ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 386
订阅者
+624 小时
+787 天
+36130 天
帖子存档
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ሚኒስቴር ዴኤታ በክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ ልኡክ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ጉብኝት አካሄደ።     በሚኒስቴር ዴኤታው የተመራው ልኡክ በኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ አመራሮች አቀባበል የተረገለት ሲሆን በዕለቱ በነበራቸው ጉብኝትም በተቋሙ ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥባቸውን ዲፓርትመንቶችና ዎርክ ሾፖች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።    ልኡኩ በተጨማሪም ኮሌጁ ትምህርትና ስልጠና አሰጣጡን በዲጂታል ለማዘመን ከ ICT ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ተግባራዊ እያደረገ ሚገኘውን የ E-LERNING ፕሮግራም የተመለከቱ ሲሆን ትግበራው ያለበትን ደረጃ እንዲሁም ያሉበትን ውስንነቶች በዲፓርትመንት ሀላፊው ሰፋ ያለ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።   በመጨረሻም የADRA PROJECT ከተቋሙ ጋር በመተባበር በ Solar System ላይ እየሰራ ሚገኘውን  ፕሮጀክት የጎበኙ ሲሆን በፕሮጀክቱ አስተባባሪም ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።    ሚኒስቴር ዴኤታው ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በዕለቱ በነበራቸው ጉብኝት  በኮሌጁ የሚያስደንቁ ስራዎችን እንደተመለከቱ ገልፀው እነዚህ ተግባሮችም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ በስፋት እየሰራባቸው ከሚገኙት ተግራት ውስጥ መሆናቸውን በመግለፅ በትግበራዎቹ አፈጻጸም ላይ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በቀጣይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አፅንኦት ሰተው ገልጸዋል፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ነሃሴ 13/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ

በ2015 ዓ.ም የተቋማት ውድድር 5ኛ ጨዋታውን ከዳሽን ባንክ ጋር ያደረገው ጤና ብድናችን ጨዋታውን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ኢትዮ-ጣሊያን 2-1 ዳሽን ባንክ በቃሉ አዳነ⚽️ ሳላዲን አብደላ⚽️

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግዢና ፈፋይናንስ ስራ ሂደት በስሩ የሚገኙ ኬዝ ቲሞችና ፈፃሚዎችን የ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የግምገማ መድረክ እያካሄደ ሲሆን መድረኩ በቀጣይ ቀናትም የሚቀጥል ይሆናል።

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የስራ ሂደት በስሩ ከሚገኙ የአራቱ ማዕቀፍ አስተባባሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር ላለፉት 3 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፓርትን ግምገማ አጠናቀቀ። ስራ ሂደቱ ባለፉት ቀናት በነበረው መድረክ በስሩ የሚገኙ ኬዝ ቲሞችና ፈፃሚዎችን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ያደመጠ ሲሆን ከቀረቡት ሪፓርቶች በመነሳትም ሰፋ ያለ ግብረ-መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን ገንቢ የሆኑ ውይይቶችን በማድረግም ለቀጣይ የትግበራ ወቅት እንደ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የጋራ መግባባትና የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል። የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም

የኢትዮ- ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የስራ ሂደት በስሩ ከሚገኙ የአራቱ ማዕቀፍ አስተባባሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር የ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርትን መገምገም ጀምሯል።   የአፈፃፅም ሪፓርት ግምገማው በስራ ሂደቱ መሪና የኮሌጁ ም/ዲን በሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ የሚመራ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋም በመድረኩ ተገኝተዋል።      መድረኩ በቀጣይ ቀናትም ቀጥሎ የሚደረግ ሲሆን የሁሉም ሪፓርት በቅደም ተከተል ከቀረበ በኋላ ግብረ መልስ በመስጠትና ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ስራ የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የሚጠናቀቅም ይሆናል። የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሐምሌ 24.2015 ዓ.ም

በ2015 ዓ.ም የተቋማት ውድድር 3ኛ ጨዋታውን ከብዙሃን መገናኛ ጋር ያደረገው ብድናችን ጨዋታውን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ኢትዮ-ጣሊያን 2-1 ብዙሃን መገናኛ ዳዊት አበራ⚽️ እዮብ መሰለ⚽️

የኢትዮ- ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህትና ስልጠና የስራ ሂደት በስሩ የሚገኙ ዲፓርትመንቶችና የስራ ክፍሎችን ጥራትን መሠረት ባደረገው የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ ካላንደር የሶስተኛ ተርም እና አመታዊ ሪፖርት ግምገማ የሂደቱ ሃላፊና አቶ ኤሊያስ አህመድ እንዲሁም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በተገኙበት አካሂዷል።   በመድረኩ የሁሉም ዲፓርትመንት ሀላፊዎች በቅደም ተከተል ሪፓርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሪፓርቶች ላይም ጠንካራ ጎኖችን እና ውስንነት የታየባቸው ተግባሮች ላይ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።     በመጨረሻም የታዩ ጠንካራ ጎኖች በቀጣዩ የትምህትና ስልጠና ዘመንም በተሻለ ጎልብተው እንዲቀጥሉ በማበረታታት እንዲሁም የነበሩ ውስንነቶች ላይ በጋራ በመስራት ትምህትና ስልጠናውን ከዚህ ከፍ ባለ ጥራት ለመስጠት መግባባት ላይ ተደርሶ የእለቱ መድረክ ፍፃሜውን አጊኝቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሐምሌ 20.2015 ዓ.ም