ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 358
订阅者
+1224 小时
+977 天
+37130 天
帖子存档
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ  ስልጠና ኤጀንሲ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት  በዚህ አመት በሁለቱ የመንግስት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና በግል ተቋማት ስልጠናቸውን ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኝ ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ባህል ግንባታ ስልጠና ተሰጠ። በዚህም ስልጠና ላይ በድሬዳዋ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ውስጥ ስልጠናቸውን አጠናቀው ስኬታማ የሆኑትን  የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ  በረጅም አመት የኮሌጅ አሰልጣኝ መምህርነትና አመራርነት  ያላቸውን ልምድና ተሞክሮአቸውን አነቃቂ በሆነ ንግግር  ለስልጠና አጠናቃቂዎች  አካፍለዋል ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማት እና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የአሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ለማስጀመር ከኮሌጆች ጋር የጋራ መድረክ አዘጋጀ፤ መድረኩ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ከተሻሻሉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰራር ስርአቶች መካከል የሙያ ደረጃ እና የሙያ ብቃት ምዘና አተገባበር ስርአት መነሻ በማድረግ በአስተዳደሩ በግልና በመንግስት ኮሌጆች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞችን በተያዘው የ2017 በጀት አመት ወደምዘና ለማስገባት የሚያስችል መግባባት ለመፍጠር ያለመ ሆኗል፡፡ በዚህም ከቢሮው የቴክኒክና ሙያ ትምህሮትና ስልጠና ኤጀንሲ እና የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ባለሙያዎች እንዲሁም ከኮሌጆቹ አባል የሆኑበት የስትሪንግ ኮሚቴ ጋር የአሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወጥነት ባለው፣ በተቀናጀ እና የስልጠና ስራውን በማይጎዳ አግባብ ለመፈጸም ውይይት የተደረገ ሲሆን በአስተዳደሩ ከሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች እና የ5ቱ የግል ኮሌጆች ለምዘና የተለዩ አሰልጣኞች ምዘና ለማከናወን ለውሳኔ የሚረዱ ሃሳቦች መለየታቸውን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት ላለፉት 5ቀናት በድሬዳዋ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለአስተዳደር ስራተኞች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ:: በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት በተልምዶ ፕሮጀክቶች ሲመጡ በእብዛኛው ትኩርት የሚያደርጉት አ/ መምህራን ላይ ብቻ እንደነበር አስታውሰው የEASE ፕሮጀክት ቀረፃው ላይ የአስተዳደር ዘርፉንም እንዲያሳትፍና የፕሮጀክት ኢኒሼቲቩንም ስንቀርፅ ትኩርት እንዲደረግበት አስበን ነው ያሉ ሲሆን በዚህም ስልጠና በተሰጠው ግብረ-መልስ መሰረት በታቀደው አግባብ እንደተሰጠ በመረዳታችን ለስራ አመራር ኢንስቲትዩት አመራሮችና ስልጠናውን ለሰጡልን አሰልጣኞች ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለንም ብለዋል:: ኮሌጁ የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫን ለማግኘት እንደ ትቋም ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እንዳከናወነ የገለፁት የኮሌጁ ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ አክለውም ተቋሙ እስካሁን ያከናወናቸው ትግበራዎች ወደኃላ እንዳይመለሱ እዚህ በሰለጠናችሁት አግባብ መሰረት ይበልጥ እንዲሻሻል ስልጠናውን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል:: የድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ በበኩላቸው ይህ የደምበኛ እገልግሎትና የስራ ሥነ-ምግባር ስልጠና ቀጥታ ሰራተኞች እለት ተእለት ከሚከውኑት የስራ ተግባር ጋር የሚገናኝ በመሆኑ የወሰዳችሁት ስልጠና ጠቀሜታው የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ኮሌጁ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ የሚሰጡት አገልግሎት እንዲሻሻል በማቀድ ይህንና መሰል ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ማመቻቸቱ የሚበረታታ በመሆኑ የኮሌጁን አመራሮችም አመስግነዋል:: የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ ስልጠናው በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን በቀጣይ ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞችም ስልጠናውን የሚወስዱ ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም

የTVT ሴክተሩ ከአመለካከት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ ችግር የሚታይበት ዘርፍ በመሆኑ ከሚድያ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተግለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች ዘርፉን አስመልክቶ የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሄደ:: የግንዛቤ መስጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በንግግራቸው በአስተዳደሩ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያሉ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሰሯቸው ስራንዎችና ለዘርፉ የሚሰጡትን የአየር ሰዓት በማሻሻል ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ገልፀው በተጨማሪም የሚዲያ ባለሙያዎች ስለዘርፉ በጥልቀት ለመገንዘብ እንዲረዳ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ አንድ የሙያ ክህሎት እንዲሰለጥኑ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል:: ማህበረሰቡ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለው አመለካከት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በዘርፉ ተገቢውን ግንዛቤ ለመፍጠር የሚዲያ አካላት በተለያየ አጋጣሚ በሚያደርጏቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርፇ ዋና ኢላማውን እንዲመታ እንዲሁም የተሻለ የስራ እድል ተፈጥሮ የወጣቱን ብሎም የማህበረሰቡን ህይወት መቀየር እንዲቻል የሚታየውን የተዛባ አመለካከትን መቀያር አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህም የሚዲያ አካላት የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም ተቋሙ በቀጣይ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ጋር በርካታና ዘላቂነት ያላቸው ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት በእቅድ መያዙን ገልፀው ለዚህም እንዲረዳ የሚዲያ አካላት ከተቋሙ ጋር በጋራ ሊሰሩባቸው የሚችሉ ሀሳቦችንም ይዘው ቢመጡ ኮሌጁ በየትኛውም መንገድ በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል:: በእዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፓሊሲ ዙሪያ ለተሳታፊዎች ግንዛቤ የሰጡት በስራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና የሰልጣኞች ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ምንልክያለው ወርቅነህ ሲሆን በዚህም ነባሩ ፖሊሲ ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ጨምሮ በአዲሱ ፖሊሲ የተካተቱ የለውጥ ሀሳቦችን በዝርዝር ለተሳተፊዎች አቅርበዋል:: በመድረኩ ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5አመት ትግበራ ምን ሊሰራ እንዳቀደ ለሚዲያ አካላት በዝርዝር የቀርበ ሲሆን ከመድረኩ በቀረቡ ሃሳቦች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ስለሚኖረው የጋራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ሰፊ ውይይትም ተካሂዷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት በተቋሙ አገልግሎት ዘርፍ ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ:: ኮሌጁ በEASE(Education and Skills for Employ Ability) ፕሮጀክት አማካኝነት ያዘጋጀው ይህን የአቅም ግንባታ ስልጠና Work Ethics & Service Delivery ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ሲሆን በአስተዳደር ከሚገኘው የስራ አመራር ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑም ተገልፇል:: ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፋት መልዕክት "ይህ ስልጠና ሲዘጋጅ በተቋሙ ጥናት ተደርጎበትና አስፈላጊነቱም በማኔጅመንቱ ታምኖበት የተዘጋጀ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች እዚህ በሚኖራችሁ የ5ቀን ቆይታ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡና በሀላፊነት ሰልጥናችሁ ወደ ኮሌጁ ስትመለሱ በየምትሰሩበት የስራ ክፍል ላይ በተግባር የሚታይ ለውጥ ማሳየት ይጠበቅባችኃል ያሉ ሲሆን ይህም ስልጠና እንደ ማስጀመርያ መሆኑን እና ተቋሙ በቀጣይ ያቀዳቸውና በየክፍሉ በተለዩ የስልጠና ፍላጎቶች ላይ ተመርኩዞ ክፍተቶችን በስልጠናዎች የሚሞላ መሆኑንም ገልፀዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም ተቋሙ በዚህ አመት በርካታ አሳይመንቶች እንዳሉበትና አንደኛውም የISO ጉዳይ መሆኑን አስታውሰው ISO በዋናነት ሚያተኩረው Costomer Focus ላይ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ያለንበት የCostomer satisfaction survey ከኛ ብዙ እንደሚጠበቅ አመላካች በመሆኑና ይህንንም ለመፈፀም የስራ ስነ-ምግባር ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ምክንያት ይህንን ስልጠና ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ አጊኝተነዋልም ብለዋል:: የአቅም ግንባታው ስልጠናው በኢንቲትዩቱ አሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናው በሁለት ዙር ተከፍሎ ሲሰጥ ይህ የመጀመርያ ዙር ስልጠና ለቀጣዮቹ 5ቀናትም የሚቆይ ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያላቸው ግንዛቤ ከሚፈለገው እኳያ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራንና የተማሪ ተወካዮችን የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሂዷል:: ፕሮጀክቱ በቀጣይ በሚኖረው የ5 አመት ትግበራ በኮሌጅ የሚሰጡ የሞያ ስልጠናዎች በእስተዳደሩ የሚገኙትን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎችን ማእከል ያደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች ስለ ዘርፉ በቂ ግንዛቤ መፍጠር ተቀዳሚው ተግባር በመሆኑ ይህ መድረክ መዘጋጀቱም ተገልፇል:: በመድረኩ ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ላይ ስለ ቴክኒክና ሙያ በቂ ግንዛቤ ባለመፈጠሩ ምክንያት ወጣቶቹ በዘርፉ የሚኖራቸውን ተጠቃሚነት ባለመገንዘብ ህይወታቸውን በማይለውጡ የትምህርት መስኮች ላይ እድሜያቸውን እያባከኑ እንደሚገኙ ገልፀው በስተመጨረሻም የተማሩትን ዲግሪ አስቀምጠው ሌሎች ስልጠናዎችን ለመውሰድ ወደ ኮሌጁ እንደሚመጡም አስታውሰዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም በአስተዳደሩ የሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከኮሌጁ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎቹ ላይ ተገቢውን የግንዛቤ የመፍጠር ስራ በመስራትና ተማሪዎቻቸው የ12 ክፍል መልቀቂ ፈተና ከመውስዳቸው አስቀድሞ ተማሪዎቹን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እሳቤ መቅረፅ የሁላችንም ድርሻ መሆን እንደሚግባውም አፅዕኖት ሰተው ተናግረዋል:: በኢንዱስትሪው ዘርፍ ሰፊ የክህሎት ክፍተት እንዳለ የተጠቀሰ ሲሆን በየፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ወጣቶችም ዝቅተኛ ክህሎቶች(Low skills) ላይ አየሰሩ ያሉ መሆናቸውም ተመላክቷል:: በመድረኩ የSTEM(Science,Technology, Engineering,Mathematics)ፅንሰ ሃሳብና ምንነት ዙሪያ በኮሌጁ ምክትል ዲን እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተሾመ ሸዋዬ በኩል ለመድረኩ ተሳታፊዎች ቀርቧል:: የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዘርፉ በሚፈለገው ልክ ውጤት እንዳይመጣ ተግዳሮት ሆነዋል ያሏቸውን ምክንያቶች በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን በቀጣይም ከኮሌጁ ጋር በቅንጅትና በባለቤትነት ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እንደሆኑና የሚታዩ ክፍተቶችንም በዘላቂነት መፈታት እንደሚሹ ሀሳብ አስተያየታቸውን ሰተዋል:: ኮሌጁ በቀጣይ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር የጋራ መግባብያ ሰነድ በመፈራረም ወደ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም