ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

前往频道在 Telegram

ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

显示更多
1 411
订阅者
+224 小时
+257 天
+8530 天
帖子存档
ጥራቱ፣ ደህንነቱና ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ የፀረ-ተባይ ማዳበሪያ ቁጥጥር ስርዓት ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ ****** የፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር በየነ ልደቱ ጥራታቸው፣ ደህነታቸውና ፍቱንነታቸው የተረጋገጠ የፀረ-ተባይና ማደበሪያዎች በሚፈለገው ደረጃ ተደረራሽነታቸውን ለማስፋት ባለስልጣኑ በሚኒስትሮች ምክርቤት በደንብ ቁጥር 509 የተሰጠውን ስልጣንና ተገባር በአግባቡ ለመፈጸም የሚያስችል አዲስ መዋቅር ተግባራዊ አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አስረድተው ፡፡ ይሄንኑ መሰረት ባደረገ መልኩ ከቀድሞ የዕፅዋት ጤናና ጥራት ዳይሬክቶሬት በመነጠል እንደተደራጀና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ በማዘጋጀት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በዚህም በሩብ ዓመቱ ለ30 የፀረ ተባይ እና ማዳበሪያ ናሙናዎች ሙከራ ምርምር ፈቃድ (trial authorization) ለመስጠት ታቅዶ 29 መሰጠቱን በሌላ በኩል 60 የፀረ ተባይእና ማዳበሪያ መስፍርቶቹን ያሟሉ ዶዜየሮችን ለመረከብ ታቅዶ 72 እንደተፈፀመና ከዕቅዱ በላይ ሊጨምር የቻለው አገልግሎቱ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ በሩብ ዓመቱ ይቀርባል ተብሎ ከታቀደው በላይ ዶዜየሮች በመቅረባቸው መሆኑን ስራ አስፈፃሚው አብራርተዋል፡፡ ዶ/ር በየነ አያይዘውም ለ600 ፀረ ተባይ እና አፈር ማዳበሪያዎች የቅድመ የማስገቢያ ፈቃድ መስጠት ታቅዶ ለ 582 የፀረ ተባይ እና አፈር ማዳበሪያዎች ወደ አገር የማስገቢያ መስፈር ማሟላታቸው ተረጋግጦ የቅድመ ማስገቢያ ፈቃድ እንደተሰጣቸው፤ለ10000 ቶን ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የፀረ-ተባይና ማዳበሪያዎች ላይ ኢንስፔክሽን በማከናወን ጥራትን ለማረጋገጥ ታቅዶ በ15181 ቶን የፀረ ተባይ /ማዳበሪያዎች ላይ የኢንስፔክሽን ስራ መከናወኑን በተመሳሳይ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ጭነቶች መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ለ500 ጭነቶች የጉምሩክ ማስለቀቂያ ደብዳቤ መስጠት የታቀደ ሲሆን ለ445 ጭነቶች አገልግሎቱን መስጠት ተችሎዋል ብለዋል፡፡ በሩብ ዓመቱ በፀረ ተባይ እና አፈር ማዳበሪያ ስራ ላይ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ አምራቾች፣አስመጪዎች፣ ጅምላ አከፋፋዮች እና የክምችት ማዕከላት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ደህንነታቸው እና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ለአዲስ 5 ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት እና ለ10 ነባር ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ለማደስ በእቅድ የተይዞ ነበረ፡፡ በዚህም ለ 17 አዳዲስ ተቋማት እና ለ66 ነባር ተቋመት የብቃት ማተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ አፈጻጸሙ በከፊተኛ ሁኔታ ሊጨምር የቻለው በፀረ ተባይ እና አፈር ማዳበሪያ ስራ አስፈፃሚ እንደ አዲስ ከተዋቀረ በሗላ ከዚህ በፊት ላለፉት 6 ዓመታት የብቃት ማረጋገጫ ሳያሳድሱ እገልግለግሎት ያገኙ የነበሩ ድርጅቶች እንዲያሳድሱ ጥብቅ ማሳሰቢያ በመተላለፉ እንደሆነ ዶ/ር በየነ አብራርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፀረ ተባይና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን (ግልፅ ለማድረግ) እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎትን ለመስጠት እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የተለያዩ የሕግ ማዕቀፍ ስራዎች እንደተሰሩ ስራ አስፈፃሚው ገልፀው በተይም እነዚህ ስራዎች መስመር ይዘው እንዲሄዱና በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲከናወኑ የህግ ማዕቀፍ ስራዎችን ማሻሻል፣ ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት እንዲሁም ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የፀረ-ተባይ ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ ስራ ሰፊና አፅንኦት ተሰጥቶት ሊሰራ የሚገባ በመሆኑ ከዚህ በተሻለ መልኩ አፈፃፀማችንን ውጤታማ ለማድረግ ከሚመለከተው አካላት ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

አቶ አበበ፦ ባለሥለጣኑ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ብልሹ አሰራሮችን በተመለከተ ጠንካራ ሥርዓት መዘርጋትና አስተማሪ እርምጃዎችን መውሰድ ለነገ የሚባል አይደለም፡፡ እኛም እንደተቋም ከአሁን ቀደም ከሕግና ከመመሪያ ውጭ ይፈጸሙ የነበሩ አንዳንድ የተለመዱ አሰራሮች እንዲቆሙና በሕግና በሥርዓት ብቻ እንዲመሩ ለማድረግ እየሰራን ነው፡፡ የተለመደን ብልሹ አሰራር ለማስቆም በምናደርገው ጥረት ቻሌንጆች ቢኖሩም ያለው ብቸኛ አማራጭ አሰራሮች ሁሉ ሕግና ሥርዓትን የተከተሉ እንዲሆኑ ማድረግ ብቻ መሆኑን በእምነት ይዘን እየሰራን ነው፡፡ በተጨማሪም ከባለሥልጣኑ ተቋማዊ የለውጥ አመራር ጋር በመሆን ጥቆማዎችና ቅሬታዎች የሚቀርቡባቸውን የኃሳብ መስጫ ሳጥኖች አስቀምጠናል፤ በእነዚህ የአስተያዬት መስጫ ሳጥን የሚቀርቡ ቅሬታዎች በየጊዜው እየተፈቱ እንዲሄዱ እናደርጋለን፡፡ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጣችን ከቅሬታና ከብልሹ አሰራር የጸዳ እንዲሆን በየጊዜው ለሠራተኞች ግንዛቤ ለመፍጠር በእቅድ ይዘን እየሰራንበት ነው፡፡ በመሆኑም ከመልካም አስተዳደር መጓደልና ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ተጨባጭ መረጃዎች በጥቆማ መልክ ከማንኛውም አካል ቢመጡ አስተማሪ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ግን ከፍ ብዬ ለመግለጽ እንደሞከርኩት አንዳንድ ከሕግና ከመመሪያ ውጭ የሆኑ ጥያቄዎችን ይዘው መጥተው ጥያቄው ሕግና አሰራርን የተከተለ አይደለም በሚል ውድቅ ሲደረግባቸው ችግሮች አሉ በሚል የሚነገረው ንግግር ትክክል አይደለም፡፡ ሁሉም አካል ልብ ሊለው የሚገባ ጉዳይ ጥያቄዬ ከሕግና ከመመሪያ ውጭ አይደለም ወይ የሚለውን ደጋግሞ እንዲያስብና ሕጋዊ ያልሆኑ አሰራሮችን መከተል እንደሌለበት በዚህ አጋጣሚ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ ከሕግ፣ ከመመሪያና ከአሰራር ውጭ ዛሬም ወደፊትም አናስተናግድም የሚለው ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በቀጣይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከ4 የባለሥልጣኑ የሥራ ክፍሎች ጋር ማለትም ከሕግ፣ ከኦዲት፣ ከሥነ ምግባር መከታትያና ከተቋማዊ ለውጥ ጋር ተቀናጅቶ ለመሥራት አቅጣጭ ተቀምጦ በተቀመጠው አቅጣጭ መሰረት እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት አቶ አበበ፦ ሥራዎች ሲሰሩ ከችግር ነጻ በሆነ መንገድ አይደለም፡፡ በሳለፍነው የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሥራዎችን ሥንሰራ ያጋጠሙ ችግሮች በርካታ ናቸው፡፡ በዋናነት ግን ተቋሙ አዲስና በሽግግር ላይ ያለ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የግብዓት (ማለትም የኮምፒውተር፣ ወንበርና ጠረጴዛ፣ ተሸከርካሪ) እጥረት፤ የበጀት፣ የሰው ኃይል እጥረት፤ የሕጻናት ማቆያና የጥበቃዎች ማረፊያ አለመኖር የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚመለከተን አካላት ተቀናጅተንና ተናበን እንድንሰራ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በተጨማሪም የተቋማችን ርዕይ፣ ተልዕኮና እቅድ ከግብ ለማድረስ ለእድገታችን እንቅፋት የሚሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን መታገል ለአንድ አካል ተለይቶ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

አቶ አበበ፦ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በህግ ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ ለሚሰጠው አገልግሎት ተመጣጣኝ የአገልግሎት ገቢ ገንዘብ መሰብሰብ ይገኝበታል፡፡ የሥራ አመራር ዋና አስፈጻሚም መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የሚሰበሰቡ ገቢዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውንና ወደ ባንክ መተላለፋቸውን ይከታተላል፡፡ ይሄን የሚከታተልበት አግባብም በባለሥልጣኑ የሚሰበሰቡ ገንዘቦችን በሚመለከት በሲቪል ሰርቪስ መደብ ተቀርጾለት ባለሙያም ተመድቦለት ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ ይሄ ባለሙያ ዋና ሥራው ገቢዎችን መሰብሰብና ለዚህ በተከፈተው አካውንት ገቢ ማድረግ ነው፡፡ ሥለዚህ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከባለሙያው የሚመጣውን ሪፖርትና የባንክ ሰነድ በመመልከት ክትትል ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከገቢና ወጭ የገብርና ምረትቶች አንድ መቶ ሃምሳ አራት ሽህ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር (154199 ብር) ፣ ከዘር ጥራት ቁጥጥር አገልግሎት ክፍያ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ብር (6800 ብር) በአጠቃላይ አንድ መቶ ስልሳ አንድ ሽህ ብር (161000 ብር) ገቢ ተደርጓል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ የባለሥልጣን መ/ቤቱ ሀብትና ንብረት እና የሎጀስቲክና የግብዓት አጠቃቀም ሕግንና ሥርዓትን የተከተለ እንዲሆን ምን እየተሰራ ነው? አቶ አበበ፦ ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ ኃብትና ንብረቱን ሕግና ሥርዓት በተከተለ መንገድ በአግባቡ መጠቀም አለበት፡፡ እንደ ሥራ አመራር ሥራ አስፈጻሚ ተቋሙ ያለው ኃብት ውስን ስለሆነ ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ ሁሉም በፍትኃዊነት እንዲጠቀም ጠንካራ እርምጃዎች መወሰድ አለበት በሚል እዚህ አካባቢ በርካታ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው፡፡ ለአብነትም ከሠው ኃብት አንድ እና ከጠቅላላ አገልግሎት ሁለት በአጠቃላይ ሶስት አባላት ያሉት ኮሚቴ በማዋቀር ተቋሙ ያለውን ውስን ንብረት በአግባቡ እና በፍትኃዊነት ለመጠቀም ትርፍ ንብረቶች ያሉባቸውን የሥራ ክፍሎች በመለዬት ከየክፍሎቹ ንብረቶቹን የማሰባሰብና እጥረት ላለባቸው ክፍሎች የማሰራጨት ሥራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም አንድ ቦታ ተከማችተው የነበሩ ኮምፒውተር፣ ጠረጴዛ የመሳሰሉ ግብዓቶችን በፍትኃዊነት ማከፋፈል ተችሏል፡፡ በተጨማሪም የግብርና ሚ/ር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቲ ተቋማችንን ሊጎበኙ በመጡበት ወቅት ተቋሙ አዲስና ሥራውም እጅግ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንደመ/ቤት ያሉብንን የግብዓትና የሎጅስቲክ ችግሮችን አንስተንላቸው የነበረ በመሆኑ በእነሱ በኩል ድጋፍ ለማድረግና ተቋሙን በግብዓት ለማጠናከር የሚያስችል አውንታዊ ምላሽ አግኝተናል፤ እሱንም በመጠባበቅ ላይ ነን፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ከግዥ መጓተትና ከትራንስፖርት ስምሪት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ምን እየተከናወነ ነው? አቶ አበበ፦ ከግዥ ጋር በተያያዘ መጓተት አለ የሚለው ቅሬታ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን አጠቃላይ የመንግስት ግዥዎች በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በማዕቀፍ የሚገዙ በመሆናቸው ከዚያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ ነው፡፡ ሆኖም በእኛ ደረጃ የሚገዙ ጥቃቅን ግዥዎች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲገዙና እንዲሰራጩ ለማድረግ የባለሙያዎችን አቅም ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ አድርገናል፡፡ ለአብነትም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 13 አካባቢ ባለሙያዎች በግዥ አፈጻጸም ዙሪያ ስልጠና አግኝተዋል፡፡ ሥለሆነም ሕግና መመሪያው በሚፈቅድልን መሰረት በእኛ ደረጃ የሚፈጸሙ ግዥዎች በተመደበልን በጀት መሰረት ተገዝተው ሥራ ላይ እንዲውሉ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው፡፡ ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች ምንጫቸው ሁለት ነው ብለን እንወስዳለን፡፡ አንደኛው ባለሥልጣኑ ካለው የትራንስፖርት እጥረት የሚነሳ ሲሆን ይሄን ለመፍታት የተቋሙ የበላይ የሥራ ኃላፊዎች ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚ/ርና ከሌሎች መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር እየተነጋገርን ነው፡፡ ሌላኛው ያለውን ትራንስፖርት ፍትኃዊ በሆነ መንገድ ካለመጠቀምና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቅሬታ ነው፡፡ ይሄን ችግር ለመፍታት ከአሁን በፊት ትራንስፖርት አካባቢ ሥራዎች በአንድ ሰው ብቻ ይሰሩ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ የሥራ ክፍፍል እንዲኖር ተደርጓል፡፡ በዚህም ሥምሪት የሚወጡ መኪኖችን ተራ የሚያሲዝና የሚቆጣጠር አንድ ባለሙያ፣ ሥምሪት የሚሰጥ አንድ ባለሙያ እና ሥምሪት የሚወጡ መኪኖችን የነዳጅ አጠቃቀማቸውን የሚቆጣጠር አንድ ሌላ ባለሙያ ተመድበው ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን መኪኖቻችን ወደ ጋራዥ በሚገቡበት ጊዜ በታዘዘው መሰረት ተሰርተው መውጣታቸውን የሚቆጣጠር ባለሙያም የተመደበ ሲሆን የመኪኖችን የነዳጅ አጠቃቀምና የጋራዥ ሂደታቸውን በተመለከተ የሚቆጣጠር 3 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድንን በኮሚቴ መልክ በማቋቋም እየሰራን ነው፡፡ በቀጣይም ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድና ጠንካራ ሥርዓት ለመዘርጋት ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር ተቀናጅተን የምንሰራ ይሆናል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ እርስዎ በሚከታተሏቸው የሥራ ክፍሎች በርካታ ብልሹ አሰራሮችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚያስከትሉ ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ ይነገራልና እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ጥቆማዎችን በምን መልኩ እየተቀበላችሁና ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ቢያብራሩልን?

ለባለሥልጣኑ ርዕይ፣ ተልዕኮና ዓላማ ከግብ መድረስ እንቅፋት የሚሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን መታገል ለአንድ አካል ብቻ የሚተው አይደለም! አቶ አበበ ገለታ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በግብርና ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ ጎጂ ተጽዕኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ የማስቻል ዓላማ ይዞ የፌዴራል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት የተቋቋመ የፌደራል መ/ቤት ነው፡፡ ይሄን የተቋቋማለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ያለውን ግብዓት በአግባቡ መጠቀም፣ ብቁ የሰው ኃይል መገንባት፣ የተመደበለት ፋይናንስ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን መቆጣጠር፣ ተቋማዊ ሪፎርም መገንባት፣ ከእቅድ ጀምሮ እስከሪፖርት ድረስ ሁሉም ሠራተኛ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግና የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን መቀነስ ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ወር የዜና መጽሔት እትማችን እነዚህን ስራዎች በዋናነት ከማያስተባብሩት የባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሆኑት አቶ አበበ ገለታ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ መልካም ንባብ! ሕዝብ ግንኙነት፦የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በዋናነት የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት ምንድን ናቸው? አቶ አበበ፡- የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ነው የሚያከናውነው፡፡ ለአብነት ለመጥቀስ ያክልም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍልን እቅድ እንዲያዘጋጁ ከማድረግ ጀምሮ ይከታተላል፤ ይመራል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮችና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል፡፡ እንዲሁም የባለሥልጣኑ ስትራቴጅካዊና ዓመታዊ እቅድ እንዲዘጋጅና እንዲተገበር በበላይነት የመከታተል፤ መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የሚሰበሰቡ ገቢዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውንና ወደ ባንክ መተላለፋቸውን መቆጣጠር፤ የተቋሙን ሐብትና ንብረት፣ የሎጅስቲክና ግብዓት አያያዝና አጠቃቀም የመንግስት ሕግንና ደንብን በተከተለ አግባብ ስለመተግበሩ መከታተል፣ የተቋሙን የግዥ አፈጻጸም ከእቅድ ጀምሮ የተገዙ የተቋም ንብረቶችና ግብዓቶች ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች እስከሚሰራጩ ድረስ ክትትል በማድረግ መምራት፣ የተቋሙ ቋሚ ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ዘመናዊ አሰራርን የተከተሉ እንዲሆኑ በበላይነት መከታተል፣ የመ/ ቤቱን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡ አሰራሮች እንዲዘረጉና እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የባለሥልጣኑን የአይሲቲ የብልጽግና ልማት እንዲተገበርና ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ ሲስተሞች እንዲዘረጉ የማስተባበር፣ ከተገልጋዩ ሕብረተሰብ የሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በፍጥነት ተገቢ ምላሽ የሚያገኙበትን ሥርዓት እንዲዘረጋ የመናድረግና የመከታተል ተግባራትንም ያከናውናል፡፡ በአጠቃላይ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በ6ቱ የሥራ ክፍሎች ማለትም ሰው ኃብት፣ መሰረታዊ አገልግሎት፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን፣ ግዥና ፋይናንስ፣ ለውጥና ስትራቴጅክ ሥራ አስፈጻሚዎች ውስጥ የሚከናወኑ ሥራዎችን በሙሉ ያስተባብራል፤ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤ ያስተገብራል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ባለሥልጣኑ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የሚያስችለው የበቃ የሰው ኃይል ከመፍጠር አኳያ ምን የታሰበ ነገር አለ? አቶ አበበ፦ በአመለካከትና በክህሎት የበቃና የጠራ ግንዛቤ ያለው የሰው ኃይል መኖር ለተቋም ስኬት እጅግ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ ይሄን ከግምት ውስጥ በማስገባት የባለሥልጣን መ/ቤታች የሰው ኃይል ልማት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህም ተቋሙ የሠው ኃብትና ብቃት ሥራ አመራር በኩል በየክፍሉ ያሉ የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥልጠና ፍላጎቶች ተለይተው እንዲታቀዱና እቅዱን መሠረት በማድረግም በብቃት፣ በክህሎትና በእውቀት ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ክፍተቱን የሚሞሉ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግ ለተቋሙ ግብ መሳካት የሚተጋ ብቃት ያለው የሰው ሀይል እንዲኖር ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም የየክፍሉ የሥልጠና ፍላጎቶች ተለይተውና ተደራጅተው ያለቁ ሲሆን በቅርቡም ለተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች የሚቀርብ ይሆናል፡፡ አሁን ላይም ለረጅም ጊዜ የትምህርት እድል ሠራተኞች በውድድር ላይ ይገኛሉ፤ በሌላ በኩል ከሥልጠና በዘለለ የሠራተኞችን አቅም ለመገንባት የሥራ ክፍሎች ከሌሎች አቻ መ/ቤቶች ጋር የልምድ ልውውጥ የሚደረጉበትን ሥርዓት እየዘረጋን ነው፤ በቅርቡም የባለሥልጣኑ ተቋማዊ የአመራር ለውጥ ደብረዘይትና ሰበታ በመሄድ ከሌሎች አቻ መ/ቤቶች ጋር የልምድ ልውውጥ ያደረገ ሲሆን ያደረገውን የልምድ ልውውጥ በመቀመር በተቋማችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ ይሄ በሌሎች ክፍሎችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ በባለሥልጣኑ የሥራና የበጀት እቅድና ሪፖርት ላይ ሁሉም ሠራተኛ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረው ብሎም ሁሉም የሥራ ክፍሎች በጀታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ውጤታማ ሥራዎችን እንዲሰሩ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ቢያብራሩልን? አቶ አበበ፦ ይሄን ጥያቄ በሁለት ከፍዬ ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡ የመጀመሪያው በባለሥልጣኑ ስትራቴጅክ እቅድ በተያያዘ ነው፡፡ ሁሉም ሠራተኛና አመራር ከእቅድ ጀምሮ ባለሥልጣኑ በሚተገብራቸው ስትራቴጅዎችና ፕሮግራሞች ዙሪያ የጋራ አረዳድ ይዞ ለተቋሙ ግብ መሳካት እንዲሰራ ለማድረግ አሳታፊነት መኖር አለበት በሚል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በሁሉም የሥራ ክፍል የሚታቀዱ እቅዶች ሠራተኞች ጭምር የተሳተፉበትና የጋራ መግባብት የተደረሰበት እንዲሆንና አፈጻጸሙም በየጊዜው የጋራ እየተደረገ መሄድ እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጦ በዚያ መልኩ እየተተገበረ ነው፡፡ በቅርቡም ለቡድን መሪ እና ለሥራ ኃላፊዎች በቅርቡ በአዳማ በሊደርሽፕ፣ በቲም ቢዩልዲንግና በተቋሙ ስትራቴጅክ እቅድ ዙሪያ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ይሄ ሥልጠና እስከታችኛው ፈጻሚ ሠራተኛ ድረስ ለመስጠትም በእቅድ ተይዞ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ ሁለተኛው የበጀት አጠቃቀምን በተመለከተ መሪ ሥራ አሥፈጻሚዎች በጀት ለእያንዳንዱ ሥራ ክፍል ተመድቦ በፋይናንስ የአሠራር ሥርዓት መሰረት የየክፍላቸውን በጀት እየተጠቀሙ ነው፡፡ የድጋፍ ሠጭ ክፍሎች በጀት በፑል ወይም በጋራ የተቀመጠ በጀት ስለሆነ እያንዳንዱ የሥራ ክፍል የበጀት እቅዱን እንዲያቀርብ ተደርጎ ሥራዎችን ለመሥራት ሲፈልግም ፕሮፖዛል እየሰራ አቅርቦ እያስፈቀደ በዚያ መንገድ በጀቱን በፍትኃዊነት እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው፡፡ ነገር ግን በጀቱ የጋራ ስለሆነ የበጀት አጠቃቀሙ እንደየሥራ ክፍሉ እንቅስቃሴ ይወሰናል ማለት ነው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ባለሥልጣን መ/ቤቱ በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት የሚሰበስበው ገንዘብ በአግባቡ እየሰበሰበ መሆኑንና ወደ ባንክ መተላለፋቸውን በምን አግባብ ክትትል እየተደረገ ነው?

የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር ለህብረ ብሄራዊ አንድነት መጎልበት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በኢትዮጵያ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን‹‹ብዝሀነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ግብርና ባስልጣን መሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት ተከበረ፡፡የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ስናከብር የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል፣ እምነትና የአኗኗር ዘይቤ ያለን ህዝቦች መሆናችን በመረዳት እነዚህን ልዩነታችንን ውበታችን መሆኑን በመረዳትና በማክበር ወደ አንድ ኅብረ ብሄራዊ አንድነት በማምጣት አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አዲስ እጅጉ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀውን መወያያ ሰነድ ገለፃ በማድረግ አገራችን ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚገኙባት በመሆኑ ይህንን ውበታችን በማስጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ የአብሮነትንና የመቻቻል መንፈስን በማላበስ አገራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ስናከብር አብሮነትን፣ ወድማማችነትንና መቻቻልን የምናሳይበትና አንድነታችንን በማጠናከር በልዩነታችን የሚመጡትን ክፍተቶች የምናርምበትና የምናስተካክልበት ነው ብለዋል፡፡በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነት ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየና ተጠብቆ የኖረ የአንድነታችንና የአብሮነታችን መገለጫ በመሆኑ ልዩነትን መሰረት በማድረግ በተለያዩ ሁኔታዎች የሚመጡ የእርስ በእርስ ነቀፌታዎችንና ግጭቶችን በማስወገድ ልዩነታችን ውበታችን መሆኑን በመረዳት መከባበርና መቻቻል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ሙስናን ለመከላከል የእያንዳንዳችን ሀላፊነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በአለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን ‹‹ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል›› በሚል መሪ ቃል ህዳር 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የስብሰባ አዳራሽ በድምቀት ተከበረ፡፡የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በመክፈቻ ንግግራቸው ሙስና ዜጎችን ለስቃይ፤ ለእንግልት እና ለከፋ ድህነት የሚዳርግ አደገኛ የህዝብ ጠላትም ወንጀልም ስለሆነ ሁሉም ሰው ይህ ወንጀል ሲፈፀም እያየ ምን አገባኝ ከማለት መንፈስ በመውጣትና ራሱንም ከዚህ ድርጊት በማራቅ ሊታገለው ይገባል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሙስናን መፀየፍ ካልቻልን የተቋማችንን ገፅታ ከማበላሸቱ ባለፈ ሰፊውን የማህበረሰብ ክፍል እየጎዳን መሆኑን በማሰብ አጥብቀን ልንከላከለውና ልንቆጣጠረው ይገባል ብለዋል፡፡የስነምግባርና ፀረ ሙስና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መሀሙድ አማን የመወያያ ሰነዱን መሰረት አድርገው ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን ሙስናን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሀገራዊ ጥረት ሰራተኛው ተረድቶ በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲቻል ለማነሳሳትና ንቅናቄ ለመፍጠር ያለመ ስለሆነ በዋነኛነት ተቋማችን የተጣለበትን ተግባርና ሀላፊነት በመረዳት አገልግሎት ሰጪ በመሆናችን ተገልጋዩ ህብረተሰብ መብትና ግዴታቸውን በውል ተገንዝቦ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ግንዛቤን ፈጥሮ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ባለስልጣኑ እንደ አዲስ ከመደራጀቱ ጋር ተያይዞ ሰፊ ኋላፊነቶችና ስራዎች እንደሚጠበቅበት ተረድቶ ለሙስና ተጋላጪ የሆኑ ቦታዎችን መለየት፤ ጥቆማዎችን መስጠትና የማጋለጥ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው ሙስና በአንድ አገር ላይ የሚያስከትለውን ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራው ቀውስ በመረዳት በተለይም ተቋማችን ሰፊ የቁጥጥር ስራዎችን የሚሰራና ትልቅ ሀላፊነት የተጣለበት በመሆኑ ሰራተኛው ይህንን ተረድቶ ከዚህ እኩይ ሀሳብና ተግባር በመራቅ በተለይም እንደዚህ አይነት ችግሮች ሲከሰቱ ሁሉም ሰራተኛ የራሱ ጉዳይ አድርጎ በመውሰድ በጥንቃቄ ሊሰራና ሙስናን በጋራ ሊታገል እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሙስና በተቋማችን ላይ ታማኒነትን ከማሳጣት አልፎ የማህበረሰባችነን ኑሮ የሚጎዳና ለከፋ ህይዎት የሚዳርግ በመሆኑ ሁሉም ሰራተኛ ለአንድ ዓላማና ለአንድ ግብ በመሰለፍ ተቋማችንን ከዚህ ፀያፍ ስራ በመጠበቅ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የህዳር ወር 2016 ዓ/ም ዜና መጽሄት

አቶ ፍሰሀ፦ ባለሥልጣኑ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ያስችለው ዘንድ የ10 ዓመት መሪ እቅድ አዘጋጅቶ ወሥራ ገብቷል፡፡ በመሪ እቅዱም ከእጽዋት ዝርያ ለቀቃ፣ ጥበቃና የዘር ጥራት አኳያ የዝርያ ለቀቃ እና ጥበቃ አሰራር ማጠናከርና ስርዓት መዘርጋት፣ የአዳቃዮች መብት ጥበቃ ሥርዓትን መተግበር፣ የድህረ-ጥራት ፍተሻ ጣቢያዎችን ማጠናከር፣ አዳዲስ ማደራጀትና የመስኖ ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ በመስክ የዘር ጥራት ማረጋገጥን ማዘመን፤ አቅም መገንባት እና የራስ በራስ ዘር ጥራት ማረጋገጥ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ፣ የዝርያ ብቃት ሙከራና የዝርያ ባለቤትነት የሚረጋገጥባቸው የዝርያ ልዩ መሆን፣ ወጥና የማይለዋወጥ መሆኑ የሚፈተሸባቸው ጣቢዎች በአገሪቱ ወካይ ሥነምህዳሮች ማቋቋም፣ የአካባቢ ዝርያዎች እውቅና አግኝተው በስፋት አንዲባዙ ለማድረግ የባህርይ ልየታ ፍተሻ ስራዎችን መደገፍ፣ የዘር ጥራት ቁጥጥርና የማረጋገጥ ሥርዓቱን ብቃት ለማረጋገጥ የምርምር ተግባራት በአራቱም ክልሎች ማካሄድ፣ የክልሎች የዘር ላቦራቶሪ አቅም መገንባት፣ የዝርያ ብቃትና ዘር ጥራት ማረጋገጥ አገልግሎቱን ለ3ኛ ወገን ማካፈል አማራጮችን ማስፋት፣ አገራዊ ሁለገብ የዕፅዋት ጤናና ጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ መገንባት፣ የዕፅዋት ዘር ጥራት ላቦራቶሪዎች ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ዋና ዋና የትኩረት መስክ ተብለው የተለዩ ናቸው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያላችሁ ቅንጅታዊ አሰራር ምን ይመስላል? አቶ ፍስሀ፦ የእጽዋት ዘር አዋጁን በጥልቀት ከተመለከትነው ማንኛውንም ዘር ከመነሻው እስከ መዳረሻው ያሉ ባለድርሻ አካለትን የሚወክል ነው፡፡ ስለሆነም የዝርያ ብቃት እና የዘር ጥራት ማረጋገጥ ስራ እጅግ ሰፊና በርካታ ተዋናዮች የሚሳተፉበት እንደመሆኑ መጠን ቅንጅታዊ አሰራርን እና ከፍተኛ የሆነ ሀብት ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተን የየበኩላችንን መወጣት የግድ ይላል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በዘርፉ ካሉ ተወናዮች ጋር ያለን ግንኙነት መልካም ሲሆን ግንኙነቱ ወደፊት የበለጠ እንዲጠናከር አስፈላጊው ሁሉ ለማድረግ ክፍሉ ዝግጁ ነው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ቀረ የሚሉት ወይም ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ? አቶ ፍስሀ፦ የህግ ማእቀፋትን ማዘጋጀት መከለስ ብቻ በቂ እንዳልሆነና በውስጡ የተዘረዘሩ አገልግሎቶችን በተገቢው ሁኔታ ለመስጠት ተቋማችንን/ክፍሉን ብቃት ባለው የሰው ኃይል ማደራጀት እንደሚያስፈልግ፣ የዝርያ ብቃት መፈተሻና የባህሪ መገለጫ ስራዎችን የሚሰሩባቸውን ቦታዎችን ለማግኘት ጥረት ማደረግ እንደሚገባ፣ የዘር ጥራት የምንፈትሽባቸውን ላብራቶሪዎች አቅም በቁሳቁስና በአሰራር ማሰደግ እንደሚገባ፣ ዘመኑን ያዋጀ የአሰራር ስርዓት (ዲጂታላይዝድ አገልግሎት አሰጣት) መዘርጋትና መገንባት እንደሚያስፈልግ ለዚህም የሚመለከታቸው እካላት እንዲያግዙን መልዕክቴን አስተላልፋለው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን፡፡ አቶ ፍስሀ፦ እኔም አመሰገናለሁ፡፡

የዘር ላቦራቶሪዎች በናሙና አውጭ ወይም በኢንስፔክተር በሚቀርብላቸው ናሙና መሰረት በላቦራቶሪ አናሊስት አማካይነት የጥራት እና ጤንነት ፍተሻ እንደሚያከናውኑና ውጤቱንም እንደሚገልጹ፣ ከዘር ጥራት ኢንስፔክሽን ጋር በተያያዘ በሀገር ውስጥ ተመርቶ ለውጭ ገበያ ለሚቀርብ ዘር በሚመረትበት ወይም በሚዘጋጅበት ቦታ በባለስልጣኑ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ተመርቶ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርብ ዘር በሚመረትበት ወይም በሚዘጋጅበት ወይም በሚሸጥበት ቦታ በክልል ባለስልጣን እንደሚከናወን ያብራራል፡፡ በተጨማሪም ሕገ-ወጥ የዘር ግብይትን ለመቆጣጠር በክልል ባለስልጣን እና እንደአስፈላጊነቱ በባለሰልጣኑ እንደሚከናወን፣ ባለስልጣኑ እና እያንዳንዱ የክልል ባለስልጣን የዚህን አዋጅና በአዋጁ መሠረት የወጣ ደንብንና መመሪያን ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ እንደአስፈላጊነቱ የግል ወይም የመንግስት የዘር ኢንስፔክተሮችን እንደሚሰየሙና እነዚህ የዘር ኢንስፔክተሮች ከዘር ጥራት ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን በምርመራ ለማረጋገጥ የዘር ናሙና የመውሰድ፣ ለዘር ላቦራቶሪ የማስረከብ፣ በአዋጁ መሰረት በወጡ ደንቦችና መመሪያዎች አፈጻጸም አግባብነት ያላቸው የምስክር ወረቀቶች፣ የማስገቢያ ፈቃዶች፣ መዛግብቶችና ሌሎች ሰነዶች እንዲቀርቡለት የመጠየቅና የመመርመር እንዲሁም ኮፒ የማድረግ፣ በማናቸውም የመንግስት የስራ ሰዓት ወደ ማናቸውም ዘር ማምረቻ ቦታ፣ ዘር መጋዘን ወይም ዘር ማዘጋጃ ተቋም በመግባት ወይም በማናቸውም ሰዓት ማንኛውንም ዘር የጫነ ተሽከርካሪ በማስቆም ኢንስፔክሽን የማካሄድ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ የዘር ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ በአራቢ ዘር፣ በቅድመ መስራች ዘር፣ በመስራች ዘር፣ በተመሰከረለት አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ የዘር ደረጃ እንዲሁም ጥራቱ በተገለጸ እና በአስቸኳይ ጊዜ ዘር ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይገልጻል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከውጭ የሚገባ ዘር ከኢትዮጵያ ዘር ጥራት ደረጃዎች ጋር እና በሀገር ውስጥ ተመርቶ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ዘር ከተቀባዩ ሀገር ወይም እንደ አሰፈላጊነቱ ከዓለም አቀፍ ጥራት ደረጃ ጋር መጣጣሙን ያረጋግጣል፡፡ በተጨማሩም ከሀገር ውጭ ለተቋቋሙ ለማናቸውም ከኢትዮጵያ ዘር ጥራት ምርመራና ማረጋገጥ ሥርዓት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው ብሎ ላመነባቸው የዘር ጥራት አረጋጋጭ ድርጅቶችና ለምርመራ ውጤታቸው እውቅና የመስጠት፣ በክልል ባለስልጣን ሲጠየቅ በአንድ ክልል መመረቱ ተረጋግጦ በሌላ ክልል ለሚከማች ዘር የላቦራቶሪ ፍተሻ አገልግሎት ይሰጣል፤ የዘር ጥራት ደረጃ ላሟላ ዘር የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ምልክት የመስጠት ሥልጣን በአዋጅ ተሰጥቶታል፡፡ በተያያዘም ባለስልጣኑ ከውጭ የገባ ዘር በብሔራዊ የዝርያ መዝገብ ከተመዘገበ ዝርያ የተገኘ ዘር መሆኑን፣ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተሰጠው የዘር አስመጪ የገባ መሆኑን፣ በአዋጁ መሠረት የተመረመረና ከዘር ጥራት ደረጃ ጋር የተጣጣመ መሆኑን፣ አዋጁን ተከትሎ በሚወጣ ደንብና መመሪያ የተወሰኑ ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን ሲያረጋግጥ የዘር ጥራት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል። በተመሳሳይ ባለስልጣኑ ወደ ውጭ የሚላክ ዘር በብሔራዊ የዝርያ መዝገብ የተመዘገበ ዝርያ መሆኑን ወይም ሳይመዘገብ ተባዝቶ ወደ ውጭ እንዲላክ የተፈቀደለት ዝርያ መሆኑን፣ የተመረተውና የተዘጋጀው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተሰጠው ሰው መሆኑን እና አዋጁን ተከትሎ በሚወጣ ደንብና መመሪያ የተወሰኑ ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን ሲያረጋግጥ የዘር ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል። ማንኛውም የዘር ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በሀሰተኛ፣ በተሳሳተ ወይም ባልተሟላ መረጃ የተገኘ ከሆነ፤ ወይም የቅድመ ወይም ድህረ ቁጥጥር ሙከራ ወይም የድጋሜ የዘር ላቦራቶሪ ፍተሻ ተካሂዶ የዘር ጥራት ደረጃዎች አሟልቶ ካልተገኘ የመሰረዝ መብት የተሰጠው ሲሆን ባለስልጣኑ ወይም የክልል ባለስልጣን የዘር ጥራት ምስክር ወረቀት ከመሰረዙ በፊት ለባለቤቱ በማሳወቅ ቅሬታው የሚደመጥበትን እድል እንደሚሰጥም በአዋጁ ተገልጽዋል፡፡ ሌላው በአዋጁ የዘር ጥራት ማረጋገጫ መለያ ምልክት ስለማድረግም የተገለጸ ሲሆን በአዋጁ ማንኛውም ዘር የባለስልጣኑ ወይም የክልል ባለስልጣን የዘር ጥራት ማረጋገጫ መለያ ምልክት ሳይደረግበት ለሀገር ውስጥ ወይም ለውጭ ገበያ ሊቀርብ እንደማይችል ተገልጽል፡፡ በአዋጁ የዘር ጥራት ደረጃ የማያሟላ ዘርን በተመለከተ በግልጽ የተገለጸ ሲሆን ፍተሻ የተደረገበት ዘር የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ካላሟላ የዘር ጥራት ደረጃው ዝቅ እንዲል ወይም ውድቅ እንዲሆን እንደሚደረግ እና የዕጽዋት ዘር ውድቅ እንዲሆን የተደረገበት ማንኛውም ሰው በሰው፣ በአንስሳት፣ በአካባቢ እና በአጎራባች ዕጽዋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደ ሌለው በባለስልጠኑ ወይም በክልል ባለስልጣን ሲረጋገጥ በራሱ መሬት ላይ መዝራት፤ ወይም የዕጽዋት ዘሩ በበሽታ ካልተበከለ እና በኬሚካል ካልታሸ ለምግብነት ወይም ለመኖነት እንዲውል የማድረግ አማራጭ ሊሰጠው እንደሚችል ተብራርቷል፡፡ ሆኖም ውድቅ እንዲሆን የተደረገ ዘር በ በጥቅም ላይ ሊውል የማይችል ሆኖ ሲገኝ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ የዕጽዋት ዘር ከውጭ ስለማስገባትና ወደ ውጭ መላክን በተመለከተ ማንኛውም ሰው ዘር ከውጭ ሀገር አስገብቶ የሚያከፋፍል ወይም ወደ ውጭ የሚልክ ከሆነ ከባለስልጣኑ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት፣ የማስገቢያ ወይም የመላኪያ ፈቃድ ከባለስልጣኑ ካልተሰጠው በስተቀር ዘርን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ወደ ውጭ መላክ አለበት፤ ይህ አንደተጠበቀ ሆኖ ዘር ከውጭ ሀገር አስገብቶ ከዘር ማምረት እና ግብይት ውጭ ለሆነ አገልግሎት የሚያውለው ከሆነ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት እንደማይጠበቅበት በአዋጁ ተመላክቷል፡፡ ገደብ የተጣለበትን ዘር ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፣ በሁለተኛው ትውልድ ራሱን የማይደግም ዘረ-መል ቴክኖሎጂ ያለበትን ዘር ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይችል አዋጁ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውና ሌሎች በአዋጁ የተገለጹ ጉዳዮች የዘር ጥራትን ለማስጠበቅ የሚረዱና በሚመለከታቸው አካላት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ናቸው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን እስከምን ድረስ ነው? አቶ ፍሰሀ፦ ማንኛውም ሰው ካመረተው ምርት ላይ ጠብቆ በሚጠቀምበት ዘር፣ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች ወይም አርብቶ አደሮች መካከል ከምርቱ ጠብቆ እርስ በእርስ በሚደረግ ልውውጥ ወይም በማንኛውም ሰው በዝርያ ባለቤትነት መብት ባልተመዘገብ ዝርያ ዘር በሚከናወን ሽያጭ እና ለምርምር እና ትምህርት ሥራ በሚውል ዘር ላይ ተፈጻሚ የማይሆን ከመሆኑ ውጭ በሌሎች በማንኛውም ዘር ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ በ10 ዓመቱ የባለሥልጣኑ መሪ እቅድ ከእጽዋጽ ዝርያ ለቀቃ፣ ጥበቃና የዘር ጥራት ቁጥጥር አኳያ የተለዩ የትኩረት መስኮች ምንድን ናቸው?

አቶ ፍሰሀ፦ አዋጁ የእጽዋት ዘር ማምረት፣ ዝግጅትና ግብይትን በተመለከተ በክፍል ሦስት ሥር የሚያብራራ ሲሆን ማንኛውም ለገበያ የሚሆን ዘር በማምረት የሚሰማራ ሰው ስለሚያመርተዉ ዘር እቅድ ለባለስልጣኑ ወይም ለክልል ባለስልጣን አስቀድሞ በሚወሰን ጊዜ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት፤ ባለስልጣኑ አገራዊ መረጃዎች የያዘ የዘር ምርት መረጃ ቋት እንደሚያዘጋጅና የዘር ምርት መረጃ ቋት ከዘር አምራቾችና አከፋፋዮች መዝገብ ጋር የተያያዘ መሆን እንዳለበት ይገልጻል፡፡ ከእጽዋት ዘር ማምረት ጋር በተያያዘም ማንኛውም ሰው በዓመታዊ ሰብሎች ዘር ማምረት ለመሰማራት፣ በደንና በፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ ሰብሎች፣ ለገበያ የሚሆን የተመሰከረለት ዘር ወይም መስራች ዘር ወይም ሁለቱንም በማምረት ተግባር ላይ ለመሰማራት፣ አራቢ ዘር እና ቅድመ መስራች ዘር ለማባዛት ለእነዚህ የዘር ደረጃዎች እና የዘር ደረጃዎች ለማባዛት የሚያስችለውን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከአንድ ክልል በላይ በዘር ማምረት የሚሰማራ ከሆነ ከባለስልጣኑ፤ በአንድ ክልል ብቻ ተወስኖ የሚያመርት ከሆነ ከክልል ባለስልጣን ማግኘት እንዳለበት ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም ለገበያ የሚሆን ዘር በማምረት ተግባር ላይ የሚሰማራ ማንኛውም ሰው የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት የውስጥ የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርበት፣ የሚያመርተውንም ዘር ምንጭ፣ ደረጃና ሌሎች የጥራት መስፈርቶችን ለባለስልጣን ወይም ለክልል ባለስልጣን የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት፤ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ዘር አምራች አግባብነት ባለው ማንኛውም ሌላ ሕግ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገቡ ዝርያዎችን አራቢ ዘር፣ ቅድመ መሥራች ዘር እና መሥራች ዘርን ከሚያባዙ ተቋማት ማግኘት እንደሚችል፣ የዘር ምንጭነት አገልግሎት ለመስጠት የእናት ዛፍ እና የማምረቻ ቦታውን በማሰመዘገብ፤ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት እንዳለበት፣ ማንኛውም ዘር አምራች ሆኖ ዘር በማምረት ለመሰማራት የሚፈልግ ሰው በራሱ መሬት ወይም በሌሎች አምራቾች መሬት በውል ላይ ተመስርቶ ዘር ማምረት እንደሚችልና ዝርዝር አፈጻጸሙ በመመሪያ እንደሚወሰን አዋጁ ተደንግጓል፡፡ ከዘር ዝግጅትና ግብይት ጋር በተያያዘም ማንኛውም ሰው ከአንድ ክልል በላይ በዘር ዝግጅትና ግብይት ሥራ ለመሰማራት ሲፈልግ ከባለስልጣኑ፤ በአንድ ክልል ብቻ ተወስኖ የሚሰራ ከሆነ ከክልል ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት እንዳለበትና ዝርዝር አፈጻጸሙ በመመሪያ እንደሚወሰን አዋጁ ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም የመንግሥት ዝርያዎች መነሻ ዘር በመጠቀም ዘር የሚያመርትና ለገበያ የሚያቀርብ ከሆነ ያልተዋወቁ አዳዲስ የመንግስት ዝርያዎችን የማስተዋወቅ ግዴታ እንዳለበት፣ የእጽዋት ዘር ግብይት በግል፣ በማህበራት፣ በመንግስት ወይም በሌሎች አቅራቢዎች ሊከናወን እንደሚችል በአዋጁ በግልጽ ተመላክቷል፡፡ በአንድ ክልል ተወስኖ ይሰራ የነበረ የዘር አምራች ወይም አዘጋጅ ወይም አከፋፋይ ከአንድ ክልል በላይ ለመሰማራት የሚፈልግ ከሆነ አስቀድሞ በክልል ውስጥ ይሰራበት የነበረውን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለክልል ባለስልጣን መመለስ እና መስፈርቶችን በማሟላት ከባለስልጣኑ አዲስ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት እንዳለበትም ይገልጻል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ የዘር ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ አዋጁ ምን ይላል? አቶ ፍስሀ፦ ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ የእጽዋትና ዘርን ጥራት ማስጠበቅና አስፈላጊውን ቁጥጥር ማድረግ ይገኝበታል፡፡ በእጽዋት ዘር አዋጁ ክፍል አራት ሥር የዘር ጥራት ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ ባለስልጣኑ የዘር ጥራት ደረጃን እንደሚያወጣና በዘር ጥራት ደረጃ ዝግጅት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር እንደሚሰራ፣ የወጣ የጥራት ደረጃ መተግበሩን ለማረጋገጥ ባለስልጣኑ እና የክልል ባለስልጣን የቁጥጥር ሥራ እንደሚያከናውኑ ያብራራል፡፡ በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የሚገኙ የዘር ላብራቶሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የዘር ጥራት ቁጥጥር የአሰራር ሥርዓት እንዲጠቀሙ የማመቻቸት፣ የዘር ላብራቶሪዎች አግባብ ባለው ሀገር አቀፍ ወይም ዓለም አቀፍ አካል እውቅና እንዲያገኙ መስፈርቶች የማስተዋወቅና የመደገፍ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሀገራዊ የዘር ላብራቶሪ የማቋቋም፣ በክልል የሚገኙ የመንግስት ወይም የግል ወይም የማህበራት ዘር ላብራቶሪዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን በየጊዜው የማረጋገጥ እና የክልል ባላስልጣን የዘር ላቦራቶሪዎች የፍተሻ ብቃት ለመገምገም ናሙና በመውሰድ ሀገራዊ የፍተሻ አሰራር መጣጣም እንዲኖር በትብብር እንደሚሰራ ይገልጻል፡፡

“የተሻሻለው የእጽዋት ዘር አዋጅ መሰራታዊ በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ነው!” አቶ ፍሰሀ ተሾመ የእጽዋት ዝርያ እና ዘር ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ****** ኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በግብርና ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ ጎጂ ተጽዕኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ የማስቻል ዓላማ ይዞ የፌዴራል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት የተቋቋመ የፌደራል መ/ ቤት ነው፡፡ ባለሥልጣኑ የተቋቋመለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የባለስልጣኑን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 509/2014 መሠረትም ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ የእጽዋት ዝርያ ብቃትንና ዘር ጥራትን ማስጠበቅና አስፈላጊውን ቁጥጥር ማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ባለሥልጣኑ የዕጽዋት ዘር አዋጅ 1288/2015 ከሌሎች አስፈጻሚ አካላት ጋር በጋራ በማዘጋጀትና በማጸደቅ በአዋጁ ላይ መነሻ ያላቸውን ማስፈጠሚያ መመሪያዎች በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡ የአዋጁ ከነበረው አዋጅ ምን ምን አዳዲስ ነገሮችን እንደሚያካትት፣ ነባሩን አዋጅ ማሻሻል ለምንስ አስፈለገ? የሚሉትን ነጥቦች እንዲያብራሩልን የባለሥልጣኑ የእጽዋት ዝርያ እና ዘር ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ከሆኑት አቶ ፍሰሀ ተሾመ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ የእጽዋት ዘር አዋጅ ማውጣት አስፈላጊነቱ ምንድን ነው? አቶ ፍስሀ፦ ባለሥልጣኑ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ያስችለው ዘንድ የ10 ዓመት መሪ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ በመሪ እቅዱም ከእጽዋት ዝርያ ለቀቃ፣ ጥበቃና የዘር ጥራት አኳያ የዝርያ ለቀቃ እና ጥበቃ አሰራር ማጠናከርና ስርዓት መዘርጋት፣ የአዳቃዮች መብት ጥበቃ ሥርዓትን መተግበር፣ የድህረ-ጥራት ፍተሻ ጣቢያዎችን ማጠናከር፣ አዳዲስ ማደራጀትና የመስኖ ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ በመስክ የዘር ጥራት ማረጋገጥን ማዘመን፤ አቅም መገንባት እና የራስ በራስ ዘር ጥራት ማረጋገጥ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ፣ የዝርያ ብቃት ሙከራና የዝርያ ባለቤትነት የሚረጋገጥባቸው የዝርያ ልዩ መሆን፣ ወጥና የማይለዋወጥ መሆኑ የሚፈተሸባቸው ጣቢዎች በአገሪቱ ወካይ ሥነምህዳሮች ማቋቋም፣ የአካባቢ ዝርያዎች እውቅና አግኝተው በስፋት አንዲባዙ ለማድረግ የባህርይ ልየታ ፍተሻ ስራዎችን መደገፍ፣ የዘር ጥራት ቁጥጥርና የማረጋገጥ ሥርዓቱን ብቃት ለማረጋገጥ የምርምር ተግባራት በአራቱም ክልሎች ማካሄድ፣ የክልሎች የዘር ላቦራቶሪ አቅም መገንባት፣ የዝርያ ብቃትና ዘር ጥራት ማረጋገጥ አገልግሎቱን ለ3ኛ ወገን ማካፈል አማራጮችን ማስፋት፣ አገራዊ ሁለገብ የዕፅዋት ጤናና ጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ መገንባት፣ የዕፅዋት ዘር ጥራት ላቦራቶሪዎች ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ዋና ዋና የትኩረት መስክ ተብለው የተለዩ ናቸው፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱ የእጽዋት ዝርያ ብቃት እና የዘር ጥራትን ከማስጠበቅ አኳያ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣትና በመሪ እቅዱ ቀጣይ የትኩረት መስክ ብሎ የለያቸውን ዝርዝር ተግባራት ከዳር ለማድረስ ነባር የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡ የዘር አዋጁም ከህግ ማዕቀፎች አንዱ እና ዋንኛው ነው፡፡ ዘር የሁሉ ነገር መነሻ ነው፤ የግብርና ሴከተር ውስጥ የተሻሻለና ጥራት ያለው ዘር መጠቀም ምርታመነትን ከማሳደግ አኳያ፣ ገቢያው የሚፈልገውን ምርት በመጠንም ሆነ በዓይነት ከማቅረብ አኳያ፣ በአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊና ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ከነባሩ አዋጅ የተሸሻለው አዋጅ መሰረታዊ ለውጦችና የተሸሻለው አዋጅ በውስጡ የያዛቸውን ጉዳዮች ቢያብራሩልን? አቶ ፍስሀ፦ የተሸሻለው አዋጅ ከነባሩ አዋጅ ያለው መሰረታዊ ለውጦች፡- ዝርያ ለቀቃና ምዘገባ ላይ አህጉራዊ ስምምነቶችን ተቀብለን እንደምንተገብር፣ የዝርያ ለቀቃና ምዝገባ አማራጮች መኖር፣ የልተመዘገበ ዝርያ በልዩ ሁኔታ እና መልሶ ወደውጪ ለመላክ ዓላማ ሲባል የማላመድ ሙከራ ሳይከናወን ወደ ሀገር የሚገባበትን መንገድ መኖሩ፣ ጊዜ ያለፈበት ዘር አወጋገድ ስርዓት እንደሚመቻች መመላከቱ፣ የዘር ጥራት ቁጥጥር አማራቾች ማለትም ራስ አገዝ እና በሶስተኛ ወገን መካተታቸው፣ የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ በዘር ደረጃ እንዲሆን መደረጉ፣ አራቢ ዘር ትራት ፍተሸ እንደሚደረግበት መመላከቱ፣ የመተባበቂያ ዘር ሲስተም እንደሚዘረጋ፣ የደን ዘር በዚህ አዋጅ እንዲታቀፍ መደረጉ የመሳሰሉት ሀሳቦች ተካተዋል፡፡ አዋጁ በስድስት ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን በክፍል አንድ የአዋጁ አጭር ርዕስና ትርጓሜን፣ በክፍል ሁለት ዝርያ መልቀቅና መመዝገብን፤ በክፍል ሦስት የእጽዋት ዘር ማምረት፣ ዝግጅትና ግብይትን፤ በክፍል አራት የዘር ጥራት ማረጋገጥን፤ በክፍል አምስት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ስለመስጠት፣ ሥለማገድና ሥለመሰረዝ እና በክፍል ስድስት ደግሞ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ተካተው የቀረቡበት ነው፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ከዝርያ ለቀቃና ምዝገባ ጋር ተያይዞ በአዋጁ የተዘረዘሩ ትግባራትን ቢያብራሩልን? አቶ ፍስሀ፦ ዝርያ ለቀቃንና በአዋጁ ክፍል ሁለት የቀረበ ሲሆን በዚህ ክፍል ከዝርያ ለቀቀና ምዝገባ ጋር ተያይዞ ባለሥልጣን መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ የዝርያ ለቀቃ እና ምዝገባን የአሰራር ሥርዓትን ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ የዝርያ ለቃቃና ምዝገባ የአሰራር ሥርዓት ማለፍ ስላለባቸው የእፅዋት ዓይነቶች ዝርዝር አግባብነት ባለው መገናኛ ብዙኃን እንዲገለጽ የማድረግ፤ በዓይነታቸው ልዩ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው፣ የተለዩ እና በውጭ አገር የተመዘገቡ ዝርያዎች በሀገር ውስጥ የዝርያ ማላመድ ሙከራ ማካሄድ ሳያስፈልግ በቀጥታ እንዲመረቱ የመፍቀድ፣ የእፅዋት ዝርያው ወደ አገር ውስጥ ገብቶ መመረት ከጀመረ በኋላ በዝርያው ምክንያት ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት የዝርያው ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሉ ሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ መሆኑን፤ የአርሶ አደሮች ወይም ከፊል አርብቶ አደሮች ዝርያ የሚለቀቅበት እና የሚመዘገብበት አሰራር የመዘርጋት ኃላፊነት እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ በተያያዘም አገሪቱ አባል በሆነችባቸውና ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የዝርያ መዝገብ ላይ የተመዘገቡትን ዝርያዎች ተቀብሎ በዝርያ መዝገቡ የማካተትና በተለያየ ምክንያት ከመመረት የወጡ ዝርያዎች ከዝርያ መዘገብ የመሰረዝ ኃላፊነት እንዳለበትም አዋጁ ያብራራል፡፡ ሕዝብ ግንኙነት፦ ከእጽዋት ዘር ማምረት፣ ዝግጅትና ግብይት ጋር በተያያዘ አዋጁ ምን ይላል?

የነሃሴ ወር/2015 ዓ.ም/ ዜና መጽሄት

በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የተገልጋይ ቻርተር ላይ ውይይት ተካሄደ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ስራ አስፈፃሚዎች እንደ ተቋም በተዘጋጀው ረቂቅ የተገልጋዮች ቻርተር ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት አካሄዱየውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ሲሆኑ እሳቸውም ይህ የተቋማችን ረቂቅ የተገልጋዮች ቻርተር አሰራራችንን ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማስኬድና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁልፍ ሚና የሚጫወት መሳሪያ በመሆኑ ፀድቆ ወደ ስራ ከመገባቱ በፊት በሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ግብዓት ለማሰባሰብ ዓላማ አድርጎ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ዶ/ር ሀሚድ አያይዘውም የሚሰጡ ዋና ዋና የአገልግሎት አይነቶች፤ የአገልግሎት ደረጃዎች ማለትም ከመጠንና ከሚወስደው ጊዜ አኳያ እና አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርት ላይ ሁሉም ስራ አስፈፃሚ ከተሰጠው የስራ መዘርዝር አንፃር በደንብ አይቶ መካተት የሚገባቸው ካሉ እንዲካተቱ ያለ አግባብ የገቡም ካሉ እንዲወጡ እንዲሁም አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ የተንዛዛ እንዳይሆን በትክክል ስራው የሚወስደው ጊዜ ተመዝኖ ሊቀመጥ ስለሚገባ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡በመቀጠልም የተዘጋጀው ረቂቅ የተገልጋዮች ቻርተር በአዘጋጆቹ አማካኝነት እንዲቀርብ ከተደረገ በኋላ ከቤቱ ተጨማሪ ማብራሪያ ለሚፈልጉ እንዲብራሩ፤ መካተት ያለባቸውን እንዲካተቱና ዝርዝር ተግባራት ገብተዋል ያሏቸውን እንዲወጡ እንዲሁም ተግባሩ ከሚወስደው ጊዜ አንፃር ረዝሟል ባሏቸው ነጥቦች ላይ ሀሳቦችና አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ለተባሉት ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ ሌሎች ጠቃሚ ሃሳቦችን እንደ ግብዓት በመውሰድ አሁንም ይህ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ስራ አስፈፃሚ ከራሱ ስራ አኳያ በስሩ ካሉ ባለሙያዎች ጋር በደንብ በመወያየት ተጨማሪ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉትን በፅሁፍ እንዲልኩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ተህዋስያን (1).docx0.21 KB