ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 691 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 014,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 155

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 691 名订阅者。

根据 29 八月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 137,过去 24 小时变化为 5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 34.17%。内容发布后 24 小时内通常能获得 17.11% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 362 次浏览,首日通常累积 2 685 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 11

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 30 八月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 691
订阅者
+524 小时
+77
+13730
帖子存档
🏛 የተቋሙን ሥነ-ምግባርና ግልጽነት ለማጎልበት የላቀ ትኩረት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ መሪዎች "በሥነ-ምግባርዊ የውሳኔ አሰጣጥና በጥቅም ግጭት መከላከል" ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና
+4
🏛 የተቋሙን ሥነ-ምግባርና ግልጽነት ለማጎልበት የላቀ ትኩረት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ መሪዎች "በሥነ-ምግባርዊ የውሳኔ አሰጣጥና በጥቅም ግጭት መከላከል" ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና ተጠናቋል። ሥልጠናው የተቋሙን የአሰራር ሥርዓት በዘመናዊና ግልጽነት በተሞላበት መንገድ ለመምራት፣ የጥቅም ግጭቶችን ለመከላከል እና ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት ወሳኝ የሆኑ መሠረቶችን ለመጣል ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደገለጹት ስልጠናው አመራሩ በተለያዩ ጉዳዮች የሚሰጣቸውን ውሳኔዎች ሥነ- ምግባር በተላበሰ መልኩ እንዲፈጽም ለማድረግ እና ከጥቅም ግጭት ውስጥ እንዳይገባ ቀድሞ ለመከላከል ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የተቋሙን-ሥነ-ምግባርና-ግልጽነት-ለማጎል&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

በተቋሙ የጥቅም ግጭት ስጋቶችን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት ይሰራል …….///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥቅም ግጭት ስጋቶችን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተለያዩ
+9
በተቋሙ የጥቅም ግጭት ስጋቶችን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት ይሰራል …….///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥቅም ግጭት ስጋቶችን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡ "ሥነ - ምግባራዊ የውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር" በሚል ርዕስ ለተቋሙ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች ስልጠና የሰጡት በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የድህረ- ምረቃ ፕሮግራሞች አስተባባሪ አወቀ አሸናፊ (ዶ/ር ) በሥነ ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችና መርሆዎች፣ የጥቅም ግጭት ምንነት፣ አይነቶች፣ መንስኤዎች፣ ተጋላጭነትና ስጋቶች እንዲሁም መከላከያ ስልቶችና ማስተዳደሪያዎች ላይ ገለፃ አድርገዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በተቋሙ-የጥቅም-ግጭት-ስጋቶችን-ለመከላከ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

