EEP Communication
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览
频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 528 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 328,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 176 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 528 名订阅者。
根据 06 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 6,过去 24 小时变化为 -3,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 27.84%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.05% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 323 次浏览,首日通常累积 2 492 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“EEP Communication”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。
15 528
订阅者
-324 小时
-97 天
+630 天
帖子存档
15 528
የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ጀመረ
............////.................
በትግራይ ክልል በጁንታው ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ ዛሬ የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝቷል።
መሠረተ ልማቱን ለመጠገን የፌዴራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት እንዳገኙ መግለፃችን ይታወሳል።
በዛሬው ዕለትም በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአድዋ የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ከተማው የመብራት አገልገሎት አግኝቷል።
የአክሱም፣ ሽሬና ሑመራ ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ ነው።
ጁንታው በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት የህግ ማስከበር ዘመቻ በሽንፈት ከከተሞች ለቆ ሲወጣ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱና የከፍተኛ የአሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን መበጣጠሱ አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም
15 528
የደጀን ደብረ ማርቆስ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል ሥራ አፈጻፀም 16 በመቶ ደረሰ
.........////........
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የተጀመረው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ የሲቪል ሥራ አፈጻፀሙ 16 በመቶ ደርሷል፡፡
ከአዲስ አበባ በ229 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደጀን ከተማ የተጀመረው የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ በአሁኑ ወቅት የትራንስፎርመር መትከያ ስፍራ መሰረት ተጠናቋል።
የደጀን ደብረማርቆስ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ እና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ታምራት እንደገለፁት የፕሮጀክቱ የቁፋሮ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የአጥር እና የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታዎች ሥራ እየተከናወኑ ነው።
ለማከፋፈያ ጣቢያው ከደብረ ማርቆስ - ደጀን የሚደርስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር ሰርኪዩት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር እንደሚዘረጋ ተገልጿል፡፡
የሲቪል ሥራ አፈጻፀሙ 16 በመቶ የደረሰ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በደጀን እና ደብረ ማርቆስ ከተሞች ለተገነቡት ፋብሪካዎች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
ፕሮጀክቱን በ14 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ለግንባታውም ከ133 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቧል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም
15 528
የኢንዱስትሪ ፍሰቱን ታሳቢ ያደረጉ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው
............////.............
በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እየጨመረ በመምጣቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያሳድጉ መሠረተ ልማቶችን የመገንባትና አቅም የማሳደግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን እና ጥገና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ውበቱ አቤ እንደገለፁት ከአሁን በፊት በተዘረጋው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በክልሉ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈላጊ ደንበኞችን ጥያቄ ማስተናገድ አልተቻለም፡፡
ባህርዳር ላይ ባለ 400/230 /132 እና 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ቢገነባም ተጨማሪ የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ እና የማሻሻያ ሥራ ይፈልጋል ብለዋል።
ይሁንና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት በአዘዞ - ጭልጋ ፣ በለስ - ጃዊ እና ደጀን - ደብረ ማርቆስ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ግንባታቸው እየተከናወነ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የቡሬና ባህርዳር ኢንዱስትሪ ዞኖችን ጨምሮ ጥናታቸው የተጠናቀቀ የኤሌክትሪክ ማከፋፊያ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 07 ቀን 2013 ዓ.ም
15 528
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፣ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ !!!
መልካም በዓል!
የኢትዮጵያ ኤክትሪክ ኃይል
15 528
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፣ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ !!!
መልካም በዓል!
የኢትዮጵያ ኤክትሪክ ኃይል
15 528
የቆቃ ሐይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
……………///…………...
የቆቃ ሐይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አመራሮች እና ሠራተኞች በምስራቅ ሸዋ ዞን ሊሞ ወረዳ ቆቃ ነገዎ ቀበሌ በመገኘት ተሳትፎ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መለስ ሲሎ እንደገለፁት የዘመቻው ዋና ዓላማ መጤ አረሙ በሐይቁና በግድቡ ላይ እያሳደረ የሚገኘውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ነው፡፡
በዕለቱም አንድ ሔክታር የሚሸፍን የእምቦጭ አረም የመንቀል እና ለአረሙ ምቹ የሆኑ ደለሎችን የማፅዳት ሥራ መከናወኑንም ነው የጣቢያው ኃላፊ የተናገሩት፡፡
በሐይቁ ላይ የእምቦጭ አረም በፍጥነት እየተስፋፋ የሚሄድ ከሆነ ወደ ግድቡ የሚገባውን የውሃ መጠን በመቀነስ የሚመረተውን ኃይል ሊቀንስ ይችላል ሲሉም ኃላፊው ተፅዕኖውን ገልፀዋል፡፡
ከ50 በላይ የጣቢያውን ሠራተኞች ያሳተፈው ዘመቻ የመጤ አረሙን የመስፋፋት ጉዞ ለመግታት ያለመ ቢሆንም ችግሩ አሳሳቢ ከመሆኑ አንፃር ድጋፉ እና ርብርቡ መቀጠል እንዳለበት አቶ መለስ ተናግረዋል፡፡
መንግሥት ልዩ ትኩረት በመስጠትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ሐይቁን እና የኃይል ማመንጫ ግድቡን ከመጤ አረም ለመታደግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከ 60 ዓመት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ/ም
15 528
ለቁፋሮ ከሚያገለግሉ ሁለት የጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኖች መካከል የአንድ ማሽን ተከላ ተጠናቋል
…………..////……………
የአሉቶ የከርሰ ምድር እንፋሎት ጉድጓድ ቁፋሮ ለማካሄድ ከሚያስፈልጉት ሁለት የቁፋሮ ማሽኖች መካከል የአንዱ ማሽን ተከላ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአሉቶ ከርሰ ምድር እንፋሎት ፕሮጀክት አስታውቋል፡፡
የፕሮጀክቱ ሳይት መሐንዲስ አቶ መሳይ ፍቃዱ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛው ማሽን ተከላም እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ማሽኖቹ የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችን ያሟሉና ከ2 እስከ 2 ነጥብ 5 ኪ.ሜ ጥልቀት መቆፈር የሚያስችል አቅም እንዳላቸውና 350 ቶን ያህል ክብደት የመሳብ ወይም የመሸከም አቅም ያላቸው መሆኑን አቶ መሳይ ተናግረዋል፡፡
ከማሽን ተከላው ጎን ለጎን ለጉድጓድ ቁፋሮ የሚያገለግሉ እያንዳንዳቸው 4 ሚሊዮን ሊትር ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የውሃ ታንከሮች ገጠማ እና የውሃ መስመር ዝርጋታ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
የውሃ መስመር ዝርጋታው እንደተጠናቀቀ የጉድጓድ ቁፋሮ ሥራው በይፋ እንደሚጀመርም ነው ያስታወቁት፡፡
የፕሮጀክቱ የሠው ኃይል አስተዳደር ባለሙያ አቶ ወርቁ ዱቄ በበኩላቸው በእስካሁኑ ሒደት ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን በፕሮጀክቱ የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልፀዋል፡፡
የቻይናው ኬሩይ /KERUI/ ኩባንያ የመቆፈሪያ ማሽኑን አምርቶ የገጠማ ስራውን በማከናወን ላይ ሲሆን የኬንያው ኬንጀን /KENJEN/ እና የቻይናው ኬሩይ ኦይል ፊልድ /KERUI Oil field/ ኩባንያዎች ደግሞ የጉድጓድ ቁፋሮውን ያከናውናሉ፡፡
የአሉቶ የከርሰ ምድር እንፋሎት ፕሮጀክት ከምድር በሚወጣ ተፈጥሯዊ እንፋሎት አማካኝነት 70 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት ያለመ ነው፡፡
ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም
15 528
ወደ ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ተጠግተው ኤሌክትሪክ የዘረጉ ግለሰቦች ለኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኑ
..............///........
ከሰኮሩ ጊቤ 2 የሚያገናኝ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ መስመርን ተጠግተው ለመኖሪያ ቤት ኤሌክትሪክ የዘረጉ ግለሰቦች ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ለ30 ደቂቃዎች አካባቢ በከፊል ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት ሆነዋል።
ኤሌክትሪክ የተቋረጠው ግለሰቦቹ ለመኖሪያ ቤታቸው ከጎረቤት በአየር ላይ የሳቡት የኤሌክትሪክ ሽቦ ወደ ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ መስመር በመቅረቡ በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መሳሳብ ነው።
በዚህም በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ለግማሽ ሰዓት ሲቋረጥ አንድ የሳር ቤትና ለመሰብሰብ የደረሰ ሰብል ተቃጥሏል።
የአካባቢው ነዋሪ ተረባርቦ እሳቱን ባያጠፋው ኖሮ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችል የነበረ ሲሆን ፖሊስ የድርጊቱን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ህብረተሰቡ ወደከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮች ተጠግቶ ምንም ዓይነት መሰረተልማት እንዳይዘረጋ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያሳስባል።
ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ/ም
15 528
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሰጠ ማሳሰቢያ
*********************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን እሁድ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በምስራቅ ኢትዮጵያ ማለትም በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በአሰበተፈሪ፣ በጅግጅጋ፣ በፊቅ ፣ በደገሃቡር፣ በአዋሽ ሰባት ኪሎ፣ በአዲጋላ፣ በሁርሶ፣ በአሰላ፣ አዳማ፣ አዳሚ ቱሉ እና ሻሸመኔ እንዲሁም በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን በኖሪያ፣ ደብረዘይት፣ በኢላላገዳ፣ በጆርጅ ጫማ ፋብሪካ፣ በሞጆ፣ በራም፣ በጎዴ፣ በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
15 528
የሻሸመኔ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የአቅም ማሳደግና የማሻሻያ ሥራ ተጠናቀቀ
............../////...........
የሻሸመኔ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የአቅም ማሳደግና የማሻሻያ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያ እና ማከፋፊያ ጣቢያ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ከሠላሳ ዓመታት በላይ ለሻሸመኔ ከተማና አጎራባች ወረዳዎች አገልግሎት እየሰጠ ቢቆይም በየጊዜው እያደገ የመጣውን የህብረተሰቡን የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ማስተናገድ እንዳልቻለ ሪጅኑ ጠቁሟል፡፡
25 ሜጋ ቮልት አምፒር የመሸከም አቅም በነበረው አንድ ትራንስፎርመር ለከተማውና አጎራባች አካባቢዎች ኃይል ለማዳረስ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም ፍላጎቱ ከጣቢያው አቅም በላይ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ይህም በሻሸመኔ ከተማ እና አጎራባች ወረዳዎች ኤሌክትሪክ በፈረቃ እንዲሰጥ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አሳድሮ እንደነበር ሪጅኑ ገልጿል፡፡
ጣቢያው ያለበትን ችግር ለመቅረፍ በተሰራው ሥራ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር መሸከም የሚችል የኃይል ትራንስፎርመር በመትከልና የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎችን በማከናወን አቅሙን በእጥፍ ለማሳደግ እንደተቻለ አስታውቋል፡፡
15 ኪሎ ቮልት አቅም ያላቸው 6 ወጪ መስመሮችን አቅም የማሳደግ፣ የመቆጣጠሪያና የመከላከያ መሳሪያዎችን በአዲስ መልክ የመትከል ሥራዎችም ተከናውነዋል፡፡
ለማስፋፊያ እና ማሻሻያ ሥራው ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ምላሽ መስጠት መቻሉን ሪጅኑ ገልጿል፡፡
ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ/ም
15 528
በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ጀምሯል
................///..............
በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን ጀምሯል።
በህወሃት ጁንታ የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሰራ ቆይቷል።
የውቅሮና አዲግራት ከተሞች የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና በመጠናቀቁ የፍተሻ ስራ ተከናውኖ ከተሞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል።
የሽሬ፣ አክሱምና አድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙም በቅንጅት በመሰራት ላይ ነው።
ታህሳስ 08 ቀን 2013 ዓ/ም
15 528
የመቀሌ ከተማና አካባቢው ኤሌክትሪክ አግኝቷል
..................////............
