ch
Feedback
Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
1 740
订阅者
+124 小时
+37
-530
帖子存档
3 ቀን ቀረው! ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ! #አረንጓዴዐሻራ #GreenLegacy
3 ቀን ቀረው! ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ! #አረንጓዴዐሻራ #GreenLegacy

የአድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት በአስተዳደሩ የገጠር ክላስተሮች ላይ ለሚገኙ ወጣቶች የSolar PV Installation & Maintenance ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ:: ፕሮጀክቱ ባለፉት አመታት ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት በሁለት ዙሮች በከተማ አአስተዳደሩ የሚገኙ ወጣቶችን አሰልጥኖ ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ እየሰራ ሲሆን በዚህ በ3ኛ ዙር ስልጠና የMobile training እሳቤን ወይም ወጣቶች ስልጠናውን ለመውሰድ ወደ ኮሌጅ መምጣት ሳይጠበቅባቸው ባሉበት የገጠር ክላስተር(የአርዳሌ ክላስተርና የቢያዋሌ ክላስተር)የስልጠና ቦታዎችን በማመቻቸት እንዲሁም የስልጠና ግብዓቶችን በማሟላት በቃልቻ የገጠር ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በተመቻቸው ቦታ ስልጠናውን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በSolar PV Installation & Maintenance ላይ በአጫጭርና መደበኛ ፕሮግራም ሰልጣኞችን ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ የገለፁት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስራ ሂደት ምክትል ዲን አቶ ኢልያስ አህመድ ሲሆኑ አክለው በፕሮጀክቱ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዙር በድምሩ 91 ለሚሆኑ የአስተዳደሩ ወጣቶች በSolar PV Installation & Maintenance ስልጠና መሰጠቱን ጠቅሰው የ3ኛውን ዙር ስልጠና በአስተዳደሩ የገጠር ክላስተሮች ላይ በመሄድ በአካባቢው ለሚገኙ ወጣቶች እየተሰጠ የሚገኝ ስልጠና በመሆኑ ካለፉት ዙሮች ለየት ያደርገዋልም ብለዋል:: የአድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት አላማ ወጣቶችን አሰልጥኖ የሙያ ባለቤት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ወጣቶቹ የስራ እድል ተመቻችቶላቸው ራሳቸውን፣ቤተሰባቸውን እንዲሁም ማህበረሰባቸውን እንዲጠቅሙና ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ለማስቻልም ነው ያሉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ በየነ አክለውም በዚህ ሂደት ውስጥም የአድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት አጠቃላይ የስልጠናውን በጀት ከመሸፈን ጀምሮ የስልጠና ግብአቶችን በማሟላት የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ በመግለፅ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም ወርክሾፖችን ከማዘጋጀት ጀምሮ አሰልጣኝ መምህራንን በመመደብና የተለያዩ ለስልጠናው ውጤታማነት አስፈላጊ የሆኑ ተግባራት በማከናወን ረገድ እንደ ተቋም የሚጠበቅበትን በማበርከት በቅንጅት የሚሰራበት ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል:: በአርዳሌ ክላስተር እና በቢያዋሌ ክላስተር በSolar PV Installation & Maintenance ስልጠናቸውን የወሰዱ ወጣቶች በቀጣይ ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊው ትብብር የሚደረግላቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ወጣቶቹ የራስቸውን ህይወት ከመለወጥ በተጨማሪ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችላቸውም ተገፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሐምሌ 18/11/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

LMIS Website Guide Amharic በብቁ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት ድረ-ገጽ በቀላሉ ለመመዝገብ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።

ELMIS Website Guide Oromiffa Karaa salphaa ta'een biquu gabaa hojii karaa marsariitii galmaa'uuf viidiyoo kana daawwadhaa

ELMIS Website Guide Somali "ADEEGA ELMIS EE BOGA XOGAHA SUUQA SHAQADA IYO SHAQALAHA SII AAD ISAGA DIWAAN GALISO DAAWO MUQALKANI"