ሪጅኑ የቴክኒሻኖች የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ የማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ........///......... የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን በሥሩ ለሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሠራተኛ መኖሪያ ቤቶ
+5
ሪጅኑ የቴክኒሻኖች የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ የማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ........///......... የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን በሥሩ ለሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሠራተኛ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እየገነባ እንደሚገኝ አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ እንደገለፁት የሸዋ ሮቢት እና የኮምቦልቻ 1 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ያለባቸውን የሠራተኛ መኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስምንት አዲስ የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው። የቤቶች ግንባታ 70 በመቶ የተከናወነ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ቤቶቹ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ሪጅኑ-የቴክኒሻኖች-የመኖሪያ-ቤትን-ጨምሮ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሮች ሙስናን ሊጠየፉ ይገባል ........///........ ተቋሙ እንደ ሀገር የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት እና ያለውን ሀብት ውጤታማ በሆነ መንገድ
+9
የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሮች ሙስናን ሊጠየፉ ይገባል ........///........ ተቋሙ እንደ ሀገር የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት እና ያለውን ሀብት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የተቋሙ ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች ሙስናን ሊጠየፉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሳሰቡ። "ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭትን መከላከል እና ማስተዳደር" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ  እንደተናገሩትት ተቋሙ በርካታ ሀብት የሚያንቀሳቅስ እና የሥራ ፀባዩ ሙስና በረቀቀ መንገድ ሊፈፀምበት የሚችል በመሆኑ ሁሉም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የተቋሙን-ተልዕኮ-ለማሳካት-የተቋሙ-ሠራተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ጉዞ! ET 🌿 ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የጀመረችው ወደ ታዳሽ የኃይል ምንጮች የመሸጋገር ጉዞ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ነፃነት ምልክትም ነው። ይህ ጉዞ ለሀገራችን ምን ጥቅም ይሰጣል? በዓለምአቀፍ መድረክስ ምን ዓይነት ቦታ ላይ ያስቀምጠናል? 1. በሀገር ውስጥ የሚኖረው ዘርፈ-ብዙ ጥቅም 🏗 • የኢንዱስትሪ መነቃቃት አስተማማኝና በአንፃራዊነት በዋጋው ርካሽ የሆነ ታዳሽ ኃይል (ከውሃ፣ ንፋስ፣ ፀሐይና የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል በመጠቀም ) ለፋብሪካዎችና ለኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆን ከፍተኛ የኢኮኖሚ መነቃቃት ይፈጥራል። • አረንጓዴ ኢኮኖሚ የአካባቢ ብክለትን በመቀነስና በከሰልና በነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት በማስቀረት የከባቢ አየርን ብክለት በመቀነስና የውጭ ምንዛሪ ወጪን በመታደግ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመፍጠር የተጀመረውን ሀገራዊ ጥረት ያግዛል። • የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ኤሌክትሪክ ያልተዳረሰባቸውን የሀገራችን ክፍሎች ብርሃን በመስጠት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ እንዲለወጥ ምክንያት ይሆናል። 2. በዓለምአቀፍ መድረክ የሚኖረው ፋይዳ 🌍 • የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ የመሪነት ሚና ያሳድጋል፤ ዓለም በካርቦን ልቀት ስጋት ውስጥ ባለችበት ወቅት ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ለቀጣናውም ሆነ ለዓለም አርአያ እንድትሆን ያደርጋታል። • ትስስርና ቀጣናዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፤ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል (Energy Hub) መሆኗ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መድረኮች ያላትን የመደራደር አቅምና ተሰሚነት ይጨምራል። • ኢንቨስትመንትን ለመሳብ አቅም ይሆናል፤ አረንጓዴ ኃይል የሚጠቀሙ ሀገራት ለዓለምአቀፍ ፋይናንስና ለታላላቅ ኩባንያዎች ተመራጭ መዳረሻ እየሆኑ በመምጣታቸው ለሀገራችን ትልቅ ዕድል ይከፍትላታል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የታደለችውን ጸጋ ወደ ታላቅ ኃይል በመቀየር አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን እያረጋገጠች ትቀጥላለች!

photo content

ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ በአረንጓዴ ልማት የመሪነት ሚናዋን በአግባቡ እየተወጣች መሆኗን ያሳያል ........///....... ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል እና በአረንጓዴ አሻራ
+6
ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ በአረንጓዴ ልማት የመሪነት ሚናዋን በአግባቡ እየተወጣች መሆኗን ያሳያል ........///....... ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል እና በአረንጓዴ አሻራ እያከናወነቻቸው ያሉ ሥራዎች ዓለም አቀፍ እውቅና እያስገኘላት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ገለፁ። ዳይሬክተሩ "ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ማማ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዳጉ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ የታዳሽ ኃይል ልማትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ በርካታ መሰረቶች አስቀምጣ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በታዳሽ ኃይል እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ እያከናወነቻቸው ያሉ ሥራዎች ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 32) እንድታዘጋጅ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዳስገኘላት አስታውቀዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ኢትዮጵያ-የኮፕ-32-ጉባኤን-እንድታስተናግድ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ግንባታና ማሻሻያ ሥራዎች ስምምነት ተፈራረመ ....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኬኢሲ ኢንተርናሽናል ከተባለ የህንድ ኩባንያ ጋር የኢትዮጵያ የኃይል
+7
ተቋሙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ግንባታና ማሻሻያ ሥራዎች ስምምነት ተፈራረመ   ....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኬኢሲ ኢንተርናሽናል ከተባለ የህንድ ኩባንያ ጋር የኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ ሪፎርም፣ ኢንቨስትመንት እና ዘመናዊነት (PRIME) ፕሮጀክት ስር የሚከናወኑ የማስተላለፊያ መስመሮች ግንባታና ማሻሻያ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና በአፍሪካ የኬኢሲ ኢንተርናሽናል ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሱከሺ ቪያሊ  ተፈራርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጥራት ለማሻሻል፣ የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እና ተደራሽነትን ለማስፋት ፋይዳው የጎላ ነው። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-የኃይል-ማስተላለፊያ-መስመሮች-ግን&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የውሃ ማማ ናት የሚለው ትርክት የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም የተገነባ ትርክት ነው ......///....... ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውሃ ማማ ናት የሚለው ትርክት የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም በሚፈለግ መንገድ በዐባይ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የተገነባ ትርክት መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ገለፁ፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ መኮንን "ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ማማ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዳጉ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ በተደረገ ውይይት እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት የሚውል እምቅ የታዳሽ ሀብት አላት፡፡ የተፈጥሮ ሀብቶቿ በሚፈለገው መልኩ በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋሉ ባይሆንም አሁን ላይ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይሏን ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ማድረጓና በርካታ ጥቅሞችን እያገኘች መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት በየዓመቱ በአማካኝ የ10 በመቶ እድገት እንዳለው የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ከኢንዱስትሪና ከከተሞች መስፋፋት እንዲሁም ከመንግስት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ እያደገ የሚሄደውን የኃይል ፍላጎት ለመሟላት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ተቋሙ "የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል" የመሆን ርዕዩን ለማሳካት በታዳሽ የኃይል ምንጮች ላይ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ የታዳሽ ኃይል ልማትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ በርካታ መሰረቶችን አስቀምጣ እየሰራች እንደሆነ የተናገሩት አቶ ሞገስ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ እና በአካባቢ ጥበቃ  ላይ እያበረከተችው ያለው አስተዋጽኦ እና የመሪነት ሚና ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባዔ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር የአፍሪካ ሀገራትን በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር የሚለውን የአፍሪካ ሕብረት የነደፈውን አጀንዳ 2063 ለማሳካት ጉልህ ሚና መወጣቷን እና የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ፖሊስ ወደ ተግባር መቀየሩን ከማሳየቱም ባለፈ የውሃ ዲፕሎማሲን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ዕድል እንዳለው አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የውሃ ማማ ናት የሚለው ትርክት ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት በዐባይ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ሲቀነቀን የኖረና ሀገሪቱ ያላትን ሀብት በትክክል ከመግለጽ ይልቅ ሀብቶቿን እንዳትጠቀም በሚፈለግ መንገድ የተገነባ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ትርክቱ ኢትዮጵያ የተለያዩ ተፋሰሶች ስላሏት የዐባይ ተፋሰስን እንዳትጠቀም በመፈልግ የተቀነቀነና በተለያዩ ጊዜያት በተፈረሙ የቅኝ ግዛት ውሎች ላይ ቆመው ኢትዮጵያን በዐባይ ተፋሰስ ላይ የልማት ሥራዎች እንዳታከናወን የሚከለክል ትርክት እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውሃ ማማ እንደሆነች የሚገለጸውን ትርክት ለመቀየር ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት የሚውሉ ተፋሶችን በአግባቡ መጠቀም እና የተለያዩ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን ጥቅም ላይ በማዋል የኃይል ስብጥሩን ማስፋት እንዲሁም ኢትዮጵያን የውሃ ማማ ሳይሆን የታዳሽ ኃይል ማማ መሆኗን ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያን የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማማነት ለማረጋገጥ የትርክት ዳግም ግንባታ ሥራውን ከሀገሪቱ ሀብት፣ ጥቅምና ፍላጎት ጋር በማያያዝ ለኃይል ማመንጫነት በሚውሉ አቅሞች አጠቃቀም ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ሊንክ፡ ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ማማ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

