EEP Communication
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览
频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 530 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 328,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 176 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 530 名订阅者。
根据 06 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 6,过去 24 小时变化为 -3,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 27.84%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.05% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 323 次浏览,首日通常累积 2 492 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“EEP Communication”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。
15 530
订阅者
-324 小时
-97 天
+630 天
帖子存档
15 527
ሪጅኑ ባለፉት 6 ወራት ከዕቅዱ በላይ የቅድመ ብልሽት ፍተሻና የጥገና ሥራ አከናወነ
………..////………..
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ ሪጅን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ ባለፉት 6 ወራት የዕቅዱን 102 ነጥብ 38 በመቶ የቅድመ ብልሽት ፍተሻና የጥገና ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
ቢሮው የስድስት ወር አፈፃፀሙን በጅግጅጋ ሲገመግም ዳይሬክተ ሩ አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን ከዛፍ ንኪኪ የማፅዳት፣ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመተካት፣ የመሬት መንሽራተት ምሰሶዎችን እንዳይጎዳ የጋቢዮን ማንጠፍና የተበጠሱ ገመዶችን በሌላ የመተካት ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
የፖርሲሊን ኢንሱሌተሮችን በፕላስቲክ ኢንሱሌተር የመተካት ስራ መስራቱንም ገልፀዋል፡፡
ይህም የሪጅኑን አፈፃፀም 102 ነጥብ 38 በመቶ አድርሶታል ብለዋል፡፡
ከተመሠረተ ሦስት ወራት ያስቆጠረው የጅግጅጋ ንዑስ ሪጅን የተቋቋመበትን ዓላማ መውጣት እንዲችል ተገቢው ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በሪጅኑ ከሪፖርት አቀራረብ፣ የሚሞሉ ዕለታዊ ሎግ ሺቶችን ኦዲት ካለማድረግና ከስልጠና ጋር የተያያዙ የአፈፃፀም ክፍተቶች መታየታቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በርካታ የጥገናና የኦፕሬሽን ሥራዎች ማከናወኑን ገለፀ
............/////..............
የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ስድስት ወራት ስኬታማ የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራዎች ማከናወኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሴ አስታውቁ፡፡
በስድስት ወራት ውስጥ 534 ነጥብ 2 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማመንጨት ታቅዶ 600 ጌጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ በማመንጨት የዕቅዱን 120 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ጣቢያው 230/132 ኪ.ቮ አቅም ያለው ስዊች ያርድ ባለቤት ሲሆን ለጌዶ፣ ሰበታና ሰኮሩ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኤሌክትሪክ የሚያቀርቡ ሶስት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
ከኦፕሬሽን ሥራዎች ባሻገር በማቀዝቀዣ፣ በዲዝል፣ በስካዳ ሲስተም እና በስዊችያርድ ላይ የጥገና ሥራዎች የተከናወኑ መሆኑን አቶ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡
በብልሽት ምክንያት ለሥራ እንቅፋት ሆኖ የቆየውን የዩኒት አንድ ሰርቨር የኮምፒውተር ሰሌዳ ወይም ስክሪን በመጠቀም እንደገና አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉን ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡
በስዊችያርድ ላይ የሞደፊኬሽን ሥራዎች በማከናወን ስዊች ያርድ ላይ ያጋጥም የነበረውን ተደጋጋሚ የኃይል መቋረጥ ማስቀረት መቻሉንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
ተቋሙ ኤች አይ ቪ እና ኮሮናን ለመከላከል የሚያስግዝ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
............/////.........
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በታላቁ የትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ የተሳተፉ ሠራተኞችን ከኤች አይቪ ኤድስ እና ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከዲኬቲ ኢትዮጵያና ከፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ስምምነቱ በፕሮጀክቱ የተሳተፉ ሠራተኞችንና የአካባቢው ማህበረሰብን ከኤች አይ ቪ ኤድስና ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግና ሌሎች ቴክኒካል ስራዎችን ለማከናወን የሚያግዝ ነው፡፡
በስምምነቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ኃይል ስራ አስፈፃሚ አቶ አታላይ አበበ፣ በኢትዮጵያ የዲኬቲ ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ እና የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጽጌሬዳ ክፍሌ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ የሁሉም ዜጋ እንደሆነ በመረዳት ተቋማቱ እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አቶ አታላይ አመስግነዋል፡፡
በህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ የተሳተፉ ሠራተኞችን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ ተቋማቱ ከዚህ በፊት ሲያከናውኑ የነበረውን ድጋፍ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
ቫይረሱ በፕሮጀክቱ ሰራተኞች ላይ እንዳይሰራጭ ተቋሙ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም አቶ አታላይ አረጋግጠዋል፡፡
የፌደራል ኤች አይ ቪኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጽጌሬዳ ክፍሌ በበኩላቸው ኤች አይ ቪ ኤድስ በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን የስርጭት አድማሱ እየተስፋፋ መሆኑን በመረዳት ለቫይረሱ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዲኬቲ ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ እንደገለጹት ድርጅታቸው የግድቡ ፕሮጀክት ከተጀመረ ጀምሮ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ሲያደርግ የቆየውን የፋይናንስና ሌሎች ቴክኒካል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
በዛሬው እለት የተካሄደው የድጋፍ ስምምነት ከ4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን ይህም ለሦስት ዓመታት የሚቆይ ድጋፍ እንደሆነ በተቋሙ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር አስተባባሪ አቶ መስፍን ደርሶ ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ በፕሮጀክቱ ላይ ለተሳተፉ ሠራተኞችና የአካባቢው ማህበረሰብ ስልጠና ለመስጠት፣ ሠራተኛው በትርፍ ጊዜው ወደ አልባሌ ቦታ እንዳይሄድ በፕሮጀክቱ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማዘጋጀት እና ሌሎች የንቅናቄ ስራዎችን ለማከናወን የሚውል መሆኑን ነው አቶ መስፍን የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
በቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚተገበር የሲስተም ልማት ዕቅድ ተዘጋጅቷል
…………….///…………..
