ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 5:1-17፡ "ወሶበ ርእየ ብዙኃነ አሕዛብ" - "ሕዝቡንም፡አይቶ፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ፤በተቀመጠም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡እርሱ፡ቀረቡ፤ አፉንም፡ከፍቶ፡አስተማራቸው፡እንዲህም፡አለ። በመንፈስ፡ድሃዎች፡የሆኑ፡ብፁዓን፡ናቸው፥መንግሥተ፡ሰማያት፡የእነርሱ፡ናትና። የሚያዝኑ፡ብፁዓን፡ናቸው፥መጽናናትን፡ያገኛሉና። የዋሆች፡ብፁዓን፡ናቸው፥ምድርን፡ይወርሳሉና። ጽድቅን፡የሚራቡና፡የሚጠሙ፡ብፁዓን፡ናቸው፥ይጠግባሉና። የሚምሩ፡ብፁዓን፡ናቸው፥ይማራሉና። ልበ፡ንጹሖች፡ብፁዓን፡ናቸው፥እግዚአብሔርን፡ያዩታልና። የሚያስተራርቁ፡ብፁዓን፡ናቸው፥የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ይባላሉና። ስለ፡ጽድቅ፡የሚሰደዱ፡ብፁዓን፡ናቸው፥መንግሥተ፡ሰማያት፡የእነርሱ፡ናትና። ሲነቅፏችሁና፡ሲያሳድዷችሁ፡በእኔም፡ምክንያት፡ክፉውን፡ዅሉ፡በውሸት፡ሲናገሩባችሁ፡ብፁዓን፡ናችሁ። ዋጋችሁ፡በሰማያት፡ታላቅ፡ነውና፥ደስ፡ይበላችሁ፥ሐሴትም፡አድርጉ፤ከእናንተ፡በፊት፡የነበሩትን፡ነቢያትን፡እንዲሁ፡አሳደ፟ዋቸዋልና። እናንተ፡የምድር፡ጨው፡ናችሁ፤ጨው፡ዐልጫ፡ቢሆን፡ግን፡በምን፡ይጣፍጣል፧ወደ፡ውጭ፡ተጥሎ፡በሰው፡ከመረገጥ፡በቀር፡ወደ፡ፊት፡ለምንም፡አይጠቅምም። እናንተ፡የዓለም፡ብርሃን፡ናችሁ።በተራራ፡ላይ፡ያለች፡ከተማ፡ልትሰወር፡አይቻላትም። መብራትንም፡አብርተው፡ከእንቅብ፡በታች፡አይደለም፡እንጂ፡በመቅረዙ፡ላይ፡ያኖሩታል፡በቤት፡ላሉት፡ሁሉም፡ያበራል። መልካሙን፡ሥራችሁን፡አይተው፡በሰማያት፡ያለውን፡አባታችሁን፡እንዲያከብሩ፡ብርሃናችሁ፡እንዲሁ፡በሰው፡ፊት፡ይብራ። እኔ፡ሕግንና፡ነቢያትን፡ለመሻር፡የመጣሁ፡አይምሰላችሁ፤ልፈጽም፡እንጂ፡ለመሻር፡አልመጣሁም።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.42 KB

25/2/2015 ዓ.ም (፳፭/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ። ወይበዝኃ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ። ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር። መዝ 91÷12 🕯 ትርጉም ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል። እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 10:32-ፍ፡ም፡ "ኲሉ እንከ ዘየአምን ብየ በቅድመ ሰብእ" - "ስለዚህ፥በሰው፡ፊት፡ለሚመሰክርልኝ፡ሁሉ፥እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እመሰክርለታለሁ፤ በሰው፡ፊትም፡የሚክደኝን፡ሁሉ፡እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እክደዋለሁ። በምድር፡ላይ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡የመጣሁ፡አይምሰላችሁ፤ሰይፍን፡እንጂ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡አልመጣሁም። ሰውን፡ከአባቱ፥ሴት፡ልጅንም፡ከእናቷ፥ምራትንም፡ከአማቷ፡እለያይ፡ዘንድ፡መጥቻለሁና፤ ለሰውም፡ቤተ፡ሰዎቹ፡ጠላቶች፡ይሆኑበታል። ከእኔ፡ይልቅ፡አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሚወድ፡ለእኔ፡ሊሆን፡አይገ፟ባ፟ውም፤ከእኔ፡ይልቅም፡ወንድ፡ልጁን፡ወይም፡ሴት፡ልጁን፡የሚወድ፡ለእኔ፡ሊሆን፡አይገ፟ባ፟ውም፤ መስቀሉንም፡የማይዝ፡በኋላዬም፡የማይከተለኝ፡ለእኔ፡ሊሆን፡አይገ፟ባ፟ውም። ነፍሱን፡የሚያገኝ፡ያጠፋታል፥ነፍሱንም፡ስለ፡እኔ፡የሚያጠፋ፡ያገኛታል። እናንተን፡የሚቀበል፡እኔን፡ይቀበላል፥እኔንም፡የሚቀበል፡የላከኝን፡ይቀበላል። ነቢይን፡በነቢይ፡ስም፡የሚቀበል፡የነቢይን፡ዋጋ፡ይወስዳል፥ጻድቅንም፡በጻድቅ፡ስም፡የሚቀበል፡የጻድቁን፡ዋጋ፡ይወስዳል። ማንም፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡ለአንዱ፡ቀዝቃዛ፡ጽዋ፡ውሃ፡ብቻ፡በደቀ፡መዝሙር፡ስም፡የሚያጠጣ፥እውነት፡እላችኋለሁ፥ዋጋው፡አይጠፋበትም።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.68 KB

