ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

前往频道在 Telegram

ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

显示更多
1 411
订阅者
+224 小时
+257 天
+8530 天
帖子存档
የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ግብርና እና ሳይንስ ኤግዚቢሽን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) እሑድ ሚያዝያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ተ
የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ግብርና እና ሳይንስ ኤግዚቢሽን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) እሑድ ሚያዝያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ተመርቆ ይከፈታል፡፡ ከሚያዝያ 30 ጀምሮ ለተከታታይ ሳምንታት ለሕዝብ እይታም ክፍት ይሆናል፡፡ …. The Agriculture and Science exhibition organized by the Ministry of Agriculture in collaboration with Ethio Telecom at the Science Museum will be inaugurated by His Excellency Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) on May 7, 2023. It will be open for public viewing for consecutive weeks starting May 8.

«በእንስሳት ኳራንቲን ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ከባለድርሻ አካላትን ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ሊኖር ይገባል!» ዶ/ር ራሻድ ሙሀመድ በባለሥልጣኑ የድሬደዋ የእንስሳት ኳራንታይን ጣቢያ አስተባበሪ **** የእንስሳት ኳራንታይን አሰራር ዓለምአቀፍ የሕግ ማዕቀፍን ተከትሎ የሚከናወን ቢሆንም አገራችን ኢትዮጵያ የእንስሳት ኳራንታይንን አስመልክቶ ዓለምአቀፉን አሰራር ለማሟላት ባለመቻሏ ባላት የእንስሳት ኃብት ልክ በዓለም አቀፉ ገበያ ተወዳድራ ገብያውን ሰብራ መግባትና ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡ ይሁንና የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት መንግስት የእንስሳት ኳራንታይን ሥራ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ እንዲሰራ ለማድረግ የፌዴራል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት “የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን”ን አቋቁሟል፡፡ የባለስልጣኑን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 509/2014 መሠረትም ባለሥልጣኑ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያዎችና ቼክ ፖስቶችን በመገንባትና በግንባታ ላይ ያሉትን ደረጃቸውን እንዲጠብቁና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የውስጥ አደረጃጀታቸውን በመፈተሸ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ሙያዊ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ በሌሎች አገራት ተቀባይነት እንዲኖራቸው እንዲሁም በተቀባይ ሀገሮች በማስገምገም እውቅና እንዲያገኙ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡   የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ክፍልም የእንስሳት ኳራንታይን ጣቢያዎች አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? የሚለውን የድሬደዋ የእንስሳት ኳራንታይን ጣቢያን እንደናሙና በመውሰድ ከኳራንቲን ጣቢያው አስተባበሪ ዶ/ር ራሻድ ሙሀመድ ጋር አጭር ቆይታ በማድረግ እንደሚከተለው የሚያስቃኛችሁ ይሆናል፤ መልካም ቆይታ! ሕዝብ ግንኙነት፦ በድሬደዋ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ምንድን ናቸው? ዶ/ር ራሻድ፦ የድሬዳዋ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያ ከተቋቋመበት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ኳራንቲን ጣቢያው ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በዋነኛነት የቁም እንስሳትን ወደ መካከለኛው ምስራቅና አረብ አገሮች እንዲሁም አጎራባች የአፍሪካ አገሮች ማለትም ጅቡቲ፣ ሶማሌላንድ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ የመሳሰሉት አገሮች ላይ ኤክስፖርት ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የእንስሳት ተረፈ ምርቶችን እንደ ማርና ወተት የመሳሰሉትን ወደ ውጪ የመላክ ሥራ የሚሰራ ሲሆን በዚህም በዓመት ከ20 እስከ 40 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ እናገኛለን፡፡ ነገር ግን ከ2013 ጀምሮ በኮቪድና ሌሎች ምክንያቶች የኤክስፖርት መጠኑ እየቀነሰ የመጣበት ሆኔታ አለ፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ኳራንቲን ጣቢያው በተሰጠው ወሰን ውስጥ ወደ ውጭ የሚላኩ የቁም እንስሳት በኳራንቲን የቁጥጥር ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግ አኳያ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ቢያብራሩልን? ዶ/ር ራሻድ ፦ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያው እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ኤክስፖርት ሲያደረግ የሌሎች አገሮችን ፍላጎትንና የኳራንቲን ጣቢያው ሕግና መመሪያ መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ወደ አገር ውስጥም ሲገባም በተመሳሳይ በተቀመጠው ሕግና መመሪያ መሰረት እየተከናወነ ነው የሚገባው፡፡ በሁሉም አገሮች ላይ የተለያዩ የእንስሳት በሽታዎች ስለሚገኙ እነዚህም በሽታዎች ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር እንዳይዛመቱ የእንስሳት ኳራንቲው ጣቢያው ጥብቅ ምርመራና ፍተሻ ያደረጋል፡፡ በዚህም ወደ ውጭ የሚላኩ እንስሳት በኳራንቲን የቁጥጥር ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፉና በዓለም አቀፍ ገበያው ተወዳዳሪ በመሆን አገራችን የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን፤ ይህ ግን በቂ አይደለም፡፡ በዘርፉ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር መኖር ወሳኝነት አለው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ሕገ-ወጥ የቁም እንስሳት ንግድን ጨምሮ ለዘርፉ እድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያላችሁ ቅንጅታዊ አሰራር ምን ይመስላል? ዶ/ር ራሻድ፦ ሕገ-ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ የዘርፉ ዋነኛ ፈተና ነው፤ በተለይ እንደ እኛ አካባቢ ከ2010 ጀምሮ  የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በሁሉም ክልል የሚገኙ ከእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያ ባለሙያዎች ጋር ተጣምሮና እስከ ታች ድረስ ወርዶ በቅንጅት ባለመስራቱ የችግሩ መጠን እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ክልሉም ለጣቢያችን ሲያደርግ የነበረው ድጋፍ እንብዛም ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሕገ-ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በአገር ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰው ያለውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ችግሩን በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል በፌደራል ደረጃ በክቡር ጠ/ሚኒስቴሩ፣ በክልል ደረጃ በክቡራን ርዕሰ መስተዳደሮች የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ውጤት መታየትም ጀምሯል፡፡ ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ነገር ግን በኮሚቴ ብቻ ሕገ-ወጥ የቁም እንስሳት ንግድን መቆጣጠር ስለማይቻል መላ ህብረተሰቡ በተለይም የአካባቢያችን ማህበረሰብ ከኮሚቴውም ሆነ ከጣቢያችን ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ህገወጥነትን ልንከላከል ይገባል። ሕዝብ ግንኙነት፦ በኳራንቲን ጣቢያው የሚሰጡ አገልግሎቶች ከብልሹ አሰራርና ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ፣ ቀልጣፋና የተገልጋዩን እርካታ በሚያሳድግ መልኩ እንዲሆን የሚከናወኑ ተግባራትን ቢገልጹልን? ዶ/ር ራሻድ ፦ በእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች የስራ ባህሪው ከብዙ ባለሀብቶች ጋር የሚያገናኛቸው በመሆኑ እና ሥራዎች በሕግ ማዕቀፍ የታገዙ ባለመሆናቸው ባለሙያዎችን ለኪራይ ሰብሳቢነት እና ለመልካም አስተዳደር የተጋለጡ ያድርጓቸዋል፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ በኳራንቲን ጣቢያዎች የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባርን ለመቀነስ የሚቻለው ባለሥልጣን መ/ቤቱ የአሰራር መመሪያዎችንና ማኑዋሎችን አዘጋጅቶ ወደ ታች በማውረድ እና ጥብቅ ክትትል በማድረግ የኳራንቲን አገልግሎት አሰጣጡ ለሁሉም ተገልጋዮች በእኩል ደረጃ የሚሰጥበትን ሁኔታ መፍጠር ሲቻል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ በመጨረሻ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ? ዶ/ር ራሻድ፦ ማስተላለፍ የምፈልገው እስከአሁን በግብርና ሚ/ር ሥር ስለነበርንና ለእንስሳት ልማቱ እንጅ ለቁጥጥሩ በቂ ትኩረት ስለማይሰጠው የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያዎች ከድጋፍና ክትትል፣ ከበጀትና ከትራንስፖርት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ችግሮች የነበሩባቸው በመሆኑ በአዲሱ አደረጃጀት ባለሥልጣን መ/ቤቱ እነዚህ ችግሮች በአፋጣኝ እንዲፈቱ ትኩረት መስጠት አለበት እላለሁ፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን! ዶ/ር ራሽድ፦ እኔም አመሰግናለሁ! ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

እንኳን አደረሳችሁ! *** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ለባለሥልጣን መ/ቤታችን አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺ 444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ይላል። በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሰብ እንዲሆንም ይመኛል! #ኢድ_ሙባረክ! @የኢትዮጵያ_ግብርና_ባለሥልጣን

በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የላቦራቶሪ ጥራት ፍተሻ አገልግሎት አሰጣጥ ዓለምአቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸወሰ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፤ **** በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ተገኝቶ የሥራ ክፍሎችን የሥራ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን የባለስልጣን መ/ቤቱን የ2015 በጀት ዓመት የ 9 ወራት እቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክቶሬቶች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህም የእንስሳትም ሆነ የእፅዋት ምርቶች እንዳይበከሉ ጥራቱን የጠበቀ የላብራቶሪ ፍተሻ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጸው ቋሚ ኮሚቴው በተለይም ከውጭ የሚገቡ የዘር ዓይነቶች ጤንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ብሎም