የመቀሌ ከተማና አካባቢው ከሳምንታት የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ በኋላ ዛሬ አገልግሎት አግኝቷል።
ከአላማጣ ከተማ አንስቶ እስከ መቀሌ ድረስ ባሉ ከተሞች በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሽቦዎች( ኮንዳክተሮች) እና ስኒዎች(ኢንሱሌተሮቸ) ላይ የህወሀት ጁንታ ቡድን ባደረሰው ጥቃት በአካባቢዎቹ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።
በጁንታው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማቶች ጠግኖ ሁሉንም የክልሉ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሁለት የጥገና ቡድኖችን አዋቅሮ ቀን ከሌት ሲሰራ ቆይቷል።
በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የተሰማራው የጥገና ቡድን በመተማ፣ሁመራና ወልቃይት የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የጥገና ሥራ በማጠናቀቅ ከተሞቹ ኃይል እንዲያገኙ አድርጓል።
ከደሴ በመነሳት ወደሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የተሰማራው የጥገና ቡድን ደግሞ ከቀናት በፊት የአላማጣ፣ ማይጨው፣ መሆኒነና ሰቆጣ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ያደረገ ሲሆን ዛሬ የመቀሌ፣ ኲዊሀ፣ አዲጉዶምና አካባቢው ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ማድረግ ችሏል።
በስፍራው የተሰማሩ የጥገና ባለሙያዎች አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎችን ታግለው ሌት ተቀን በመስራት ለዚህ ውጤት በመድረሳቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አልፎ ሀገርንና ህዝብን እንደማገልገል የሚያስደስት ነገር እንደማይኖር በተግባር ስላሳያችሁን በሥራችሁ ኮርተናል ሲሉ የተሰማቸውን ስሜት ገልፀዋል።
ታህሳስ 04 ቀን 2013 ዓ/ም
15 528
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ እየተሠራ ነው
..............///........
በትግራይ ክልል ስግብግቡ የህወኃት ጁንታ ጉዳት ያደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማቶች ጠግኖ ሁሉንም የክልሉ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን አስታወቁ፡፡
የጥገና ስራውን በክልሉ ሙሉ በሙሉ ለማከናወንም ከተቋሙ የተውጣጣ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን በሁለት መስመር መሰማራቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ሞገስ ገለፃ አንደኛው ቡድን በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በመንቀሳቀስ ከባህርዳር ተነስቶ ወልቃይት፣ሁመራ፣ ወልቃይት፣ ሽሬ፣ አክሱም እና አድዋ ለሚገኙ የኃይል መሰረተ ልማቶች የጥገና ሥራዎችን በማከናወን ላይ ሲሆን በሰሜን ምስራቅ የተንቀሳቀሰው ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ከደሴ በመነሳት አላማጣ፣መሆኒ፣ሰቆጣ፣አሸጎዳ፣መቀሌና አዴግራት አካባቢዎች ላይ የጥገና ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
እስከአሁን በመተማ፣ሁመራ፣ወልቃይት እና ማይጨው የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የጥገና ሥራ ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ከአላማጣ-ሰቆጣ የተዘረጋውን ባለ 66 ኪ.ቮ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገን የአላማጣ እና ሰቆጣ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ መደረጉንም ነው አቶ ሞገስ ያብራሩት፡፡
በአሁኑ ጊዜ የመቀሌ-መሆኒ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል መስመር የጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ የመቀሌ ከተማ በቅርቡ የኤሌክትሪክ ኃይል እንድታገኝ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
እስከመጪው እሁድ አብዛኞቹ የትግራይ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙ በሙሉ አቅም ርብርብ እየተደረገ ነውም ብለዋል
15 528
ተቋሙ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን እና የፀረ ሙስና ቀን አከበረ
………../////……….
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሰራተኞች “እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል 15ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ፡፡
የተቋሙ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ስናከብር በህዝቦች እኩልነት ላይ የተመሰረተ እውነተኛና ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት ዲሞክራሲ ለመገንባት ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማገዝ ተቋማችን አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሚከበረው ከሃዲው የህወሓት ጁንታ ለመደምሰስ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባደረገው ታላቅ ተጋድሎ በተገኘው ድል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ባሸነፈበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በተያያዘ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች “የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራት ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥን” በሚል መሪ ቃል 16ኛው የፀረ ሙስና ቀን አክብረዋል፡፡
ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም.
