን ዘይሔውዛ ለቤተክርስቲያን/2/
@EOTCW
🌱ዚቅ
ነፍሳተ ጻድቃን አውያን አመ ይሁቡ መአዛ ለዘምግባረ ጽድቅ አልብነ ይኩነነ ቤዛ ንግደትኪ ማርያም እስከ ደብረ ቊስቋም እምሎዛ
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ጽጌ
ሰመዩኪ ነቢያት እለ ርእዩ ኅቡአት፤ገነተ ጽጌ ዕፁተ ወኆኅተ ምስራቅ ኅትመተ፤ እግዚአብሔር ወሀበ ለቤተ ዳዊት ትንቢተ፤ከመ ትጸንሲ ድንግል ወትወልዲ ሕይወተ፤ ኢሳይያስኒ ነገረ ክሡተ
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ነቢያት ሰመዩኪ እለ ርእዩ ኅቡአት ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ/2/
ገነተ ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወኆኅተ ምስራቅ/2/
@EOTCW
🌱ዚቅ
መሰንቆሁ ለዳዊት ወአክሊሉ ለሰሎሞን ገነት ዕፁት አዘቅተ ኅትምት መሶበ ጽንስ ምስለ ድንግልና ዘኢሳይያስ
@EOTCW
@EOTCW
🔹🌱ዓዲ ዚቅ፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ገነት ዕፁት ገነት ዕፁት አዘቅት ሕትምት፤ተሰውጠ ዲቤሃ ምዑዝ ዕፍረት
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ማህሌተ ጽጌ፦
ፄነወኒ ተአምርኪ ሶበ ይነፍሑ ነፋሳት፤ ከመ ጼና ገነት ዘይፄኑ እምርኁቅ ፍኖት፤ መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ቡርክት፤ ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት፤ጽጌ ጽጌ ጽጌ አሮን ዘክህነት
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ
ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት/2/
መዓዛ አፈዋት ማርያም መዓዛ አፈዋት ወጽጌ መንግሥት ቡርክት/2/
@EOTCW
🌱ዚቅ
ሠርፀ መንግስት ዘእምሥርወ ዕሤይ ወጽጌ ንጽሕት ዘእምጕንደ ዳዊት፤ወብኪ ይትሜዓዙ ኲሎሙ ቅዱሳን
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ/2/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/2/
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል፤ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ/2/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ/2/
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት
@EOTCWW
@EOTCWW
✨ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።
@EOTCW
❣❣ወረብ
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/2/
ማርያም ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/2/
@EOTCW
🌱ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤ወለመላትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።
@EOTCW
@EOTCW
❄️መዝሙር በ6፦
በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤ ቆመ በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት፤ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት፤ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጎታት ማ፦ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ነአኩቶ ለዘፀግወነ ሠናይቶ።
https://t.me/Eotcw
# Join & share #