25/02/2015 ዓ.ም (፳፭/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር። እግዚኦ አነ ገብርከ። ገብርከ ወልደ ዓመትከ፡፡ መዝ. 115÷15 🕯 ትርጉም የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው። አቤቱ እኔ ባሪያህ ነኝ። ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

ቧም ፍሬ ይሆንልኝ ይሆን ስትል ራእይን አየች። ❤ ከእንቅልፏም በነቃች ጊዜ ራእይን እንዳየች ለባሏ ነገረችው እርሱም እርሷ እንዳየችው ያለ ማየቱን ነገራት እግዚአብሔርንም አብዝተው አመሰገኑት ትሩፋትንና ተጋድሎን በመጨመር በየሁለት ቀን የሚጾሙ ሆኑ ምግባቸውም እንጀራና ጨው ነው። ❤ ይህን ቅዱስ እብሎይን በፀነሰችው ጊዜ እናቱ በገድል ወንዶችን እስከምታሸንፍ ድረስ በየሌሊቱ ሁሉ አንድ ሽህ ስግደትን ትሰግዳለች ሕፃኑን እስከ ወለደችው ድረስ ዘጠኝ ወር ያህል እንዲህ ስትጋደል ኖረች። በወለዱትም ጊዜ እብሎይ ብለው ሰየሙት በጐለመሰም ጊዜ የምንኩስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ምክንያትም እስቲያገኝ እንዲህ ኖረ አቢብ የሚባል ወዳጅ ነበረውና እርሱ በሌሊት ወሰደው ከላዕላይ ግብጽ በሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ መነኰሰ በገድልም በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ❤ ከጥቂት ወራትም በኋላ በጥቅምት ወር ሃያ አምስት ቀን አባ አቢብ ዐረፈ ያን ጊዜ አባ እብሎይ አብሎግ ወደሚባል ገዳም ሔደ ወደርሱም ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እርሱም በበጎ አምልኮ እግዚአብሔርን መፍራትን የሚያስተምራቸው ሆነ። ❤ ቅዱስ አቢብም በዐረፈበት ቀን መታሰቢያውን ሲያደርጉ ይህ ቅዱስ አባ አብሎይ "ወንድሞች ሆይ በአባ አቢብ ስም ዛሬ ጸሎትን የሚጸልየውን ኃጢአቱን እግዚአብሔር ያስተሰርይለታል በዕረፍትህ መታሰቢያ ቀን የአባ አቢብ ፈጣሪ ሆይ ኃጢአቴን ሁሉ ተውልኝ ብሎ አንዲት ጸሎትን የሚጸልየውን ሁሉ እኔ ኃጡአቱን እተውለታለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ሰጥቶታልና አላቸው። ❤ በዚያችም ሰዓት ከመነኰሳት አንዱ ዐረፈ እነርሱም ሊገንዙት በዚያ ቁመው ሳሉ አባ እብሎይ ስለ ተናገረው ቃል ከመነኰሳት አንዱ ተጠራጠረ በዚያንም ጊዜ ያ የሞተው ተነሥቶ ይናገር ዘንድ ጀመረ "አባ እብሎይ ስለተናገረው ቃል ለምን ትጠራጠራላችሁ ለአባታችን አቢብ በመታሰቢያው ቀን በዚህ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሰጥቶናልና" አላቸው ። ይህንንም ብሎ ተመልሶ ዐረፈ መነኰሳቱም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ❤ ይህ አባ እብሎይም ብዙ ዘመናት ኖረ ልጆቹ መነኰሳትም በዙ ብዙ ገዳማትም ተሠሩለት። የኖረበትም ዘመኑ በታላቁ አባ መቃርስ ዘመን ነው የአባ እብሎይንም የትሩፋቱን ዜና አባ መቃርስ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኘበት እርሱን እያጽናና እያረጋጋ መነኰሳት ልጆቹንም እግዚአብሔር የሚወደውን በመሥራት ያጸናቸው ዘንድ መልእክትን ጻፈለት። ይህንንም በአስቄጥስ ገዳም ሁኖ አባ መቃርስ ሲጽፍ አባ እብሎይ በላዕላይ ግብጽ ሳለ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በዙሪያው ያሉትን መነኰሳት እንዲህ አላቸው። "እነሆ ማጽናናትን የተመላች መልእክትን አባ መቃርስ ጻፈልን"። ❤ ከዚህም በኋላ ከአባ መቃርስ ዘንድ የተላኩትን መነኰሳት ሁሉ ወጥተው በደስታ ተቀብለው አስገቧቸው መልእክቱንም በመነኰሳቱ ሁሉ ፊት አነበቡ በታላቅ ደስታም ደስ አላቸው። ይህም አባ እብሎይ ወደ አባ አሞንዮስ የሔደ ከእርሱ ዘንድም የምትኖረውን ስሟ የዋሂት የተባለችውን የተቀደሰች ሴት ያየ ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው ወዶ በየካቲት ወር በአምስተኛው ቀን ዐረፈ እኛ ግን የአባ እብሎይን ዜና ከወዳጁ ከአባ አቢብ ጋር ጻፍን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ እብሎይ ጸሎት ይማረን። + + + ❤ አቅፋሐስ ከሚባል አገር ሰማዕት ለሆነ ለቅዱስ ዮልዮስ ቤተ ክርስቲያኑ መከበር፦ ይህም ቅዱስ ዮልዮስ በሀገረ ጥዋ በሰማዕትነት በዐረፈ ጊዜ በገድሉ እንደተጻፈ ዲዮቅልጥያኖስ ከጠፋ በኋላ ጻድቅ ሰው ቈስጠንጢኖስ ሳይጠመቅ ነገሠላቸው በጥቂት ወራትም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ የቤተ ክርስቲያንም ሥልጣን ከፍ ከፍ አለ ከሀድያን ነገሥታት ለገደሏቸው ንጹሐን ሰማዕታት በስማቸው አብያተ ክርስቲያናት ታነፁ። ❤ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትም ስለ ሥጋቸው እንዲአስብ ገንዞ በመሸከም ወደ አገራቸው እንዲአደርሳቸው ከአገልጋዮቹም ጋር ገድላቸውን እንዲጽፍ እግዚአብሔር እንደአቆመውና እንደጠበቀው ከዚህም እርሱ ራሱ በሰማዕትነት እንዴት እንደ ሞተ የቅዱስ ዮልዮስን ዜና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በሰማ ጊዜ ስለበጎ ተጋድሎው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቅዱስ ዮልዮስን አመሰገነው። ስለዚህም ለቅዱስ ዮልዮስ ያማረች ቤተ ክርስቲያን በግብጽ አገር ሠርተው ሥጋውን በውስጧ ያኖሩ ዘንድ ንጉሡ ወደ ግብጽ አገር ብዙ ገንዘብ ላከ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ እንዳዘዘ አነፁለት። ❤ የቅዱስ ዮልዮስንም ሥጋ አፍልሰው በውስጧ አኖሩት ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር አከበራት እንደዛሬዪቱም ቀን በዓል አከበረባት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮልዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 25 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአቢብ ዘአስተጋብአ አሐትኔ። ምግባረ ጻድቃን ዘገዳም ወምግባረ ሰማዕት በኵርጓኔ። እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኰቴት ማኅዘኔ። ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኵነኔ። ዘመጠነዝ ታፃሙ ነፍሰከ በቅኔ"። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት25። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር። እግዚኦ አነ ገብርከ። ገብርከ ወልደ አመትከ"። መዝ115፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥32-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ። ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ። ትኩላን እምንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር"። መዝ91፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ኢፌ 7፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ጼጥ 3፥10-18 እና የሐዋ ሥራ 11፥23-27። የሚነበበው ወንጌል ማቴ5፥1-17። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ቡላ አቢቡ የዕረፍት በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ አባት ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና በእንተ (ስለ) አባ አቢብ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ስብሐት ብሎ ያሰበውን እምርልሃለሁ ብለው ታላቅ ቃል ኪዳንን መድኃኔዓለም ለሰጣቸው፤ የጌታችንን መከራ መስቀሉን በማሰብ ራሳቸውን ሰባት ጊዜ ለገደሉ ለታላቁና ክቡሩ ለሆኑ አባ አቢብ ለተባሉት ለመስተጋድል አባ ቡላ፣ አክሚም ከሚባል አገር የመላእክት አምሳል ለሆነ ለአባ እብሎኝ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ አቢብ ማኅበር ከሆኑ ዐሥር ሺህ አርባ ሦስት ወንዶችና ሦስት መቶ ሰባት ሴቶች ሰማዕታትና ከሰማዕቱ ከቅዱስ ዮልዮስ ከሥጋው ፍልሰትና ቤተ ክርስቲያኑ ከከበረችበት ዕለት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለፀአተ ነፍስከ በሐቅለ ገዳም ወበዳ። እንበለ ፃር ወጻማ እምሥርወ ኵሉ ክብዳ። ኀበ አዕረፍከ አቢብ ምስለ ሰማዕታት ዘምድረ ልዳ። እመዊት ግሩም ከመ ትትነሣእ በእዳ። ለዘሐፀነተከ ማርያም ወክርስቶስ ወልዳ"። ትርጉም፦ ከልዳ ምድር ሰማዕታት ጋር ወደ ዐረፍኽበት ምድረ በዳና ያለ ፃዕርና ድካም በክብደቷ ኹሉ ለፀአተ ነፍስህ ሰላምታ የሚገባህ ጻድቅ አባታችን አቢብ ሆይ በአሳደገችህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ድንግል ማርያም ፊት እጅ እንደምትነሣ እኔንም ከሚያስፈራ ሞት አስነሣኝ። መልክአ አቡነ አቢብ። + + + ❤ በአባ ብላ (አቡነ አቢብ)፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው እነርሱም ከሮሜ አገር ሉፊ ከሚባል አውራጃ ናቸው በዘመናቸውም ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራ ስለ አመጣ ስደት ሁኖ ነበርና እነርሱም በስደት ብዙ ዘመን ኖሩ። ❤ ልጅንም በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው። ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ "ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው" የሚል ጽሑፍ ነበረበት። ❤ በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዛችው እርሱም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ስሙንም "ቡላ" ብሎ ሰየመው እናትና አባቱም ሳይነግሩት "ቡላ" ብሎ ስለሰየመው አደነቁ "ዕፁብ ዕፁብ" አሉ። ❤ ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ በጸለየ ጊዜ የቊርባን ኅብስትና ወይን የተመላ ጽዋ ከሰማይ ወረደ እርሱም ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ከሕፃኑ ጋር አቀበላቸው በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ የአንድ ዓመት ልጅ ሲሆን "በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ አብ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ ወልድ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከአብ ከወልድ ጋር አንድ የሆነ መንፈስ ቅዱስ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው" ብሎ ተናገረ። ❤ ከጥቂት ዘመንም በኋላ አባትና እናቱ ኅዳር ሰባት ቀን ሙተው ሕፃኑ ብቻውን ቀረ። ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በአካል ታናሽነቱን አይቶ እጅግ አደነቀ በዚያንም ጊዜ በችንካር እንዲቸነክሩት ሥጋውንም እንዲሠነጥቁት ቆዳውንም ከዐጥንቱ እንዲገፋ እጆቹንና እግሮቹንም በመጋዝ እንዲቆርጡ ጀርባውንም እንዲገርፋ በሾተሎችና በጦሮች መካከል አድርገው በመንኰርኲር ውስጥ እንዲጨምሩት ዳግመኛም በመንገድ ላይ እንዲጐትቱት አዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ መኰንን ሒዶ እርሱንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ መኰንኑም ተቆጥቶ በሚያዝያ ወር ዐሥራ ስምንት ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ የምንኲስና ልብስንና አስኬማን በመስቀልም ምልክት አለበሰው። እንዲህም አለው "ከቅዱሳን ጻድቃን አንድነት ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር አዝዞሃል"። ያን ጊዜም ቅዱስ አባ ቡላ ከደረቅ ተራራ ላይ ወጣ ያለ ማቋረጥም በውስጧ እየተጋደለ ኖረ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውንና ስቅለቱን በአሰበ ጊዜ ከረጅም ዕንጨት ላይ በመውጣት ራሱን ወደታች ሁል ጊዜ ይወረውር ነበር። ❤ በአንዲትም ቀን ከዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን ሊገድለው ስለ በረታበት ሞተ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ከሞት አነሣውና እንዲህ አለው "ከእንዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ይባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህና"። እርሱም የክርስቶስን