የሚላኩ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የተቋሙ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ ብቁ ባለሙያ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል። የወንዝ ዳር የግብርና ምርት ቁጥጥርን በሚመለከት በአመጋገብ ችግር ከሚመጡ በሽታዎች የዜጎችን ጤና ከመታደግ አኳያ ተቋሙ መከታ ሊሆን እንደሚገባ የተናገሩት የቋሚ ኮሚቴው የመስክ ቡድን አስተባባሪ የተከበሩ አቶ ባርጠማ ፍቃዱ ተቋሙ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ በዘርፉ የተጀመሩት የሪፎርም ስራዎች ተጠናቀው ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል በሂደት ላይ ያሉ የሕግ ማዕቀፎች ወደ ስራ እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት የተከበሩ አቶ ባርጠማ የእንስሳት እና የእፅዋት ዘር አስመጪዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር በማጠናከር ሕገ-ወጥነትን መከላከል ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ተቋሙ ዓለምአቀፍ ተፎካካሪ መሆን መቻል እንዳለበት ያነሱት የቋሚ ኮሚቴው አስተባባሪ ተቋሙ ባስቀመጠው ስታንዳርድ የማይሰሩ ድርጅቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድና የባለሙያዎችን አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በሁሉም ላብራቶሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች በዓለምአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲኖራቸውና ተአማኒ የቁጥጥር ተቋም እንዲሆን የተጀመሩ ሥራዎችን ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ነገር ግን በተቋሙ ጥርት ያለ የሕግ ማዕቀፍ አለመኖሩ ችግር መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደር ድሪባ አያይዘውም የማያሰሩ የፖሊሲ ማዕቀፍ እና ደንቦች ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው ጠቁመው ለዚህም የቋሚ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

እንኳን አደረሳችሁ! *** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ለባለሥልጣን መ/ቤታችን አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል! በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሰብ እንዲሆንም ይመኛል! #መልካም_ፋሲካ! @የኢትዮጵያ_ግብርና_ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከአመራሮቹና ሠራተኞቹ ጋር ወይይት አካሄደ፤ **** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን “ድሎችን የማጽናት ፈተናዎችን የመሻገር!” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከባለሥልጣኑ አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ወይይት አካሄዷል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውይይቱ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አሁን ላይ አገራችን ባለፉት 5 ዓመታት በርካታ ታሪክ ቀያሪ የሆኑ ለውጦች ያስመዘገበች ቢሆንም የሰላም እጦት፣ የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነትና መሰል ችግሮች አሁንም ድረስ ፈተናዋ ሆነው መቀጠላቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች ሰላምን በማደፍረስ ሕዝብን ለማሸበርና አገር ለማፍረስ የሚደረጉ የተሳሳቱ አካሄዶች መኖራቸውን የገለጹት አምባሳደር ድሪባ ችግሮቹ ሕግን በተከተለ መንገድ በሰከነ መልኩ በውይይትና በሰላም እንዲፈቱ ሁሉም የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ድሎችን በማጎልበት፣ ፈተናዎች ላይ ደግሞ ተናቦና ተባብሮ በመስራት በአንድነት ለመሻገር የሁሉም አገር ወዳድ ሚና ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ሰላምን በማስፈን የአገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ፣ ሥራ አጥነትን ለመቀነስ፣ የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ በሚደረገው አገራዊ ጥረት የባለሥልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች ድርሻውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ባለፉት 5 የለውጥ አመታት የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ፈተናዎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚመለከት “ድሎችን የማጽናት ፈተናዎችን የመሻገር!” በሚል ርዕስ ዝርዝር አገራዊ የውይይት ሰነድ በባለሥልጣኑ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሚድ ጀማል ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ ከሰላም፣ ከኑሮ ውድነትና ከተገኙ አገራዊ ስኬቶች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበዋል፡፡ በተለይም ከጎጠኝነትና ዘረኝነት አስተሳሰብ ወጥተን ሁላችንም ለሰላም ዋጋ በመስጠት በየተሰማራንበት የስራ መስክ ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን፤ የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ለመንግስት ሰራተኛ በመንግስት በኩል ምን ታስቧል? አገልግሎት አሰጣጣችን ከሙስናና ከሕገ-ወጥ ተግባራት የጸዳ እንዲሆን በቀጣይ ሊታዩ ይገባሉ ያሏቸውንና ሌሎች በ5 አመቱ ውስጥ በተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡ የመንግስት አቅጣጫዎች በየጊዜው እየቀረቡ ከሰራተኛው ጋር ውይይት እየተደረገባቸው የጋራ ኃሳብና አረዳድ እየያዝን ከሄድን