15 528
በተቋሙ የድጋፍና እንክብካቤ ትግበራ እየተከናወነ ነው
………………////……………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር የሥራ ክፍል የኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽንን ከመከላከል በተጨማሪ የድጋፍና እንክብካቤ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
ኤች.አ.ቪ / ኤድስ በተቋሙ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ ለመከላከል በፖሊሲ የተደገፈ የድጋፍና ክብካቤ ሥርዐት ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን የስራ ክፍሉ አስታውቋል፡፡
ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሠራተኞች ከኤችአይቪ ጋር የተያያዘ ህመም ከታከሙ ለሕክምና የሚያዋጡት የ10 በመቶ ወጪ መጋራት እንዲቀር ተደርጓል፡፡
እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሠራተኞቹ ጤነኛ ሆነው በሥራቸው እንዲቀጥሉ የማድረግ ስራዎችም ተከናውነዋል፡፡
የተቋሙ ሠራተኞች ከደመወዙ በወር ብር 5 ብር በማዋጣት በድምሩ በየወሩ እስከ ብር 35 ሺህ በኤድስ አስተዋጽኦ (Contrubtion ) አካውንት እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡
በተሰብሳቢ ገንዘቡም ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ 39 (ሰላሳ ዘጠኝ) የተቋሙ ሠራተኞች በየወሩ 7 መቶ ብር ከደሞዝ ጋር በአካውንታቸው እንዲገባ፣ ወላጆቻቸውን በኤች.አ.ቪ / ኤድስ ላጡ 21(ሃያ አንድ) ህፃናት በየወሩ በአሳዳጊዎቻቸው አካውንት ብር 500 እና በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ለትምህርት ቁሳቁስ መግዣ በአንድ ልጅ እስከ ብር 1650 ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሰራተኞች በወር 35 ሺህ ብር ቢሰበሰብም ወጪ ድጋፍ እየተደረገ ያለው ከሚሰበሰበው በላይ በመሆኑ ልዩነቱ ድጋፉ ከመጀመሩ በፊት በአካውንቱ ውስጥ ከተጠራቀመ ገንዘብ ላይ እየተከፈለ ይገኛል፡፡
ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም.
15 528
የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ሀብታቸውን እያስመዘገቡ ነው
=========////=========
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ቋሚ ሠራተኞች ሀብት የመመዝገብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በተቋሙ የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ መርጋ ተረፈ እንዳስታወቁት የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሀብትና ንብረትን ለማስመዝገብ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ሁሉም የተቋሙ ቋሚ ሠራተኞችና አመራሮች ሀብታቸውን እያስመዘገቡ ነው፡፡
በተቋሙ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የሥራ መሪዎች እና በተመረጡ የሥራ መደቦች ላይ የሚገኙ ሠራተኞች ሀብታቸውን አሳውቀው ማስመዝገባቸውን ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሁሉም የመንግስት ሠራተኛ ሀብቱን እንዲያሳውቅና እንዲያስመዘግብ የተደረገው የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ለማስፈፀም የወጣው የተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 1/2013 ስለሚያስገድድ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ መርጋ ገለፃ በተቋሙ ሀብታቸውን ማስመዝገብ ከሚጠበቅባቸው 6 ሺህ 565 ቋሚ ሠራተኞችና አመራሮች ውስጥ ለ5 ሺህ 7 መቶ ሠራተኞች የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ ቅጽ ተደራሽ ተደርጓል፡፡
ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስም ከ3 ሺህ 7 መቶ በላይ አመራሮችና ሠራተኞች ሀብትና ንብረታቸውን አስመዝግበዋል፡፡
ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ/ም
15 528
በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖራታል
.................///..................
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖራት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ በዌቢናር በተካሄደው የዩይትድ ኪንግደምና የአፍሪካ የኢነርጂ ሚኒስትሮች ሲምፖዚየም ላይ እንደገለፁት በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ደግሞ ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር አቅዳ እየሰራች ነው።
ኢትዮጵያ እስካሁን 6ዐ በመቶ የሚሆኑት ዜጎቿ የኃይል ተጠቃሚ እንዳልሆኑና የኃይል አቅርት ችግሩ ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ይሁንና ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀየር መንግስት የተለያዩ እቅዶችን በማውጣት እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2025 ኢትዮጵያ በግሪድና በኦፍ ግሪድ ለዜጎች ሙሉ በሙሉ ኃይል ለማቅረብ ማቀዷን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ሃገራት ባለሃብቶች በዘርፉ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሲምፖዚየሙ ላይ የኢትዮጵያ፣ የሞሮኮ፣ የግብጽ፣ የሞዛምቢክና የሞሪታኒያ ሃገራት የኢነርጂ ሚንስትሮች ንግግር ያደረጉ ሲሆን 183 ባለድርሻዎችም የዌቢናር ውይይቱን ታድመውታል፡፡
ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ/ም
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