ፍቅር እጅግ ጨመረ ፊቱንም እየጸፋ ሥጋውን በየጥቂቱ እየቆረጠ ጀርባውንም ሰባት መቶ ጊዜ እየገረፈ ኖረ ጌታችንም ይፈውሰው ነበር በየእሑድም ቀን ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም እንደተወለደ በሌሎች ቀኖችም እንደተያዘና ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበለ ሁኖ ይገለጽለት ነበር። ስለዚህም ሳይበላ ሳይጠጣ አርባ ሁለት ዓመት ኖረ ዳግመኛም ናላው ፈስሶ እስቲአልቅ ዐሥራ ሁለት ወር በራሱ ተተክሎ ኖረ። ❤ በአንዲትም ቀን የጌታችንን መከራ በአሰበ ጊዜ ሰይፋን በአንጻሩ ተከለ ከዕንጨት ላይም ወጥቶ በላዩ ወድቆ ሞተ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥታ "የእኔና የልጄ ወዳጅ ሰላምታ ይድረስህ" አለችው። ከበድኑም ቃል ወጥቶ "የሰማይና የምድር ንግሥት እመቤቴ ሰላምታ ይገባሻል" አላት እርሷም በከበሩ እጆቿ ዳሥሣ ከሞት አስነሣችው። ❤ ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችም ይዞ ተገለጠለት "ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔና ስምህን ለሚጠራ፣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንድ በራሴ ማልኩልህ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን፣ ለተጠማ የሚያጠጣውን፣ የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን፣ በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ" ይህንም ብሎ አፋን ሳመው በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ጥቅምት 25 ቀን ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት በአባ ብላ (አቡነ አቢብ) ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አክሚም ከሚባል አገር የሆነ የመላእክት አምሳል የሆነ አባ እብሎይ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አሞኒ የእናቱ ስም ሙስያ ነው ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሆኑ በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ድኆችንና መጻተኞችን የሚወዱ የሚረዱ ናቸው። ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም ሙስያም ዕንጨት የያዘ ብርሃናዊ ሰው በቤቷ ውስጥ ሲተክለውና ወዲያውኑ ለምልሞ አብቦ ሲያፈራ ያ ብርሃናዊው ሰውም ከዚህ ፍሬ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል ሲላት እርሷም ከፍሬው ወስዳ ስትበላና በአፏ ውስጥ ጣፋጭ ሲሆንላት በል

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ጥቅምት ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያ ጻድቅ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአጎት ልጅ ለታላቁ አባት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነትን ለተቀበሉት ለአቡነ ሕፃን ሞዐ ቃል ኪዳን ለተቀበሉባት ለመታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ሕፃን ሞዐ፡- በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡ ❤ እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜና ማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ❤ ከአራባ ሰባቱ የአገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸ በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የሁለት ሰዓት መንገድ ርቀት ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

የጥቅምት መድኃኔ ዓለም እኁድ ሲሆን የሚባል እስመ ለዓለም @EOTCW

፮ኛ ወልድ እኁየ @EOTCW

፭ኛ ወረብ ገጹ ብሩህ @EOTCW