ችግሮችን በፍጥነት ለመቅረፍ እድል ይሰጣል ያሉት በባለሥልጣኑ የእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የተጣለብንን አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣትና የአገራችንን አንድነትና እድገት ለማረጋገጥ የባለሥልጣኑ አመራሮችና ሠራተኞች ከአፍራሽ ድርጊቶች በመቆጠብ የተሰጠንን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ አቶ ወንዳለ አክለውም የለውጡ መንግስት ለውጡን የጀመረው በሪፎርም በመሆኑና ሪፎርም ደግሞ በባህሪው በአጭር ጊዜ ሥር-ነቀል ለውጥ የሚያመጣና የሚተገበር ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ በአጭር ጌዜ የሕዝብን ፈላጎት ማሟላት እንደማይቻል በመገንዘብ ሁላችንም ከጽንፈኝነት፣ ከአክራሪ ብሔርተኝነት እና ከጎጠኝነት አስተሳሰብ ወጥተን ሪፎርሙን በመደገፍ አውንታዊ ሚናችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ተቋማችን የሬጉላቶሪ ተቋም መሆኑን በውል በመረዳት ከሌብነትና ከሕገ-ወጥ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት አቶ ወንዳለ ከተሰጠን ተግባርና ኃላፊነት ጎን ለጎን የአገራችንን ሰላም ከውጭና የውስጥ አፍራሽ ኃይሎች ልንጠብቅ ይገባል በሚል አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥርዓቱን በአገርአቀፍ ደረጃ ወጥና ተመጣጣኝ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ገለፀ፤ **** 12ኛው አገር አቀፍ የዘር ጥራት ቁጥጥር የጋራ የምክክር መድረክ በሐዋሳ ከተማ ከመጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተካሂዷል። የመድረኩ ዋና አላማ ክልሎች ከፌዴራል ጋር በትብብር እንዲሰሩ እና መረጃ በቀላሉ በመለዋወጥ የዘር ቁጥጥር ሥራው ስኬታማ እንዲሆን ማስቻል መሆኑ የተናገሩት የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥርዓቱን በአገርአቀፍ ደረጃ ወጥና ተመጣጣኝ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የዘር ጥራት ፍተሻ አሰራር በመስክና በላብራቶሪ ተቀራራቢነት እንዲኖረው መደረጉንም የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ መስፈርቱን የሚያሟላ ማንኛውም ዘር በቀላሉ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላኛው ማሰራጨት መቻሉንም ተናግረዋል። የጥራት ቁጥጥር ተግባር ቅንጅታዊ አሰራርን የሚጠይቅ መሆኑንም የገለፁት አምባሳደሩ ተናቦ የመስራት ሁኔታው በይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባውም አምባሳደር ድሪባ አሳስበዋል። በደብብ ክልል የግብርና ግበዓት ቁጥጥርና ኳረንቲን ዋና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ዋቴ ከድህነት ለመውጣት ጥራት ያለው ዘር ወደ አርሶ አደሩ በማድረስ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚቻለው ጥራት ያለውን ዘር ወደ አርሶአደሩ በማድረስ ነው ያሉት አቶ እዮብ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ ያለው የጥራት ቁጥጥር ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። በሲዳማ ክልል የግብርና ግበዓት ቁጥጥርና ኳረንታዪን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ሰለሞን በበኩላቸው የአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የዘር ጥራት ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ሕገ-ወጥ የዘር ዝውውር እንዳይኖር ቁጥጥር እየተደረገ ነው ያሉት አቶ ብርሃኑ ጥራቱ የተረጋገጠ ዘር ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ባለስጣን የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሎች የግብርና ግበዓት ቁጥጥርና ኳረንቲን ዋና ዳይሬክተሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተዋል። @የደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ

«የመኖ ጥራትና ደኅንነትን በመጠበቅ የእንሰሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው!» አቶ ዘላለም አበበ የእንስሳት መኖ ጥራት ደረጃ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  **** የእንስሳት መኖ ጥራትና ደኅንነትን ማስጠበቅ ከእንስሳት ዘርፉ የሚገኜውን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ እኛም በአገር አቀፍ ደረጃ የመኖ ምርት ጥራትና ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያ ምን እየተሰራ ነው ስንል ከግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መኖ ጥራት ደረጃ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከአቶ ዘላለም አበበ ጋር ቆይታ አድርገን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡   ሕ/ግ፦ የስራ ክፍሉ  በመኖ  ላይ ሚኖረው የቁጥጥር ስልጣን እሰከምን ድረስ ነው? አቶ ዘላለም ፦ በቀድሞው የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን  በአዋጅ ቁጥር 728/2004 መሠረት፡- “መኖ ማለት ለንግድ ዓላማ የተመረተ ወይም የተዘጋጀ የእንስሳት ምግብ ነው” ሲል፤ በመመሪያ ቁጥር 16/2010 መሠረት ደግሞ መኖ ማለት በመኖ አምራች ድርጅት በሀገር ውስጥ የሚመረት፣ ከውጭ ወደ ሀገር የሚገባ፣ በሀገር ውስጥም ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ለንግድ የሚዘዋወር ወይም ወደ ውጭ ሀገር ገበያ ለሽያጭ የሚወጣ የእንስሳት ምግብ ነው ሲል ያስቀምጣል፡፡ በአዲሱ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በመኖ ላይ የሚኖረዉ የቁጥጥር ሥልጣን ደግሞ በንግድ መኖ (Commercial Feed) ላይ ብቻ ሲሆን፣ ቁጥጥር የሚያደርገውም በመኖ ጥራትና ደህንነት ላይ ብቻ ሲሆን የስራ ክፍሉም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመኖ ምርት ጥራትና ደህንነት ላይ  ያስቀመጠውን ደረጃ መሰረት በማድረግ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡ ሕ/ግ፦ የመኖ ምርት ጥራትና ደህንነት ለማስጠበቅ የስራ ክፍሉ የሚያከናወናቸው ተግባራት  ምን ምን ናቸው? አቶ ዘላለም፦ የስራ ክፍሉ የመኖ ምርት ጥራትና ደህንነት ለማሰጠበቅ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል፦ የእንስሳት መኖ ግብዓትና ምርት ጥራትና ደህንት ባለስልጣኑ ባወጣው መስፈርት መሰረት በመገምገም ይመዘግባል፣ ለገበያ አንዲቀርብ ፈቃድ ይሰጣል፣  ያግዳል፤ ይሰርዛል ፣ አጠቃላይ የመኖ ደህንነትና ጥራት ቁጥጥር  ሥራዎችን ያቅዳል፣  አፈፃፀማቸውን በመገምገም ይተግብራል ፣ የእንስሳት መኖ ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የቅድመና ድህረ ግብይት ናሙና ይሰበስባል፤ በላቦራቶሪ ምርመራ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ ውጤቱንም መሰረት አድርጎ አግባብ ያለው እርምጃ ይወስዳል፣ ለእንሰሳት መኖ  ባለሙያዎች እና ለእንሰሳት መኖ አስተዋዋቂዎች የሙያ ፈቃድ እንዲሰጥ እና እንዲታደስ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ይፈፅማል፣ ከመኖ እና መኖ ጥሬ ዕቃ ጥራትና ጤንነት ጋር ተያያዥ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ጥራትና ደኅንነቱ የተጠበቀ መኖ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የጥራትና ደኅንነት ደረጃዎችን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ በተቀረጸው የሕግ ማዕቀፍ እና በፀደቀው ደረጃ መሰረት መከናወኑን መከታተልና  ለአፈጻጸሙም አሰፈላጊውን ድጋፍና ቁጥጥር ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ሕ/ግ፦ ከ2006 ዓ.ም እስካሁን ድረስ በመኖ ደህነትና ጥራት አጠባበቅ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ቢጠቀሱ? አቶ ዘላለም፦ የመኖ ጥራትና ደኅነትና ለማስጠበቅ ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ የንግድ መኖ አምራች ፋብሪካዎች፣ የመኖ ግብዓት አስመጪዎች እና የመኖና የመኖ ጥሬ እቃ ጅምላ ንግድ ድርጅቶች የተመዘገቡ ሲሆን በተጨማሪም ከባለሥልጣኑ መቋቋም በኋላ ለአምራቾችና ለተጠቃሚዎች በተከታታይ በተሰጠው ሥልጠና የመኖ ንግድ ሥራው እየተለመደ በመምጣቱ የማምረቻ ፋብሪካዎች በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ የሚገኝ የንግድ መኖ በመጠንም ሆነ በጥራት ብዙ ችግር ያለበት ሲሆን የጥራትና ደህንነት ቁጥጥሩ ካለፉት 8 ዓመታት ወዲህ በተሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችና የአቅም ማጎልበቻ ሥራዎች በ2006 ዓ.ም ተመዝግቦ ከነበረውና አሁን ላይ ከ50% በላይ እድገት አሳይተዋል፡፡ ሕ/ግ፦  የመኖ ጥራትና ደኅንነት የቁጥጥር ስራ ለመስራት እንቅፋት የሆነው ችግር ምንድን ነው? አቶ ዘላለም፦ የመኖ ጥራትና ደኅንነት የቁጥጥር ስራ ለመስራት እንቅፋት ከሆኑት መካከል አንዱ የመኖ ጥሬ እቃ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች መበራከት ሲሆን፣ የመኖ ጥሬ ዕቃዎችን ጥራትና ደህንነቱ በማይጠበቅበት ቦታ በማከማቸት እና ለመኖ አቀነባባሪዎች ዋጋ ጨምሮ ማቅረብ ነው፡፡ ሌላኛው ችግር ደግሞ የመኖ አምራች ድርጅቶች የራሳቸው የጥራት ምርመራ የላብራቶሪ ማእከል ስለሌላቸው፣ መኖ ለማምረት የሚጠቀሟቸውን የመኖ ጥሬ እቃ ሲቀበሉና በመጨረሻም ምርቱን አቀናብረው ለገበያ ሲያቀርቡ ምርቱ የተቀመጠውን የጥራትና ደኅንነት ደረጃ ማሟላቱን ለማረጋገጥ አዳጋች መሆኑ ነው፡፡   ሕ/ግ፦ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያላችሁ ቅንጅታዊ አሰራር ምን ይመስላል? አቶ ዘላለም ፦ የመኖ ምርት ጥራትና ደህንነትን የማስጠበቅ ስራ በስራ ክፍሉ ብቻ ውጤታማ ማድረግ ሰለማይቻል ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ መስራት ግድ ይላል፡፡ ስለሆነም   ከጥናትና ምርምር ተቋማት፣ የመኖን ጥራትና ደህንነት ቁጥጥርን ከሚደግፉ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመወያት ፣ በመተባበርና በመቀናጀት  እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሕ/ግ፦   በመጨረሻም የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ? አቶ ዘላለም፦ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመኖ ጥራትና ደህንነት የቁጥጥር ስራን ውጤታማ ለማድረግ ራሱን በቴክኖሎጅ ማብቃት፣ ለቁጥጥር ስራ ምቹ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋትና ከተለመደው አሰራር ወጥቶ በላብራቶሪ ፍተሻ ላይ መሰረት ያደረገ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጂታዊ አሰራር በመፍጠር የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ መሥራት አለበት፡፡ የግብርና ሚኒስቴርም ለመኖ ጥራትና ደህንነት መሰረታዊ ነገር የሆነውን የግብርና መልካም አመራረት (Good Agricultural Practices - GAP) ዘዴ እንዲስፋፋ ተግባሩን በበላይነት መምራት አለበት ስል መልእክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

በተጨማሪም ሕገ-ወጥ ሥራዎችን ለመከላከል ከሕብረተሰቡ የሚመጡ ጥቆማዎችን በመቀበልና ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ በኩል ውጤታማ ሥራ በመሥራታችን በአሁኑ ስዓት ሕገ-ወጥ ስራዎች እየቀነሱ የመጡበት ሆኔታ እንዳለ ለማስተዋል ችለናል፡፡ ሌላው ቅርንጫፍ ጽቤ/ቱ ሲቋቋም ሰፊ ሥራዎችን ያካተተ ስለሆነ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተን በመስራት ትልቅ ለውጥ አምጥተናል፡፡ ሕ/ግ፦ በቁጥጥር ወቅት በእንስሳት መድኃኒት ወይም መኖ ላይ ችግር እንዳለበት ካረጋገጣችሁ በኋላ የምትወስዱት እርምጃ ምንድን ነው? በወሰዳችሁት እርምጃ ሌሎች ምን ያህል ከጥፋት ተምረውበታል? ወ/ሮ ሚስራ፦ በሕገ-ወጥ የገቡ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ሲያጋጥሙን ወይም ጥራታቸው፣ ፈዋሽነታቸው ደኅንነታቸው ያልተረጋገጡ የእንስሳት መድኃኒትና ጥራታቸውና ደኅንነታቸው ያልተረጋገጡ የእንስሳት መኖዎች  ሲያጋጥሙን የዳሰሳ ጥናት ወይም ድኅረ ገበያ በመስራት ከዋና መ/ቤት ጋር በመሆን መድሃኃቱ ወይም መኖው እንዲሰበሰብና  እንዲወገድ ወይም ወደመጣበት አገር እንዲመለስ እናደርጋለን፡፡ በተጨማሪም ሕግና መመሪያውን ተከትለን አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ ሲሆን በዚህም መሰረት ሁለት ጅምላ ነጋዴዎች ላይ ህግና መመሪያውን ተከትለው ባለመስራታቸው ምክንያት ፈቃዳቸው እንዲሰረዝባቸው ተደርጓል፡፡ ሕ/ግ፦ አገልግሎት አሰጣጣችሁን ከብልሹ አሰራርና ኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ ለማድረግ የምታከናውኗቸው ተግባራት ምንድን ናቸው? በስራችሁ ላይስ ቅሬታዎች ሲኖሩ የምታስተናግዱባቸውና የምትፈቱባቸው መንገዶች ካሉ ቢገልፁልን? ወ/ሮ ሚስራ፦ ከኪራይ ሰብሳቢነትና ከብልሹ አሰራር ለመራቅ በዋነኛነት የቅንጅት ስራ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን፡፡ ስለሆነም ቁጥጥርና ድጋፍ ለማድረግ ስንሄድ ከባለስልጣኑ ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የቁጥጥር ሥራዎችን እናካሂዳለን፡፡ ባለሙያዎቹ ሲሄዱ በቅንጅት ሰለሆነ ለኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሆኔታ እስካሁን አልገጠመንም፡፡ ችግሮች ወይም ቅሬታዎች ሲኖሩም ውይይት በማድረግ ችግሮች የሚፈቱበትን አቅጣጫዎች አስቀምጠንም እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሕ/ግ፦ የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀማችሁ ምን ይመስላል? ወ/ሮ ሚስራ፦ የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ስንመለከት ካለው የበጀት እጥረትና የትራንስፖርት ችግር የተነሳ በሚፈለገው መጠን ውጤት የተመዘገበበት ነው ብሎ መናገር አይቻልም፤ ሆኖም በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የኬላ ድጋፍና ክትትል አድርገናል፡፡ እንዲሁም በዚህ በጀት ዓመት የእንስሳት መኖ ወደ  ውጪ አገር እንዳይወጣ ተጥሎ የነበረው እገዳ እንዲነሳ ባደረግነው ጥያቄ መሰረት እገዳው ተነስቶ ወደ ስራ መግባት ችለናል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን በዚህ ግማሽ ዓመት ክልሎችንና ግብር ሀይሎችን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ አቅደን በዕቅዱ መሰረት ማከናወን አልቻልንም ይህም የስልጠና በጀት ባለመኖሩ ምክንያት ነው፡፡ ሆኖም ግን በተቻለንና ባለን አቅም የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ማለት ነው፡፡ ሕ/ግ፦ ያጋጠሙ ችግሮች እና ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ?     ወ/ሮ ሚስራ፦ የምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በጣም ሰፊ ቦታዎችን የሚሸፍን ሆኖ ሳለ የመንቀሳቀሻ ተሸከርካሪ አለመኖሩ ለስራችን እንቅፋት ሆኖብናል፡፡ በተለይም የኢንስፔክሽን ሥራዎችን በምንሰራበት ወቅት በፍጥነትና በታቀደለት ጊዜ ለመስራት አዳጋች የሆነበት ሆኔታ አለ፤  ሌላው መስራት ያለባቸው ኬላዎች መዘጋታቸው ለሕገ-ወጥ ንግድ ዝውውር መስፋፋት ትልቅ ችግር ሆኖብናል እንዲሁም የቁም እንስሳ ኮንትሮባንድ ንግድ ቅርንጫፍ መ/ቤቱ ለመቆጣጠር ወደ ማይችልበት አቅም ላይ ደርሷል፡፡ እነዚህንም ችግሮች ባለስልጣን መ/ቤቱ በትኩረት አይቶ መፍትሄ ቢሰጠውና የቅንጅት ስራውም ተጠናክሮ ቢሰራ አሁን ካለው በተሻለ ሆኔታ ቀልጣፋና ግልፅ የሆነ እንዲሁም ውጤታማ አሰራርን ለመፍጠር ያግዛል፡፡ በተጨማሪም የግብረ ኃይሎች ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ የሚሄድበት አግባብ ቢኖር መልካም ነው እላለሁ፡፡ ሕ/ግ፦  ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን! ወ/ሮ ሚስራ፦ እኔም አመሰግናለሁ! ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

«ሕገ-ወጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ንግድ ዝውውርን በዘላቂነት ለመቀነስ የአጋር አካላት ሚና ወሳኝ ነው!» ወ/ሮ ሚስራ ሁሴን በባለሥልጣኑ የምስራቅ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ **** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በግብርና ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ ጎጂ ተጽዕኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ የማስቻል ዓላማ ይዞ በደንብ ቁጥር 509/2015 የተቋቋመ የፌደራል መ/ቤት ነው፡፡ የሕዝብ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባለሥልጣን መ/ቤቱ ይሄን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የከፈታቸውን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሥራ እንቅስቃሴ በመዳሰስ በየ2 ወሩ በሚያዘጋጀው የውስጥ ዜና መጽሔት የሚያቀርብ ሲሆን በዚህ ወር እትምም ከምስራቅ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ከወ/ሮ ሚስራ ሁሴን ጋር በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በእንስሳት መድኃኒትና መኖ ላይ እየተሰሩ ያሉ የቁጥጥር ሥራዎችንና አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ቆይታ አድርገን ለአንባቢያን በሚመች መልኩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፤ መልካም ንባብ፡፡ ሕ/ግ፦ የምስራቅ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባራትና የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ምንድን