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ለመተግበር ባዘጋጀው የሲስተም ልማት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመምከር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በዕቅዱ መሰረት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅሙን ከ4 ሺህ 515 ሜጋዋት ወደ 17 ሺህ 56 ሜጋዋት ለማሳደግ፣ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮችን ርዝመት አሁን ካለበት19 ሺህ 746 ኪ.ሜ. ወደ 33 ሺህ 497 ኪ.ሜ. ለማድረስ ታቅዷል፡፡
በተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ የተዘጋጀው የአስር ዓመት ዕቅድ እንደሚያሳየው በዕቅድ ዘመኑ ከ132 ኪሎ ቮልት በላይ አቅም ያላቸው 176 ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 265 ለማሳደግም ይሰራል፡፡
በኃይል ማስተላለፍ ወቅት የሚያጋጥመውን የ6 በመቶ የኤሌክትሪክ ብክነት ወደ 3 ነጥብ 5 በመቶ ለመቀነስና የተቋሙን ገቢ ደግሞ ከ300 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ 5 ነጥብ 32 ቢሊየን ለማሳደግ ዕቅድ ተይዟል፡፡
አሁን ከግሪድ ጋር ያለውን የ33 በመቶ ግንኙነት ወደ 96 በመቶ ለማሳደግ፤ ከውሃ የሚገኘውን የ93 በመቶ የማመንጨት ድርሻ ወደ 73 በመቶ በመቀነስ በአንፃሩ ከንፋስ፣ ከጂኦተርማልና ከፀሐይ ኃይል የማመንጨት ድርሻን ለማሳደግ እንደሚሰራም በዕቅዱ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
ጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ስድስት ወራት ከዕቅድ በላይ ኃይል ማመንጨት ችሏል
…………////………..
የጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በግማሽ ዓመቱ 958 ጌጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማመንጨት አቅዶ 1028 ነጥብ 5 ጌጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ማመንጨቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሐብታሙ ገረመው አስታወቁ፡፡
ጣቢያው ያመነጨው ከዕቅዱ የ 7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ከጊቤ 3 እና ከበለስ ቀጥሎ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የሆነው የጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 420 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት አንፃር የጎላ ሚና በመጫዎት ላይ የሚገኝ ጣቢያ ነው፡፡
ከሰው ኃይል ልማት አኳያም ለዘጠኝ አዲስ መሐንዲሶች እና ለአራት ቴክኒሺያኖች ለሁለት ወራት ያህል የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
የጣቢያው የጥገና ክፍል ተወካይ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ተስፋ በበኩላቸው ከኦፕሬሽን ተግባራት ጎን ለጎን ጣቢው ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የጥገና ሥራዎች ሲከናወኑ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
ዘይት እያፈሰሰ የኃይል ማመንጨቱን ስራ ያስተጓጉል የነበረውን የውሃ መቀበያ ዋና አሸንዳ እና የመቆጣጠሪያ ክፍል የአየር ማቀዝቀዣ በጥገና ክፍሉ ባለሙያዎች ተጠግኖ ወደ ስራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
በ2002 ዓ.ም ተመርቆ በይፋ ስራ የጀመረው የጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሶስት ትራንስፎርመሮችን የያዘ ባለ 400 ኪ.ቮ ስዊችያርድ አለው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 15 ቀን 2013
15 527
የሴቶችን ተጠቃሚነትና ውሳኔ ሰጭነትን ለማሳደግ የሚያግዙ ውሳኔዎች ተላልፈዋል
………///………
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሴት ሠራተኞችን ተጠቃሚነትና ውሳኔ ሰጭነትን ለማሳደግ የሚያግዙ የተለያዩ አወንታዊ የድጋፍ እርምጃ (Affirmative action) ዉሳኔዎች መተላለፋቸውን በተቋሙ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢዲኤ እንደገለፁት የተላለፉት ውሳኔዎች የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ውሳኔ ሰጪነትን ለማሳደግና እኩልነትን በተግባር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ውሳኔዎች የተላለፉት በተቋሙ ሥራ አመራር እና መሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር በተመሰረተ ኮሚቴ አማካይነት ጥናትና ውይይቶች ከተካሄዱ በኋላ ነው፡፡
በዚህ መሰረት በተቋሙ በጀት ተይዞ በየዓመቱ እስከ ዲፕሎማ የትምህርት ደረጃ 25 ሴቶችን፣ በመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መስክ 20 ሴቶችን እና በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ 10 ሴቶችን ለማሰልጠን የሰው ኃይል እና የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በጋራ በሚያወጡት ግልፅ መስፈርት ተወዳድረው እንዲማሩ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል - ዳይሬክተሯ፡፡
ወ/ሮ ሌንሴ እንደገለጹት ተቋሙ የሴቶችን ፍትሐዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አዲስ ቅጥር በሚያከናውንበት ጊዜ ለፈተና ከሚመረጡ ተወዳዳሪዎች መካከል 30 በመቶው ለሴቶች ዕድል እንዲሰጥና ፈተናውን ካለፉት ተወዳዳሪዎች መካከልም 30 በመቶ ድርሻ ለሴቶች ብቻ እንዲሰጥ ተደርጎ 70 ከመቶ ከወንዶች ጋር ዕድል እንዲሰጥ የሚያደርግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
15 527
የአክሱምና ሽሬ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማምሻውን አግኝተዋል
............////.................
