Gamo zone RMNCH-N team
前往频道在 Telegram
This channel is used to exchange new initiatives, ideas and updates within Gamo zone for sustainable, reliable and timely interaction among zone, woreda and PHCU staffs to strengthening routine immunization.
显示更多432
订阅者
-124 小时
无数据7 天
+730 天
帖子存档
Gamo Zone Health Department Health Related Meeting
Friday, Jul 3, 11:00 AM – Thursday, Dec 31, 12:00 PM
Google Meet joining info
Video call link: https://meet.google.com/wyh-bhcs-zmi
ሠላም ሠላም!!
እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ!!
ዛሬ መስከረም 19/2019 ዓ.ም በ 8፡00 ላይ በወባ፣ ሥርዓተ-ምግብ አለመመጣጠን እንዲሁም በመሠረታዊ የጤና አገልግሎት አፈጻጸም ዙሪያ በበይነ-መረብ መደበኛ ውይይት ለማድረግ ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡
ስለሆነ ከመዋቅራችሁ የጽ/ቤት ኃላፊ፣ የዩኒት አስተባባሪ፣ የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ፣ የእናቶችና ህጻናት ስርዓተ-ምግብና ወጣቶች ጤና ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ፣ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ እንዲሁም የዘርፈብዙ ኤች.አይ..ቪ/ኤድስ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ ከታች በተያያዘው ሊንክ በመጠቀም እንድትገቡ እናሳስባለን፡፡
የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከመላዉ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገለፀ
አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)
በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና በ2019 ዓ.ም ዕቅድ ፈፃሚ ማዘጋጃ ሲካሄድ የነበረዉ የምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡
የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ባንጌ ባንጃ የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከአጋር ድርጅቶችና ከመላዉ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በልማት ኮሪደሮች አከባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለበሽታዉ ተጋላጭነታቸዉ ከፍ ያለ በመሆኑ ስርጭቱን ለመከላከል በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበትም ወ/ሮ ባንጌ አሳስበዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ መምሪያው ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ስላዘጋጀዉ የምክክር መድረክ በማመስገን መድረኩ አቅማቸዉን የፈተሹበትና ብዙ ልምድ የቀሰሙበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የመድረኩ ተሳታፊዎች በዘርፊ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከርና ክፍተቶችን በመሙላት የተሻለ አፈጻፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎቸና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የዘርፈ ብዙ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የጉበት በሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፤
አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ በበጀት ዓመቱ በዘርፈ ብዙ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የጉበት በሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ባንጌ ባንጃ ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው በጤናው ዘርፍ የተነደፉትን የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሣካት በዞኑ ጤና መምሪያ በኩል ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ሲከናውኑ መቆየታቸውን አውስተው በበጅት ዓመቱ በርካታ ሃገራዊ እና ክልላዊ የዘመቻ ስራዎች ላይ እንዲሁም በዞኑ የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት አደጋና የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር በስፋት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
ወ/ሮ ባንጌ በንግግራቸው አክለው በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች የሚላኩ የኮማንድ ፖስት ሪፖርቶች በአበዛኛው ወቅታዊነት እና ጥራት የትጓደለባቸው ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ ተግዳሮት እየሆኑ የመጡ መሆኑን ጠቁመው በየደረጃው የሚላኩ ሪፖርቶችን ገምግሞ መላክ ላይ ትኩረት መሰጠት ይገባል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዳይሬክቶሬቱ ሪፖርት በዳይሬክቶሬቱ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ እሸቱ ሙአ በኩል የቀረበ ሲሆን በዚህም በበጀት ዓመቱ 65 ሽህ 432 ሰዎች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክርና ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ምርመራ ካደረጉ መካካል 183 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏ፡፡ በሌላ በኩል በበሽታው ከተያዙ ግለሠቦች መካከል 164 ሰዎች የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እንዲጀምሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እየተከታተሉ ከሚገኙ ወገኖች መካከል ለ3 ሺህ 199 ሰዎች የቫይራል ሎድ ምርመራ የተካሄደላቸው ሲሆን በዚህም 3 ሺህ 050 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ከ 50 ኮፒ በታች እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል ይህም ሶስተኛው 95 አፈጻጸም 95 በመቶ ያህል መድረሱን ያሣያል፡፡