ናቸው? ወ/ሮ ሚስራ፡- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከተቋቋመበት 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም  ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ሲቋቋም በዋነኛነት የባለስልጣኑን ርዕይና ተልዕኮ ለማሳካትና ጥራቱ፣ ደኅንነቱና ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አቅርቦትን በማሳደግ አገሪቱ ከእንስሳት ሐብቷ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝና ከአደጉ አገሮች ጋር ተርታ እንድትሰለፍ ማስቻል ነው፡፡ ስለሆነም የአገራችን የምስራቁ ክፍል የእንስሳት መድኃኒትና መኖ በስፋት የሚንቀሳቀስበት ቦታ ስለሆነና ከባለስልጣን መ/ቤቱ የተሰጠንን ተልዕኮ ለማሳካት በዚህ በሰፊው ክፍል ውስጥ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ወሳኝ በመሆናቸው ሕገ-ወጥን ከመቆጣጠር አንፃር የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮችን ከባለስልጣኑ ጋር በማዘጋጀት፣ ግብረ ኃይሎች በማቋቋምና ሕገ-ወጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ቁጥጥር ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በማድረግ እና ኬላዎችን ድጋፍና ክትትል ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡፡ የምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ መግቢያና መውጫ ኬላዎች አካቶ የያዘ በመሆኑና ለሕገ-ወጥ ንግድ ዝውውርም ተጋላጭ ስለሆነ ጥብቅ የሆነ ድጋፍና ክትትል እናደርጋለን፡፡ በተጨማሪም ግብረ ኃይሎችን የመደገፍና የመከታተል ሥራዎችን መስራትና አግባባዊ የእንስሳት  መድኃኒት አያያዝና አጠቃቀም ላይ ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በምንቆጣጠራቸው ክልሎች በመገኘት የእንስሳት መድኃኒት አቅራቢዎች መስፈርቱን ማሟላታቸውንና አለማሟላታቸውን የቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት ሕግ ተላልፈው በተገኙት ላይ መመሪያውን መሰረት አድርገን እርምጃ እንዲወሰድባቸው እናደርጋለን፡፡ ሌላው አምስት (5) የእንስሳት መድኃኒት ጅምላ ነጋዴዎችንና አንድ (1) የእንስሳት መድኃኒት አስመጪ ተቋማትን ድጋፍና ክትትል አድርገን ከምዝገባና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን ሥራቸውን እንዲሰሩ አድርገናል፡፡ በተጨማሪም የእንስሳት  መኖ ማቀነባበሪያ ተቋም በዚሁ ዓመት ፈቃድ ተሰጥቶት ሥራ ላይ ይገኛል ማለት ነው፡፡  ሕ/ግ፦ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚወጡና በሚገቡ የእንስሳት መድኃኒት፣ መኖና የላቦራቶሪ መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም በእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስመጭና ጅምላ አከፋፋይ ተቋማት ላይ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር ሥራ የምታደርጉት በምን አግባብ ነው? ወ/ሮ ሚስራ፦ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት በተቋማችን አምስት የእንስሳት መድኃኒት ጅምላና አንድ አስመጪ እንዲሁም አንድ ኬላ ነው ያለን፤  ኬላው በድሬዳዋና ጅቡቲ በኩል ያለው ሲሆን ሁለት የመድኃኒትና አንድ የመኖ ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን እስከአሁን አንድ ዙር ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የእንስሳት መኖ ግብዓት ጥራቱና ደኅንነቱ ተረጋግጦ እንዲወጣ አድርገናል፡፡ የእንስሳት መድኃኒቱ ግን አሁን ካለው የአገሪቱ የሰላም ችግር የተነሳ ማስገባት አልተቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት በሕጋዊ መልኩ መድኃኒቶች ወደ አገር ውስጥ የሚገቡበት እድል ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ አብዛኛው መድሀኒቶች በሕገ-ወጥ የሚገቡ ስለሆኑ እነዚህንም ችግሮች ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ ትኩረት አድርገን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሕ/ግ፦ ሕገ-ወጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ንግድ የሚያደርሰውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበረሰባዊ የጤና ችግርን በተመለከተ ለማኅበረሰቡ በቂ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ የሚከናወኑ ተግባራት ምን ይመስላሉ? ወ/ሮ ሚስራ፦ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በመስጠት ሕብረተሰቡ በችግሩ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው እያደረግን ነው፡፡ በተጨማሪም አሁን በትምህርት ቤቶች ላይ በራሪ ወረቀቶችንና ብሮሸሮችን በማዘጋጀት ሚኒ ሚዲያዎችን በመጠቀም ወደ ማኅበረሰቡ ለመድረስ እየሰራን ሲሆን ከዋናው መስሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን በፋና ሬደዮ ጣቢያ ሕገ-ወጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አያያዝና አጠቃቀም ላይ በሶማሌኛ፣ በአማረኛ፣ በአፋረኛና በኦሮሚኛ ቋንቋዎችን መልዕክቶችን በማስተላለፍ ግንዛቤ ፈጥረናል። እንደሚታወቀው ባለስልጣኑ ላይ የበጀት እጥረት ስላለ ችግሩን ለመቅረፍ የሐብት ማፈላለግ ሥራዎችን በመስራት በመድኃኒት አያያዝና አጠቃቀም ላይ ባነሮችን በማዘጋጀት ለእንስሳት መድኃኒት ባለሙያዎችና ፋርማሲ ነጋዴዎች ስልጠናዎችን ሰጥተናል፡፡ ከዚህ ባለፈም በተለያዩ የስብሰባ መድረኮች ላይ የባለስልጣኑን ደንቦችንና መመሪያዎችን እንዲሁም አዋጆቹን የማሳወቅ ሥራዎችን ሰርተናል፡፡  ሕ/ግ፦ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ሕገ-ወጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ንግድ በብዛት የሚታይባቸውን አካባቢዎች ከመለየትና