ADRA ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ከፕሮጀክቱ ጅማሮ እስከ አሁን የተጏዘበትን ውጤታማ የአፈፃፀም ልምድ በተለያዩ ክልሎች ፕሮጀክቱን ለሚያስተገብሩ አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ:: ADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ባለፉት አመታት በ Solar PV Installation Maintenance ስልጠና 120 ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ስራ እንዲገቡ ከማድረግ አኳያ ኘሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው ከያትኛውም አካባቢዎች የተሻለ ውጤታማ አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደሆነም ተገልፇል:: በዛሬው እለት ከADRA ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ጋር ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የመጡት የፕሮጀክቱ ቅርንጫፎች(ከአርባምንጭ፣ ከአፋር፣ ከወልቂጤ) የተገኙ ሲሆን ፕሮጀክቱ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: የልምድ ልውውጡ ዋና አላማ በADRA ኢትዮጵያ በምስራቁ ክፍል ድሬዳዋ ላይ በፕሮጀክቱ አፈፃፀም የተፈጠረውን ትልቅ አቅምና ልምድ ወደተቀሩት አካባቢዎችም ማስተላለፍ እንዲቻል የመማማሪያ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም በመድረኩ ተገልፇል:: የADRA ፕሮጀክት ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ከጅምሩ አንስቶ የመጣበትን መንገድና የተሰሩ ውጤታማ ተግባራትን በዝርዝር የሚያመላክት ገለፃ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ በየነ አማካኝነት ለመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን ለልምድ ልውውጡ በኮሌጁ የተገኙ ተሳታፊዎችም በየአካባቢያቸው ያከናወኗቸውንና ተመኩሮ ሊሆኑ የሚችሉ ተግባራትን እቅርበው የምክክር መድረክም ተካሂዷል:: የADRA ፕሮጀክት በአስተዳደሩ የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ትግበራ ማከናወኑ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም ኮሌጁን ጨምሮ በአስተዳደሩ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጉዳዩን በባለቤትነት በመያዝ ተገቢውን ድጋፍ በማድረጋቸው ጭምር የተመዘገበ ውጤት መሆኑም በመድረኩ ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት ኢንድርስትሪው ላይ ለሚገኙ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የክህሎት ስልጠና ተጠቀቀ:: በኮሌጁ ለ15 ቀናት ኢንዱስትሪዎች ላይ በተለየው የክህሎት ክፍተት መሰረት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን ተከትሎ የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የስልጠናው አጠቃላይ ሂደት የሚያመላክት የሪፖርት መድረክ ተካሂዷል:: በEASE ፕሮጀክቱ አማካኝነት ከዚህ ቀደም በኮሌጁ ከተለመደው የክህሎት ክፍተት ስልጠና አሰጣት በተለየ ሁኔታ የክህሎት ስልጠናው ውጤታማ እንዲሆን በማቀድ ኢንዱስትሪዎች ላይ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ተደርጎ ወደ ትግበራ መገባቱን ያስታወሰሱት የኮሌጁ የቴ/ሽ/ኢ/ኤ አገልግሎት ዋና ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም በተለየው ፍላጎት መሰረትም በመጀመሪያ ዙር ትግበራ በሁለት አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ለሚገኙ ባለሙያዎች በተመረጡ የሙያ ዘርፎች የክህሎት ስልጠናው መስጠት መቻሉንም ገልፀዋል:: የክህሎት ስልጠናውን በማሰልጠንም ሆነ በማስተባበር የተሳፉትን አካላት ማመስገን ያስፈልጋል ያሉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ አክለውም ይህ ስልጠና ኮሌጁ በፕሮጀክቱ አማካኝነት ኢንዱስትሪዎች ላይ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀው የክህሎት ስልጠናው እንደ ጅማሮ ጥሩ አፈፃፀም ያገኘንበትና በቀጣይ በሌሎች የሙያ ዘርፎች ኢንዱስትሪዎች ላይ ለምንሰጠው የክህሎት ስልጠና ምርጥ ተሞክሮ የተገኘበትም ነበር ብለዋል:: የክህሎት ስልጠናው ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው የነበረውን አጠቃላይ ሂደት ዝርዝር ሪፖርት የኢንዱርስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ክፍል ተጠሪ በሆኑት አቶ አቤል ዘገየ አማኝነት ለመድረኩ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርትም የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ከማካሄድ ጀምሮ የማሰልጠኛ ሞጁል በማዘጋጀት ከኢንዱስትሪዎች ለተወጣጡ ሰራተኞች በኮሌጁ ወርክሾፖች የክህሎት ስልጠናው መሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን እንዲሁም በስልጠናው ሂደት የተገኙ መልካም አጋጣሚዎችና የተሰተዋሉ ክፍተቶችም በሪፖርቱ ተካተው ቀርበዋል:: የክህሎት ስልጠናው በአስተዳደሩ በሚገኙ የConel Industrial P.l.c እና የFerida Plastic Recycling በተሰኙ አምራች ድኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚገኙ 58 ባለሙያዎች በHydraulics,Pneumatic በmachining እና በWelding የሙያ መስኮች የክህሎት ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በተጨማሪም በLeadership እንዲሁም በOccupational Safety and Health (OSH) ስልጠናዎችን በመስጠት ባለሙያዎቹን ማብቃት መቻሉም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም

የውጭ ሃገር የሥራ ዕድል... በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል። አሁንም ህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ የሰው ሃይል በተለያዩ የሞያ ዘርፎች በቁጥር ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል ይፈለጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች መሰማራት የምትፈልጉ በሙሉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት ፎርሙን ሞልታችሁ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ስንል እናሳውቃለን። Driving & Transportation 1. Light Vehicle Driver 2. Heavy Vehicle Driver (e.g., Grader Operator) 3. House Driver 4. Trolley Operator Security & Safety 5. Security Guard 6. CCTV Surveillance Operator 7. Office Security Personnel 8. Plumber 9. Electrician 10. HVAC Technician 11. AC Technician 12. Pumper Domestic & Facility Services 13. Housekeeper 14. House Maid 15. House Cleaner 16. Housekeeping Supervisor 17. Houseman 18. Caretaker 19. Steward 20. Laundry Attendant 21. Bellman Hospitality & Food Services 22. Receptionist 23. Waiter/Waitress 24. Barista 25. Sous Chef 26. Pastry Chef / Dessert Chef 27. Garde Manger Chef 28. Arabica Cuisine Chef 29. Kitchen Assistant 30. Private Cook 31. Room Attendant 32. Hotel Assistant Manager Healthcare & Caregiving 33. Nurse 34. Junior Nurse 35. Home Care Nurse 36. Private Nurse 37. Junior Midwife / Clinical Nurse 38. Elderly Care Assistant 39. Live-in Support Assistant 40. Neonatal Intensive Care Unit (NICU) Nurse 41. Junior Physiotherapist Childcare Services 42. Babysitter 43. Childcare Worker Beauty & Salon Services 44. Hairdresser 45. Hairstylist 46. Beauty Therapist 47. Salon Manager 48. Nail Technician 49. Nail Art Instructor 50. Massage Therapist 51. Makeup Artist Agriculture & Farming 52. Indoor Farmer 53. General Farm Worker Administrative & Marketing 54. Junior Administrative Assistant 55. Junior Marketing Assistant 56. Junior Account Manager 57. Sales Representative 58. Purchaser Skilled Labor 59. Construction Worker 60. Laborer 61. Tailor 62. Storekeeper 63. Supervisor Retail & Customer Services 64. Cashier 65. Promoter https://forms.gle/TF5BcYBtrhwkyjR59 መልካም ዕድል! የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!