ከኤ.ች.አይ.ቪ/ኤድስ የመከላከል ተግባር ጋር በተያያዘ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ለሚገኝ ወገኖች እና ወላጃቸውን ላጡ ህጻናት በአጠቃላይ ለ 4 ሺህ 364 ወገኖች ቢያንስ አንድ አይነት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድሩግ ተችሏል፡፡ በበጀት ዓመቱ 250 ሺህ 811 ኮንዶም ማሰራጨት ተችሏል፡፡
በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት ላይ እና በኮማንድ ፖስት ሪፖርት አደራረግ ላይ ከተሣታፊዎች ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት እንደሚካሄድ የሚጠበቅ ሲሆን በሌላ በኩል የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ተግባቦት ይፈጸማል ተብሎ ይገመታል፡፡
መምሪያው የሳምንታዋ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ፣ የወባና የስርዓተ ምግብ ክስተት አስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ሣምንታዊ ተግባራትን ገመገመ።
አርባ ምንጭ፡-መስከረም 4/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)
በዞኑ የወባና የስርዓተ ምግብ ክስተት አስተዳደር ሥርዓት ተዘርግቶ በተሰሩ የተቀናጁ ሥራዎች የወባ ስርጭት ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት እየቀነሰ መምጣቱ ተገልጿል።
የወባ ስርጭቱ አሁንም ከወረርሽኝ ማስጠንቀቂያ ወሰን (epidemic threshold) አንጻር ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ማዕከሉ አስታውቋል።
የወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የበሽታ ቅኝት፣ ቅድመ ልየታ፣ የላቦራቶሪ ምርመራ፣ ተገቢ የሕክምና አገልግሎት፣ የትንኝ መራቢያ አከባቢ ቁጥጥርና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።
የስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን ችግርን ለመቀነስ የሚከናወኑ የቅኝት ሥራ፣ የቅድመ ልየታና የምላሽ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል።
የዞኑ ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ባንጌ ባንጃ እንደገለጹት፣ ከአየር ፀባይ ለውጥና መዛባት ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ቀድሞ ለመለየት የቅኝትና የአሰሳ ሥራዎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።
ከመሠረታዊ የጤና አገልግሎት አንፃር የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል እና በጉድለት የተገመገሙ ጉዳዮች ላይ የማካካሻ ዕቅድ በማውጣት በጥብቅ ዲሲፒሊን ሊመራ ይገባል ብለዋል።
በእለቱ ስብሰባ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ባንጌ ባንጃ፣ የመምሪያው ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት አመራር እና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
Gamo Zone Health Department Health Related Meeting
Friday, Jul 3, 11:00 AM – Thursday, Dec 31, 12:00 PM
Google Meet joining info
Video call link: https://meet.google.com/wyh-bhcs-zmi
ሠላም ሠላም!!
እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ!!
ዛሬ መስከረም 4/2019 ዓ.ም በ 8፡30 ላይ በወባ፣ ሥርዓተ-ምግብ አለመመጣጠን እንዲሁም በመሠረታዊ የጤና አገልግሎት አፈጻጸም ዙሪያ በበይነ-መረብ መደበኛ ውይይት ለማድረግ ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡
ስለሆነ ከመዋቅራችሁ የጽ/ቤት ኃላፊ፣ የዩኒት አስተባባሪ፣ የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ፣ የእናቶችና ህጻናት ስርዓተ-ምግብና ወጣቶች ጤና ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ፣ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ እንዲሁም የዘርፈብዙ ኤች.አይ..ቪ/ኤድስ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ ከታች በተያያዘው ሊንክ በመጠቀም እንድትገቡ እናሳስባለን፡፡
ይድረስ ለመምሪያው የኮማንድ ፖስት ሪፖርት ለመከታተል ወረዳ የተሠጣችሁ የዞን ከፍተኛ ባለሙያዎች ዛሬ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የምትደግፏቸው መዋቅሮች የኮማንድ ፖስት ሪፖርት እንዲያስገቡ ትከታተሉ ዘንድ ብናስታውሳችሁም መረጃው ወደ ጎግል ሺት እየገባ ባለመሆኑ ተቸግረናል፡፡ ስለሆነም አፋጣኝ እርምጃ ትወስዱ ዘንድ ደግን እናሳስባለን፡፡
ግልባጭ
ለአቶ ሴይፉ ዋናቃ
ለወ/ሮ ባንጌ ባንጃ
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሴይፉ ዋናቃ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ
ኃላፊው በመልዕክታቸው እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን በማለት! ዓመቱ ለመላው የዞናችን ህዝብ የሠላም ፣ የጤናና የአንድነት እንዲሁም የብልጽግና እንዲሆንልን ምኞቴን መግለጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የዚህ አዲስ አመት አከባበርን ለየት የሚያደርገው ታሪካዊና አህጉራዊ ትኩረት በሳበው ሀገራዊ የምክክር መድረክ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስብስብ ልዩነቶቿን በሰለጠነ ውይይት፣ በሰከነ ምክክርና በመደጋገፍ ሊፈቱ በቆረጡ ታማኝ ልጆቿ አማካኝነት ዳግም አሸናፊ መሆኗ ነው። ለዚህ ድል በመብቃታችን መላውን የዞናችን ማህበረሰብን እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ፡፡
ያለፈው 2018 ዓመት ነገን በተስፋ እንድናይ የሚያደርጉን መልካም ነገሮችን አይተንበታል፤ ሰምተንበታልም፡፡ በሌላ መልክ ደግሞ ሁላችንም እንደምናውቀው የጤናው ዘርፍ በብዙ ውስብስብ ተግዳሮቶች ውስጥ ቢያልፍም በባለሙያዎቻችን ብርታት በዞናችን የገጠመንን የማህበረሰብ የጤና ቀውስ የወባ በሽታ ወረርሽኝ፣ ተፈጥሯዊ የመሬት መንሸራተት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋዎች ገጥመውን ፈጣን የነፍስ አድን ስራ በምስራት ተጨማሪ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ማድረግ ተችሏል።
የተከበራችሁ በየደረጃው የምትገኙ የዞናችን የጤና ባለሙያዎች፣ የጤናው ሴክተር አመራሮች እና የአስተዳደር ሰራተኞች የገጠሟችሁን ተግዳሮቶች ተቋቁማችሁ የዞናችንን ህዝብ ከልብ ለማገልገል ላሳያችሁት ተነሳሽነት እና በበጀት ዓመቱ የዞኑ ጤና መምሪያ በክልል ደረጃ በቲቢ፣ ሥጋ-ደዌ እና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ በ1ኛ ደረጃ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ እውቅና እንድናገኝ በማድረግ ሂደት ውስጥ ለተመዘገበው ስኬት በራሴና በዞኑ ጤና መምሪያ ስም ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብኩ በአዲሱ ዓመት ለምናከናውናቸው ተግባራት መሰረቱ ጥራት ያለውና በጊዜ የሚለካ ዕቅድ ማዘጋጀት በመሆኑ በዞኑ የምትገኙ የጤና ባለሙያዎቻችን ይህንኑ ተፈጻሚ በማድረግ ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንድናደርግ የአደራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡
በመጨረሻም ለመላው የዞናችን ህዝብ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የአንድነት፣ የስኬት፣ የልማት ተስፋዎቻችንን የምናስፋፋበት፣ የምናድግበት፣ ችግሮቻችንን የምንቀርፍበት፣ ዕቅዳችንን ወደ ውጤት የምንለውጥበት ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
አቶ ሴይፉ ዋናቃ
ጳጉሜ 2018 ዓ.ም
አርባ ምንጭ
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ በዳራማሎ ወረዳ ለአቅመ-ደካማ ቤተሰብ ያስገነባው መኖሪያ ቤት በይፋ ርክክብ እደረገ
አርባ ምንጭ:- ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)
በዳራማሎ ወረዳ ማሎ ማጬ ቀበሌ በ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ አገልግሎት አካል የሆነ የአቅመ-ደካማ ቤት ግንባታ “በጎነት ለራስ ነው” በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን ዛሬ የምሪያው ኃላፊ አቶ ሴይፉ ዋናቃ፣ የዳራማሎ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ጢሞቲዎስ ጥላሁን እና ባለድርሻ አካለት በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
የጋሞ ዞን ጤና መመሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ዋናቃ፣ የበጎ ቤቱ ግንባታ ዋና ዓላማ በክረምት ወቅት በጎ ፈቃደኝነትንና የማህበረሰብ ተሳትፎን በማጠናከር ተጠቃሚዋ ተገቢውን የመኖሪያና የድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።
የዳራማሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጢሞቴዎስ ጥላሁን በበኩላቸው፣ በጎ ፈቃደኞችና የማህበረሰቡ አባላት የሚያከናውኗቸው የበጎ ተግባራት ማህበራዊ አንድነትን፣ መተጋገዝንና የጋራ ኃላፊነትን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
የበጎ ቤቱ ግንባታ ከመኖሪያ ቤት ግንባታ ባለፈ በማህበረሰቡ ውስጥ የበጎነት ባህልን ለማስፋፋት አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑንም አቶ ጢሞቴዎስ ጠቁመዋል።
በምረቃው ዕለት ለቤቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችና ለዓመት በዓል የሚሆን አስቤዛ በሙምሪያው በኩል በመያዝ ለወ/ሮ ፋናዬ ባልፃ ቤቱ ርክብክብ ተደርጓል።
በመርሃ ግብሩ የዞኑ ጤና መመሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ዋናቃ፣ የዳራማሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጢሞቴዎስ ጥላሁን፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኦሶ ኦሻ፣ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘማች ዘለቀ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በቀጣይም የተጀመረውን የበጎ ተግባር በማጠናከር ተጨማሪ የማህበረሰብ ችግሮችን በትብብር ለመፍታትና የበጎ ፈቃደኝነት መንፈስን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተገልጿል።