ለሥራ አመልካቾች በሙሉ፤ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለወጣውን የሥራ ማስታወቂያ አመልካቾች እንዲመዘገቡበት የተገለፀው የመመዝገቢያ ሊንክ በጊዜያዊ የቴክኒክ ችግር ምክን
ለሥራ አመልካቾች በሙሉ፤ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለወጣውን የሥራ ማስታወቂያ አመልካቾች እንዲመዘገቡበት የተገለፀው የመመዝገቢያ ሊንክ በጊዜያዊ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አመልካቾችን ማስተናገድ አልቻለም። በአሁኑ ወቅትም ተቋማችን ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ሲሆን የመመዝገቢያ ሊንኩ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ወዲያውኑ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻችን እና በቴሌግራም ቻናላችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን። አመልካቾች ለተፈጠረው መስተጓጎል ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን፣ ችግሩ ተፈትቶ ምዝገባው እስከሚጀምር ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኃይል አቅርቦት የተመዘገቡት ውጤቶች ሀገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን የሚያሳዩ ናቸው …..///…. ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኃይል አቅርቦት እንዲሁም በመንገድ፣ በመስኖ እና በከተማ ማስዋብ ዘርፎች የተመዘገቡት ውጤቶች ሀገሪቱ በትክክለኛ የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን የሚያሳዩ መሆናቸውን የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ “ኢትዮጵያ ትገነባለች!” በሚል መሪ ቃል በኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ሀገራዊ የመሠረተ ልማትና የኮንስትራክሽን ሣምንት በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በይፋ ተከፍቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ወቅት የሥራና የውጤት ዘመን መሆኑንና ሣምንቱ ለቀጣይ የግንባታ ሥራዎች ግብዓት የሚገኝበትና ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በግንባታ ሥራዎች ላይ የተመዘገቡት ውጤቶች ከሥራ ዕድል ፈጠራ ባለፈ የሙያ ባለቤቶችን በማፍራት ረገድም የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው አብራርተዋል። እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት የመደመር መንግሥትን የልማት እይታና ሀገራዊ ራዕይ ያስተሳሰረ ነው። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው ሣምንቱ የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የግንባታ ሂደት ትኩረት አድርጎ የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ታላላቅ የፕሮጀክት ግንባታ ሥራዎች ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶችን በመዳሰስ ለቀጣይ ሥራዎች ልምድ የሚወሰድበት መሆኑንም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል። ሣምንቱ የሀገር ውስጥ የዘርፉ ተዋናዮች አዳዲስ ፈጠራዎችና ልምዶችን እንዲቀስሙ፣ የቴክኖሎጂ እድገቶችን እና የአሰራር ሥርዓቶችን እንዲገበዩ የሚያግዝ መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ ጫልቱ በዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ በኢነርጂ፣ በውሃ፣ በኢኖቬሽን፣ በኮንስትራክሽን፣ በሎጂስቲክስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና ፖሊሲ ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ መሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሣምንት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+2

🌍 COP32 በኢትዮጵያ፡ የአየር ንብረት የዲፕሎማሲያችን አዲስ ምዕራፍ! 🇪🇹 COP (Conference of the Parties) ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚ
🌍 COP32 በኢትዮጵያ፡ የአየር ንብረት የዲፕሎማሲያችን አዲስ ምዕራፍ! 🇪🇹 COP (Conference of the Parties) ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚካሄድ ትልቁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ነው። ኢትዮጵያ በ2027 (እ.ኤ.አ) ይህንን ጉባኤ ለማስተናገድ መመረጧ ምን ጥቅሞች አሉት? 1. በአረንጓዴ አሻራ እና በተፈጥሮ ጥበቃ የተጀመሩ ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኛሉ፤ 2. በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ልዑካን ወደ አገራችን ስለሚመጡ ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ገቢ ያስገኛል፣ 3. ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድር ያላትን ተሰሚነት ያሳድጋል፣ 4. የኃይል ሽያጭና የኢንቨስትመንት አጋርነት ለመፍጠር ይረዳል፣ 5. ተቋማችን የሚያመነጨው ንጹህና ታዳሽ ኃይል (ውኃና ንፋስ) ለዓለም ገበያ ይተዋወቃል። በጥቅሉ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይልና በአረንጓዴ ልማት ያላትን እምው አቅም ለዓለም የምታሳይበት ታሪካዊ መድረክ ነው! 💚🌿 #COP32 #Ethiopia #GreenLegacy #RenewableEnergy 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ በሀገር አቀፍ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን አውደርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ….///…. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ ሚያዝያ 9 ቀን 2018
+3
ተቋሙ በሀገር አቀፍ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን አውደርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ….///…. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ መሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሣምንት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። በኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ ዝግጅት ላይ በሀገራዊ የመሠረተ ልማት አመራር፣ ቅንጅት እና አፈጻጸም ዙሪያ እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የታዩ ስኬቶች እና የተገኙ ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡ ከዛሬ ሚያዚያ 9-12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው የኢትዮጵያ መሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሣምንት ላይ በኢነርጂ፣ በውሃ፣ በኢኖቬሽን፣ በኮንስትራክሽን፣ በሎጂስቲክስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና ፖሊሲ ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ......///....... መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በኢነርጂ ዘርፍ ላይ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የመንግስት ዋነኛ ትኩረት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልና ጫናዎችን ማቃለል ነው፡፡ የአሰላ የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑንም ተናግረዋል። መንግስት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በኃይል ማመንጨት ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ሽመልስ  አብራርተዋል። አሰላ ቀደም ሲል በግብርና ምርታማነቷ በስፋት የምትታወቅ ቢሆንም አሁን ላይ ደግሞ በኃይል ማመንጨት በኩል ጉልህ አስተዋጽዖ እያበረከተች መሆኑን ገልፀዋል። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአካባቢው ያለውን ምርታማነት በማሳደግ ለአርሶ አደሩ ከፍተኛ እገዛ ከማድረጉም ባሻገር አርሶ አደሩ ካለበት ባህላዊ አሰራር ወጥቶ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ በአርሲና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታው ያላቸዉን ተስፋ ገልፀው የማመንጫ ጣቢያው ሥራ መጀመር ድህነትንና ወደኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሱ የሆነ ሚና እንደሚኖረውም ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ የአካቢውን የኢኮኖሚ እድገት ከማፋጠኑም በላይ የማህበረሰቡ የኑሮ ሁኔታ ወደተሻለ ደረጃ ያሸጋግራል ብለዋል። የዞኑ ህዝብ ያገኘውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ድህነት እና ኋላ ቀርነትን ለማስወገድ መረባረብ እንዳለበት አቶ ሽመልስ አሳስበዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+4

ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ የምታደርውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች .......///......... ዴንማርክ የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱን ክሮግስትራፕ ገለጹ። አምባሳደሩ እንደገለፁት የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በዴንማርክና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራና የላቀ አጋርነት ማሳያ ነው። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ቀጣይነት ላለው የኢትዮጵያ ዕድገት ወሳኝ ምዕራፍ  መሆኑን አምባሳደሩ ተናግረዋል:: ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂን ተግባራዊ በማድረግ ንፁህና አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል:: ዴንማርክ በንፋስ ኃይል ማመንጨትና በዘላቂ የኃይል አጠቃቀም ረገድ ያላትን ሰፊና የበለጸገ ልምድ በመጠቀም የኢትዮጵያን የኃይል ስርዓት ለማዘመን አስተዋጽኦ በማበርከቷ ኩራት እንደሚሰማቸው አምባሳደሩ ተናግረዋል። ይህ የሁለቱ ሀገራት ትብብር የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደጉም በላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አብራርተዋል። ፕሮጀክቱ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በንጹህ ኢነርጂ አቅርቦት ረገድ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አምባሳደሩ አስረድተዋል። ዴንማርክ ወደፊትም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ዘርፍ ለማልማትና ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያን የአረንጎዴ አሻራ ለማስቀጠል እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያከናውነውን የኢነርጂ ልማት ዴንማርክ እንደምትደግፍ አምባሳደሩ አረጋግጠዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

የምናስመርቃቸው ፕሮጀክቶች የተቋሙን አፈጻጸም የሚያሳዩ የድል ማህተሞች ናቸው - አንጂነር አሸብር ባልቻ .......///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እያስመረቃቸው ያሉ የኃይል ማመንጫ ፕ
+9
የምናስመርቃቸው ፕሮጀክቶች የተቋሙን አፈጻጸም የሚያሳዩ የድል ማህተሞች ናቸው - አንጂነር አሸብር ባልቻ .......///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እያስመረቃቸው ያሉ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞን የሚያፋጥኑ እና የተቋሙን የላቀ አፈጻጸም የሚያሳዩ የድል ማህተሞች መሆናቸው የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገለፁ። ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምርቃት ላይ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ከተለያዩ የኃይል አማራጮች ከ160 ጊጋ ዋት በላይ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል እምቅ አቅም አለ። ተቋሙ ይህን እምቅ አቅም በመጠቀም እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ መልኩ ለመመለስ ትውልድን ታሳቢ ያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እየገነባ ይገኛል ብለዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የምናስመርቃቸው-ፕሮጀክቶች-የተቋሙን-አ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም