1 623
订阅者
-124 小时
-27 天
无数据30 天
帖子存档
በኮሚሽኑ በየአስራ አምስት ቀን የሚዘጋጀው የግንቦት ወር 2ኛ ዙር ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ
***
ዲጂታል ጋዜጣውን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇
https://heyzine.com/flip-book/0fcd16fbb0.html
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።
🫘 🌾 የሀገር ውስጥ ገበያን ከማረጋጋት እስከ ዓለማቀፋዊ አቅርቦት! 🫘 🌾
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመሠረታዊ የእህል እንዲሁም የቡና ምርት ንግድ በሀገር ውስጥ አቅርቦት የህብረተሰቡን የምርት ፍላጎት ከማሟላትና ገበያን ከማረጋጋት ባሻገር የሀገራችንን የተፈጥሮ በረከቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ የማቅረብ ድርብ ተልዕኮን በብቃት እየተወጣ የሚገኝ ልማታዊ የንግድ ተቋም ነው፡፡
🌾 በሀገር ውስጥ ገበያ
ለሀገር ውስጥ ገበያ የምናቀርባቸው ጥራታቸው የተጠበቀ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሽንብራ፣ባቄላ እና ሌሎች ሰብሎች የኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ገበታ ግብዓትና የምግብ ዋስትና መሠረት፤ ለአምራቹም የገቢ ምንጭ ናቸው፡፡ የኅብረተሰቡን የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለማሻሻል በሀገር ደረጃ በተያዘው አቅጣጫ መሠረትም ጥራቱን የጠበቀና በንጥረ-ነገሮች የበለጸገ የስንዴ ዱቄት በማስመረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ የስነ-ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል፡፡
☕️ በዓለም ገበያ
ለዓለም ገበያ በከፍተኛ ጥራትና በተወዳዳሪ ዋጋ የምናቀርባቸው የላቀ ጥራት ያላቸውና ሀገራችን የምትታወቅባቸው ጥዑም የአረቢካ ቡናዎች፣ ለተለያዩ ዓለም አቀፋዊ የምግብ ማቀነባበሪያዎች ግብዓት የሚሆኑ የቅባት እህሎችና ጥራጥሬዎች የውጭ ምንዛሪ ምንጮች ናቸው፡፡
🔬 ዘመናዊ አውታሮች
የቡና ቅምሻ ላቦራቶሪን ጨምሮ ባሉን ዘመናዊ የምርት ማደራጃ አውታሮች በመታገዝ፣ አስተማማኝና ጥራቱን የጠበቀ ምርት እስከ መዳረሻው ድረስ እናቀርባለን፡፡
🤝 አብረውን በመሥራት ትርፋማነትዎን ያሳድጉ፤ የኅብረተሰብ አጋርነትዎንም ያረጋግጡ!
📞 ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር +251939575757 ይደውሉ፡፡
🛒 መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ!
ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ከውጭ አምራቾች በጥንቃቄ ተመርጠው የገቡና በብዛትና በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡልዎትን የስንዴ ዱቄት፣ ማካሮኒና ፓስታ፣ ሩዝ፣ የምግብ ዘይት፣ የአትክልት ቅቤ፣ የወጥ ማጣፈጫዎች፣ ስኳርና ሌሎችንም የምግብ ሸቀጦች ከአለ በጅምላ መደብሮችና ከኮርፖሬሽኑ ሚኒ-ማርኬቶች ዛሬውኑ ይሸምቱ፤ ማዕድዎን ያድምቁ!
በደስታ ያብስሉ፣ በፍቅር ይመገቡ! ❤️
✨ ንጹህ ቤትና አካባቢ የጤናማና ዘመናዊ ኅብረተሰብ መገለጫ ነው!
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአለ በጅምላ መደብሮቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀረበልዎትን ጥራት ያላቸው የግልና የቤት ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች በመጠቀም የራስዎንና የቤተሰብዎን ጤንነት ይጠብቁ፤ የመኖሪያና የሥራ አካባቢዎንም አንጸባራቂ ያድርጉ!
በመደብሮቻችን፡-
🧼 የገላ ሳሙናዎች እና ሻምፑዎች
🧺 የልብስ ሳሙናዎች እና ዲተርጀንቶች
🍽 የቤትና የወጥ ቤት ዕቃ ማጠቢያ ፈሳሽ ሳሙናዎች
🚽 የመጸዳጃ ቤት ፀረ-ጀርም ሳሙናዎችና ሌሎችንም የግልና የቤት ንጽህና መጠበቂያዎች ያገኛሉ፡፡
ከሀገር ውስጥ አምራቾች እና ከውጭ ሀገር በጥንቃቄ ተመርጠው የቀረቡ፣ ጥራታቸውን የጠበቁና ከበጀትዎ ጋር ፍጹም በሚስማማ ዋጋ የቀረቡ ምርቶቻችንን አሁኑኑ ይሸምቱ!
🌿 ንፁህ አካባቢ፣ ጤናማ ህይወት፣ ሀገር ኩራት!
ምርቶቹን በኮርፖሬሽኑ የአለ በጅምላ መደብሮችና ሚኒ-ማርኬቶች ያገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ የ118 ዓመታት የንግድ ሚኒስቴር ታሪክ የመጀመሪያው የንግድ ፖሊሲ
(አዲስ አበባ ፡ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወጥ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ በይፋ አፅድቃለች። ይህ የላቀ ስኬት ሀገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ከተቋቋመበት የ118 ዓመታት ረጅም ታሪኳ ውስጥ ራሱን የቻለና የነፃ ገበያ ሥርዓቱን የሚመራ ወጥ የፖሊሲ ሰነድ ያገኘችበት የመጀመሪያው ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።
ቀደም ሲል ወጥ የሆነ የንግድ ፖሊሲ አለመኖሩና የንግድ ሕጎች በተለያዩ አዋጆችና መመሪያዎች ውስጥ ተበታትነው መገኘታቸው በገቢና ወጪ ንግድ መካከል ቅንጅት እንዳይኖር ከማድረጉም በላይ፣ በንግድ ሥርዓቱ ላይ ፍትሃዊ ውድድር እንዲጠፋ፣ ሕገ-ወጥነት እንዲስፋፋና ሸማቾች ለከፍተኛ ምሬት እንዲዳረጉ በምክንያትነት ይጠቀሳል።
በአሁኑ ወቅት የጸደቀው ፖሊሲ እነዚህን መዋቅራዊ ክፍተቶች በመሙላት የሀገር ውስጥና የውጭ ንግድ አስተዳደርን በሳይንሳዊ መንገድ ለመምራት፣ የወጪ ንግድን በማዘመን ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በታሪፍና ማበረታቻዎች ለመደገፍ እንዲሁም የሸማቾችን መብትና ደህንነት ለመጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ አዲስ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ በዋናነት በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ፣ በትብብርና ቅንጅት፣ በግልፅነትና ተገማችነት እንዲሁም በፍትሃዊ ውድድር መርሆዎች ላይ የተገነባ ነው። የሰነዱ አጠቃላይ ይዘትም የሀገር ውስጥ የግብይት ሥርዓትን ማዘመን፣ የገቢና ወጪ ንግድ አስተዳደር ማዕቀፍን ማጠናከር፣ ፍትሃዊ ንግድን ማስፈንና የዲጂታል ንግድ (E-commerce) ሥርዓትን መገንባት ላይ ያተኩራል።
በአጠቃላይ ፖሊሲው በንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ከፍተኛ መተማመንን በመፍጠር፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብና የሀገሪቱን የንግድ ምህዳር ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የተጣለ ትልቅ መሠረት ነው።
Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