የተለዩትን አካባቢዎች ላይም ትኩረት ሰጥቶ ከመሥራት አንጻር የተሰሩ ሥራዎች ምን ይመስላሉ? ወ/ሮ ሚስራ፦ የዳሰሳ ጥናት እስካሁን ሁለት ዙር የተሰራ ሲሆን በተደረገው ዳሰሳዊ ጥናትም አራት ቦታዎች ማለትም ሀረር፣ ባብሌ፣ ኮምቦልቻና በዴሳ ተለይተው በትኩረት እየተሰራባቸው የሚገኙ ቦታዎች ሲሆኑ በዚህም መሰረት የተሻለ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡    ሕ/ግ፦ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ እስከአሁን የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ቢገልጹልን? ወ/ሮ ሚስራ፦ ቅርንጫፍ መ/ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን እንዳከናወነ በመግቢያችን ላይ ለመግለፅ ተሞክሯል፡፡ ተጨማሪ የምገልፀው ሕገ-ወጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ዝውውሮችን ቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአዋሽ፣ በሜይሶ፣ በሀረር፣ በባብሌ፣ በበዴሳ፣ በጅጅጋና በኮምቦልቻ ላይ ግብረ ሃይሎችን በማቋቋም ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌላው ክልሎችን ድጋፍና ክትትል በምናደርግ ጊዜ ደንብና መመሪያዎችን እንዲሁም አዋጆችን በመውሰድ የባለስልጣኑን ኃላፊነትና ተግባር እያስተዋወቅን እንገኛለን፡፡

እንስሳት ኳራንቲን ኢንስፔክሽን ሰርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት በ2015 ግማሽ በጀት ዓመት የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገለፀ፤ **** በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእንስሳት ኳራንቲንና ሪጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት በ2015 ግማሽ በጀት አመት በእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያዎች ወደ ውጪ ለኤክስፖርት የተዘጋጁ ቁም እንስሳት፣ የእንስሳት ውጤቶች ማርና ሰምን ጨምሮ የምርመራ እና የሠርተፍኬሽን አገልግሎት በተሻለ መልኩ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የገለጹት በባለሥልጣኑ የእንስሳት ኳራንቲንና ሪጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድማገኝ ደጀኔ ከውጪ ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ የቁምና የቤት እንስሳትን ጨምሮ ከሚመጥቡት አገር ከበሽታ ስጋት ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥና ወደ አገር የመግቢያ ፈቃድ እንዲያገኙ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ወንድማገኝ አክለውም በግማሽ በጀት ዓመቱ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያዎችና ቼክ ፖስቶችን በመገንባትና ተደራሽነታቸውን በማስፋት እንዲሁም በግንባታ ላይ ያሉትን ደረጃቸውን እንዲጠብቁና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የውስጥ አደረጃጀታቸውን በመፈተሽ አሁን ካሉበት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ሙያዊ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ በተቀባይ አገሮች በማስገምገም እውቅና እንዲያገኙ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ በ2015 በጀት ዓመት የ6 ወር ስራ አፈጻጸም በተመለከተ በኳራንቲን ጣቢያዎች ለሚገኙ ኢንስፔክሽን የሰርተፍኬሽን አገልግሎት 42000 ቁም እንስሳት (ዳልጋ ከብት በግና ፍየል፤ ግመል) የኳራንቲን አገልግሎት መሰጠቱን የተናገሩት ዶ/ር ወንድምአገኝ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጽር አገልግሎቱ 58 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ሆኖም በተናጥል ለግመል የተሰጠው የኢንስፔክሽን የሰርተፍኬሽን አገልግሎት ዝቅተኛ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይህም ክፍላችን የሚቀርብለትን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መሰጠት ከመሆኑ አንጻር የግመል ኤክስፖርት ጥያቄ ዝቅተኛ በመሆኑ ክንውኑ ሊቀነስ(21%) መቻሉን ገልፀዋል፡፡ በተመሳይይ ከውጪ ለሚገቡ የአንድ ቀን ጫጩት እና የለማ እንቁላል ከተገልጋዮች በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት አገልግሎቱ የሚሰጥ በመሆኑ ምክንያት ከእቅድ አኳያ ወጥ አፈጻጸም ባያሳይም እስካሁን ያለው አፈፃፀም የተሻለ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በኳራንቲን ኢምፖርት ኢክስፖርት ኢንስፔክሽንና ሰርተፊኬሽን የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ግልፅና ተጠያቂ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት ተገልጋዮች የአሰራር መመሪያዎችን በግልጽ ተረድተው መብትና ግዴታቸውን አውቀው እንዲገለገሉና ለአላስፈላጊ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳይጋለጡ ለማድረግ ጥረት መደረጉን የሚናገሩት ዶ/ር ወንድማገኝ ይህንንም ለማድረግ በአሰራር ሥርዓቶች ዙርያ በየዓመቱ እቅድ ተይዞለት ለባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በማዘጋጀትና ለባለሙያዎች ከዚህ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ችግሮች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ግልጽ ውይይት በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳይከሰቱ፤ ካሉም በጊዜ እንዲከስሙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ክፍሉ ካለው ሰፊ የስራ ጸባይ እንዲሁም ካለው ሰፊ የውጪ ተገልጋይ አንጻር በተቋሙ በኩል ለክፍሉ ልዩ ትኩሩት ተሰጥቶት ቢሰራ መልካም ነው ሲሉ ዶ/ር ወንድማገኝ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