ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 370
订阅者
+1124 小时
+997 天
+37430 天
帖子存档
ትናንት አልቋል። ዛሬም እየተገባደደ ነው። ነገ ግን ገና አልተነካም። ነገን ለመጠቀም ታድያ ዛሬ መሥራት አለብን። ሕዳሴ ግድብ፤ የገበታ ለሀገርና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፤ መንገዶችና ግድቦች፤ የ
ትናንት አልቋል። ዛሬም እየተገባደደ ነው። ነገ ግን ገና አልተነካም። ነገን ለመጠቀም ታድያ ዛሬ መሥራት አለብን። ሕዳሴ ግድብ፤ የገበታ ለሀገርና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፤ መንገዶችና ግድቦች፤ የተቋም ግንባታ ሥራዎች፤ አረንጓዴ ዐሻራና ኢትዮጵያ ታምርት፤ የኮሪደር ልማትና የሌማት ትሩፋት ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ እና የትምህርት ቤት ምገባ፤ ሀገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ፤ ሌሎችም.. ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንሠራቸው ናቸው። የነገው ትውልድ እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያን እንደሚረከብ ርግጠኞች ነን። ለነገ ዛሬ እየሠራን ነውና። Kaleessi dhumeera. Har'is xumuramaa jira. Bor garuu ammayyuu hin tuqamne. Boritti fayyadamuuf garuu har'a hojjechuu qabna. Hidhi Haaromsaa, piroojektoonni Maaddiin Biyyaafiifi Maaddiin Dhalootaaf, daandiiwwaniifi hidhawwan, hojiileen ijaarsa dhaabbilee, Ashaaraa Magariisaafi Itoophiyaan Haa Hoomishtu, Misoomni Kooriidariifi Maaddii Guutuun, Itoophiyaa Dijitaalofteefi sooruun manneen barnootaa, Mariin Biyyaalessaafi Haqni Cehumsaa, kanbiroonis... bor kan wayyu akka ta'uuf hojiilee hojjennudha. Dhaloonni borii Itoophiyaa baay'ee wayyitu akka dhaalu kan mirkanaa'edha. Boriif har'a waan hojjetaa jirruuf.

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ግቢ ለሚያገኙ የተቋሙ ሰራተኞች ድጋፍ አደረገ:: በዛሬው እለት ጳጉሜ 4 "ሕብራችን ለሰላማችን" በሚል መሪቃል እየተከበረ ሚገኘውን "የሕብር ቀን" ምክንያት በማድረግ ኮሌጁ ባዘጋጀው የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር 50 ለሚሆኑና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች አዲስ ዓመትን የሚያሳልፋበት የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተከናውኗል:: በመርሃ-ግብሩ ላይ በመገኘት ለሰራተኞቹ ለ2017 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም ተቋም ሲባል ዋና መገለጫው በውስጡ የሚሰሩትን ሰራተኞች መሆናቸውን ገልፀው ተቋማት ሰው ሰው የሚሸቱና የሰውን ችግር የሚረዱ መሆን እዳለባቸው አቅጣጫ የተቀመጠ መሆኑ በመግለፅ ኮሌጁም በቀጣይ መሰል በዓላት ሲመጡ ብቻ ሳይሆን ሰራተኛውን በዘላቂነት ለመደገፍ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝና በቀጥይ የተሻለ ነገር እንደሚኖር በመጠቆም በዕለቱ የዘጋጀውን ማዕድ ከማኔጅመንቱ ጋር በመሆን ለሰራተኞቹ አስረክበዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ጳግሜ 4/2016 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ እምነቶች፣ የብዙ ሥልጣኔዎች፣ የብዙ ጀግኖች፣ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ኅብር ናት። ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራ
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ እምነቶች፣ የብዙ ሥልጣኔዎች፣ የብዙ ጀግኖች፣ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ኅብር ናት። ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራለን፤ በሁሉም እንኮራለን። ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው። እነዚህ ኅብራዊ ጸጋዎች በአንዲት ሀገር በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ዓላማችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ግባችን የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው። ይህ ነው አንድነታችን። የተበታተንን ኅብሮች አይደለንም፤ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶችም አይደለንም። እኛ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለን ኢትዮጵያውያን ነን። Itoophiyaan biyya saboota hedduu, afaanota hedduu, aadaawwan hedduu, amantaawwan hedduu, qaroominoota hedduu, gootota hedduuti. Itoophiyaan daneettiidha. Hunduu nuyiin unuuf kan kennaman keenyadha. Hundayyuu ni kabajna; hundaanuu ni boonna. Sabdaneessummaan keenya bifa keenya, tokkummaan keenyammoo waa'ee jiraachuu keenyaati. Kennaawwan danummaa kunneen biyya tookko, Itoophiyaatti kan argamanidha. Kaayyoon keenya hawaasa siyaasaafi dinagdee tokko ijaaruudha. Galmi keenya badhaadhina Itoophiyaati. Tokkummaan keenya kanadha. Daneessota faffacaane miti; Akaakuu walitti baqne tokkos miti. Nuti Itoophiyaanota tokkummaa sabdaneessa qabnudha.

ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን መኖራችን ያኮራናል። የግዛት ሉዓላዊነት ብቻውን እንደማይቆም ግን ተረድተናል። ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት። የምግብ ሉዓላዊነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ፣ የበጀት ሉዓላ
ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን መኖራችን ያኮራናል። የግዛት ሉዓላዊነት ብቻውን እንደማይቆም ግን ተረድተናል። ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት። የምግብ ሉዓላዊነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ፣ የበጀት ሉዓላዊነት፣ ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ ናቸው። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበር አዲሱ ዓይነት ዐርበኝነት ያስፈልገናል። የብሔራዊነት ዐርበኝነት። የብሔራዊነት ዐርበኝነት በተሠማራንበት መስክ ሁሉ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር የጊዜ፣ የዕውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት መሥዋዕትነትን መክፈል ነው። ሀገር በልጆቿ ትገነባለች ትጠበቃለችም። Birmadummaa keenya eegnee jiraachuun keenya nuboonsa. Birmadummaan daangaa biyyaa qofaasaa akka hin dhaabanne garuu hubanneerra. Birmaddummaan gama hundaan ta'uu qaba. Birmadummaa nyaataa, birmadummaa teknooloojii, birmadummaa bajataa, birmadummaa biyyaa isa guddaa cimsanii kan dhaabanidha. Dameewwan birmadummaa kanneen kabachiisuuf gootummaa gosa haaraa nubarbaachisa. Gootummaa boyyaalessummaa. Gootummaan biyyaalessummaa bakka itti bobbaane hundattuu birmadummaa Itoophiyaa gama hundaa kabachiisuuf aarsaa yeroo, beekumsaa, kan maallaqaafi, kan humnas kaffaluudha. Biyyi ilmaansheetiin ijaaramti, eegamtis.

#ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!!! #ጳጉሜ 1 "የመሻገር ቀን"፣ #ጳጉሜ 2 "የሪፎርም ቀን"፣ #ጳጉሜ 3 "የሉዓላዊነት ቀን"፣ #ጳጉሜ 4 "የኅብር ቀን" #ጳጉሜ 5 "የነገው ቀን" ....... #
+2
#ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!!! #ጳጉሜ 1 "የመሻገር ቀን"፣ #ጳጉሜ 2 "የሪፎርም ቀን"፣ #ጳጉሜ 3 "የሉዓላዊነት ቀን"፣ #ጳጉሜ 4 "የኅብር ቀን" #ጳጉሜ 5 "የነገው ቀን" ....... #Danoomni Walabummaa hunda galeessaaf!! #Qaammee 1 " Guyyaa ''Cehuumsaa" #Qaammee 2 " Guyyaa "Riifoormii" #Qaammee 3 " Guyyaa "Walabummaa" #Qaammee 4 " Guyyaa "Danoomaa" #Qaammee 5 " Guyyaa "Boruu" ...... #Hal-ku-dhagyada maalmaha Baagume!! #Maalinta 1 "Ka gudubka caqabada #Maalinta 2 "Dib uhabaynada" #Maalinta 3 "Madaxbanaanida" #Maalinta 4 "Iskaashiga" #Maalinta 5 "Rajada barri"

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ የጋራ አገልግሎት ሰራተኞች በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አዘገጃጀት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ አካሄደ:: የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ያስፈለገበት ዋና አላማ ፈፃሚዎች ላይ ከዚህ ቀደም የሚታየውን የእቅድና ሪፖርት አዘገጃጀትን ክፍተት ለመሙላት እንዲሁም ሰራተኛው የተሰጠውን የስራ ሀላፊነት በዝርዝር ተረድቶ በሀላፊነት ስሜት እንዲተገብርና የሚጠበቅበትን እቅድን ሪፖርት በወቅቱ እንዲያዘጋጅ በማድረግ በሚፈለገው አቅጥጫ ለማስኬድ ታልሞ የተዘጋጀ የግንዛቤ መስጫ ስልጠና ነው:: ኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም

በአገር አቀፍ ደረጃ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰልጣኞችና አስተባባሪዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ማለትም ድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና ኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ላይ የሚያሰለጥኑ አሰልጣኝ መምህራን በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኝ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎን በበጎ አድራጎት ስራዎች የደም ልገሳ መርኃግብር አካሂደዋል፤ ዘርፉን ከስልጠና በላይ በማሰብ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ በምንሰራው ስራ አጠቃላይ ኢኮኖሚውን ትራንስፎርም የሚያደርግ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠርም አልፎ የዘርፉን አቅም በመጠቀም ፈጥነን ከድህነት እንድወጣም የሚያስችል ነው፤ ከዚህ በመነሳት እነዚህን እሳቤዎች የዘርፉ ሁሉም አሰልጣኝ መምህራን በግንዛቤ የጨበጧቸውን ወደ ተግባር በመቀየር በቀጣይም በስልጠና ማዕከሉ አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦችን በበጎ አድራጎት ስራዎች ተደራሽ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የአስተዳደሩን አሰልጣኝ መምህራን በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና እና የዘርፉ እሳቤ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እንዲሁም የአሰልጣኞችን ባህሪያዊና ቴክኒካዊ ብቃት ለማሳደግ ያለመ ስልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ ይገኛል። በሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ም/ኃላፊ  ክብርት ፈጡም ሙስጠፋ ሀሮማያ ዩኒሸርሲቲ በመገኘት የስልጠና ሂደቱን ተመልክተዋል። በምልከታው ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር በስልጠናው የሚሳተፉ አሰልጣኝ መምህራን ጋር በመነጋገር አበረታቸዋል፡፡ የቢሮው ኃላፊዎች በቆይታው ከሰልጣኞችና ከስልጠና አስተባባሪዎች ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን ስልጠናው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሆነ እና እንደ አስተዳደር የተሰሩ ስራዎች በተሞክሮ መቅረባቸው ተጠቁሟል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

"ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራንና የስልጠና አስተባባሪዎች ስልጠና ተጀመረ፡፡ በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የአሰልጣኞችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት ማዘጋጀት ዓላማ ያደረገ ሲሆን እንደ አገር 17 የስልጠና ማዕከላት 24 ሺህ የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት ይካሄዳል፡፡ በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ላይ የሚያሰለጥኑ 285 የሚሆኑ አሰልጣኝ መምህራንና የስልጠና አስተባባሪዎች በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል ስልጠናውን የሚከታተሉ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