በትግራይ ክልል በጁንታው ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ የአድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው ዛሬ የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝተዋል።
መሠረተ ልማቱን ለመጠገን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ቀደም ሲል አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ማግኘታቸውንና የአድዋ ከተማ ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በፊት ኤሌክትሪክ እንዳገኘ መግለፃችን ይታወሳል።
በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ማምሻውን ከተሞቹ የመብራት አገልገሎት አግኝተዋል።
የሑመራ እና ወልቃይት ከተሞችና አካባቢያቸውን ኤሌክትሪክ ለማገናኘትም ርብርብ እየተደረገ ነው።
በዚህ አጋጣሚ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የጥገና ስራውን በኋላፊነት ስሜት የተወጡ የተቋሙ ሠራተኞችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በተቋሙ ሥራ አመራርና ሰራተኞች ስም አመስግነዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ጀመረ
............////.................
በትግራይ ክልል በጁንታው ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ ዛሬ የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝቷል።
መሠረተ ልማቱን ለመጠገን የፌዴራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት እንዳገኙ መግለፃችን ይታወሳል።
በዛሬው ዕለትም በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአድዋ የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ከተማው የመብራት አገልገሎት አግኝቷል።
የአክሱም፣ ሽሬና ሑመራ ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ ነው።
ጁንታው በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት የህግ ማስከበር ዘመቻ በሽንፈት ከከተሞች ለቆ ሲወጣ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱና የከፍተኛ የአሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን መበጣጠሱ አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
የደጀን ደብረ ማርቆስ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል ሥራ አፈጻፀም 16 በመቶ ደረሰ
.........////........
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የተጀመረው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ የሲቪል ሥራ አፈጻፀሙ 16 በመቶ ደርሷል፡፡
ከአዲስ አበባ በ229 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደጀን ከተማ የተጀመረው የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ በአሁኑ ወቅት የትራንስፎርመር መትከያ ስፍራ መሰረት ተጠናቋል።
የደጀን ደብረማርቆስ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ እና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ታምራት እንደገለፁት የፕሮጀክቱ የቁፋሮ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የአጥር እና የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታዎች ሥራ እየተከናወኑ ነው።
ለማከፋፈያ ጣቢያው ከደብረ ማርቆስ - ደጀን የሚደርስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር ሰርኪዩት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር እንደሚዘረጋ ተገልጿል፡፡
የሲቪል ሥራ አፈጻፀሙ 16 በመቶ የደረሰ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በደጀን እና ደብረ ማርቆስ ከተሞች ለተገነቡት ፋብሪካዎች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
ፕሮጀክቱን በ14 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ለግንባታውም ከ133 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቧል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም
15 527
የኢንዱስትሪ ፍሰቱን ታሳቢ ያደረጉ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው
............////.............
በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እየጨመረ በመምጣቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያሳድጉ መሠረተ ልማቶችን የመገንባትና አቅም የማሳደግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን እና ጥገና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ውበቱ አቤ እንደገለፁት ከአሁን በፊት በተዘረጋው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በክልሉ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈላጊ ደንበኞችን ጥያቄ ማስተናገድ አልተቻለም፡፡
ባህርዳር ላይ ባለ 400/230 /132 እና 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ቢገነባም ተጨማሪ የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ እና የማሻሻያ ሥራ ይፈልጋል ብለዋል።
ይሁንና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት በአዘዞ - ጭልጋ ፣ በለስ - ጃዊ እና ደጀን - ደብረ ማርቆስ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ግንባታቸው እየተከናወነ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የቡሬና ባህርዳር ኢንዱስትሪ ዞኖችን ጨምሮ ጥናታቸው የተጠናቀቀ የኤሌክትሪክ ማከፋፊያ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 07 ቀን 2013 ዓ.ም
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
