ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 406
订阅者
+1024 小时
+507 天
+34930 天
帖子存档
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልዩ የኢፍጣር ፕሮግራም በኮሌጃችን የውጤት ተኮር ምክትል ዲን ኢሊያስ አህመድ መኖሪያ ቤት የኮሌጁ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በተገኙበት መልካም ጊዜ ማሳለፍ ተችሏል፡፡

በጦርነት ለተጎዱ ድጋፍ ተደረገ። ==================== ❤ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግምቱ 1,211,283 ብር የሆነ ልዩ ልዩ የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ለቢሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፤ ❤ ይህንንም ድጋፍ ከኮሎጁ ሁሉም የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችና የስራ ክፍሎች መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመገኘት የኮሌጃችን ዲን አቶ ታደለ አሠፋ ማስረከብ ችለዋል። ድሬዳዋ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን

በጦርነት ለተጎዱ ድጋፍ ተደረገ። ==================== ❤ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግምቱ 1,211,283 ብር የሆነ ልዩ ልዩ የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ለቢሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፤ ❤ ይህንንም ድጋፍ ከኮሎጁ ሁሉም የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችና የስራ ክፍሎች መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመገኘት የኮሌጃችን ዲን አቶ ታደለ አሠፋ ማስረከብ ችለዋል። ድሬዳዋ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን

"አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ ወ/ገብርኤል" ============================== 🥇በድሬ ዳዋ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ባዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውድድር የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህር የሆኑት ዮሴፍ እንዳልካቸው የአንደኝነት ደረጃ በማግኘታቸው የተሰማንን ደስታ መግለፃችን ይታወሳል በተያያዘም በድሬዳዋ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በቀን 05/08/2014 ዓ.ም ባካሄደው የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህር የሆኑት አቤል ዘገየ ወ/ገብርኤል “Improving Industry Extension Service in the Case of Ethio-Italy Poly Technic College” በሚል ርዕስ ባቀረቡት የተግባራዊ ጥናት አንደኛ መውጣት ችለዋል፤ 🥇 በዚህም በተገኘው ድርብ ድል የተሰማንን ድርብ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን፤ በቀጣይም ጥናቱን ወደ ተግባር ለማስገባት በልዩ ትኩረት በመስራት የዘርፉን ውጤታማነት እንደሚያሻሽል የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም ስኬት የኮሌጁ ማህበረሰብ ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ መሰል ስራዎችን እና የሚሰሩትን አሰልጣኝ መምህራን ልናበረታታቸው ይገባል። ድሬዳዋ ሚያዝያ 09/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን

"Laminated Managerial Table" ======================== ✍️ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዉድ ወርክ ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት በድሬዳዋ አቀፍ በተካሄደ የቴክኖሎጂ ውድድር ላይ በመሳተፍ "Laminated Managerial Table" በመስራት ከአቻ ኮሌጅ ዲፓርትመንት በመላቅ አንደኛ መውጣት ችሏል፤ ✍️ ይህም ቴክኖሎጂ በዋናነት ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ በከፍተኛ ገንዘብ የሚገባውን እንዲሁም እዚሁ በማምረት የውጭ ምንዛሬን የሚያስቀር ሀገራዊ ፋይዳው ቀላል የማይባል ስራ ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ዲፓርትመንቱ የተለያዩ የፈርኒቸር ውጤቶችን በጥራት በመስራት ላይ ይገኛል፤ ✍️ በሌላ በኩል ጥያቄዎችን ተቀብሎ በጊዜ ሰርቶ ከማስረከብ አንጻር የሚነሱ ቅሬታዎችንም ለመፍታት ከሰው ሃይል፤ ከማቴሪያል አቅርቦትና ግዢ፤ እንዲሁም አጠቃላይ አሰራር ላይ የኮሌጁ ምርትና አገልግሎት መመሪያ ተሻሽሎ ተግባራዊ ከመሆኑ ሂደት የሚያመጣው ማሻሻያ ጎን ለጎን ከሚመለከታቸው ሂደቶች እና የስራ ክፍሎች ጋር በመናበብ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የዲፓርትመንቱ ተጠሪ አሰልጣኝ መምህር ዮሴፍ እንዳልካቸው ለኮምንኬሽን ክፍላችን ገልጸዋል። ድሬዳዋ ሚያዚያ 06/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን

"የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ቅኝት" ======================= ✍️ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ተልዕኮዎች ውስጥ ችግር ፈቺና አዋጪ የሆነ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስልጠና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች በማቅረብና ኢንተርኘራይዞችን በማሰልጠን ቴ/ጂዎችን ለማሸጋገርና ብቃቱ የተረጋገጠ ኢንተርኘራይዝ መፍጠር ጥራት ያለው ተወዳዳሪ የሆነ ምርት በማምረት ራሳቸውም ማህበረሰቡንም በመጥቀም ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግ ሀብት ማፍራት እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን በዚህ ቴክኖሎጂ ተሳታፊና በቴክኖሎጂው በመጠቀም የራሳቸውን ሀብት፤ እውቀት፣ ቴክኖሎጂን100 ፐርሰንት የመቅዳት አቅም ከፍ ያደርጋሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ✍️ በአስተዳደሩ የሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ገበያን መሠረት ያደረጉ እና በጥራት፣ በምርታማነት፣ በጊዜና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ማቅረብ እንዲችሉ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ማመቻቸት የግድ ይላል፤ ለዚህም ኮሌጁ የማህበረሰቡን ችግር ሊፈታ የሚችል ቴክኖሎጂ የመስራት አቅሙን ከፍ ለማድረግና ብቃቱ የተረጋገጠ ቴክኖሎጂን ማለትም የዳቦ ማሽን ሙሉ ፓኬጅን የያዘ ይህም የማቡኪያ፤ማኮፈሻና የመጋገሪያውን ናሙና እና የፕላስቲክ ተረፈ ምርትን ወደ ምርትነት የሚቀይር ማሽን በመስራት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች በማሸጋገር ምርታማነታቸው እንዲጨምርና ሀብት እንዲያፈሩ አላማው በማድረግ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡ ✍️ በዚህም አሰልጣኝ መምህራን በዚህ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ሲሳተፉ ቴክኖሎጂውን 100 ፐርሰንት የመቅዳት አቅም ከፍ ያደርጋሉ ተብሎ ይታመናል፤ በትግበራው ያገኙትን ዕውቀት ክህሎት በመጠቀም በገበያ ተወዳዳሪ አዳዲስ የሆኑ ምርቶችን በማቅረብ ማህበረሰቡን እንዲሁም እራሳቸውን ወደ ተሻለ ቴክኖሎጂ መግባትና መጠቀም አንዲችሉ ያስችላል፤ ተፈትሾ ጥራታቸው የተረጋገጠ ቴክኖሎጂዎች ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች በማሸጋገር ምርታማነታቸው እንዲጨምርና ሀብት እንዲያፈሩ ማድረግ ስለሚያስችል እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግር በመፍታት ተቋሙን እና አሰልጣኝ መምህሩን በሃገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የኮሌጁ ኮምንኬሽን ክፍል የቴክኖሎጂ ስራዎቹም አሁናዊ ሁኔታ ቅኝት በማድረግ ስራዎቹ የደረሱበትን ደረጃ ለመመልከት ችሏል፡፡ ድሬዳዋ ሚያዚያ 04/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

የኮሌጅ የቦርድ አመራር __ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከረጅም ጊዜ በኋላ የኮሌጁ የቦርድ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሮ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድና ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ሰብሳቢነት በኮሌጁ ስማርት የመሰብሰቢያ ክፍል የመጀመሪያውን ስቡሰባ አድርጓል በዚህም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ለቦርዱ አባላት እንደ ከተማ አስተዳደር በኮሌጁ ትኩረት ሊያገኙ እና ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አቅርበው ውይይት ማድረግ ተችሏል። ድሬዳዋ ሚያዚያ 01/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

የኮሌጅ የቦርድ አመራር __________ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከረጅም ጊዜ በኋላ የኮሌጁ የቦርድ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሮ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድና ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ሰብሳቢነት የመጀመሪያውን ስብሰባ በኮሌጁ ስማርት የመሰብሰቢያ ክፍል የመጀመሪያውን ስቡሰባ አድርጓል በዚህም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ለቦርዱ አባላት እንደ ከተማ አስተዳደር በኮሌጁ ትኩረት ሊያገኙ እና ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አቅርበው ውይይት ማድረግ ተችሏል። ድሬዳዋ ሚያዚያ 01/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

የአገልግሎት ማሻሻያ ጥናቶች ላይ ውይይት ተደረገ ==================================== በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም ትኩረት የተሰጠበት ስራዎች በዋናነት የሚሰጡ አገልግሎቶችን አሰራርና መመሪያዎችን በማሻሻል ለትግበራ አመቺ የሚሆኑበትን መንገድ ቀይሶ ይህንንም ለማስፈጸም በኮሌጁ የሚገኙ የA ደረጃ መምህራንና የሚመለከታቸውን በማዋቀር የተለያዩ ጥናቶች እንዲጠኑ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሠረት የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎቶችን ለማሻሻል የተጠኑ ጥናቶች በተጨማሪም የምርትና አገልግሎት መመሪያ ለኮሌጁ አመራር ፑል ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል በዚህም ውይይት ላይ ተሳታፊዎች ቢታይ እና ቢሻሻል ያሏቸውን ሀሳብና አስተያያት ያነሱ ሲሆን በቀጣይም ጥናቶቹ ዳብረው የሚጠናቀቁበት አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል። ድሬዳዋ መጋቢት 30/2014 ዓ.ም የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

ተማሪዎች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ ====================== በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቀደም ሲል ከተለያዩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረገው ውይይትና በተደረሰው የጋራ መገባባትና በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ ማለትም(STEM) ግንዛቤ ለማስጨበጥ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዓ.ም ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በዚህም ተማሪዎቹ የተግባር ስልጠና የሚሰጥባችውን የትምህርት ክፍል(workshop) በመጎብኘት ስለቴክኒክና ሙያና በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ (STEM) ግንዛቤ ማስጨበጥ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ተማሪዎቹ የማኑፋክቸሪግ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል፤ የአውቶሞቲቭ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል፤ የውድ ቴክኖሎጂ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል እና የኤሌክትሪክና ኢሌክትሮኒክስ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል አሰልጣኝ መምህራን ለጉብኝት ለመጡት ተማሪዎቹ የተግባር ስልጠና የሚስጥበትን ክፍሎች(workshops) በማስጎብኘት ተማሪዎቹን ግንዛቤ እንዲጨብጡ አድርገዋል፡፡ ድሬዳዋ መጋቢት 30/2014 የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን